ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
251 subscribers
1.96K photos
16 videos
90 files
159 links
#እኛ_የአቡየ_ልጆች
ማንም አላዋቂ ምንም ቢል እኛ ግን እምናገለግለውን እናቃለን እርሱም እንደ ሰው ተወልዶ እንደ መላእክት የኖረ እንደ መላእክት ኑሮ በክብር እንደ ሰው ያረፈውን በነጎድጓድ ላይ ስልጣን የተሰጠውን አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ነው።

ለማንኛውም አስተያየት👉 0902092705- @finotehiwotdk
Download Telegram
በጉባኤ አናሲሞስ

የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎችና መፍትሔዎች በሚል ርዕስ በዲ/ን ደረጀ ገበያው ተካሄደ።

ጉባኤው ቤተ ክርስቲያኒቱ መፈተን እና መሰደድ የሚባለውን ደረጃ አልፋ የደረሰችበትን የመውደም ሁኔታ እውቅና መፍጠር እና እንደ አማኝ ቁጭት እንዲሰማን፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ከመሆን እንድንቆጠብ፣ አጥፊዎቻችን ለማጥፋት የጸኑበትን ልክ፤ እኛ ቤተ ክርስቲያናችንን ለመጠበቅ የምንሄድበት የስንፍና መንገድ እንድናውቅ፣ እንዲሰማን፣ የመፍትሔ አካል መሆን እንድንችል ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን መምህራችን ዛሬ መግቢያውን በጥቂቱ የዳሰሱልን ሲሆን በዚሁ ቀን እና ሰዓት በየ ሳምንቱ እንደሚቀጥል ታውቆ በጉባኤው ተቀሳቅሰን እንድንገኝ የትምሕርት ክፍላችን መልእክት ነው።

እግዚአብሔር አምላክ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ከመሆን ይጠብቀን


ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሚድያ ክፍል
መንፈሳዊ ተከታታይ ትምሕርት ለምትፈልጉ በሙሉ እነሆ የክረምት መርሐ ግብር ምዝገባ እስከ ሰኔ 21 ድረስ:-
1, በሰ/ት/ቤቱ ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
2, በሰ/ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍት
እንዲሁም በስልክ ቁጥር 0957338408/0918208484 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

#ፍኖተ_ሕይወት ሰ/ት/ቤት
በዚህች ዕለት የወጣቶች ገበዝ ወጣቱ ሰማዕት ቅዱስ ሚናስ የቅዳሴ ቤቱ መታሰቢያ ነው።
ሰማዕቱ ቅዱስ ሚና
ከቅዱሳን ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ሚና በ 4ኛው መቶ  ክፍለ ዘመን ተጋድሎውን የፈፀመ ግብፃዊ ሰማዕት ሲሆን ህዳር 15 ቀን የሚነበበው ስንክሳር ቅዱስ ሚናስ በሚል ስያሜ ይገልፀዋል። በሶሪያ ቋንቋ ማር የሚለው ቃል  ‘ቅዱስ’ የሚልትርጉም ሲኖረው ለወንድ የሚሰጥ ቅጥያ ሲሆን ለሴት ደግሞ ማርታ ይሆናል ይሄውም ቅድስት ማለት ነው።
ቅዱስ ሚናስ ከእናቱ ከአውፌምያ እና 
ከአባቱ ከአውዶስዮስ ልዩ ስሙ ኒቆስ ሻቲ በተባለ መንደር በ 276 ዓ∙ም ተወለደ። እናቱ አውፌምያ ልጅ መውለድ ባለመቻሏ ታዝንና ትጨነቅ ነበር። ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስትሄድም እናቶች ልጆቻቸውን ሲያቆርቡ ስታይ በማልቀስ ፈጣሪዋን ልጅ እንዲሰጣት ትለምን ነበር። ግዚአብሔርም የልመናዋን ቃል ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጣት።
አባቱ አውዶስዮስ የናይል ዴልታ አስተዳዳሪ የነበረ ሲሆን ለህዝቡ ባለው ፍቅርና ሐዘኔታ ንዲሁም በትክክለኛ ፍርድ ሰጭነቱ በአካባቢው ሰው ተወዳጅነትን ያተረፈ ሰው ነበር። አውፌምያም እግዚአብሔርን የምትፈራና ባለቤቷ በሚፈፅማቸው ቀና ምግባሮች ሁሉ ከጎኑ ሆና የምትደግፈውና የምታበረታታው ሴት ነበረች።

ቅዱስ ሚናስ ወላጆቹን ያጣው በልጅነት ጊዜው ሲሆን ከወላጆቹ የወረሰውንም ሃብትና ንብረት በመሸጥና ለድሆች በማከፋፈል እሱ ግን ይህችን አለም ንቆ መነነ። በዘመኑ በነበሩ ጣዖት አምላኪ ነገስታት ተይዞ ለጣዖት አልሰግድም በማለቱ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ ይህም የሆነው በ 24 ዓመቱ ነው።
ማር ሚና (ቅዱስ ሚናስ) በኢትዮጵያ ብዙም ባይታወቅም በጣና ቂርቆስ ከሰማዕቱ ከቅዱስ ቂርቆስና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጋር መቅደስ ታንፆለት እንደነበር


"ጠቢበ ጠቢባን ቂርቆስ ወእማዕምራን ማዕምር
ሐውፃ ለመቅደስከ እንተ ተሃንፀት በባህር፡
ምስለ እስጢፋኖስ ሰማዕት ወሚናስ ፍቁር።" የሚለው የመልክዐ ቂርቆስ ንባብ ምስክር ነው።
የጠቢባን ጠቢብ የአዋቂዎች አዋቂ የምትሆን ቂርቆስ ሆይ ከሰማዕቱ እስጢፋኖስ
ና ከተወዳጁ ከሚናስ ጋር በባህር ላይ የታነፀች መቅደስህን ጎብኛት ማለት ነው። እዚሁ መልክዕ ውስጥ በግብፅ በታወቀው የስም አጠራሩ "ሚና" በማለት የሚጠራውን ንባብ እናገኛለን።
"ሰላም ዕብል ዘምስለ ካልዕከ ሚና ፤
 ቂርቆስ ሕፃን ዘእያብፅሕኮ ውርዝውና" 
 ለጉልምስና ያልበቃህ ሕፃን ቂርቆስ ሆይ ከጓደኛህ ከሚና ጋር ሰላም እልሃለሁ (ሰላምታ ላንተ ይሁን) ማለት ነው።በማለት በካይሮ አባስያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅድስት ማርያም ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀው የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ እና የፓትርያሪክ ቄርሎስ ፮ኛ የህይወት ታሪክ በሚል የተዘጋጀው መፅሃፍ ይገልጻል።


ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኘው ብቸኛው የቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርሰቲያን ምን ያህል ያውቃሉ?
የቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርሰቲያን ከባህር ዳር  ከተማ በግምት 23 ኪ∙ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ጎጃም እና በደቡብ ጎንደር መሀከል ወይም በደራ ክፍለሃገር ከአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም በግምት ከ3-4 ኪ∙ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን አካባቢውም በተለምዶ ሚናስ እየተባለ ይጠራል።
ቤተ-ክርስቲያኑ የተተከለበት ዘመን በውል ባይታወቅም ቤተክርስቲያኑ ግን በአፄ ፋስልዘመነ መንግስት እንደነበር ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ያስረዳል።
በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በ 1597 ዓ∙ም በነበረው የሐይማኖት መፋለስ ቅዱሳን በሃይማኖታቸው ሲሰደዱ ብዙ እንግልት መከራ እና ስቃይ ሲደርስባቸው በነበረበት በዚያ ዘመን የንጉሱ ግብረ አበሮች እና አድርባዮች ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ሲመዘበሩና በእሳት ሲያቃጥሉ ይህን ቤተ-ክርስቲያን ግን ለማቃጠል ቢሞክሩም በእግዚአብሔር ተዓምር የቤተክርስቲያኑን በር መክፈትም ሆነ ቤተ-ክርስቲያኑን ማቃጠል አልተቻላቸውም ነበር። ከዚያን ጊዜ በኋላም ለማንም ሊከፈት ባለመቻሉ ለ 17 ዓመት ተዘግቶ እንደቆየ አባቶች ይናገራሉ።
ገድለ አቡነ ሐራ ድንግልም የሃይማኖት መፍለስም ከሆነ ከ 16 ዓመት በኋላ በአፄ ፋሲለደስ ንጉስ ትዕዛዝ ሃይማኖት እንደቀድሞዋ ሆነች የሮም ሃይማኖትም ፈለሰች በማለት ያስረዳል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም ወደ እርሳቸው ከመጡ መነኮሳት ጋር ተሰብስበው ወደ ቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርስቲያን ሄደው በመፀለይ ለ 17 ዓመት ተዘግቶ የነበረ ቤተ-ክርስቲያን ተከፈተላቸው። በአንድነትም ቆሙ በማህሌትና በእልልታ በከበሮና በጸናጽንም አመስግነው የጌታችንና የመድሓኒታችንን ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው ወደ በዓታቸው እንደተመለሱ ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ይናገራል።
ቅዱሱ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ከአረፉ በኋላ ግን ይህ ቤተክርስቲያን ሰው በማጣት ጠፍ የአራዊት መኖሪያ ሆኖ ለ 400 ዓመት እንደቆየ አባቶች ይናገራሉ። ምንም እንኳን ይህ ቦታ የአራዊት መኖሪያ ቢሆንም ቅዱሳን ግን እንዳልተለዩት የአካባቢው ነዋሪዎችና የቀደሙ አባቶች ይናገራሉ። የቤተክርስቲያን ደወል እና የእጣን መዓዛ ይሸታቸው እንደነበርም ይመሰክራሉ።
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም እገዛ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ትብብር ዛሬ ያለው መቃረቢያ (መቃኞ) ተሰርቶ ታቦቱ ለመግባት ችሏል። 
የቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ በዓሉ ህዳር ፲፭ ቀን በድምቀት ይከበራል። በዚህች ቀንም ሰኔ ፲፭ ቀን ቅዳሴ ቤቱ ይከብራል።
የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ በረከት እና ረድኤት አይለየን
ሚናስ ሚናስ ይላል
ደቂቀ ሐብተ ማርያም
ሚናስ ሚናስ ይላል

ሚናስ ሚናስ ይላል አንደበቴ /፪/
አማልዶኛልና ከሰማዩ አባቴ
ሚናስ ሚናስ ይላል አንደበቴ

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል ምድርና ሰማዩ
ሚናስ(2) ይላል ተዓምርህን ይንገሩ
ሚናስ(2) ይላል ፍጥረታት በሙሉ
ሚናስ(2) ይላል ለክብሩ ዘምሩ

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል ለእምነትህ መቆምህ
ሚናስ(2) ይላል አድርሶሃል ለሞት
ሚናስ(2) ይላል ሲቆረጥ አንገትህ
ሚናስ(2) ይላል ፈሶሀል ደም ወተት

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል በሰራኸው መቅደስ
ሚናስ(2) ይላል በረከት ጠገቡ
ሚናስ(2) ይላል አቡነ ሐራ ድንግል
ሚናስ(2) ይላል ቀድሰው ቆረቡ

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል ያከበርከው ጌታ
ሚናስ(2) ይላል ከፍከፍ በልልን
ሚናስ(2) ይላል በአለም አንስቶ
ሚናስ(2) ይላል በሚናስ ባረከን

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ነገስታት ካህናት ነቢያት ሁነን ተሹመናል

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደፃፈው

ልጆቼ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን ተሰኝተን ከማህፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ስንወለድ ነገስታት፣ ካህናት፣ ነቢያት ሁነን ተሹመናል።

"አባታችን ዛሬ ደግሞ ምን እያልከን ነው?" ትሉኝ ይሆናል  እኔም እንዲህ ብየ እመልስላችኋለሁ

👉 ራሳችንን እንድንገዛ፣ ያሻነውን እንድንፈርድ ነገስታት ሆነን ተሹመናል
👉 ከክርስቶስ ጋር ለዚህ አለም ስራ ሞተን ራሳችንን የተወደደ መስዋዕት አድርገን ለአምላካችን እናቀርብ ዘንድ ካህናት ሆነን ተሹመናል (2ኛ ጢሞ 2፦3)
👉 ዳግመኛም ሊመጣ ያለውን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ መነፀርነት  እንድናውቅ ነቢያት ሆነን ተሹመናል።

📌 ወታደሮች ወደ አንድ ማዕረግ ሲሰጣቸው ልዩ የሆነ ማህተም እንደሚደረግላቸው ሁሉ እኛ ክርስቲያኖችም ነገስታት ካህናትና ነቢያት ሁነን ለመሾማችን ይህን ማዕረግ ባገኘንበት በአርባና በሰማኒያ ቀናችን የመንፈስ ቅዱስ ማህተም ታትሞብናል።

ስለዚህ ንግስናችንን ክህነታችንን ነቢይነታችንን በንፅህና በቅድስና እንያዘው

ሰማዕትነት አያምልጣችሁ ገፅ138

ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
ባሳለፍነው ቅዳሜ "የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው" በሚል ርዕስ የተካሄደው የጉባኤ አናሲሞስ ጉባኤ ክፍል 2 በቀጣይ ቅዳሜ ማለትም ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ስለሚቀጥል እንድንገኝ ይሁን።

መልእክቱን ላላዩት ይዳረስ ዘንድ ሼር አድርጉ።

ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
ካለፈው ሳምንት የሚቀጥለው የጉባኤ አናሲሞስ ክፍል 2 መርሐ ግብር ነገ 11:00 ስለሆነ በሰዓት እንድንገኝ ይሁን።

ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት
እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም (ህንጸተ ቤተክርስቲያን)

ሰኔ ሃያ አንድ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች።

ይኸውም ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ።

ቅዱሳን ሐዋርያትም እንዲህ ብለው መለሱላቸው ክብር ይግባውና ያለ #ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ #እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው እንዲህም አዘዙአቸው።

በሱባዔውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ተገለጸላቸው ቅዱሳን ሐዋርያትንም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዮስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ጳውሎስና በርናባስ ነበሩ #ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በ #ማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት እንድታንፁ የፈቀድኩባት ናት።"

ይህንንም ብሎ ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኲል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱንም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የ #እግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈፀመ ድረስ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበረ #ጌታችንም ነዋየ ቅድሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ።

ከዚህ በኋላ #ጌታችን እጁን በ ቅዱስ ጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማእዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም "ሊቀ ጳጳሳት" ማለት ነው። ለሐዋርያት አለቃ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ።

ከዚህም በኋላ #ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ #መድኃኒታችን ቀድሶ #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው።

ከዚህም በኋላ #መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያችም ቀን ጀመሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያሳንፁ ሆኑ።

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የ #እመቤታችን#ማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም። ከዚያም አልፎ በመድፈር በ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የ #እመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። #እመቤታችንም_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የ #እመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳቸው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ #ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ #እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከ #እመቤታችን_ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ #እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።
በዛሬው ዕለት የቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ክብረ በዓል በደብራችን በደብረ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

በዚህም ዕለት ከክብረ በዓሉ ኹነቶች በተጨማሪ ብፁዕነታቸው በሰ/ት/ቤቱ አገልግሎት በመደሰታቸው ለሰ/ት/ቤቶች ቋሚ የመጽሐፍ መምህር ቅጥርን አስመልክቶ ተፈጻሚ እንዲሆን መመሪያ መስጠታቸው ሰንበት ትምሕርት ቤታችንን አስደስቷል።

የቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት በሕይወታችን ይኑር።

📷 Ⓒ ፈለገ ገነት ሚድያ