ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕር ዳር
251 subscribers
1.96K photos
16 videos
90 files
159 links
#እኛ_የአቡየ_ልጆች
ማንም አላዋቂ ምንም ቢል እኛ ግን እምናገለግለውን እናቃለን እርሱም እንደ ሰው ተወልዶ እንደ መላእክት የኖረ እንደ መላእክት ኑሮ በክብር እንደ ሰው ያረፈውን በነጎድጓድ ላይ ስልጣን የተሰጠውን አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ነው።

ለማንኛውም አስተያየት👉 0902092705- @finotehiwotdk
Download Telegram
Forwarded from የባሕር ዳር ደ/ም/ቅ/ኪዳነ ምሕረት ሰ/ት/ቤት (ደብረ ምሕረት ሚዲያ DMK Media (ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሰንበት ት/ቤት) ባሕር ዳር)
በዛሬው ዕለት ከጋምቢ ሜዲካል እና ቢዝነስ ኮሌጅ በሜዲካል ላብራቶሪ ለተመረቅሽው እኅታችን ቤተ ልሔም ሞላ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ ያለሽ ትላለች።
በዛሬው ዕለት ከጋምቢ ሜዲካል እና ቢዝነስ ኮሌጅ በBSC ነርስ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በማዕረግ ላጠናቀቅሽው እኅታችን ሰናይት አብርሃም ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ ያለሽ ትላለች።
በዛሬውዕለት ከጋምቢ ሜዲካል እና ቢዝነስ ኮሌጅ በሜዲካል ላብራቶሪ ለተመረቅሽው እኅታችን የምስራች ደረጀ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት እንኳን ደስ ያለሽ ትላለች።
"ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ"መዝ.117፥26

በዛሬው ዕለት በሰንበት ት/ቤታችን ለተከታታይ 3 ወራት በቀዳማይ እና በካልዓይ በሁለቱም የት/ት ደረጃዎች ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ሲያስተምራቸው የነበሩ ከ100 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎቹን አስመርቋል።

ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!!!

"ትጉ በሃይማኖት ቁሙ ታገሱ ጽኑ ሁሉን በፍቅር አድርጉ"1ኛቆሮ. 16፥3

🌐ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ባሕርዳር

🛜በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ያድርሱ...

👉 Telegram
t.me/finotehiwotgroup
👉 Facebook
https://www.facebook.com/finotehiwotss
👉Email address
fenotehiwotmedia@gmail.com
👉YouTube
https://youtube.com/@finotehiwet?si=_g8FL0uKUvoyQq8U
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@finotehiwet?_t=8rt6kilIeTo&_r=1
“ዐይን ይጹም፣ ጆሮ ይጹም፣ አንደበት ይጹም”

መምህር ጌታቸው በቀለ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጾም ወራት ጥሉላት መባልዕትን ከመመገብ የሚከለክለውን ጾም ብቻ በማወጅ አታቆምም፡፡ ልጆቿ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ ከምቀኝነት በመጾም የመንግሥተ ሰማይት ዜጎችን እንዲሆኑ ትምህርቷን ትናኛለችም እንጂ፡፡
ክርስቲያን ምንጊዜም ከኃጢአት ርቆ፣ ከበደል ተጠበቆ በቅድስና በንጽሕን መኖር አለበት፡፡ ይህም ከኃጢአት፣ ከክፋት፣ ከርኩሰት የምንጾመው ጾም ፋሲካና ቅበላ የሌለው የዕድሜ ልክ ጾም ነው፡፡ የህም የዐይን፣ የአንደበት፣ የጆሮ፣ የእጅ፣ የእግር፣ የኅሊና ወዘተ… ጾም ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው “ይጹም ዓይን፤ ይጹም ልሳን፤ ዕዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ሕሡም በተፋቅሮ - ዓይን ክፉ ከማየት ይጹም አንደበት ክፉ ከመናገር ጆሮም ክፉ ከመስማት ይጹም“ በማለት ገልጾታል። ሊቁ በዐይን በአንደበትና ጆሮ መነሻነት መላ ሕዋሶቻችን በፍቅር ሆነው መጾም እንዳለባቸው ገልጾልናል፡፡

ዐይን ይጹም

ማየት የኃጢአት መጀመሪያ ነውና ዐይናችን ክፉ ከማየት መቆጠብ ይኖርበታል። ማየት የልቡናን ፍላጎት ስለሚቀሰቅስ ኃጢአትን ወደመሥራት ይወስደናል። የያዕቆብ ልጅ ዲና ከአሕዛብ ወገን የምትሆን ጓደኛዋን ለማየት ብላ ወደማይመስሏት ሰዎች ሄደች በዚያም የአሕዛብ ወንድ አይቶ ተመኛት ከእርሱም ጋር በዝሙት በመውደቅዋ ለራሷም ጥፋት እና ለወንድሞቿ የጥል መንስኤ ሆናለች /ዘፍ. ፴፬/። ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ሲያስተምር ሴትን አይቶ የተመኛት ሁሉ በልቡ አመነዘረ ብሏል /ማቴ.፭፥፳፰/፡፡ ማር ይስሐቅ “ኃጢአትን ወደ መውደድ አንተን ከሚስቡህ ከማየት ከመስማት ተጠበቅ” ሲል ይመክራል፡፡
ዐይን ካላየ ልብ አይመኝምና እንዲህ አለ፡፡ በዐይን ክፉ ነገርን ማየት ስሜትን ይቀሰቅሳል፣ ምኞትንም ያሳድራል ማየት የኃጢአት ምንጭ ነው፡፡

ሰው በዐይኑ አይቶ በልቡ ይመኛል፡፡ ምኞትም ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፣ ኃጢአትም ከአደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች፣ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች/ያዕ.፩፥፲፬/፡፡ ስለዚህ ከማየት የተነሣ ከሚመጣ ምኞት ጋር ታግሎ ማሸነፍ ይገባል፡፡ ከማየት የተነሣ ምኞት መጓጓት ይመጣል፡፡ ምኞቱም በሰው ልብ ውስጥ በተሰጠው መጠን የሰውን ፈቃደኝነት ያገኛል፣ ስለ እርሱ በታሰበ መጠንም በልብ ውስጥ ያድጋል፣ ከዚያም ስለ ወደ መጎምዠት፣ ቀጥሎም በተግባር ወደ መፈጸም ያደርሳል፡፡  ስለዚህ አይቶ ከመመኘት መሸሽና ማምለጥ አስፈላጊ ነው፡፡ አንጋረ ፈላስፋ ገጽ 76-77፤ ስለዚህ “ዐይንን ክፉ ከማየት አይቶ ከመመኘትና ከመጎምዠት ከመስረቅም ማስጾም” ይገባል፡፡ ስለዚህ በዐይናችን መጽሐፍ መመልከትን የዘወትር ተግባራትን ማድረግ ይገባል፡፡ ክቡር ዳዊት በቀንና በሌሊት ሕጉ የተጻፈበትን መጽሐፍ የሚመለከት ሰው ንዑድ ክቡር ነው እንዲል/መዝ.፩፥፪-፫/፡፡ ስለዚህ በምንጾምበት ወቅት ክፉ ከማየት መቆጠብ ይኖርብናል። መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊፈትንና ክፉ ምኞትን ሊቀሰቅስ ወደ ሚችል ነገር ማተኮር ተገቢ አይደለም። በመሆኑም ዛሬ በቴክኖጂ አማካኝነት መንፈሳዊ ሕይወታችንን ሊፈትኑ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ እንደ ክርስቲያንነታችን ከነዚህ ሁሉ ልንጾም ይገባናል።

ጆሮ ይጹም

ለሰውነታችን እርስ በርሱ ነገር ለነገር ተስማምቶ ጠባይ ለጠባይ ተግባብቶ የሚኖርበት ጆሮ አለው፡፡ ጆሮ ንቁ ከሆነ ጠላት ቤት ሊያቃጥል፣ ሌባ ገንዘብ ሊዘርፍ፣ አውሬም እንስሳትን ሊነጥቅ ሲመጣ ከሩቅ ሰምቶ ሌሎች ሕዋሳትን ለውጊያ እንዲዘጋጁ፣ ለጠላት እንዳይሸነፉ ያነቃቸዋል፡፡ ጆሮ ቢደነቁር የነገሩትን ትቶ ያልነገሩትን ይመልሳል፣ ያዘዙትን ሳይሆን፣ ያላዘዙትን ይሠራል፣ ያልተነገረውን የተነገረ አስመስሎ አቅርቦ ከሰው ያጣላል፡፡
ሕዝበ እስራኤልን በባርነት ከነበሩበት ከግብጽ ምድር አውጥቶ፣ ባሕር አሻግሮ በምድረ በዳ መና ከሰማይ እየመገበ፣ ውኃ ከአለት እያፈለቀ፣ መዓልቱን በደመና ሌሊቱን በፋና እየመራ ያደረሳቸውን አምላክ ከሐሰተኛ ሰዎች በሰሙት ክፉ ወሬ ብቻ ተሰናክለው የእግዚአብሔርን ኃይልና ረድኤት ዘንግተው እንደገና ወደ ግብጽ መመለስ በመመኘታቸው የተስፋዋን ምድር እንዳያዩ ሆነዋል /ዘዳ.፲፫፥፲፬/። አበው “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይበልጣል” እንዲሉ፣ እንደ እስራኤላውያን ለክፉ ወሬ ጆሯችንን መስጠት አገልግሎታችንን ሊጎዳ ብሎም በሃይማኖታችን ላይ ኑፋቄን ሊያመጣብን ስለሚችል፣ ጆሯችን ከክፉ ወሬ እንዲጾም ማድረግ ይገባል:፡ 
ጆሮ ከንቱን ሐሰት የሆነውን ነገር ለመስማት አቀርቅሮ ከማድመጥ ሊጾም ይገባዋል፡፡ ማር ይስሐቅ “ለነፍስህ ድንቁርናን የሚያመጣ ልስማ ልስማ ልናገር ልናገር ማለት ነው” ይላል፡፡ አረጋዊ መንፈሳዊም “የፈቲውን ጾር የሚያሳስብህ ገንዘብ ልይ ልይ ልስማ ልስማ ማለትን ቢያሳስብህ ወግድ በለው” ሲል ይመክራል፡፡ ጆሮ የሚሰማውን ሊመርጥ ያስፈልገዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ከዘፈን መዝሙርን መስማት ሊመርጥ ይገባዋል፤ ምክንያቱም ሰው በቤቱም ይሁን በሌላ ሥፍራ ሥራ ፈትቶ ተቀምጦ ዘፈን በሚያዳምጥበት ሰዓት የዝሙት መንፈስ በሕሊናው ሊቀረጽ ይችላልና፡፡ መስማት ስለ ሰሙት ነገር ማሰብን ከዚያም ያንን ነገር መፈለግና መመኘትን ወደ መፈጸም ያደርሳል፡፡ ምኞትም ውሎ ሲያድር ገቢር ኃጢአትን ወደ መፈጸም ያደርሳል፡፡ ስለዚህ ከመስማት የተነሣ ድቀት እንዳያገኘን የምንሰማውን ነገር መምረጥና መለየት ያስፈልገናል፡፡ ይህ ሲባል ጆሮአችን ምንም እንዳይሰማ እንድፈነው ማለት አይደለም፡፡ ሰምቶ እንደማይጠቀም ዐውቆ መተው ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ ክፉ ነገርን ከመስማት መታቀብ ከጸዋሚው የሚጠበቅ ነው፡፡ ለመስማት የሚያስገድድ ሁናቴ ቢያጋጥመው እንኳ ሐሳቡን እንዳይሰጠው መሆን ነው፡፡
ከዚህም በላይ የሐሰት ወሬ፣ የተሳሳተ ፍርድና የመሳሰለውን እንዳይሰሙ መሆን ነው፡፡ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ የተሳሳቱ ቃላትን ሲናገርና ያለ ርኅራኄ ሲተቸው ጆሮን ከፍቶ መስማት ለድርጊቱ ተባባሪ መሆን ነውና፡፡ ቅዱስ ሙሴ ጸሊም “ስም ከሚያጠፉ ሰዎች ጋር አትሂድ፣ በምንም ሰው ላይ የተደረገ ስም ማጥፋትን አትመን” ብሏል፡፡  ሰሚው በሰማው ነገር አእምሮውና ልቡናው ሊረክስና በክፉው ነገር ሊረበሽ ይችላል፡፡ የሰማውን ነገር ሳያጣራ እውነት ነው ብሎ ከተቀበለም ከነዚያ ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት የሻከረ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሰውን ጥፋትና በደል ከመስማት መጾም ይገባል፡፡ በአጋጣሚ ብንሰማም እንኳ የሚወራውን ወሬ ርእስ መቀየር ካልሆነም ቸር መሐሪ እግዚአብሐር በእርሱም ሆነ በእኛ ላይ ምሕረቱን እንዲያደርግ እንጸልይ በማለት ነገሩን መቅጨት ይቻላል፡፡ ቅዱስ ባሕታዊ ኢሳይያስ እንዲህ ይላል፡- “በባሕርይ ከአንተ አንድ የሚሆን የወንድምህን ኃጢአት ለመስማት ወይም ሰምተህ እርሱን ለማውገዝ አትፍቀድ” ብሏል፡፡ ቅዱስ ይስሐቅ “እሳት ከአንተ ወጥታ ሌሎችን ብታቃጥል በተናገርካቸው ክፉ ቃላት ስለተቃጠሉት ነፍሳት እንደሚጠይቅህ ዕወቅ፡፡ እሳት ባትወረውር ዳሩ ግን በሌላ ሰው እንዲወረወር ብትስማማና እሳቱ በመለኮሱ ብትደሰት ከእሳት ለኳሹ ጋር ተካፍለሃል” በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲያውም በጾም ወቅት ከምንጊዜውም በበለጠ ገድለ ቅዱሳንን ልንሰማ፣ ልናሰማ ይገባናል፤ ምክንያቱም የቅዱሳን ጽናትና ተጋድሎ የእኛን ሕይወት የምንመዝንበት፣ ተጋድሏቸውን በማሰብ የምንጸናበት ሕይወትን እናገኝ ዘንድ ይረዳናል።