ሐምሌ 7 ተወልዶ ሐምሌ 7 ያረፈው
በአብርሃም ቤት እንግዶች ክብር ተመሥጠን ልደቱንና ዕረፍቱን ሳንዘክር እንዳንቀር የምንሰጋለት የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ሊቅና የድንቅ መጻሕፍት ደራሲ እጅግ ትሑት ድንቅ ባለ ቅኔ የሥነ ጽሑፍ ከፍታ ማሳያ የዜማ ሊቅ የምናኔ መገለጫ
በረከቱ ይድረሰንና ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ
“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው" መጽሐፈ ምሥጢር 24:20
Ⓒ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

እንደ ሕጻን ቂርቆስ ባንተ ለታመነ
ገብርኤል ታደገኝ ብሎ ለለመነ
ዖፈ ነደ እሳት አርያማዊ መልአክ
ትደርሳለህ ፈጥነህ ሠላምን በመስበክ
በቅርብ ቀን #በመሥዋዕተ_አቤል ዩቲዩብ ቻናል
ገብርኤል ታደገኝ ብሎ ለለመነ
ዖፈ ነደ እሳት አርያማዊ መልአክ
ትደርሳለህ ፈጥነህ ሠላምን በመስበክ
በቅርብ ቀን #በመሥዋዕተ_አቤል ዩቲዩብ ቻናል
✨✨✨በዛሬው ዕለት ቅዱስ ጋብቻችሁን ለፈጸማችሁ የሰ/ት/ቤታችን አባል የሆንሽው እኅታችን አታክልት ታረቀኝ🌸
እንዲሁም ወንድማችን እንዳለው የሺ ፍኖተ ሕይወት እንኳን ደስ ያላችሁ ትላለች።✨✨✨

ስንጠብቀው የነበረው የቅዱስ ገብርኤል መዝሙር ተለቋል እየገባችሁ አድምጡ።
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ሜሶፖታሚያ በምትገኝ ንጽቢን ከተማ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች መካከል በ፫፻፮ ዓ.ም ገደማ የተወለደው ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም አባቱ ክርስትናን የሚጠላ ሰው እንደነበር ይነገራል፡፡ እንዲያውም ካህነ ጣዖት ስለመሆኑ መጽሐፈ ስንክሳር ይጠቅሳል፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፲፭)
ቅዱስ ኤፍሬም ከወላጆቹ ጋር የኖረው እስከ ፲፭ ዓመት ድርስ ብቻ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዳመለከተውም ወደ ንጽቢን ጳጳስ ቅዱስ ያዕቆብ በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል በመማር የክርስትና ጥቅምትን ተጠምቋል፡፡ በጸሎት እንዲሁም በጾም እየተጋደለ ለበርካታ ዓመት በእርሱ ዘንድ ከተቀመጠ በኋላም በብሕትውና ሕይወት በመወሰን ብዙዎችን አስተምሯል፡፡ ንጽቢን በሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም ኃላፊ ሆኖ አገልግሏል፡፡
በ፫፻፳፭ ዓ.ም በተደረገው የኒቅያው ጉባኤም ከተገኙት አባቶች መካከል አንዱም ነው፤ ከመምህሩ ቅዱስ ያዕቆብ ጋር በመሆን የ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ስብሰባንና ውግዘተ አርዮስን መመልከት ችሏል፡፡ ከጉባኤውም በተመለሰ ጊዜ ዓምደ ብርሃን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ሌሊት በሕልሙ ራእይ አየ፡፡ ‹‹ራእዩን እንደገጽክልኝ ባለቤቱንም ግለጥልኝ›› ብሎም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹ባስሌዮስ ዘቂሳርያ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ዓምድ ጽንዕ ነውና፤ በትምህርቱ የሰውን ልቡና ብሩህ ያደርጋልና እንዲህ ባለ አርአያ አየኸው›› አለው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ወደ ቂሣርያ ከሄደ በኋላ ቅዱስ ባስልዮስን አገኘው፤ ቅዱስ ያዕቆብም ዲቁና ሾሞ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ እንዲያስተምር አደረገው፤ ቅዱሱም በዚያም ሥፋራ ብዙ ተአምራትን አደረገ፤ መጻሕፍትንም ደረሰ፡፡
በ፫፻፺፫ ዓ.ም የንጽቢን ከተማ በጠላት እጅ ወድቃ ስትወረር ቅዱስ ኤፍሬም ሮም፣ ኤዴሳ ከተማ ለመሰደድ ተገዶ ነበር፡፡ አብረውትም ሌሎች ክርስቲያኖች ተሰደዋል፡፡ በከተማዋም መናፍቃን ይገኙባት ስለነበር ይህ ቅዱስ የክህደት እምነታቸውን ለማጥፋት ከእነርሱ ጋር በእጅጉ ተጋደለባት፤ የተሳሳተ ትምህርታቸውና አመለካከታቸውንም በመቃወም ያለ መታከት ሞግቷቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ በርካታ ትምህርቶችን አዘጋጀ፤ መጻሕፍትንም ጻፈ፡፡ ድርሰቶቹም ዐሥራ አራት ሽህ ድርሳናትንና ተግሣጻት ናቸው፡፡ በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተጻፈው ‹‹አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ›› እስከሚል ድረስ ድርሳናትን ደርሷል፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፲፭) እርሱ የደረሳቸው አብዛኛዎቹ መጻሕፍት ወደ ግእዝ ተተርጉመዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቅሳቸውና የምትጠቀምባቸው የጸሎት ድርሰቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ‹ውዳሴ ማርያም› ነው፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም በእመቤታችን ስም ይመጸውትና ለእርሷም በነበረው ፍቅር የተነሣ ‹‹የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው›› እያለ ሲመኝ ይኖር ስለነበር የተመኙትን መስጠት ልማዱ ነውና እግዚአብሔር የልቡን መሻት ፈጸመለት፡፡ እመቤታችንም ተለገልጻለት እርሷን ለማወደስ በቅቷል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሰኞ ነግህ በሆነ ጊዜ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን መጣች፤ የብርሃን ምንጣፍ ተነጠፈ፤ የብርሃን ድባብ ተዘረጋ፡፡ ከዚያም ላይ ሁና ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቅርየ ኤፍሬም፤ ወዳጄ ኤፍሬም ሰላም ለአንተ ይሁን›› አለችው፤ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ቆመ፡፡ ‹‹ወድሰኒ›› አለችው፤ ‹‹እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ፤ ሰማያውያን ወምድራውያን ምድራውያን ጻድቃን ሰማያውያን መላእክት አንችን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል?›› አላት፤ ‹‹በከመ አለበወ፤ በመንፈስ ቅዱስ ተናገር›› አለችው። ከዚህ በኋላ ‹‹ባርኪኝ›› አላት፤ ‹‹በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ፤ የልጄና የአባቱ እና የመንፈስ ቅዱስ በረከት በላይህ ላይ ይደርብህ›› አለችው፤ ተባርኮም ምስጋናዋን ጀምሯል፡፡ በእንደዚህም ሁኔታ የሰባቱን ዕለታት ውዳሴ ማርያም መድረስ ችሏል፡፡ (ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ)
አባታችን ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው የሰባቱ ሰዓታት ክርስቲያን ለተባለን ሰዎች በሙሉ የክርስቲያናዊ ሕይወታችን ስንቅ በመሆኑ እያንዳንዱን የጸሎት ሰዓት ልናውቅና ልንጸልይ ይገባል፡፡ በርግጥ ዓለም ላይ ሆነን ካለንበት የአናናር ዘይቤ የተነሣ ለኑሯችን ዘወትር እሩጫ ላይ በመሆናችን ሰባቱንም ሰዓት ጠብቆ መጸለይ ሊከብደን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየዕለቱ ቢያንስ የሦስት ጊዜያቱን የጸሎት ሰዓት መጠበቅ እንደሚገባን ያስተምራሉ፡፡ ያለበለዚያ መንፈሳዊ ሕይወታችን ሙሉ እንደማይሆን ልናውቅ ይገባል፡፡ በነግህ፣ በሠለስት (በሦስት ሰዓት)፣ በቀትር፣ በተሰዓት፣ (ዘጠኝ ሰዓት)፣ በሠርክ፣ በንዋም (በመኝታ ሰዓት) እንዲሁም በመንፈቀ ሌሊት ከዘወትር ጸሎት ጋር ውዳሴ ማርያምን እንዳርሳለን፡፡
በእግዚአብሔር ረድኤት በእነዚህ የጸሎት ሰዓቶች ውስጥ በጸሎት ልንተጋ ይገባል፡፡ በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነን መጸለይ ቢያቅተን እንኳን ጠዋት ከመኝታችን ስንነሣና ማታ ወደ መኝታችን ስናመራ መጸለይ ይገባናል፡፡ በገዳማት ተወስነው፣ ዳዋ ጥሰው፣ ጤዛ ልሰው፣ ቁርበት ለብሰውስ፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ጸብና አጋንንቱን ታግሰው የሚኖሩ ገዳማውያን መነኰሳት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሰባቱን የጸሎት ሰዓታት ለዓይን ጥቅሻ ለምታክል ጊዜ እንኳን ሳያስታጉሉ እስካሁን ጸንተው ኖረዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ምንኩስናን በገቢር የገለጣት አባት ነው፡፡ በተጋድሎውም እስከ መሠረሻው ጸንቶ በሐምሌ ፲፭ ቀን ዐርፏል፡፡ ቅዱሱ ለሰዎች ሁሉ የሕይወት ስንቅ የሚሆነውን ይህንን የጸሎት ሥርዓት ደርሶ ለእኛ አበርክቶልናልና እስከ ሕይወታችን መሠረሻ ድረስ እንጠብቀው!
የአባታችን ቅዱስ ኤፍሬም በረከት ይደርብን፤ አሜን፡፡
‹ጥዑመ ልሳን›፣ ‹መምህረ ዓለም›፣ ‹ዓምደ ቤተ ክርስቲያን›
ሐምሌ ፲፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
𝙁𝙤𝙡𝙡𝙤𝙬 𝙏𝙝𝙞𝙨 𝙋𝙖𝙜𝙚

የ3 ዓመት ሕፃን የፈላ ውኃ በያዘ ድስት ውስጥ ቢጣል ምን ይፈጠራል ብላችሁ ታስባላችሁ?
በ3ኛው ክፍለ ዘመን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ቅድስት ኢየሉጣና የ3 ዓመቱ ልጅዋ ቅዱስ ቂርቆስ ቢሸሹም፣ በጨካኙ ገዢ አሌክሳንደር እጅ ወደቁ።
እናት ኢየሉጣ ሃይማኖቷን ለመካድ ፈቃደኛ ባለመሆኗ
የ3 ዓመት ሕጻን ልጇም "እኔ ክርስቲያን ነኝ፤ ድንጋይና እንጨት ለሆነው ጣዖት አልሰግድም" እያለ በመመስከሩ
ገዢው ተናዶ ሐምሌ 19 ቀን የፈላ ውኃ በያዘ የብረት ድስት ውስጥ እንዲጣሉ አዘዘ
ነገር ግን ሕፃኑ ሲጸልይ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ እሳቱን አቀዘቀዘው፤ ከዚህ የፈላ ውኃ ሁለቱም ምንም ሳይሆኑ ወጡ።
ከድንጋይ ይልቅ የጠጠረ ልብ ያለው አሌክሳንደር ግን በመጨረሻም አንገታቸውን በሰይፍ በመቁረጥ የሰማዕትነት አክሊል እንዲቀበሉ አደረገ።
በመሆኑም ይህ ቀን የቅዱስ ገብርኤል ተራዳኢነት የተገለጠበት ቢሆንም በዓሉ ግን የቅዱስ ቂርቆስ እና የእናቱ የኢየሉጣ ሰማዕትነትን የተቀበሉበት ዕለት ነው።
ለዚህም መጽሐፈ ስንክሳር ይገልጣል። እንዲሁም መልአክ ዘበምድር የተባለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የሐምሌ 19ኝን ክብረ በዓል ቀለም ለእነዚህ ለሰማዕታቱ ብቻ ወስኖ አመስጥሮታል።
ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
(ይወዳጁን)
👇👇👇👇👇
https://linktr.ee/finotehiwot_sundayschool?utm_source=linktree_profile_share<sid=f62cf905-ffbd-4af4-bf12-2f29df393f8c

ከ90 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬው ቀን...
ዕለቱ ከበድ ያለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ልብን
የሚያስጨንቅ ስሜት ያዘለ ነፋስ ይነፍሳል፡፡
ሐምሌ 22 ቀን
1928 ዓ.ም.!
ቁመታቸው ረዘም ያለ - ፊታቸው ዘለግ ያለ - መልካቸው
ጠየም ያለ - ዐዋቂነታቸው እና ትሕትናቸው ከገጻቸው
የሚነበብ - ጥቁር እና በጭቃ የተለወሰ የጵጵስና ካባ የለበሱ
ታላቅ አባት ችሎት ፊት በአደባባይ ቀርበዋል - አቡነ ጴጥሮስ!
“አቡነ ቄርሎስ የጣሊያንን መንግሥት ገዢነት ሲቀበሉ እርስዎ
ለምን አመጹ? ለምንስ ብቻዎን አፈንጋጭ ኾኑ?" ሲል ዳኛው
ጠየቃቸው፡፡
ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት እና ሀገሩን እና
ሃይማኖቱን እንደሚያፈቅር በሚያስታውቅ አንደበት “አቡነ
ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን
የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ! ኃላፊነትም
ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚኽ ስለሀገሬና
ስለቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለኹ፡፡ ከዚኽ በቀር ለእናንተ ችሎት
የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን
እናገራለኽ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችኹ አውቃለኹ፡፡
ስለዚኽ በእኔ ላይ የፈለጋችኹትን አድርጉ ግን ተከታዮቼን
አትንኩ" አሉ፡፡
ይኽንንም ብለው በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት
ታዝዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልዕክት
አስተላለፉ!
“አረማዊ የኾነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን
ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን
ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ
ለመሥራት ስላልመጣ ለዚኽ ግፈኛ አትገዙ!!! ስለውድ
ሀገራችኹ - ስለቀናች ሃይማኖታችኹ ተከላከሉ!!! ነጻነታችኹ
ከሚረክስ ሙታችኹ ስማችኹ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው
ክብርን ታገኛላችኹ!!! የኢትዮጵያ ሕዝብ ኾይ! ለጠላት
እንዳትገዛ አውግዣለው!!! የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን
ብትቀበል የተረገመች ትኹን!!! በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ
ስም የተረገመች ትኹን!!!"
ወዲያውም የእረፍታቸው ሰዓት መድረሷን ስለተረዱ
ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ፡፡ ምንም ፍርኃት
በገጻቸው አይነበብም ነበር፡፡ የሞታቸውን ፍርድ የሚያነበው
ጣልያናዊ ዳኛ ግን ልቡ በሽብር ተሞልቶ ፍርዳቸውን ሲያነብ
ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ የፈረዱባቸውንም ዳኞች ጸልየው
በመስቀል ባረኳቸው፡፡
ከዚያም በስምንት ጥይት ተኩሰው መቷቸው፡፡ ነገር ግን
በስምንቱ ጥይት ባለመሞታቸው ሌላ ወታደር ተጠርቶ በሦስት
ጥይት የራስ ቅላቸው ላይ መትቶ ገደላቸው፡፡
አስክሬናቸውንም ማንም እንዳይወስድ በምሥጢር ተደብቀው
ተቀበሩ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥም በየቤቱ ለቅሶ እና ዋይታ
ኾነ፡፡
በዛሬው ዕለት ሰማዕትነትን የተቀበሉት የአባታችን የብጹዕ
አቡነ ጴጥሮስ ረድኤት በረከት ይደርብን! ጽናታቸው አርአያ
ኾኖን እስትንፋሳችን ለኾነችው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን
በእምነት እና በጽናት እንድንቆም ያድርገን!! አሜን!!!
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ይወዳጁን
👇👇👇👇👇👇👇👇