ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
251 subscribers
1.94K photos
16 videos
90 files
159 links
#እኛ_የአቡየ_ልጆች
ማንም አላዋቂ ምንም ቢል እኛ ግን እምናገለግለውን እናቃለን እርሱም እንደ ሰው ተወልዶ እንደ መላእክት የኖረ እንደ መላእክት ኑሮ በክብር እንደ ሰው ያረፈውን በነጎድጓድ ላይ ስልጣን የተሰጠውን አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ነው።

ለማንኛውም አስተያየት👉 0902092705- @finotehiwotdk
Download Telegram
🔴ለ8ኛው ዙር ጉዟችን እየተዘጋጁ ነው?

መጋቢት 18,19 እና 20(አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ)
በተቀደሰው የአብይ ጾም የዕረፍት ቀናችንን በበረከት ቦታ እናሳልፍ!
በጣና ሐይቅ በሚገኙ 19 ገዳማትና አድባራት እንባረክ!

🧾ትኬቱን
👉አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
👉አባይ ማዶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
👉ታዬ ሞላ ስቴሽነሪ
👉ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር

⭕️እስከ መጋቢት 16 ትኬቱን በእጅዎ ያስገቡ!

0902092705
0920114370
0940908594
ይደውሉልን!

🌐ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕርዳር

🛜በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ያድርሱ...

👉 Telegram
t.me/finotehiwotgroup
👉 Facebook
https://www.facebook.com/finotehiwotss
👉Email address
fenotehiwotmedia@gmail.com
👉YouTube
https://youtube.com/@finotehiwet?si=_g8FL0uKUvoyQq8U
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@finotehiwet?_t=8rt6kilIeTo&_r=1
በዛሬው እለት የጋብቻ ሥርዓታችሁን በምሥጢረ ተክሊል የፈጸማችሁ የሰ/ት/ቤታችን አገልጋይ ዲ/ን አማረ ተስፋ እንዲሁም እኅታችን ወ/ሪት መድኅን አበበ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ አላችሁ ትላለች።

ጋብቻችሁ ለጽድቅ ይሁን።
ጾመ ሐዋርያት
(በተክለሐዋርያት)

ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡
ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትም ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን  ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ  በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡
የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)።  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡
እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡
ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡
ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡
የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት
የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡

ምንጭ:- eotc.org

https://t.me/finotehiwet
https://t.me/finotehiwet
https://t.me/finotehiwet
በጉባኤ አናሲሞስ

የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎችና መፍትሔዎች በሚል ርዕስ በዲ/ን ደረጀ ገበያው ተካሄደ።

ጉባኤው ቤተ ክርስቲያኒቱ መፈተን እና መሰደድ የሚባለውን ደረጃ አልፋ የደረሰችበትን የመውደም ሁኔታ እውቅና መፍጠር እና እንደ አማኝ ቁጭት እንዲሰማን፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ከመሆን እንድንቆጠብ፣ አጥፊዎቻችን ለማጥፋት የጸኑበትን ልክ፤ እኛ ቤተ ክርስቲያናችንን ለመጠበቅ የምንሄድበት የስንፍና መንገድ እንድናውቅ፣ እንዲሰማን፣ የመፍትሔ አካል መሆን እንድንችል ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን መምህራችን ዛሬ መግቢያውን በጥቂቱ የዳሰሱልን ሲሆን በዚሁ ቀን እና ሰዓት በየ ሳምንቱ እንደሚቀጥል ታውቆ በጉባኤው ተቀሳቅሰን እንድንገኝ የትምሕርት ክፍላችን መልእክት ነው።

እግዚአብሔር አምላክ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ከመሆን ይጠብቀን


ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሚድያ ክፍል
መንፈሳዊ ተከታታይ ትምሕርት ለምትፈልጉ በሙሉ እነሆ የክረምት መርሐ ግብር ምዝገባ እስከ ሰኔ 21 ድረስ:-
1, በሰ/ት/ቤቱ ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
2, በሰ/ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍት
እንዲሁም በስልክ ቁጥር 0957338408/0918208484 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

#ፍኖተ_ሕይወት ሰ/ት/ቤት
በዚህች ዕለት የወጣቶች ገበዝ ወጣቱ ሰማዕት ቅዱስ ሚናስ የቅዳሴ ቤቱ መታሰቢያ ነው።
ሰማዕቱ ቅዱስ ሚና
ከቅዱሳን ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ሚና በ 4ኛው መቶ  ክፍለ ዘመን ተጋድሎውን የፈፀመ ግብፃዊ ሰማዕት ሲሆን ህዳር 15 ቀን የሚነበበው ስንክሳር ቅዱስ ሚናስ በሚል ስያሜ ይገልፀዋል። በሶሪያ ቋንቋ ማር የሚለው ቃል  ‘ቅዱስ’ የሚልትርጉም ሲኖረው ለወንድ የሚሰጥ ቅጥያ ሲሆን ለሴት ደግሞ ማርታ ይሆናል ይሄውም ቅድስት ማለት ነው።
ቅዱስ ሚናስ ከእናቱ ከአውፌምያ እና 
ከአባቱ ከአውዶስዮስ ልዩ ስሙ ኒቆስ ሻቲ በተባለ መንደር በ 276 ዓ∙ም ተወለደ። እናቱ አውፌምያ ልጅ መውለድ ባለመቻሏ ታዝንና ትጨነቅ ነበር። ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስትሄድም እናቶች ልጆቻቸውን ሲያቆርቡ ስታይ በማልቀስ ፈጣሪዋን ልጅ እንዲሰጣት ትለምን ነበር። ግዚአብሔርም የልመናዋን ቃል ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጣት።
አባቱ አውዶስዮስ የናይል ዴልታ አስተዳዳሪ የነበረ ሲሆን ለህዝቡ ባለው ፍቅርና ሐዘኔታ ንዲሁም በትክክለኛ ፍርድ ሰጭነቱ በአካባቢው ሰው ተወዳጅነትን ያተረፈ ሰው ነበር። አውፌምያም እግዚአብሔርን የምትፈራና ባለቤቷ በሚፈፅማቸው ቀና ምግባሮች ሁሉ ከጎኑ ሆና የምትደግፈውና የምታበረታታው ሴት ነበረች።

ቅዱስ ሚናስ ወላጆቹን ያጣው በልጅነት ጊዜው ሲሆን ከወላጆቹ የወረሰውንም ሃብትና ንብረት በመሸጥና ለድሆች በማከፋፈል እሱ ግን ይህችን አለም ንቆ መነነ። በዘመኑ በነበሩ ጣዖት አምላኪ ነገስታት ተይዞ ለጣዖት አልሰግድም በማለቱ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ ይህም የሆነው በ 24 ዓመቱ ነው።
ማር ሚና (ቅዱስ ሚናስ) በኢትዮጵያ ብዙም ባይታወቅም በጣና ቂርቆስ ከሰማዕቱ ከቅዱስ ቂርቆስና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጋር መቅደስ ታንፆለት እንደነበር


"ጠቢበ ጠቢባን ቂርቆስ ወእማዕምራን ማዕምር
ሐውፃ ለመቅደስከ እንተ ተሃንፀት በባህር፡
ምስለ እስጢፋኖስ ሰማዕት ወሚናስ ፍቁር።" የሚለው የመልክዐ ቂርቆስ ንባብ ምስክር ነው።
የጠቢባን ጠቢብ የአዋቂዎች አዋቂ የምትሆን ቂርቆስ ሆይ ከሰማዕቱ እስጢፋኖስ
ና ከተወዳጁ ከሚናስ ጋር በባህር ላይ የታነፀች መቅደስህን ጎብኛት ማለት ነው። እዚሁ መልክዕ ውስጥ በግብፅ በታወቀው የስም አጠራሩ "ሚና" በማለት የሚጠራውን ንባብ እናገኛለን።
"ሰላም ዕብል ዘምስለ ካልዕከ ሚና ፤
 ቂርቆስ ሕፃን ዘእያብፅሕኮ ውርዝውና" 
 ለጉልምስና ያልበቃህ ሕፃን ቂርቆስ ሆይ ከጓደኛህ ከሚና ጋር ሰላም እልሃለሁ (ሰላምታ ላንተ ይሁን) ማለት ነው።በማለት በካይሮ አባስያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅድስት ማርያም ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀው የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ እና የፓትርያሪክ ቄርሎስ ፮ኛ የህይወት ታሪክ በሚል የተዘጋጀው መፅሃፍ ይገልጻል።


ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኘው ብቸኛው የቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርሰቲያን ምን ያህል ያውቃሉ?
የቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርሰቲያን ከባህር ዳር  ከተማ በግምት 23 ኪ∙ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ጎጃም እና በደቡብ ጎንደር መሀከል ወይም በደራ ክፍለሃገር ከአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም በግምት ከ3-4 ኪ∙ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን አካባቢውም በተለምዶ ሚናስ እየተባለ ይጠራል።
ቤተ-ክርስቲያኑ የተተከለበት ዘመን በውል ባይታወቅም ቤተክርስቲያኑ ግን በአፄ ፋስልዘመነ መንግስት እንደነበር ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ያስረዳል።
በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በ 1597 ዓ∙ም በነበረው የሐይማኖት መፋለስ ቅዱሳን በሃይማኖታቸው ሲሰደዱ ብዙ እንግልት መከራ እና ስቃይ ሲደርስባቸው በነበረበት በዚያ ዘመን የንጉሱ ግብረ አበሮች እና አድርባዮች ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ሲመዘበሩና በእሳት ሲያቃጥሉ ይህን ቤተ-ክርስቲያን ግን ለማቃጠል ቢሞክሩም በእግዚአብሔር ተዓምር የቤተክርስቲያኑን በር መክፈትም ሆነ ቤተ-ክርስቲያኑን ማቃጠል አልተቻላቸውም ነበር። ከዚያን ጊዜ በኋላም ለማንም ሊከፈት ባለመቻሉ ለ 17 ዓመት ተዘግቶ እንደቆየ አባቶች ይናገራሉ።
ገድለ አቡነ ሐራ ድንግልም የሃይማኖት መፍለስም ከሆነ ከ 16 ዓመት በኋላ በአፄ ፋሲለደስ ንጉስ ትዕዛዝ ሃይማኖት እንደቀድሞዋ ሆነች የሮም ሃይማኖትም ፈለሰች በማለት ያስረዳል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም ወደ እርሳቸው ከመጡ መነኮሳት ጋር ተሰብስበው ወደ ቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርስቲያን ሄደው በመፀለይ ለ 17 ዓመት ተዘግቶ የነበረ ቤተ-ክርስቲያን ተከፈተላቸው። በአንድነትም ቆሙ በማህሌትና በእልልታ በከበሮና በጸናጽንም አመስግነው የጌታችንና የመድሓኒታችንን ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው ወደ በዓታቸው እንደተመለሱ ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ይናገራል።
ቅዱሱ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ከአረፉ በኋላ ግን ይህ ቤተክርስቲያን ሰው በማጣት ጠፍ የአራዊት መኖሪያ ሆኖ ለ 400 ዓመት እንደቆየ አባቶች ይናገራሉ። ምንም እንኳን ይህ ቦታ የአራዊት መኖሪያ ቢሆንም ቅዱሳን ግን እንዳልተለዩት የአካባቢው ነዋሪዎችና የቀደሙ አባቶች ይናገራሉ። የቤተክርስቲያን ደወል እና የእጣን መዓዛ ይሸታቸው እንደነበርም ይመሰክራሉ።
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም እገዛ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ትብብር ዛሬ ያለው መቃረቢያ (መቃኞ) ተሰርቶ ታቦቱ ለመግባት ችሏል። 
የቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ በዓሉ ህዳር ፲፭ ቀን በድምቀት ይከበራል። በዚህች ቀንም ሰኔ ፲፭ ቀን ቅዳሴ ቤቱ ይከብራል።
የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ በረከት እና ረድኤት አይለየን
ሚናስ ሚናስ ይላል
ደቂቀ ሐብተ ማርያም
ሚናስ ሚናስ ይላል

ሚናስ ሚናስ ይላል አንደበቴ /፪/
አማልዶኛልና ከሰማዩ አባቴ
ሚናስ ሚናስ ይላል አንደበቴ

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል ምድርና ሰማዩ
ሚናስ(2) ይላል ተዓምርህን ይንገሩ
ሚናስ(2) ይላል ፍጥረታት በሙሉ
ሚናስ(2) ይላል ለክብሩ ዘምሩ

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል ለእምነትህ መቆምህ
ሚናስ(2) ይላል አድርሶሃል ለሞት
ሚናስ(2) ይላል ሲቆረጥ አንገትህ
ሚናስ(2) ይላል ፈሶሀል ደም ወተት

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል በሰራኸው መቅደስ
ሚናስ(2) ይላል በረከት ጠገቡ
ሚናስ(2) ይላል አቡነ ሐራ ድንግል
ሚናስ(2) ይላል ቀድሰው ቆረቡ

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
ሚናስ(2) ይላል ያከበርከው ጌታ
ሚናስ(2) ይላል ከፍከፍ በልልን
ሚናስ(2) ይላል በአለም አንስቶ
ሚናስ(2) ይላል በሚናስ ባረከን

አዝ-----

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/

አምላከ ሚናስ ደስ ይላል/፪/
የሰማዕቱ ልጆች አርጎናል/፪/
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ነገስታት ካህናት ነቢያት ሁነን ተሹመናል

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደፃፈው

ልጆቼ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን ተሰኝተን ከማህፀነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ስንወለድ ነገስታት፣ ካህናት፣ ነቢያት ሁነን ተሹመናል።

"አባታችን ዛሬ ደግሞ ምን እያልከን ነው?" ትሉኝ ይሆናል  እኔም እንዲህ ብየ እመልስላችኋለሁ

👉 ራሳችንን እንድንገዛ፣ ያሻነውን እንድንፈርድ ነገስታት ሆነን ተሹመናል
👉 ከክርስቶስ ጋር ለዚህ አለም ስራ ሞተን ራሳችንን የተወደደ መስዋዕት አድርገን ለአምላካችን እናቀርብ ዘንድ ካህናት ሆነን ተሹመናል (2ኛ ጢሞ 2፦3)
👉 ዳግመኛም ሊመጣ ያለውን ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ መነፀርነት  እንድናውቅ ነቢያት ሆነን ተሹመናል።

📌 ወታደሮች ወደ አንድ ማዕረግ ሲሰጣቸው ልዩ የሆነ ማህተም እንደሚደረግላቸው ሁሉ እኛ ክርስቲያኖችም ነገስታት ካህናትና ነቢያት ሁነን ለመሾማችን ይህን ማዕረግ ባገኘንበት በአርባና በሰማኒያ ቀናችን የመንፈስ ቅዱስ ማህተም ታትሞብናል።

ስለዚህ ንግስናችንን ክህነታችንን ነቢይነታችንን በንፅህና በቅድስና እንያዘው

ሰማዕትነት አያምልጣችሁ ገፅ138

ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
ባሳለፍነው ቅዳሜ "የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች እና መፍትሔዎቻቸው" በሚል ርዕስ የተካሄደው የጉባኤ አናሲሞስ ጉባኤ ክፍል 2 በቀጣይ ቅዳሜ ማለትም ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ስለሚቀጥል እንድንገኝ ይሁን።

መልእክቱን ላላዩት ይዳረስ ዘንድ ሼር አድርጉ።

ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
ካለፈው ሳምንት የሚቀጥለው የጉባኤ አናሲሞስ ክፍል 2 መርሐ ግብር ነገ 11:00 ስለሆነ በሰዓት እንድንገኝ ይሁን።

ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት