“ዐይን ይጹም፣ ጆሮ ይጹም፣ አንደበት ይጹም”
መምህር ጌታቸው በቀለ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጾም ወራት ጥሉላት መባልዕትን ከመመገብ የሚከለክለውን ጾም ብቻ በማወጅ አታቆምም፡፡ ልጆቿ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ ከምቀኝነት በመጾም የመንግሥተ ሰማይት ዜጎችን እንዲሆኑ ትምህርቷን ትናኛለችም እንጂ፡፡
ክርስቲያን ምንጊዜም ከኃጢአት ርቆ፣ ከበደል ተጠበቆ በቅድስና በንጽሕን መኖር አለበት፡፡ ይህም ከኃጢአት፣ ከክፋት፣ ከርኩሰት የምንጾመው ጾም ፋሲካና ቅበላ የሌለው የዕድሜ ልክ ጾም ነው፡፡ የህም የዐይን፣ የአንደበት፣ የጆሮ፣ የእጅ፣ የእግር፣ የኅሊና ወዘተ… ጾም ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “ይጹም ዓይን፤ ይጹም ልሳን፤ ዕዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ሕሡም በተፋቅሮ - ዓይን ክፉ ከማየት ይጹም አንደበት ክፉ ከመናገር ጆሮም ክፉ ከመስማት ይጹም“ በማለት ገልጾታል። ሊቁ በዐይን በአንደበትና ጆሮ መነሻነት መላ ሕዋሶቻችን በፍቅር ሆነው መጾም እንዳለባቸው ገልጾልናል፡፡
ዐይን ይጹም
ማየት የኃጢአት መጀመሪያ ነውና ዐይናችን ክፉ ከማየት መቆጠብ ይኖርበታል። ማየት የልቡናን ፍላጎት ስለሚቀሰቅስ ኃጢአትን ወደመሥራት ይወስደናል። የያዕቆብ ልጅ ዲና ከአሕዛብ ወገን የምትሆን ጓደኛዋን ለማየት ብላ ወደማይመስሏት ሰዎች ሄደች በዚያም የአሕዛብ ወንድ አይቶ ተመኛት ከእርሱም ጋር በዝሙት በመውደቅዋ ለራሷም ጥፋት እና ለወንድሞቿ የጥል መንስኤ ሆናለች /ዘፍ. ፴፬/። ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር ሴትን አይቶ የተመኛት ሁሉ በልቡ አመነዘረ ብሏል /ማቴ.፭፥፳፰/፡፡ ማር ይስሐቅ “ኃጢአትን ወደ መውደድ አንተን ከሚስቡህ ከማየት ከመስማት ተጠበቅ” ሲል ይመክራል፡፡

ዐይን ካላየ ልብ አይመኝምና እንዲህ አለ፡፡ በዐይን ክፉ ነገርን ማየት ስሜትን ይቀሰቅሳል፣ ምኞትንም ያሳድራል ማየት የኃጢአት ምንጭ ነው፡፡
ሰው በዐይኑ አይቶ በልቡ ይመኛል፡፡ ምኞትም ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፣ ኃጢአትም ከአደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች፣ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች/ያዕ.፩፥፲፬/፡፡ ስለዚህ ከማየት የተነሣ ከሚመጣ ምኞት ጋር ታግሎ ማሸነፍ ይገባል፡፡ ከማየት የተነሣ ምኞት መጓጓት ይመጣል፡፡ ምኞቱም በሰው ልብ ውስጥ በተሰጠው መጠን የሰውን ፈቃደኝነት ያገኛል፣ ስለ እርሱ በታሰበ መጠንም በልብ ውስጥ ያድጋል፣ ከዚያም ስለ ወደ መጎምዠት፣ ቀጥሎም በተግባር ወደ መፈጸም ያደርሳል፡፡ ስለዚህ አይቶ ከመመኘት መሸሽና ማምለጥ አስፈላጊ ነው፡፡ አንጋረ ፈላስፋ ገጽ 76-77፤ ስለዚህ “ዐይንን ክፉ ከማየት አይቶ ከመመኘትና ከመጎምዠት ከመስረቅም ማስጾም” ይገባል፡፡ ስለዚህ በዐይናችን መጽሐፍ መመልከትን የዘወትር ተግባራትን ማድረግ ይገባል፡፡ ክቡር ዳዊት በቀንና በሌሊት ሕጉ የተጻፈበትን መጽሐፍ የሚመለከት ሰው ንዑድ ክቡር ነው እንዲል/መዝ.፩፥፪-፫/፡፡ ስለዚህ በምንጾምበት ወቅት ክፉ ከማየት መቆጠብ ይኖርብናል። መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊፈትንና ክፉ ምኞትን ሊቀሰቅስ ወደ ሚችል ነገር ማተኮር ተገቢ አይደለም። በመሆኑም ዛሬ በቴክኖጂ አማካኝነት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊፈትኑ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ እንደ ክርስቲያንነታችን ከነዚህ ሁሉ ልንጾም ይገባናል።
ጆሮ ይጹም
ለሰውነታችን እርስ በርሱ ነገር ለነገር ተስማምቶ ጠባይ ለጠባይ ተግባብቶ የሚኖርበት ጆሮ አለው፡፡ ጆሮ ንቁ ከሆነ ጠላት ቤት ሊያቃጥል፣ ሌባ ገንዘብ ሊዘርፍ፣ አውሬም እንስሳትን ሊነጥቅ ሲመጣ ከሩቅ ሰምቶ ሌሎች ሕዋሳትን ለውጊያ እንዲዘጋጁ፣ ለጠላት እንዳይሸነፉ ያነቃቸዋል፡፡ ጆሮ ቢደነቁር የነገሩትን ትቶ ያልነገሩትን ይመልሳል፣ ያዘዙትን ሳይሆን፣ ያላዘዙትን ይሠራል፣ ያልተነገረውን የተነገረ አስመስሎ አቅርቦ ከሰው ያጣላል፡፡
ሕዝበ እስራኤልን በባርነት ከነበሩበት ከግብጽ ምድር አውጥቶ፣ ባሕር አሻግሮ በምድረ በዳ መና ከሰማይ እየመገበ፣ ውኃ ከአለት እያፈለቀ፣ መዓልቱን በደመና ሌሊቱን በፋና እየመራ ያደረሳቸውን አምላክ ከሐሰተኛ ሰዎች በሰሙት ክፉ ወሬ ብቻ ተሰናክለው የእግዚአብሔርን ኃይልና ረድኤት ዘንግተው እንደገና ወደ ግብጽ መመለስ በመመኘታቸው የተስፋዋን ምድር እንዳያዩ ሆነዋል /ዘዳ.፲፫፥፲፬/። አበው “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይበልጣል” እንዲሉ፣ እንደ እስራኤላውያን ለክፉ ወሬ ጆሯችንን መስጠት አገልግሎታችንን ሊጎዳ ብሎም በሃይማኖታችን ላይ ኑፋቄን ሊያመጣብን ስለሚችል፣ ጆሯችን ከክፉ ወሬ እንዲጾም ማድረግ ይገባል:፡
ጆሮ ከንቱን ሐሰት የሆነውን ነገር ለመስማት አቀርቅሮ ከማድመጥ ሊጾም ይገባዋል፡፡ ማር ይስሐቅ “ለነፍስህ ድንቁርናን የሚያመጣ ልስማ ልስማ ልናገር ልናገር ማለት ነው” ይላል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊም “የፈቲውን ጾር የሚያሳስብህ ገንዘብ ልይ ልይ ልስማ ልስማ ማለትን ቢያሳስብህ ወግድ በለው” ሲል ይመክራል፡፡ ጆሮ የሚሰማውን ሊመርጥ ያስፈልገዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ከዘፈን መዝሙርን መስማት ሊመርጥ ይገባዋል፤ ምክንያቱም ሰው በቤቱም ይሁን በሌላ ሥፍራ ሥራ ፈትቶ ተቀምጦ ዘፈን በሚያዳምጥበት ሰዓት የዝሙት መንፈስ በሕሊናው ሊቀረጽ ይችላልና፡፡ መስማት ስለ ሰሙት ነገር ማሰብን ከዚያም ያንን ነገር መፈለግና መመኘትን ወደ መፈጸም ያደርሳል፡፡ ምኞትም ውሎ ሲያድር ገቢር ኃጢአትን ወደ መፈጸም ያደርሳል፡፡ ስለዚህ ከመስማት የተነሣ ድቀት እንዳያገኘን የምንሰማውን ነገር መምረጥና መለየት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ሲባል ጆሮአችን ምንም እንዳይሰማ እንድፈነው ማለት አይደለም፡፡ ሰምቶ እንደማይጠቀም ዐውቆ መተው ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ ክፉ ነገርን ከመስማት መታቀብ ከጸዋሚው የሚጠበቅ ነው፡፡ ለመስማት የሚያስገድድ ሁናቴ ቢያጋጥመው እንኳ ሐሳቡን እንዳይሰጠው መሆን ነው፡፡
ከዚህም በላይ የሐሰት ወሬ፣ የተሳሳተ ፍርድና የመሳሰለውን እንዳይሰሙ መሆን ነው፡፡ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ የተሳሳቱ ቃላትን ሲናገርና ያለ ርኅራኄ ሲተቸው ጆሮን ከፍቶ መስማት ለድርጊቱ ተባባሪ መሆን ነውና፡፡ ቅዱስ ሙሴ ጸሊም “ስም ከሚያጠፉ ሰዎች ጋር አትሂድ፣ በምንም ሰው ላይ የተደረገ ስም ማጥፋትን አትመን” ብሏል፡፡ ሰሚው በሰማው ነገር አእምሮውና ልቡናው ሊረክስና በክፉው ነገር ሊረበሽ ይችላል፡፡ የሰማውን ነገር ሳያጣራ እውነት ነው ብሎ ከተቀበለም ከነዚያ ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት የሻከረ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሰውን ጥፋትና በደል ከመስማት መጾም ይገባል፡፡ በአጋጣሚ ብንሰማም እንኳ የሚወራውን ወሬ ርእስ መቀየር ካልሆነም ቸር መሐሪ እግዚአብሐር በእርሱም ሆነ በእኛ ላይ ምሕረቱን እንዲያደርግ እንጸልይ በማለት ነገሩን መቅጨት ይቻላል፡፡ ቅዱስ ባሕታዊ ኢሳይያስ እንዲህ ይላል፡- “በባሕርይ ከአንተ አንድ የሚሆን የወንድምህን ኃጢአት ለመስማት ወይም ሰምተህ እርሱን ለማውገዝ አትፍቀድ” ብሏል፡፡ ቅዱስ ይስሐቅ “እሳት ከአንተ ወጥታ ሌሎችን ብታቃጥል በተናገርካቸው ክፉ ቃላት ስለተቃጠሉት ነፍሳት እንደሚጠይቅህ ዕወቅ፡፡ እሳት ባትወረውር ዳሩ ግን በሌላ ሰው እንዲወረወር ብትስማማና እሳቱ በመለኮሱ ብትደሰት ከእሳት ለኳሹ ጋር ተካፍለሃል” በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲያውም በጾም ወቅት ከምንጊዜውም በበለጠ ገድለ ቅዱሳንን ልንሰማ፣ ልናሰማ ይገባናል፤ ምክንያቱም የቅዱሳን ጽናትና ተጋድሎ የእኛን ሕይወት የምንመዝንበት፣ ተጋድሏቸውን በማሰብ የምንጸናበት ሕይወትን እናገኝ ዘንድ ይረዳናል።

አንደበት ይጹም
ሰው የመባልዕትን ጣዕም ቀምሶ የሚለይበት ተናግሮ ሐሳቡን የሚገልጥበት አፍ፣ ምላስ አለው፡፡ ለክርስትናውም ሐሳቡን የሚገልጥበት አፍ ምላሱ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋግሮ ሐሳቡን ለእግዚአብሔር መግለጥ ነው፡፡ አንደበት ከቁጣ፣ ከጠብ፣ ክርክር፣ ከጭቅጭቅ በሰው ከመፍረድ፣ ከመራገም፣ ከንትርክና ከመሳሰለው ሁሉ ሊጾም ይገባዋል፡፡ ክቡር ዳዊት “በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ” በማለት ተናግሯል /መዝ.፴፰፥፩/፡፡ ሲራክም “ለአንደበቴ ጠባቂ ማን በሰጠኝ፣ ለከንፈሬስ የጥበብ ፍጻሜ የምትሆን አርምሞን ማን በሰጠኝ በሊህ ክፉ ነገር ተናግሬ እንዳልጠፋ አንደበቴም ክፉ ተናግሮ መከራ እንዳያመጣብኝ” በማለት ባልገለጸ ነበር/ሲራ.፳፪፥፳፯/፡፡ ይህ ማለቱም አንደበት በተናገረው ፊት ይጸፋል፣ ጀርባ ይገረፋል በሰውነት ይቀጣል፣ እጅ እግር ይቆረጣልና ነው፡፡“አንደበትም እሳት ነው፡፡ አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፣ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፣ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፣ በገሃነምም ይቃጠላል፡፡ የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፣ ደግሞም ተገርቷል፤ ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው” /ያዕ.፫፥፮—፰/፡፡ “የእህል ጣዕም በጉረሮ፣ የነገር ጣዕም በጆሮ እንዲሉ” ክርስቲያን በዘመኑ ሁሉ ከአንደበቱ ክፉ ነገር መነገር የለበትም፡፡
የሰው ክብሩ፣ አሳሩ፣ መከራው፣ ውርደቱ በቃሉ አነጋገር ነው /ሲራ.፭፥፲፬/፡፡ ሰው ከቃሉ የተነሣ ይጸድቃል፣ ከቃሉም የተነሣ ይኮነናል/ማቴ.፲፪፥፴፯/፡፡ ሕይወትና ሞት በአንደበት እጅ ናቸው፡፡ ስለዚህ “አፉን ክፉ ከመናገር የሚጠብቅ ሰው ሰውነቱን ከመከራ እንደ አደራ ይጠብቃታል” ነገር ግን አገኝ አጣውን የሚቀባጥር ራሱን ያዋርዳል፣ ያስነቅፋልም፣ ለነገሩም መውደድ የለውም፡፡ “በአንደበትህ ክፉ ተናግረህ ከምትሰናከል በእግርህ ተሰናክለህ ብትወድቅ ይሻልሃል ክፉ ከመናገር ክፉ መከራ ሆኖ ይመጣልና”/ሲራ.፳፥፲፰/፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊም “አንደበቱን ከቧልት፣ ከሐሜት ያየውን መስጢር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቡናውን ከሐልዮ ኃጢአት ያርቀዋል” ይላል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም “ከከንፈሩ ክፉ ነገር ከመናገር የማይታገስ ሰው በመከራ ይሰነካከላል”፤“ክፉ ነገርን ለመናገር የሚቸኩል ሰው ራሱን ያጠፋል” ብሏል/ምሳ.፲፥፰/፡፡
በጾም ወቅት አርምሞን ገንዘብ ማድረግ ይገባናል። አርምሞ የሌለበት ጾም ዋጋ አይኖረውም “ዝምታ፣ መታገስ ሃይማኖትን ትጠብቃለች” እንዳለ ቅዱስ ያሬድ። እንጾማለን እያልን ወንድማችንን በማማት የምንጎዳ ከሆነ ጾማችን እርባና አይኖረውም። “የወንድምህን በደል ባሰብክ ጊዜ ተነሥተህ ጸልይለት በቆራጥ ልቦና ይቅር በልለት” /ጾመ ድጓ ዘወረደ/፤ ምክንያቱም ጾም አፍቅሮ ቢጽን የምናጎለብትበት ዓይነተኛው መሣሪያ ነውና። ወንድምን በክፉ ከማንሳት ይልቅ ስለ ወንድምና እህታችን ብለን መጸለይ እና ይቅር ማለት ከእግዚአብሔር ዘንድ የይቅርታ በር እንዲከፈትልን ያደርግልናል።
እንደ ማጠቃለያ
በአጠቃላይ በጾም ወራት ክፉ ከመሥራት፣ ክፉ ከማየት፣ ክፉ ከመናገር ተቆጥቦ ራስን ገዝቶ ወደ ፈጣሪ መቅረቡ እጅግ መልካም ነው፡፡ በፍስክ ጊዜያት ጥሉላት መባልዕትን ለመብላት እንደሚፈቀድ ሁሉ፤ በጾም ወራት የተውናቸውንም ክፉ ግብራት ለመሥራት እንደ ተፈቀደ አድርገን ወደ ቀደሚ አነዋወራችን ከመመለስ ልንጠበቅ ይገባናል፡፡
በጾማችን ጊዜ መለወጥ ያለበት ምግብ ብቻ ሳይሆን ሕይወታችንም ወደ ተሻለ ቅድስና ለማደግ መለወጥ ይገባዋል፡፡ የጾም ወቅት በእኛና በእግዚአብሔር መካከል እንደ ግንብ የተጋረዱ ስሕተቶችንና ድክመቶችን አስወግደን መልካም ግንኙነት የምንመሰርትበት ነው፡፡ ጾም ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች መጠቀሚያ የተሰጠ በረከት እንጂ የተቀመጠ ወግ ወይም ደንብ አይደለም፡፡ ጾም የተቀደስ ልዩ ሥራ ነው፤ የተለየ መንፈሳዊ ዕቅድንም ይፈልጋል፡፡ የጾም ዕለታት የቅድስና ሕይወትን ለመኖር ራሳችንን የምናሰለጥንባቸው ልዩ ዕለታት ናቸው፡፡ እንዲያም ከሆነ ዕለታቱ ከሌሎች ቀናት በተለየና በበለጠ ለመንፈሳዊ ተግባር መዋል ይኖርባቸዋል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዋቤ መጻሕፍት
✍️ መጽሐፍ ቅዱስ
✍️ መጽሐፈ ድጓ
✍️ ሃይማኖት አበው
✍️ ፍትሐ ነገሥት
✍️ መጽሐ መነኮሳት
✍️ አንጋረ ፈላስፋ
@EOTC

ተከታታይ ትምህርት መማር ለምትሹ ሁሉ:-
ቀዳማይ (1ኛ ደረጃ)
ካዕላይ(2ኛ ደረጃ)
ሳልሳይ (3ኛ ደረጃ)
ተከታታይ ትምህርት ቀጣይ ሳምንት የሚጀምር ስለሆነ ትምህርቱን መከታተል የምትፈልጉ ከታች የተጠየቁትን መረጃዎች በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ፡፡
👉 ሙሉ ሥም (አለማዊ)
👉 ስልክ ቁጥር
👉 አድራሻ
👉 መማር የምትፈልጉት (የምትችሉት) የት/ት ደረጃ
👇👇👇
ማሳሰቢያ ፡-
1.ከምዝገባ ውጭ አናስተናግድም
2. መማር የምትችሉት ቀዳማይ የጨረሳችሁ ካዕላይ ፤ ካዕላይ የጨረሳችሁ ሳልሳይ ነው፡፡
3. ከዚህ በፊት በተለያየ ምክንያት ተመዝግባችሁ ትምህርቱን ያልቀጠላችሁ አሁን መመዝገብና ትምህርቱን መከታተል ትችላላችሁ፡፡
4.ሳልሳይ ተከታታይ ትምህርት ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ስለሆነ ክረምቱንም ይቀጥላል ስለሆነም መማር የምትችሉት ክረምትም እዚሁ ከተማ የምትኖሩ ብቻ ናችሁ፡፡
የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል

ሰላም ለናንተ ይሁን እንዴት አመሻችሁ
ትምህርት የሚጀምርበት ቀን በተመለከተ!
👇👇👇
ቀዳማይ (1ኛ ደረጃ)
👉 የሚጀምርበት ቀን ፡- ቀጣይ ሳምንት
ሰኞ (23/06/18)
👉 የሚሰጥበት ዕለታት፡- ከሰኞ ፣
ማክሰኞ ፣ ሐሙስ ፣ አርብ
👉ቦታ፡- በርሚል አዳራሽ
👉ሰዓት ፡- 11፡30--12፡30
👇👇👇
ካዕላይ (2ተኛ ደረጃ)
👉 የሚጀምርበት ቀን ፡- በዚ ሳምንት
አርብ (20/06/18)
👉 ት/ት የሚሰጥበት ዕለታት፡- ሐሙስ ፣
አርብ ፣ ቅዳሜ ፣ እሑድ
👉ቦታ፡- G+1 BLD Under ground
👉ሰዓት ፡- 11፡30--12፡30
(እሑድ 11፡00--12፡30)
👇👇👇
ሳልሳይ (3ተኛ ደረጃ)
👉 የሚጀምርበት ቀን ፡- በዚ ሳምንት
አርብ (20/06/18)
👉 የሚሰጥበት ዕለት፡- አርብ እና ቅዳሜ
👉 ቦታ፡- አርብ ፡ ጥራር አዳራሽ
ቅዳሜ፡ በርሚል አዳራሽ
👉ሰዓት ፡-11፡30--12፡30
👇👇👇
ማሳሰቢያ ፡-
1. በሁሉም ት/ት ደረጃ የሚማር
ማንኛውም ተማሪ ት/ት
ከሚሰጥባቸው ዕለታት በተጨማሪ
ከታች በተጠቀሱት ዕለታት የመገኘት
ግዴታ አለበት
👉ረቡዕ 11፡30--12፡30 ፀሎት
መ/ግብር
👉እሑድ 08፡30--11፡00 የሰንበት ት/ት
ቤቱ ሳምንታዊ መ/ግብር
👉ቦታ፡- ትልቁ አዳራሽ
2. ያለ ምዝገባ ምንም አይነት ተማሪ
ስለማናስተናግድ ከታች በተጠቀሰው
ቀነ ገደብ ድረስ ምዝገባ
እንድትመዘገቡ እናሳስባለን!!!
👉 ቀዳማይ እስከ እሑድ 12፡00
👉 ካዕላይ እስከ አርብ 06፡00
👉 ሳልሳይ (መስፈርት የምታሟሉ ብቻ)
እስከ አርብ 06፡00
የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል
ትምህርት የሚጀምርበት ቀን በተመለከተ!
👇👇👇
ቀዳማይ (1ኛ ደረጃ)
👉 የሚጀምርበት ቀን ፡- ቀጣይ ሳምንት
ሰኞ (23/06/18)
👉 የሚሰጥበት ዕለታት፡- ከሰኞ ፣
ማክሰኞ ፣ ሐሙስ ፣ አርብ
👉ቦታ፡- በርሚል አዳራሽ
👉ሰዓት ፡- 11፡30--12፡30
👇👇👇
ካዕላይ (2ተኛ ደረጃ)
👉 የሚጀምርበት ቀን ፡- በዚ ሳምንት
አርብ (20/06/18)
👉 ት/ት የሚሰጥበት ዕለታት፡- ሐሙስ ፣
አርብ ፣ ቅዳሜ ፣ እሑድ
👉ቦታ፡- G+1 BLD Under ground
👉ሰዓት ፡- 11፡30--12፡30
(እሑድ 11፡00--12፡30)
👇👇👇
ሳልሳይ (3ተኛ ደረጃ)
👉 የሚጀምርበት ቀን ፡- በዚ ሳምንት
አርብ (20/06/18)
👉 የሚሰጥበት ዕለት፡- አርብ እና ቅዳሜ
👉 ቦታ፡- አርብ ፡ ጥራር አዳራሽ
ቅዳሜ፡ በርሚል አዳራሽ
👉ሰዓት ፡-11፡30--12፡30
👇👇👇
ማሳሰቢያ ፡-
1. በሁሉም ት/ት ደረጃ የሚማር
ማንኛውም ተማሪ ት/ት
ከሚሰጥባቸው ዕለታት በተጨማሪ
ከታች በተጠቀሱት ዕለታት የመገኘት
ግዴታ አለበት
👉ረቡዕ 11፡30--12፡30 ፀሎት
መ/ግብር
👉እሑድ 08፡30--11፡00 የሰንበት ት/ት
ቤቱ ሳምንታዊ መ/ግብር
👉ቦታ፡- ትልቁ አዳራሽ
2. ያለ ምዝገባ ምንም አይነት ተማሪ
ስለማናስተናግድ ከታች በተጠቀሰው
ቀነ ገደብ ድረስ ምዝገባ
እንድትመዘገቡ እናሳስባለን!!!
👉 ቀዳማይ እስከ እሑድ 12፡00
👉 ካዕላይ እስከ አርብ 06፡00
👉 ሳልሳይ (መስፈርት የምታሟሉ ብቻ)
እስከ አርብ 06፡00
የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ትምህርት ክፍል
🔴ለ8ኛው ዙር ጉዟችን እየተዘጋጁ ነው?
መጋቢት 18,19 እና 20(አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ)
በተቀደሰው የአብይ ጾም የዕረፍት ቀናችንን በበረከት ቦታ እናሳልፍ!
በጣና ሐይቅ በሚገኙ 19 ገዳማትና አድባራት እንባረክ!
🧾ትኬቱን
👉አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
👉አባይ ማዶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
👉ታዬ ሞላ ስቴሽነሪ
👉ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር
⭕️እስከ መጋቢት 16 ትኬቱን በእጅዎ ያስገቡ!
0902092705
0920114370
0940908594
ይደውሉልን!
🌐ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕርዳር
🛜በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ያድርሱ...
👉 Telegram
t.me/finotehiwotgroup
👉 Facebook
https://www.facebook.com/finotehiwotss
👉Email address
fenotehiwotmedia@gmail.com
👉YouTube
https://youtube.com/@finotehiwet?si=_g8FL0uKUvoyQq8U
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@finotehiwet?_t=8rt6kilIeTo&_r=1

በዛሬው እለት የጋብቻ ሥርዓታችሁን በምሥጢረ ተክሊል የፈጸማችሁ የሰ/ት/ቤታችን አገልጋይ ዲ/ን አማረ ተስፋ እንዲሁም እኅታችን ወ/ሪት መድኅን አበበ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ አላችሁ ትላለች።
ጋብቻችሁ ለጽድቅ ይሁን።
ጋብቻችሁ ለጽድቅ ይሁን።
ጾመ ሐዋርያት
(በተክለሐዋርያት)
ጾመ ሐዋርያት በወርኃ ሰኔ ስለሚጾም በምእመናን ዘንድ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፤ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማትም አንዱ ነው፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡
ይህም ጾም ከበዓለ ኀምሳ በኋላ የሚጾም ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በአርባኛው ቀን ቅዱሳን ሐዋርያት በጸሎት ይተጉ ወደ ነበረበት ቤት በመሄድ ደቀመዛሙርቱን ይዟቸው ከቤት በመውጣት መንገድ ጀመረ፡፡ እርሱ ከፊት እየመራቸው እነርሱ እየተከተሉት ወደ ረጅሙና በረጃጅም ዛፎች ወደ ተሞላው ደብረ ዘይት ተራራ ይዟቸው ወጣ፡፡ ይህንንም እየነገራቸው ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ፤ከፍ አለ፡፡ ነጭ የሆነች ብሩህ ደመናም አምላካችንን ተቀበለችው፡፡ከዓይናቸውም እየራቀ፤ከእይታቸው በርቀት ሳይሆን በርኅቀት ተሰወረባቸው፡፡ሐዋርያትም ኢየሱስ ክርስቶስን በጣም ይወዱት ስለነበር ሲለያቸው አዝነው አተኩረው ሰማዩን ለረጅም ሰዓት ተመለከቱ፡፡ ድንገትም ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ቅዱሳን መላእክት በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡መላእክትም ሐዋርያትን እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እያያችሁ ለምን ቆማችኋል፡፡ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል›› አሏቸው፤ (ሐዋ. ፩፥፰-፲፩)፡፡ ሐዋርያትም የመላእክትን ማረጋጊያ ቃል ከሰሙ በኋላ በኢየሩሳሌም ወደ ምትገኘው ቤተ መቅደስ በመሄድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸው እስኪፈጸም ድረስ ቀን ከሌሊት በአንድነት ሆነው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከመካከላቸው አድርገው በጾምና በጸሎት እየተጉ ቆዩ፡፡
የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት›› (ማቴ.፱፥፲፬)። ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ያንጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፭)፡፡
እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስም ካልተሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን አምላከ ሐዋርያት ተለመነን እያልን ለመማጸን ነው፡፡
ይህን ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ግን አብዛኛው ምእመን ‹‹የቄስ ጾም›› ነው በማለት ከጾሙ ሽሽት ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተክርስትያንን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ መስተካከል ይገባዋል፡፡
ሐዋርያትን አብነት በማድረግ ጾመን በረከትን ልናተርፍ ይገባናል፡፡
የአምላካችን የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት
የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
የቅዱሳን ሐዋርያት በረከት
የጻድቃን የሰማዕታት ጸሎት እና ምልጃ አይለየን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን፡፡
ምንጭ:- eotc.org
https://t.me/finotehiwet

Telegram
ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
#እኛ_የአቡየ_ልጆች
ማንም አላዋቂ ምንም ቢል እኛ ግን እምናገለግለውን እናቃለን እርሱም እንደ ሰው ተወልዶ እንደ መላእክት የኖረ እንደ መላእክት ኑሮ በክብር እንደ ሰው ያረፈውን በነጎድጓድ ላይ ስልጣን የተሰጠውን አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ነው።

በጉባኤ አናሲሞስ
የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ፈተናዎችና መፍትሔዎች በሚል ርዕስ በዲ/ን ደረጀ ገበያው ተካሄደ።
ጉባኤው ቤተ ክርስቲያኒቱ መፈተን እና መሰደድ የሚባለውን ደረጃ አልፋ የደረሰችበትን የመውደም ሁኔታ እውቅና መፍጠር እና እንደ አማኝ ቁጭት እንዲሰማን፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ከመሆን እንድንቆጠብ፣ አጥፊዎቻችን ለማጥፋት የጸኑበትን ልክ፤ እኛ ቤተ ክርስቲያናችንን ለመጠበቅ የምንሄድበት የስንፍና መንገድ እንድናውቅ፣ እንዲሰማን፣ የመፍትሔ አካል መሆን እንድንችል ታልሞ የተዘጋጀ ሲሆን መምህራችን ዛሬ መግቢያውን በጥቂቱ የዳሰሱልን ሲሆን በዚሁ ቀን እና ሰዓት በየ ሳምንቱ እንደሚቀጥል ታውቆ በጉባኤው ተቀሳቅሰን እንድንገኝ የትምሕርት ክፍላችን መልእክት ነው።
እግዚአብሔር አምላክ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ከመሆን ይጠብቀን
ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሚድያ ክፍል
መንፈሳዊ ተከታታይ ትምሕርት ለምትፈልጉ በሙሉ እነሆ የክረምት መርሐ ግብር ምዝገባ እስከ ሰኔ 21 ድረስ:-
1, በሰ/ት/ቤቱ ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ
2, በሰ/ት/ቤቱ ቤተ መጻሕፍት
እንዲሁም በስልክ ቁጥር 0957338408/0918208484 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
#ፍኖተ_ሕይወት ሰ/ት/ቤት

ሰማዕቱ ቅዱስ ሚና
ከቅዱሳን ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ሚና በ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተጋድሎውን የፈፀመ ግብፃዊ ሰማዕት ሲሆን ህዳር 15 ቀን የሚነበበው ስንክሳር ቅዱስ ሚናስ በሚል ስያሜ ይገልፀዋል። በሶሪያ ቋንቋ ማር የሚለው ቃል ‘ቅዱስ’ የሚልትርጉም ሲኖረው ለወንድ የሚሰጥ ቅጥያ ሲሆን ለሴት ደግሞ ማርታ ይሆናል ይሄውም ቅድስት ማለት ነው።
ቅዱስ ሚናስ ከእናቱ ከአውፌምያ እና ከአባቱ ከአውዶስዮስ ልዩ ስሙ ኒቆስ ሻቲ በተባለ መንደር በ 276 ዓ∙ም ተወለደ። እናቱ አውፌምያ ልጅ መውለድ ባለመቻሏ ታዝንና ትጨነቅ ነበር። ወደ ቤተ-ክርስቲያን ስትሄድም እናቶች ልጆቻቸውን ሲያቆርቡ ስታይ በማልቀስ ፈጣሪዋን ልጅ እንዲሰጣት ትለምን ነበር። ግዚአብሔርም የልመናዋን ቃል ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጣት።
አባቱ አውዶስዮስ የናይል ዴልታ አስተዳዳሪ የነበረ ሲሆን ለህዝቡ ባለው ፍቅርና ሐዘኔታ ንዲሁም በትክክለኛ ፍርድ ሰጭነቱ በአካባቢው ሰው ተወዳጅነትን ያተረፈ ሰው ነበር። አውፌምያም እግዚአብሔርን የምትፈራና ባለቤቷ በሚፈፅማቸው ቀና ምግባሮች ሁሉ ከጎኑ ሆና የምትደግፈውና የምታበረታታው ሴት ነበረች።
ቅዱስ ሚናስ ወላጆቹን ያጣው በልጅነት ጊዜው ሲሆን ከወላጆቹ የወረሰውንም ሃብትና ንብረት በመሸጥና ለድሆች በማከፋፈል እሱ ግን ይህችን አለም ንቆ መነነ። በዘመኑ በነበሩ ጣዖት አምላኪ ነገስታት ተይዞ ለጣዖት አልሰግድም በማለቱ አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ ይህም የሆነው በ 24 ዓመቱ ነው።
ማር ሚና (ቅዱስ ሚናስ) በኢትዮጵያ ብዙም ባይታወቅም በጣና ቂርቆስ ከሰማዕቱ ከቅዱስ ቂርቆስና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጋር መቅደስ ታንፆለት እንደነበር
"ጠቢበ ጠቢባን ቂርቆስ ወእማዕምራን ማዕምር
ሐውፃ ለመቅደስከ እንተ ተሃንፀት በባህር፡
ምስለ እስጢፋኖስ ሰማዕት ወሚናስ ፍቁር።" የሚለው የመልክዐ ቂርቆስ ንባብ ምስክር ነው።
የጠቢባን ጠቢብ የአዋቂዎች አዋቂ የምትሆን ቂርቆስ ሆይ ከሰማዕቱ እስጢፋኖስ
ና ከተወዳጁ ከሚናስ ጋር በባህር ላይ የታነፀች መቅደስህን ጎብኛት ማለት ነው። እዚሁ መልክዕ ውስጥ በግብፅ በታወቀው የስም አጠራሩ "ሚና" በማለት የሚጠራውን ንባብ እናገኛለን።
"ሰላም ዕብል ዘምስለ ካልዕከ ሚና ፤
ቂርቆስ ሕፃን ዘእያብፅሕኮ ውርዝውና"
ለጉልምስና ያልበቃህ ሕፃን ቂርቆስ ሆይ ከጓደኛህ ከሚና ጋር ሰላም እልሃለሁ (ሰላምታ ላንተ ይሁን) ማለት ነው።በማለት በካይሮ አባስያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅድስት ማርያም ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀው የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ እና የፓትርያሪክ ቄርሎስ ፮ኛ የህይወት ታሪክ በሚል የተዘጋጀው መፅሃፍ ይገልጻል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኘው ብቸኛው የቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርሰቲያን ምን ያህል ያውቃሉ?
የቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርሰቲያን ከባህር ዳር ከተማ በግምት 23 ኪ∙ሜ ርቀት ላይ በምዕራብ ጎጃም እና በደቡብ ጎንደር መሀከል ወይም በደራ ክፍለሃገር ከአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም በግምት ከ3-4 ኪ∙ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን አካባቢውም በተለምዶ ሚናስ እየተባለ ይጠራል።
ቤተ-ክርስቲያኑ የተተከለበት ዘመን በውል ባይታወቅም ቤተክርስቲያኑ ግን በአፄ ፋስልዘመነ መንግስት እንደነበር ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ያስረዳል።
በአፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በ 1597 ዓ∙ም በነበረው የሐይማኖት መፋለስ ቅዱሳን በሃይማኖታቸው ሲሰደዱ ብዙ እንግልት መከራ እና ስቃይ ሲደርስባቸው በነበረበት በዚያ ዘመን የንጉሱ ግብረ አበሮች እና አድርባዮች ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ሲመዘበሩና በእሳት ሲያቃጥሉ ይህን ቤተ-ክርስቲያን ግን ለማቃጠል ቢሞክሩም በእግዚአብሔር ተዓምር የቤተክርስቲያኑን በር መክፈትም ሆነ ቤተ-ክርስቲያኑን ማቃጠል አልተቻላቸውም ነበር። ከዚያን ጊዜ በኋላም ለማንም ሊከፈት ባለመቻሉ ለ 17 ዓመት ተዘግቶ እንደቆየ አባቶች ይናገራሉ።
ገድለ አቡነ ሐራ ድንግልም የሃይማኖት መፍለስም ከሆነ ከ 16 ዓመት በኋላ በአፄ ፋሲለደስ ንጉስ ትዕዛዝ ሃይማኖት እንደቀድሞዋ ሆነች የሮም ሃይማኖትም ፈለሰች በማለት ያስረዳል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም ወደ እርሳቸው ከመጡ መነኮሳት ጋር ተሰብስበው ወደ ቅዱስ ሚናስ ቤተ-ክርስቲያን ሄደው በመፀለይ ለ 17 ዓመት ተዘግቶ የነበረ ቤተ-ክርስቲያን ተከፈተላቸው። በአንድነትም ቆሙ በማህሌትና በእልልታ በከበሮና በጸናጽንም አመስግነው የጌታችንና የመድሓኒታችንን ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለው ወደ በዓታቸው እንደተመለሱ ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል ይናገራል።
ቅዱሱ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ከአረፉ በኋላ ግን ይህ ቤተክርስቲያን ሰው በማጣት ጠፍ የአራዊት መኖሪያ ሆኖ ለ 400 ዓመት እንደቆየ አባቶች ይናገራሉ። ምንም እንኳን ይህ ቦታ የአራዊት መኖሪያ ቢሆንም ቅዱሳን ግን እንዳልተለዩት የአካባቢው ነዋሪዎችና የቀደሙ አባቶች ይናገራሉ። የቤተክርስቲያን ደወል እና የእጣን መዓዛ ይሸታቸው እንደነበርም ይመሰክራሉ።
የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በአቡነ ሐራ ድንግል ገዳም እገዛ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ትብብር ዛሬ ያለው መቃረቢያ (መቃኞ) ተሰርቶ ታቦቱ ለመግባት ችሏል።
የቅዱስ ሚናስ ዓመታዊ በዓሉ ህዳር ፲፭ ቀን በድምቀት ይከበራል። በዚህች ቀንም ሰኔ ፲፭ ቀን ቅዳሴ ቤቱ ይከብራል።
የሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ በረከት እና ረድኤት አይለየን