እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)
ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።
ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ።
ቅዱሳን ሐዋርያትም እንዲህ ብለው መለሱላቸው ክብር ይግባውና ያለ #ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ #እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው እንዲህም አዘዙአቸው።
በሱባዔውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገለጸላቸው ቅዱሳን ሐዋርያትንም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዮስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ጳውሎስና በርናባስ ነበሩ #ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በ #ማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንድታንፁ የፈቀድኩባት ናት።"
ይህንንም ብሎ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኲል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱንም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የ #እግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈፀመ ድረስ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበረ #ጌታችንም ነዋየ ቅድሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ።
ከዚህ በኋላ #ጌታችን እጁን በ ቅዱስ ጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማእዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም "ሊቀ ጳጳሳት" ማለት ነው። ለሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ።
ከዚህም በኋላ #ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ #መድኃኒታችን ቀድሶ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው።
ከዚህም በኋላ #መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያችም ቀን ጀመሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያሳንፁ ሆኑ።
በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የ #እመቤታችን የ #ማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።
ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም አልፎ በመድፈር በ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።
ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የ #እመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። #እመቤታችንም_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የ #እመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።
ቅዱስ ባስልዮስም #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።
ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳቸው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።
ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ #ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ #እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።
እንዲሁም ከ #እመቤታችን_ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።
በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ #እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

በዛሬው ዕለት የቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ክብረ በዓል በደብራችን በደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ዋለ።
በዚህም ዕለት ከክብረ በዓሉ ኹነቶች በተጨማሪ ብፁዕነታቸው በሰ/ት/ቤቱ አገልግሎት በመደሰታቸው ለሰ/ት/ቤቶች ቋሚ የመጽሐፍ መምህር ቅጥርን አስመልክቶ ተፈጻሚ እንዲሆን መመሪያ መስጠታቸው ሰንበት ትምሕርት ቤታችንን አስደስቷል።
የቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት በሕይወታችን ይኑር።
📷 Ⓒ ፈለገ ገነት ሚድያ

ሐምሌ ፯ ቀን እግዚአብሔር አምላክ በአብርሃም ቤት የገባበትና ሣራ ይስሐቅን እንደምትወልድ የተናገረበት ዕለት ነው፡፡ ይህ የቅድስት ሥላሴ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በደማቅ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ታሪኩም በአጭሩ እንዲህ ነው፤
አባታችን አብርሃም ከተመሳቀለ ጐዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ መንገደኞችን ዅሉ በእንግድነት እየተቀበለ ሲያስተናግድ ይኖር ነበር፡፡ ጥንተ ጠላታችን ሰይጣን ለተንኮል አያርፍምና ይህንን መልካም ግብሩን ለማሰናክል አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ፤ የተጐዳ ሰው መስሎ ከጐዳና ቆሞ አብርሃም እንግዳ መቀበል እንደ ተወ፤ እርሱ ሊበላ ሊጠጣ ከቤቱ ቢሔድ ራሱን ፈንክቶ፣ ደሙን አፍሶ፣ አጥንቱን ከስክሶ፣ ልብሱን ገፎ እንደ መለሰው ወደ አብርሃም ቤት ለሚሔዱ ሰዎች ይናገር ጀመር፡፡ በዚህ የተነሣም እንግዳ ወደ አብርሃም ቤት አልመጣ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ አብርሃምም ማዕደ እግዚአብሔርን ያለ ምስክር (ያለ እንግዳ) አልመገብም ብሎ ሦስት ቀን ሳይመገብ ጾሙን አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን ይህን ደግነቱን እግዚአብሔር ተመልክቶ በሦስት ሰዎች አምሳል አንድም በሥላሴው (በሦስትነቱ) ከአብርሃም ቤት ገብቷል (ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ፣ ፬፥፴፪)፡፡
በኦሪት ዘፍጥረት ፲፰፥፩-፲፱ ተጽፎ እንደምናገኘው በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በሦስት ሰዎች አምሳል በመምሬ አድባር ዛፍ ተገልጦለታል፡፡ አብርሃምም ሦስት ሰዎች ቆመው ባየ ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ወደ እነርሱ ሮጠ፡፡ ወደ ምድርም ሰገደና ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባርያህን አትለፈኝ?›› ብሎ ተማጸነ፡፡ በመቀጠል አብርሃም ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚህችም ዛፍ በታች ዕረፉ፡፡ ቍራሽ እንጀራም ላምጣላችሁ፤ ልባችሁንም ደግፉ፡፡ ከዚያም በኋላ ትሔዳላችሁ፡፡ ስለዚህ ወደ ባርያችሁ መጥታችኋልና›› ሲላቸው እነርሱም ‹‹እንዳልህ አድርግ›› ብለውታል፡፡
የኦሪት ዘፍጥረት አንድምታ ትርጓሜ እንደሚያስረዳው አብርሃም ሥላሴን ‹‹ጌቶቼ ከቤት ገብታችሁ ዕረፉ›› ሲላቸው ‹‹ደክሞናልና አዝለህ አስገባን›› አሉት፡፡ እርሱም እሺ ብሎ አንዱን አዝሎ ቢገባ ሁለቱ በግብር አምላካዊ (በአምላካዊ ጥበብ) ከቤቱ ገቡ፡፡ አብርሃምም ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ሔደና ‹‹ሦስት መሥፈሪያ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም፤ እንጎቻም አድርጊ›› አላት፤ እርሷም እንዳዘዛት አደረገች፡፡ አብርሃምም ወይፈን አርዶ አወራርዶ አዘገጅቶላቸው ተመግበዋል፡፡ ወይፈኑም ተነሥቶ ‹‹ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፤›› ብሎ እግዚአብሔርን አመስገኗል፡፡
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?›› አለው፡፡ አብርሃምም ከድንኳኑ ውስጥ እንዳለች ነገረው፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች›› ብሎ ለአብርሃም አበሠረው፡፡ ሣራ ይህንን ቃል በሰማች ጊዜ ባለቤቷም አርጅቶ፤ እርሷም የሴቶች ግዳጅ ትቷት ነበርና ‹‹‹ሲያረጁ አምባር ይዋጁ› እንዲሉ ‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ቆንጆ ነኝን? ጌታዬ አብርሃምስ ገና ጐረምሳ ነውን?›› ብላ በማሰቧና መውለዷን በመጠራጠሯ ሳቀች፡፡ እግዚአብሔርም ምሥጢሩን በአጽንዖት ለማስረዳትና አስረግጦ ለመንገር አብርሃምን ‹‹ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› አለው፡፡ ሣራም ስለፈራች ‹‹አልሳቅሁም›› አለች፡፡ እግዚአብሔርም መሳቋን እንዳወቀባት ከነገራት በኋላ በድጋሜ በዓመቱ ወደ አብርሃም ቤት እንደሚመጣና ሣራ ወንድ ልጅ (ይስሐቅን) እንደምትወልድ አብሥሯቸዋል፡፡
በዚህ ትምህርት ብዙ ምሥጢራት ይገኛሉ፤ ጥቂቶቹን በመጠኑ ለማስታወስ ያህል፦ ‹‹… ሦስት ሰዎች … ሊቀበላቸው … ወደ እነርሱ …›› የሚሉትና ሌሎችም በብዙ ቍጥር የተገለጹ ተመሳሳይ ሐረጋት የእግዚአብሔርን ሦስትነት፤ ‹‹… በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ኾነ ባሪያህን አትለፈኝ? …›› የሚለው ዐረፍተ ነገር ደግሞ አንድነቱን ያመለክታል፡፡ ሣራ ዳቦ ያዘጋጀችበት ሦስቱ መሥፈሪያ የሦስትነቱ፤ ዳቦው አንድ መኾኑ ደግሞ የአንድነቱ ምሳሌ ነው፡፡ ሥላሴ አብርሃም ያዘጋጀውን እንስሳ ተመገቡ ተብሎ መነገሩም በሰው አምሳል ስለ ተገለጡና ለአብርሃም የበሉ መስለው ስለ ታዩት ነው እንጂ ለሥላሴ መብል መጠጥ አይስማማቸውም (አይነገርላቸውም)፡፡ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን እንዳስተማሩን ሥላሴ ምግብ በሉ (እግዚአብሔር ምግብ በላ) ማለት ቅቤ ከእሳት ገብቶ አልቀለጠም እንደ ማለት ነው፡፡ መብላት፣ መጠጣትን የመሰሉ የሥጋ ተግባራት የመለኮት ባሕርያት አይደሉምና፡፡ ከዚህ በተለየ ምሥጢር ሥላሴ ‹‹ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› ብለው ከጠየቁበት ኃይለ ቃል መካከል ‹‹ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› የሚለውን እመቤታችንን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ሲያበሥራት ‹‹ወንድ ሳላውቅ ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› (ሉቃ. ፩፥፴፯) ብላ በጠየቀችው ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ደግሞ መናገሩ የእግዚአብሔር ቃል በዘመን ብዛት የማይለወጥ ሕያውና እውነተኛ መኾኑን ያጠይቃል፡፡
እግዚአብሔር አብርሃምን ‹‹ሣራ ወዴት ናት?›› ሲል መጠየቁም ያለችበት ጠፍቶበት ሳይኾን የሚነግራት ታላቅ የምሥራች እንዳለ ለማጠየቅ ነው፡፡ ሰውን ያለበትን ጠይቆ፣ ጠርቶ፣ አቅርቦ አስደሳች ዜና መንገር የተለመደ ነውና፡፡ ይኸውም ‹‹አዳም ወዴት ነህ?›› ከሚለው ጥያቄ ጋር ተመሳሳይነት አለው (ዘፍ. ፫፥፱)፡፡ እግዚአብሔር አምላክ አባታችን አዳምን ‹‹ወዴት ነህ?›› ሲል የጠየቀው ያለበትን ዐላውቅ ብሎ ሳይኾን ቃል በቃል ሊያነጋግረው፣ ‹‹ከልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ›› የሚለውን የድኅነት ቃል ኪዳን ሊሰጠው ፈቅዶ ነበር፡፡ እንደ አዳም ዅሉ ለሣራም ለጊዜው ይስሐቅን እንደምትወልድ፤ ለፍጻሜው ደግሞ ከአብርሃም ዘር ከምትኾን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ሥጋ ለብሶ እንደሚገለጥና ዓለሙን እንደሚያድነው ለመንገር አብርሃምን ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?›› ሲል ጠይቆታል፡፡ ከዚያም የይስሐቅን መወለድ አብሥሯቸዋል፡፡ ይኸውም አምስት ሺሕ ከአምስት መቶ ዓመት ሲፈጸም እግዚአብሔር ከአብርሃም የልጅ ልጅ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ተወለደ (በአካለ ሥጋ ወደ ምድር እንደ መጣ)፤ በዚህ ጊዜም በሣራ የተመሰለች ወንጌል በይስሐቅ የሚመሰሉ ምእመናንን እንዳስገኘች ማለትም ሐዲስ ኪዳን ተመሥርታ ብዙ ክርስቲያኖችን እንዳፈራች የሚያመለክት ምሥጢር አለው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንደ ተረጐሙልን የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ነው፤ ‹‹ተናግዶቱ (ተአንግዶቱ) ለአብርሃም፤ ለአብርሃም የሃይማኖቱን (የእንግዳ ተቀባይነቱን) ዋጋ የምታሰጪው አንቺ ነሽ፤›› እንዳሉ አባ ሕርያቆስ፡፡ በአብርሃም ድንኳን አላፊ አግዳሚው ይመግብበት፣ ያርፍበት እንደ ነበረ ዅሉ በእመቤታችንም አማላጅነትም መንገደኞች ማረፍያ፤ እንግዶች መጠለያ፤ ስደተኞች ተስፋ ያገኛሉና፡፡ ከዅሉም በላይ የነፈስ የሥጋ መድኀኒት፤ የዘለዓለም ማረፍያ፤ እውነተኛ መብልና መጠጥ የኾነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች እርሷ ናትና በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ ቀትር በኾነ ጊዜ ማለትም በስድስት ሰዓት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደ ገቡ ዅሉ፣ አምስት ሺሕ አምስት መቶው ዓመት ተፈጽሞ በስድስተኛው ሺሕ ዓመት እግዚአብሔር አብ ለአጽንዖ፤

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፤ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመልበስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አድረዋልና እመቤታችን በአብርሃም ድንኳን ትመሰላለች፡፡ ‹‹በስድስተኛው ወር ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እመቤታችን ተላከ፤›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሉቃ. ፩፥፳፮)፡፡ በዚህ ቃለ ወንጌል ‹‹ስድስተኛው ወር›› የሚለው ሐረግ አምስት ሺሕ አምስት መቶው ዘመን ተፈጽሞ በስድስተኛው ሺሕ ዘመን ቅዱስ ገብርኤል ወደ እመቤታችን ለብሥራት መላኩን ያመለክታል፡፡
በአብርሃም ቤት (በድንኳኑ) ውስጥ ወይፈኑ ‹‹ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ›› ብሎ እንዳመሰገነ ዅሉ እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን በተወለደ ጊዜም ቅዱሳን መላእክትና የሰው ልጆች ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ፤ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን፤ ሰላምም በምድር፤ ለሰውም በጎ ፈቃድ›› እያሉ እግዚአብሔርን በአንድነት አመስግነዋል (ሉቃ. ፪፥፲፬)፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለአብርሃም የይስሐቅን መወለድ እና በሥጋ ማርያም መገለጡን ከነገረው በኋላ ተመልሶ ሔዷል፡፡ ‹‹ሔዷል›› ስንልም ሥላሴ ከአብርሃም ቤት በሰው አምሳል ሲወጡ መታየታቸውን ለማመልከት እንጂ እግዚአብሔር መሔድ መምጣት የሚነገርለት ኾኖ አይደለም፡፡ እርሱ በዓለሙ ዅሉ ሰፍኖ የሚኖር አምላክ ነውና፡፡ ነገር ግን በልዩ ልዩ ምሳሌ እየተገለጠ ጸጋውን፣ በረከቱን ማሳደሩን ለመግለጽ መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ እየተባለ ይነገርለታል፡፡
ትምህርታችንን ለማጠቃለል ያህል ሐምሌ ፯ ቀን እግዚአብሔር በአብርሃም ቤት ተገኝቶ የይስሐቅን መወለድና የእግዚአብሔርን ሰው መኾን የተናገረበት ዕለት ከመኾኑ ሌላ የአብርሃምን ዘሩን እንደሚያበዛለትና አሕዛብ ዅሉ በእርሱ እንደሚከብሩ ማለትም ከአብርሃም ዘር በተገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ አሕዛብ እንደሚቀደሱ፤ ይህንን ምሥጢርም እግዚአብሔር ከወዳጁ ከአብርሃም እንደማይሠውር ቃል ኪዳን የገባበት ቀን ነው፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር በኀጢአታቸው ብዛት የተነሣ ሰዶምንና ገሞራን ያጠፋው፤ አብርሃምም በአማላጅነት በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ የተማጸነው በዚሁ ዕለት ነው፡፡
ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፊት ቆመው ዘወትር ስለ ሰው ልጅ ድኅነት እንደሚጸልዩ እና እንደሚያማልዱ፤ እንደ አብርሃም ልቡናቸው ቅን በኾነና በለጋሾች ማለትም ምጽዋትንና እንግዳ መቀበልን የዘወትር ተግባራቸው አድርገው በሚኖሩ ሰዎች ቤት እግዚአብሔር እንደሚገኝ፤ እግዚአብሔር በረድኤት ወደ ሰው ቤት ሲገባም የተዘጋ ማኅፀን እንደሚከፍትና ቤቱን በበረከት እንደሚሞላ፤ እንደዚሁም የተሠወረ ምሥጢር እንደሚገልጽ ከዚህ ታሪክ እንረዳለን፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋርም እግዚአብሔር አምላክ በአንድነቱም በሦስትነቱም እየታየ አምላክነቱን ለዘመናት እንደሚገልጥና የቸርነቱን ሥራ እንደሚሠራም ከታሪኩ እንማራለን፡፡
በአጠቃላይ ይህ የእግዚአብሔር በአብርሃም ቤት የመገለጥ ትምህርት በአንድ ወቅት ብቻ የተፈጸመና ‹‹ነበር›› እየተባለ የሚነገር ያለፈ ታሪክ ሳይኾን፣ ለዘለዓለሙ ሲነገርና ሲፈጸም የሚኖር ሕያው ቃል ነው፡፡ ይህንም እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በልዩ ልዩ መንገድ እየተገለጠ ለዘመናት በሚያደርገው ድንቅ ሥራና ተአምር መገንዘብ እንችላለን፡፡ ዛሬም ሀብት ንብረት ያለን ምእመናን በትሩፋት ሥራ በመሠማራት ማለትም እንግዶችን በመቀበል፣ ለተራቡ በማብላት፣ በመመጽወት እና በመሳሰለው ተግባር ከኖርን፤ በቂ ንብረት የሌለን ደግሞ ልቡናችንን ንጹሕ ከማድረግና ከኀጢአት ከመለየት በተጨማሪ ለተቸገሩ በመራራት፣ በደግነት፣ በቀና አስተሳሰብ ከተጓዝን እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ያድራል፡፡ አድሮም ይባርከናል፤ ይቀድሰናል፡፡ እርሱ ያደረበት ሰውነት ይባረካል፤ ይቀደሳልና፡፡ ደግሞም ልጅ ለሌለን ልጅ፤ ዘመድ ላጣን ዘመድ በመስጠት ዘራችንንም ይባርክልናል፡፡ በጥቅሉ የልባችንን መሻት ዐውቆ የምንሻውን መልካም ነገር ዅሉ ይፈጽምልናል፡፡ ይህ ዅሉ የእግዚአብሔር ጸጋ ይበዛልን ዘንድ እኛም በርትዕት የተዋሕዶ ሃይማኖት እንጽና፤ በክርስቲያናዊ ምግባርም እንትጋ።
Ⓒ Mk.org

ሐምሌ 7 ተወልዶ ሐምሌ 7 ያረፈው
በአብርሃም ቤት እንግዶች ክብር ተመሥጠን ልደቱንና ዕረፍቱን ሳንዘክር እንዳንቀር የምንሰጋለት የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ሊቅና የድንቅ መጻሕፍት ደራሲ እጅግ ትሑት ድንቅ ባለ ቅኔ የሥነ ጽሑፍ ከፍታ ማሳያ የዜማ ሊቅ የምናኔ መገለጫ
በረከቱ ይድረሰንና ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ አለ
“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::
እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው" መጽሐፈ ምሥጢር 24:20
Ⓒ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

እንደ ሕጻን ቂርቆስ ባንተ ለታመነ
ገብርኤል ታደገኝ ብሎ ለለመነ
ዖፈ ነደ እሳት አርያማዊ መልአክ
ትደርሳለህ ፈጥነህ ሠላምን በመስበክ
በቅርብ ቀን #በመሥዋዕተ_አቤል ዩቲዩብ ቻናል
ገብርኤል ታደገኝ ብሎ ለለመነ
ዖፈ ነደ እሳት አርያማዊ መልአክ
ትደርሳለህ ፈጥነህ ሠላምን በመስበክ
በቅርብ ቀን #በመሥዋዕተ_አቤል ዩቲዩብ ቻናል
✨✨✨በዛሬው ዕለት ቅዱስ ጋብቻችሁን ለፈጸማችሁ የሰ/ት/ቤታችን አባል የሆንሽው እኅታችን አታክልት ታረቀኝ🌸
እንዲሁም ወንድማችን እንዳለው የሺ ፍኖተ ሕይወት እንኳን ደስ ያላችሁ ትላለች።✨✨✨

ስንጠብቀው የነበረው የቅዱስ ገብርኤል መዝሙር ተለቋል እየገባችሁ አድምጡ።
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ሜሶፖታሚያ በምትገኝ ንጽቢን ከተማ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች መካከል በ፫፻፮ ዓ.ም ገደማ የተወለደው ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም አባቱ ክርስትናን የሚጠላ ሰው እንደነበር ይነገራል፡፡ እንዲያውም ካህነ ጣዖት ስለመሆኑ መጽሐፈ ስንክሳር ይጠቅሳል፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፲፭)
ቅዱስ ኤፍሬም ከወላጆቹ ጋር የኖረው እስከ ፲፭ ዓመት ድርስ ብቻ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዳመለከተውም ወደ ንጽቢን ጳጳስ ቅዱስ ያዕቆብ በመሄድ የእግዚአብሔርን ቃል በመማር የክርስትና ጥቅምትን ተጠምቋል፡፡ በጸሎት እንዲሁም በጾም እየተጋደለ ለበርካታ ዓመት በእርሱ ዘንድ ከተቀመጠ በኋላም በብሕትውና ሕይወት በመወሰን ብዙዎችን አስተምሯል፡፡ ንጽቢን በሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም ኃላፊ ሆኖ አገልግሏል፡፡
በ፫፻፳፭ ዓ.ም በተደረገው የኒቅያው ጉባኤም ከተገኙት አባቶች መካከል አንዱም ነው፤ ከመምህሩ ቅዱስ ያዕቆብ ጋር በመሆን የ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት ስብሰባንና ውግዘተ አርዮስን መመልከት ችሏል፡፡ ከጉባኤውም በተመለሰ ጊዜ ዓምደ ብርሃን ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ ሌሊት በሕልሙ ራእይ አየ፡፡ ‹‹ራእዩን እንደገጽክልኝ ባለቤቱንም ግለጥልኝ›› ብሎም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክት የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹ባስሌዮስ ዘቂሳርያ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ዓምድ ጽንዕ ነውና፤ በትምህርቱ የሰውን ልቡና ብሩህ ያደርጋልና እንዲህ ባለ አርአያ አየኸው›› አለው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ወደ ቂሣርያ ከሄደ በኋላ ቅዱስ ባስልዮስን አገኘው፤ ቅዱስ ያዕቆብም ዲቁና ሾሞ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ እንዲያስተምር አደረገው፤ ቅዱሱም በዚያም ሥፋራ ብዙ ተአምራትን አደረገ፤ መጻሕፍትንም ደረሰ፡፡
በ፫፻፺፫ ዓ.ም የንጽቢን ከተማ በጠላት እጅ ወድቃ ስትወረር ቅዱስ ኤፍሬም ሮም፣ ኤዴሳ ከተማ ለመሰደድ ተገዶ ነበር፡፡ አብረውትም ሌሎች ክርስቲያኖች ተሰደዋል፡፡ በከተማዋም መናፍቃን ይገኙባት ስለነበር ይህ ቅዱስ የክህደት እምነታቸውን ለማጥፋት ከእነርሱ ጋር በእጅጉ ተጋደለባት፤ የተሳሳተ ትምህርታቸውና አመለካከታቸውንም በመቃወም ያለ መታከት ሞግቷቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ በርካታ ትምህርቶችን አዘጋጀ፤ መጻሕፍትንም ጻፈ፡፡ ድርሰቶቹም ዐሥራ አራት ሽህ ድርሳናትንና ተግሣጻት ናቸው፡፡ በመጽሐፈ ስንክሳር እንደተጻፈው ‹‹አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ›› እስከሚል ድረስ ድርሳናትን ደርሷል፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፲፭) እርሱ የደረሳቸው አብዛኛዎቹ መጻሕፍት ወደ ግእዝ ተተርጉመዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትጠቅሳቸውና የምትጠቀምባቸው የጸሎት ድርሰቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ‹ውዳሴ ማርያም› ነው፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም በእመቤታችን ስም ይመጸውትና ለእርሷም በነበረው ፍቅር የተነሣ ‹‹የእመቤቴ ምስጋናዋ እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ እንደ ልብስ ለብሼው እንደ ምግብ ተመግቤው ጠግቤው›› እያለ ሲመኝ ይኖር ስለነበር የተመኙትን መስጠት ልማዱ ነውና እግዚአብሔር የልቡን መሻት ፈጸመለት፡፡ እመቤታችንም ተለገልጻለት እርሷን ለማወደስ በቅቷል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሰኞ ነግህ በሆነ ጊዜ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን መጣች፤ የብርሃን ምንጣፍ ተነጠፈ፤ የብርሃን ድባብ ተዘረጋ፡፡ ከዚያም ላይ ሁና ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቅርየ ኤፍሬም፤ ወዳጄ ኤፍሬም ሰላም ለአንተ ይሁን›› አለችው፤ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ቆመ፡፡ ‹‹ወድሰኒ›› አለችው፤ ‹‹እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ፤ ሰማያውያን ወምድራውያን ምድራውያን ጻድቃን ሰማያውያን መላእክት አንችን ማመስገን የማይቻላቸው ለእኔ እንደምን ይቻለኛል?›› አላት፤ ‹‹በከመ አለበወ፤ በመንፈስ ቅዱስ ተናገር›› አለችው። ከዚህ በኋላ ‹‹ባርኪኝ›› አላት፤ ‹‹በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ፤ የልጄና የአባቱ እና የመንፈስ ቅዱስ በረከት በላይህ ላይ ይደርብህ›› አለችው፤ ተባርኮም ምስጋናዋን ጀምሯል፡፡ በእንደዚህም ሁኔታ የሰባቱን ዕለታት ውዳሴ ማርያም መድረስ ችሏል፡፡ (ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ)
አባታችን ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው የሰባቱ ሰዓታት ክርስቲያን ለተባለን ሰዎች በሙሉ የክርስቲያናዊ ሕይወታችን ስንቅ በመሆኑ እያንዳንዱን የጸሎት ሰዓት ልናውቅና ልንጸልይ ይገባል፡፡ በርግጥ ዓለም ላይ ሆነን ካለንበት የአናናር ዘይቤ የተነሣ ለኑሯችን ዘወትር እሩጫ ላይ በመሆናችን ሰባቱንም ሰዓት ጠብቆ መጸለይ ሊከብደን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየዕለቱ ቢያንስ የሦስት ጊዜያቱን የጸሎት ሰዓት መጠበቅ እንደሚገባን ያስተምራሉ፡፡ ያለበለዚያ መንፈሳዊ ሕይወታችን ሙሉ እንደማይሆን ልናውቅ ይገባል፡፡ በነግህ፣ በሠለስት (በሦስት ሰዓት)፣ በቀትር፣ በተሰዓት፣ (ዘጠኝ ሰዓት)፣ በሠርክ፣ በንዋም (በመኝታ ሰዓት) እንዲሁም በመንፈቀ ሌሊት ከዘወትር ጸሎት ጋር ውዳሴ ማርያምን እንዳርሳለን፡፡
በእግዚአብሔር ረድኤት በእነዚህ የጸሎት ሰዓቶች ውስጥ በጸሎት ልንተጋ ይገባል፡፡ በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነን መጸለይ ቢያቅተን እንኳን ጠዋት ከመኝታችን ስንነሣና ማታ ወደ መኝታችን ስናመራ መጸለይ ይገባናል፡፡ በገዳማት ተወስነው፣ ዳዋ ጥሰው፣ ጤዛ ልሰው፣ ቁርበት ለብሰውስ፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ጸብና አጋንንቱን ታግሰው የሚኖሩ ገዳማውያን መነኰሳት አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሰባቱን የጸሎት ሰዓታት ለዓይን ጥቅሻ ለምታክል ጊዜ እንኳን ሳያስታጉሉ እስካሁን ጸንተው ኖረዋል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ምንኩስናን በገቢር የገለጣት አባት ነው፡፡ በተጋድሎውም እስከ መሠረሻው ጸንቶ በሐምሌ ፲፭ ቀን ዐርፏል፡፡ ቅዱሱ ለሰዎች ሁሉ የሕይወት ስንቅ የሚሆነውን ይህንን የጸሎት ሥርዓት ደርሶ ለእኛ አበርክቶልናልና እስከ ሕይወታችን መሠረሻ ድረስ እንጠብቀው!
የአባታችን ቅዱስ ኤፍሬም በረከት ይደርብን፤ አሜን፡፡
‹ጥዑመ ልሳን›፣ ‹መምህረ ዓለም›፣ ‹ዓምደ ቤተ ክርስቲያን›
ሐምሌ ፲፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
𝙁𝙤𝙡𝙡𝙤𝙬 𝙏𝙝𝙞𝙨 𝙋𝙖𝙜𝙚