ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.31K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
#አሐቲ_ድንግል ለ6ተኛ ጊዜ ታትማለች!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍32🙏1
💧#ዜና_መጽሐፍ

#ሃይማኖታዊ_ገድል

“ወንድማችን ዲ/ን ዘአማኑኤል ገና በወጣትነት ዕድሜው ሀሁ ብሎ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ራሱን ያዘጋጀ፣ ለብዙ ወጣቶች አርኣያና ሞደል መኾን የሚችል፣ ብስለትን ከትሕትና አንድ አድርጎ የያዘ፣ ትጉህና ቅን፣ አርቆ አሳቢ የኾነ ድንቅ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው።
በዚህ የወጣትነት ዕድማው የሐዋርያው የቅዱስ ይሁዳን መልእክት መሠረት አድርጎ ስለሃይማኖታዊ ገድል በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ላለነው በሚመጥን መልኩ አዘጋጅቶ አቅርቦልናል። የይሁዳ መልእክት አንድ ምዕራፍ ብቻ ያለው ሲሆን ዶግማና ቀኖናን በጠበቀ መልኩ በብዙ መንገድ ተንትኖ እና አብራርቶ ትልቅ መጽሐፍ አድርጎ ጽፎ እነሆ ይለናል። በእንድ ምዕራፍ ተነሥቶ ትልቅ መጽሐፍ መጻፍ እንደሚቻልም ሞዴል ኹኖ አሳይቶናል።
በዚያ ላይ ወጣት እንደመሆኑ ብዙ ፍላጎቶች ያሉት ሲሆን ነገር ግን ራሱን ገዝቶ ከራሱ ይልቅ በተ ክርስቲያንን አስቀድሞ ይህን የመሰለ መንፈሳዊ ሥራ ሠርቶ ትውልድ ለሚታነጽበት ለቤተ ጉባኤ መስጠቱ ለቤተ ክርስቲያን ይበልጥ ያለውን አርቆ አሳቢነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
ስለዚኸ ምእመናን ሆይ ይኸን መጽሐፍ ገዝተን በማንበብ ራሳችንን እንድናንጽበት ወዲኸም ት/ቤቱን እንድናግዝበት ለማለት እወዳለኹ።


✍️ሊቀ ሊቃውንት ትሕትና ተስፋዬ በሐይቅ እስጢፋኖስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ አንድነት ገዳም የኖኅተ ብርሃን ሸቱ ጉባኤያት መጻሕፍተ ትርጓሜ አዳሪ ት/ቤት የቅኔ፣ የአቡሻኸርና የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍተ ትርጓሜ ምስክር መምህር።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816
5🙏4
---
#ዲያብሎስ የሚዋጋው ሁሉን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ በማደግ ላይ ያሉትን እንኳ ይዋጋል፡፡ እንዲያውም ውጊያው በእነርሱ ላይ ይበረታል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው ራሱን ከውጊያዎቹ ነጻ ወይም የበላይ አድርጎ የማሰብና ቸልተኛ መሆን የለበትም::

ንጉሥ ዳዊትን እናስታውስ! እርሱ ምንም አንኳ የእግዚአብሔር መንፈስ ቢያድርበትና በእግዚአብሔር የተቀባ ቢሆንም በዝሙት ወድቆ የከፋ ኃጢአትን ፈጽሞአል፡፡ በዚህም ዲያብሎስ ሁሉን እንደሚዋጋ እናስተውላለን:: «ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደ አንበሳ ይዞራል፤» (1ኛ ጴጥ 5÷8) ተብሎ ተጽፎአልና። ይህን ማለት ታዳኙን ለማጥመድ ያለ ማቋረጥ ይዞራል ማለት ነው::

በኢዮብ ታሪክ ውስጥ እንደምናነበው እግዚአብሔር ሰይጣንን «ከወዴት መጣህ›› ብሎ ሲጠይቀው እንዲህ በማለት ነበር በግልጽ የመለሰው:- ‹‹ምድርን ሁሉ ዞርኋት በእርሷም ተመላለስሁ፤» (ኢዮ 1፡7፤ኢዮ 2፡2) በማለት፡፡ በእርግጥም ይህ ዙረት የሚታደን ለመፈለግ ብሎም ለመጣል የሚደረግ ዙረት ነው፡፡

ዲያብሎስ የሚዋጋው ሰው በመንፈሱ ብርቱ ቢሆንም እንኳ ቶሎ አይተወውም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ኃጢአት እንዲህ የሚል ቃል አለ:- «ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤እርሷም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው::» ምሳ 7:26:: ዲያብሎስ አሥራ ሁለቱን የጌታ ሐዋርያት ለመዋጋት እንኳ አላመነታም፡፡ ስለዚህ ውጊያም ጌታችን ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ በማለት ነግሮታል፦ «ስምዖን፤ስምዖን ሆይ፦ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፧ ...»ሉቃስ 22:31-32::

#ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ [የዲያቢሎስ ዉጊያዎች]

ፍኖተ መጻሕፍት
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816
9👍2🙏2
-----📖📖------
†ገድለ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ †

መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ [አዲግራት] ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው:: ::

#የ፯ቱ እና የ፵፯ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው ፫ቱ ሳሙኤሎች [ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ] : የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ፤አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር ፫ ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም ፻፹ ነው::

" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" [መጽሐፈ ሰዓታት]

# የታላላቅ አባቶች ገድል በእውነቱ በሊቃውንት ጉባኤ አባል በኾኑት በጥራት ሲዘጋጅ ያስደስታል። [መጋቤ ምሥጢር ፍሬ ስብሐት ዱባለን]፥እየመረቅን ገድሉን በመግዛት ገዳሙን እንርዳ !

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
10
#በቅርብ_ቀን_ይጠብቁ

‹‹ነገረ አበው ኢትዮጵያውያን››

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
አበው ሕይወትና ሥነ-ጽሑፋዊ ቅርስ

#Ethiopian_Patrology

አዘጋጅ #በኃይሉ #በቀለ ወልደጊዮርጊስ (MTh, MA)

የዚህ ታላቅ ሥራ ዋና ዋና ገጽታዎች

1. ቀዳሚ ቃል: በመምህር በአማን ነጸረ (ደብተራ እና የሕግ ባለሙያ) የተጻፈለት ሲሆን የመጽሐፉን ጥልቀትና ፋይዳ ያብራራል።

2. የታላላቅ ምሁራን አስተያየትም ታክሎበታል: እነ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ቀሲስ ግርማ ባቱ እና ዶክተር አቤሰሎም ነቅዐ ጥበብ ለመጽሐፉ የሰጡት ገንቢ አስተያየት ለጥናቱ ጥራት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።

3. አንኳር ይዘቱ ደግሞ ይህን ይመስላል: መጽሐፉ ከሐዋርያዊ ዘመን ጀምሮ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አበው የኖሩትን መንፈሳዊ ሕይወት፣ ያስተማሩትን ቀና የተዋሕዶ ትምህርት እና ቤተ ክርስቲያኒቱን ከኑፋቄ እንዴት እንደጠበቁት ይመረምራል።

4. ጥናቱ ነገረ አበው ኢትዮጵያውያን፣ የቅዱስ ያሬድ መለኮታዊ ዜማዎች፣ የዛግዌ ዘመን አበው ሥራዎች፣ የገዳማውያን ሊቃውንት ዘመን፣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አስተዋጽኦዎች፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የሃይማኖት ውዝግቦች፣ እና በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የአበው ትውፊት ቀጣይነት ባሉ ሰፊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።

5. የታሪክ ዳሰሳው ደግሞ: በዐድዋ ድል የተመዘገበው ድል፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ራስ ገዝነት፣ እና የሃይማኖት አንድነትን የማምጣት ጥረቶች ከመጽሐፉ አንኳር ነጥቦች መካከል ናቸው።

• የመጀመሪያ ዕትም: ፳፻፲፰ ዓ.ም. (2025 A.D.)

#በቅርቡ_ገበያ_ላይ_ይጠብቁ!

📚
ፍኖተ መጻሕፍት

 [ እንደ መጻሕፍት ያለ ዘመድ ከወዴት ይገኛል?]

📱
ይደውሉልን ፦0913083816
👍3🙏3🎉1
💧📖💧
ጠፍቶ የነበረው ታላቁ
#ድርሳነ_መድኃኔዓለም_ወገድለ_መባዓ_ጽዮን
በድጋሚ ታትሟል ለመጪው በዓል ደግሞ ማለትም ለጥቅምት 27 ዓመታዊ በዓለ መድኃኔዓለምወ መባዓ_ጽዮን እጃችሁ መግባት አለበት!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🙏3
📔#መድሎተ_ጽድቅ
[በመምህር ያረጋል አበጋዝ]

#መንፈስ_ቅዱስ በነቢይ ዳዊት አድሮ “ይትባረክ እግዚአብሔር አምላኪየ ዘመሀሮን ጸብአ ለእደውየ ወቀትለ ለአጻብእየ - ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ለእጆቼ ሰልፍን፣ ግራ ቀኝ ማማተብን፣ ለአእምሮዬ እቀውትን ለአንደበቴ መልስን የሰጠኝ ይክር ይመስገን ብሏል መዝ. 143፡1 “መድሎተ ጽድቅ - የእውነት ሚዛን በእጅህ አስጨብጦ፤ ቀዳሚውን፣ ማእከላዊውን፣ ደኃራዊውን፤ አማኒ፣ መናፍቅ፣ ተርጓሚ፣ ተቃዋሚ፣ አስተማሪ፣ ተከራካሪ የሚገናኝበት የምሥጢር ሜዳ ስለ ጻፍህ መንፈስ ቅዱስ በጥበቡ አሠርቶሃል፡፡ በተለይም ዛሬ በልቡናው ሳይሆን በሆዱ የሚያስብ አስተማሪ (ሰባኪ) ነኝ ባይ እንደ ተምች በወረደበት ጊዜ፣ በትረ ኖሎት ያዝን ባዮችም ከሜዳው ሸሽተው ከበጐች ተለይተው በትራቸውን በበትረ መንግሥት በቀየሩበት ጊዜ ይህን መጽሐፍ ማውጣትህ የተኙትን ያነቃል፣ እምነታቸው የዛገባቸውን ይወለውላል፣ መምሰል የማረካቸውና መሆን ያቃታቸውን ከቻሉ እንዲያስቡ ያደርጋል እላለሁ፡፡

#የንታ_መምህር_ደጉ_ዓለም_ካሳ [የመጻሕፍት እና የቅኔ መምህር]

#የንታ ያለምክንያት ይህን እንዳላሉ ልብ ልትል ይገባል!!ጊዜውን የሚዋጅ ይህን ምርጥ የጦር እቃ እነኾ..!

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
5👍3🙏2🔥1
📖#ኦርቶዶክሳዊ_ቅዱሳት_ሥዕላት📖

#በዚህ_ክልስ_ዕትም ከቀደመው ዕትም አንጻር ተጨማሪ ሃሳቦችና ርእሶች ከአስረጂ ቅዱሳት ሥዕላት ተካትተውበት የተዘጋጀ ነው። በይበልጥ ቅዱሳት ሥዕላትን ስለሚያዘጋጁ ሠዓሊያን የትምህርት ዝግጅት ሒደት፣ የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች፣ የአሣሣል ቅደም ተከተሎችና ጥንቃቄዎች፣ ስለሚያጋጥማቸው ፈተናዎችና መፍትሔዎችቻውን አካቷል። በተጨማሪም በዚህ ዘመን የተለያዩ የሕንጻ ቤተ ፈተናዎችና ክርስቲያን አሠሪ ወይም እድሳት ኮሚቴዎች ከማማከርና በአካል ከመጎብኘት የሚታዩ ክፍተቶችን ከነመፍትሔዎቹ ቀርቧል። በተጨማሪም በዚህ ዘመን የሚታዩ የሌላ እምነት ሥዕሎችን እና ቅሰጣዎችን እንደ ንጽጽር ከሚገኙባቸው ደብራት በናሙና በማስረጃ ቀርቧል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6👍2
#የብርሃን_እናት 12ኛ ጊዜ ታትማለች!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7🙏3👍1
💧💧💧ወጥቷል !!!
በጉጉት ስንጠብቀው የከረምነው #መምህር_ያረጋል_አበጋዝ
📖ኢቮሊዩሺን
የተረጋገጠ ሳይንስ ወይስ እምነት ?
የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ገበያ ላይ ውሏል..!

# ደብተራ_በአማን_ነጸረ እንዳሉት ...👇
ድሮ፣ የነገሥታት መልእክት ሲደርስህ ባለህበት ቆመህ እጅ ትነሣለህ። የተክለ ጻድቅ መኩሪያ (ተጻመ) ግለ ታሪክ ላይ፥ ጃንሆይ ሲደውሉ ተጻመ እጅ ነሥተው ነው ስልኩን የሚያነሡት። ወጉ ሥርዓቱ ነው። ወገኛ ሆኜ ነው መሰል እኔም ትልቅ ሰው ሲደውል ቁጭ ብዬ አላናገርም። መቆም የማልችበት ቦታ ከሆንኩ ስልኩን አላነሳም። ያረጋል በዚህ ልክ ከማከብራቸው ወንድሞች መካከል ነው። መንፈሳዊ ሕይወትን ከዘመናዊ ንባብ ጋራ በመቃኘት ሁለት ዓይኖች አሉን። አንዱ ያረጋል ነው። ንግግሩንም መጽሐፉንም መንፈሴን ሰበር አድርጌ ነው የምሰማው የማነበው።

የምንወድህ Yaregal Abegaz Kebede ስለችሮታህ እናመሰግናለን።
---
➮እኛም እጅ ነስተን አመስግነን በልዩ ቅናሽ አቅርበናልና እናንተም መጥታችኹ ሳያልቅ ሸማምቱ...!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍4🥰2🤩2🙏1🕊1
#ሠለስቱ_ሐዲሳት

➥ረዘም ላለ ጊዜ ከበያ ላይ ጠፍቶ የነበረው፦ግብረ ሐዋርያት
፦ሰባቱ መልእክታት
፦ራእየ ዮሐንስ አንድምታ ተሻሽሎ በጥሩ ኹኔታ በድጋሚ ታትሟል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🙏4
💧💧
እነኾ አዲስ የመጽሐፍ ችሮታ
#ከመምህር_በትረ_ማርያም_አበባው

📚#ኦርቶዶክሳዊ_ተዋስኦ
[መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው]

#በእግረ ሥጋም በእግረ ልቡናም ወደ ጉባኤ ቤት፣ ዐይኖቻቸውን ወደ መጻሕፍት ካቀኑ ወንድሞች መካከል አንዱ መምህር በትረ ማርያም ነው። ዘመኑ ያስገኘውን መገናኛ መረብ ተጠቅሞ ወንጌልን ለሕዝብ በማድረስ የሚደክመው ድካም የልጅ ቁም ነገረኛ አድርጌ በትኩረት እንድመለከተው አድርጎኛል። ዛሬ ደግሞ በዚህ መጽሐፍ በምዕመናን መካከል ለሚመላለሱ ጥያቄዎች አስቦ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ከርሠ መጻሕፍትን በርብሮ መልስ አዘጋጅቶ ማቅረቡ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሆኖ ስላገኘሁት ጥያቄ ቢኖርብንም ባይኖርብንም የሚያነሣቸው ጥያቄዎችና የሚመልሳቸው መልሶች የዕውቀት ዳርቻችንን ስለሚያሰፉልን እንድታነቡ እጋብዛለሁ።

✍️ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
[በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢና የአራቱ ጉባኤያት መምህር]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🙏2🕊1
ዜና እረፍት!

ኅዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

➾ዐራት ዐይና ቆሞስ አባ ይባቤ በላይ የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የአቡሻኽር፣ የፍትሐ ነገሥት እና የቅኔ መምህር፤ የክብረ ደናግል ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰማ።

#ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ወንበር ተክለው በማስተማር በርካታ ሊቃውንትን ወልደዋል። ገዳሙን በማስተዳደርም ጭምር ብዙ አልምተዋል። አሁን ሁሉንም ጥለውት ሔዱ። ናዳ ማርያም ገዳም ላይ ታላቅ ሐዘን ወደቀ።
➥ከዚህ ቀጥሎ ያለው ጽሑፍ የመልአከ ምሕረት ግሩም አለነ ነው። 👇

#ለካ ገዳሙን የሚመራ መሪ - በጉባኤ ቤቱ የሚያስተምር መምህር ፈልጉ! ያሉን የስንብት ቃል ነበርን⁉️ እርሳቸው የተናገሩት እኛም በማስታወሻችን ላይ የጻፍንበት የብርዕ ቀለም ሳይደርቅ ዜና እረፍታቸውን ከመስማት በላይ ምን የሚገርምና የሚከብድ ነገር አለ⁉️ የኔታ ባደረባቸው ፅኑእ ህማም ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

#በየኔታ ይባቤ በላይ እረፍተ ሥጋ የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው፣ ለገዳሙ መነኮሳትና መነኮሳይት መጽናናትን እንመኛለን።

#ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ በ23 የሚፈፀም ይኾናል!
በረከታቸው ይደርብን።🙏
💔21😢96
💧በድጋሚ ታትሟል ...

#የነገረ_መለኮት_መግቢያ
[በቀሲስ ግርማ ባቱ]

#ተማሕልሏዊ ነገረ መለኮት ማለት ከመስማትና ከማገናዘብ ተነሥቶ በጸሎትና በምሥጢራት ወደሚደረሰበት ፍጹም የመገለጥ እምነት መድረስ ማለት ነው። ስለዚህ "መንገድ ነኝ" ሲል ጌታችን ያስተማረውን ትምህርት በትክክል እንድንረዳው የሚጋብዘንን ይህን መልካም መጽሐፍ በመጠቀም ከስሜት ከዚያም ከዐውቃለሁ ባይነት ተገብዞ ተላቅቀን ወደ ሕይወት መንገድ እንድንደርስ #ይህን መልካም መጽሐፍ አንብበን እናስነብበው ዘንድ በአዝመራው ባለቤት በመልካሙ ገበሬ ስም አሳስባለሁ።”

[ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ] (MA)


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
11👍2🙏2
📖#ዜና_አበው 📖
[ዘውእቱ መጽሐፈ ገነት ካልዕ]


#የአባቶች ንግግር የመንፈሳዊ ሕይወት ትርጉም ነው፡፡ በቅድስና አኗኗር ውስጥ የሚነገሩ ቃላቶች የመንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ፍሬዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር የባሕርይ መገለጫዎቹን ማደሪያዎቹ በሆኑ በቅዱሳን ኑሮ ላይ እናገኛቸዋለን፡፡ ያ የመንፈስ ፍሬም ነገረ እግዚአብሔር ይባላል፡፡ ቢሰሙት የማይሰለቹት ቢያወሩት የማይጠግቡት ሁልጊዜ መንፈስን የሚያድስ ህሊናን የሚያለመልም ንግግር ነው። #በመምህር_አብርሃም_ፈቃዴ ተተርጉሞ የቀረበልን ዜና አበዊነ ቅዱሳን የሚለው መጽሐፍም ይሄው የአባቶች ጥልቅ ድንቅ የሕይወት ጣዕመ ንግግር ነው᎓᎓ በዘመናቸው ደርሰን በአካለ ሥጋ የማናያቸው አባቶቻችን ዕለት ዕለት እንዲመክሩን የሕይወት ጣዕማቸው ይሄው ደርሶናል፡፡ ወንጌል በሕይወት ስትገለጥ ምን እንደምትመስል ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡በጣዕመ መንፈስ ቅዱስ ከታሹ አባቶች ጋራ ማውራት ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ለመረዳት እስከ መጨረሻው ማንበብ ነው።

#የኔታ_ገብረ_መድኅን_እንየው

📚ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

 [ እንደ መጻሕፍት ያለ ዘመድ ከወዴት ይገኛል?]


📱ይደውሉልን ፦0913083816

https://t.me/GhionBookStore1623
8🙏2😍2🕊1
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
ለማጋራት መዘግየታችን አመክንዮአዊ ነው በመኾኑም የደረስንበትን እነኾ

📚መጻሕፍትን ለመጻሕፍት ተማሪዎች📚
📚አንድ መጽሐፍ - ለአንድ ተማሪ📚

የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም የ“ፈለገ ጥበብ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መታሰቢያ የ፬ቱ ጉባኤያት ትርጓሜ አዳሪ ትምህርት ቤት” ሰሞኑን ከምእመናን መጻሕፍትን በማሰባሰብ ላይ ይገኛል!!

➠ለምን መጻሕፍትን ማሰባሰብ አስፈለገ!?
🖊📚 መጻሕፍት ለሰው ኹሉ አስፈላጊዎች መኾናቸው ምንም አያጠያይቅም ፥ ጉባኤያችን ደግሞ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት መኾኑ ፥ ደቀመዛሙርትም ወደ አገልግሎት ሊሰማሩ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ከመገኘታቸው አንጻር ፥ ከትርጓሜ ትምህርታቸው በተጓዳኝ ኹሉንም የሐሳብ ዘውጎች በንባብ የማየት ዕድሉ ሊመቻችላቸው የሚገባ በመኾኑ ነው። ይኽም ለነገ አገልግሎታቸው ስንቅ ከመኾኑም ባሻገር - ለእንግዳ አስተሳሰቦች አዲስ ካለመኾናቸውም በተጨማሪ .. መረዳት የታከለበት ርቱዓዊ የኾነውን ኦርቶዶክሳዊ እሳቤ ከሐሳባት ኹሉ ከፍ አድርገው በልዕልና ለማንበር [ለማስቀመጥ/ለመግለጥ] ይጠቅማቸዋል። ለዚኽም “የመጻሕፍት ክምችቱ” አስፈልጓል።

➠ሌላስ ምክንያት ይኖሮ ይኾን!?
🖊📚 እንደ ጉባኤ ቤታችን የምንከተላቸው ልዩ ልዩ መርሖዎች አሉን ፤ ከእነሱ መካከል አንዱ ፥ ደቀመዛሙርት ከወንበራቸው ማካከል አንዱን መጽሐፍ [ለምሳሌ የማቴዎስን ወንጌል] ሲዘልቁ ፥ ወደ ቀጣይ ወንበር ከማለፋቸው በፊት ፥ በዘለቁት መጽሐፍ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፥ በዚኽ ጊዜ የማ’ይ’ወ’ጣ የመጽሐፍ ዳገት ፣ የማይወረድ የንባብ ቁልቁለት ፣ የማይሮጥ የተብሰልስሎት ሜዳ አይኖርም። በዚኽ መካከል የመጽሐፍ እጥረት ቢከሰት ተነሣሽነትን ያሳጣል ፤ የእይታ አድማስን ያሳጥራል ፤ የምርምር መጠንን ይገድባል ፤ ይኽ እንዳይከሰት ፥ ደቀ መዛሙርት ዋኝተው የማያቋርጡት ፥ ዝቀው የማይጨርሱት የመጽሐፍ ክምችት መኖሩ እጅግ አስፈላጊ በመኾኑ “የመጻሕፍት ስብስቡ” አስፈልጓል።

➠ሌላ ተጨማሪ ምክንያት ይኖር!?
🖊📚 አንባቢ በብዙ ጉዳዮች ላይ መረዳት ይኖረዋል ፥ መረዳቱንም ለሌሎች በተለያየ ቅርጽ ያጋራል። አሳቢነትም ደራሲነትም ከንባብ ማሕፀን ይወለዳሉ። የጉባኤያችን ደቀመዛሙርት ደግሞ አንደኛ የመጻሕፍት ተማሪዎች ናቸው ፥ ሲቀጥል በንባብ ልምድ የዳበረ ሰብእናን ከፈጠሩ - ደራሲ በመኾን በድርሰት ቤተክርስቲያንን የማገልገል ዕድላቸው ሰፊ ነው ፤ በመኾኑም ጉባኤ ቤታችን ከደቀመዛሙርት መካከል ደራሲያንንም የመፍጠር ዓላማ አለው። የአባቶችን በሳል የድርሰት ወርቃማ ዘመን ለመድገም - ደቀመዛሙርት የንባብ ልምድን እንዲያዳብሩ ማገዝ ፥ የንባብ አማራጮችን በማስፋት መፍቀርያነ መጻሕፍት እንዲኾኑ መርዳት ስለሚኖርብን “የመጻሕፍት ስብስቡ” አስፈልጓል!!

📚የማያስቆጭ ፥ ሰጪውንም እንደ ዕድለኛ የሚያስቆጠር ስጦታ ቢኖር “የመጻሕፍት ስጦታ” ነው ፤ ይኽ ደግሞ ጉባኤ ቤት ላይ ሲኾን ፥ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ውለታን መዋል ነው!! በተጨማሪም ምእመናን አገልጋዮች ላይ ያላቸውን ቅሬታ ከማሰማት የበለጠ ፥ በመሠራት ላይ ባሉ አገልጋዮች የድርሻቸውን መወጣት ቢችሉ ፥ ወደፊት የሚመኟቸውን ዓይነት አገልጋዮች ማየት ይችላሉ!! ስለኹሉም ነገር እግዚአብሔር ይርዳን!!

📚ምእመናን፦ “መጻሕፍትን ለመጻሕፍት ተማሪዎች” ፥ በማገዝ #አገልጋያችኹን_ፍጠሩ!! በሥጦታውም እየተሳተፋችኹ ያላችኹ ፥ “የሥጦታችኹ ብድራቶች በመድኃኔዓለም ዓይኖች ሥር ይጠ’በ’ቁ’ላችኹ” ዘንድ ምኞታችን ነው📚


የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያም ገዳም የ“ፈለገ ጥበብ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መታሰቢያ የ፬ቱ ጉባኤያት ትርጓሜ አዳሪ ትምህርት ቤት

☝️እንዲህ ብለውናልና እንተባበር ጉባኤ ቤታቸውን እንደግፍ ..!
🙏63🕊3
#ራእየ_ኒፎን

የይቅርታ ፏፏቴ የርኅራኄ ባለጠጋ የሆንክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ማረኝ፤ ይቅርም በለኝ፡፡

ጌታ ሆይ “አላውቅህም አትበለኝ!' ጌታ ሆይ እስከዛሬ የት ነበርክ?' ብለህም አትቆጣብኝ፡፡ በኃጢአት የቆሸሽሁ፧ በበደል እንደ ጢስ የጠቆርሁ፤ ሕግህን በመተላለፍ የበሰበስሁ፤ ፍቅርህን በመርሳት የተዋረድሁ፤ በርኵሰት የሽተትሁ፤ በዲያብሎስ ምክር የጠፋሁ፤ ሰዎች በሚሠሩት አስነዋሪ ሥራም ዋነኛ የሆንኩ የማልጠቅም ትቢያና ጉድፍ ልጅህን አትናቀኝ፤ ከፊትህም አፍሬ አልመለስ፡፡

መምህሬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ ራራልኝ፤ አድነኝም፡፡ ሰው ወዳጅ ሆይ “አንተ የኃጢአተኛን በንስሐ ከክፉ መንገዱ መመለሱን እንጂ መጥፋቱን እንደማትሻ' አውቃለሁና ተመልሰህ እስክትረዳኝና ምሕረትህን እስካገኝ አላርፍም፡፡"

(ራእየ ኒፎን ገጽ 59)


📚ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ ዘመድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን !📞፦0913083816

https://t.me/GhionBookStore1623
11🕊5
📖"ነገረ ማርያም"
[በሶርያ አባቶች እና ሌሎች ]


መነሻው #የመንፈስ_ቅዱስ_ዋሽንት በተሰኘው በተወዳጁ #ቅዱስ_ኤፍሬም ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጻፋቸው ድርሳናት ነው ፥ ከዚም መለስ ሲባል እያንዳንዱ ገጽ ሕይወት ያለው ነው!-መምህር ዲያቆን ሽመልስ መርጊያ በርካታ የትርጉም ሥራ አበርክተውልናል... ግን እመኑኝ ይኽኛው እጅግ ልዩ ነው ልዩ ስለኾነችዋ ስለ #ድንግሏ_እመቤት -ከጽንሰቷ እስከ እርገቷ ጥፍጥ ባለ መልኩ ስለጌታም አስተዳደግ በመጠኑ የሚያትት ስለሐዋርያቱና -እመቤታችን የጠበቀ ወዳጅነት በተለይ በሶርያ ቤተክርስቲያን እዴት እንደምትከበር ሲተነትን አንዳንድ የእመቤታችን ክብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፈጠረችው እንጂ በሌሎች ኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስያናት የማትከበር ለሚመስላቸው መናፍቃን የማያዳግም ምላሽ የሚሰጥ የሚሉትም ኹሉ የእነርሱ ተረት እና እሳቤ እንደኾነ የሚያስረዳ..ነው። በጥቅሉ እጅግ ተወዳጅ መጽሐፍ ነው! -ስታነቡት እንደምትጋሩኝ አልጠራጠርም ...!
💧ሱባኤውን በንባብ ለማሳለጥ ደግሞ አይነተኛ ምርጫም ነው!

መጽሐፉን ለማግኘት ደግሞ ምንም መጨነቅ አይጠበቅም #በግዮን_መጻሕፍት በተለመዱት የሥራ ቀናት እና እኹድ ደግሞ ከቅዳሴ ሰዓት በኋላ ተሰናድቶ ይቆያችኋል!

📚ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

 [ እንደ መጻሕፍት ያለ ዘመድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን !📞፦0913083816
https://t.me/GhionBookStore1623
11🙏2🕊2
💧እነኾ
ይህ ዕንቊ -የምዕመናን ምርኩዝ
-የጉባኤ ቤትና የሊቃውንት ስንቅ
- የመነኮሳት አለኝታና መካሪ
የኾነ መጽሐፍ ገበያ ላይ እንደሌለ ይነገራል እርግጥምም የለም... ነገር ግን
የተወሰኑ ቅጂዎች እኛ ዘንድ የሚገኙ ሲኾን ስለመጽሐፉ ደግሞ የዲያቆን ያረጋልን ክታብ እየጋበዝን በኋላ ካለቀ እንዳትቆጩ እናሳስባለን ..!👇

ዮሐንስ ዘሰዋስው በምሥራቁ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ እንዲያውም በገዳማዊ ሕይወት ውስጥ ከወንጌል ቀጥሎ ተጠቃሹና ተሰሚነት ያለው መጽሐፍ ይህ መጽሐፍ መሆኑ በስፋት የተነገረለት ነው፡፡ እስከ ዛሬ ወደ እኛ ባለመምጣቱ የቀረብንን ይኸው ዛሬ መጽሐፉ ተተርጉሞ በመቅረቡ አንድ ጉድለት ተሸፍኗል፡፡ መጽሐፉ የክርስትና ሕይወትን ምንነት በአግባቡ ለመረዳትና ለመኖር በሚሹ ዘንድ ሁሉ የሚፈለግና የሚጠቅም መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በተለይ ደግሞ እግዚአብሔር አምላካቸውን በገዳማዊ ሕይወት ለሚያገለግሉ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡❞
           ✍️ ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ


📚
ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

 [ እንደ መጻሕፍት ያለ ዘመድ ከወዴት ይገኛል?]

📱
ይደውሉልን ፦0913083816

http://t.me/FinoteBooks1623
🙏54🕊3
📚#መዋዕያን

#በዚህ መጽሐፍ፦ጽሑፎቹ በምንጭ አጠቃቀም ረገድ የሀገር ውስጥም የውጪም ምንጮችን ግብዓት አድርገዋል። የውጮቹን ምንጮች ተጠቅመን በውስጣዊ እይታ ለማንጠርና ዳግም ታሪኩን በብሔራውያን ሊቃውንት ኅሊና ተገብቶ አማናዊውን ምስል ለማግኘት ጥረት ተደርጓል - በተለይ የሚሲዮናውያኑን ጉዳይ በሚዳስሰው ምዕራፍ አራት። በተፋላሚ ሜዳም ብቅ እያሉ የቅድመ መከላከል ተግባር መከወን የዘመኑ ፈሊጥ ስለሆነ፡፡ ቤቱ በቂ መልስ ያለበት ነውና ሐሳብ አይፈራም። የ19ኛው ክፍለ ዘመን ሊቃውንት ተዋሥኦ ያንን ያሳያል።
በዚህች ንዕስት መጽሐፍ በክብር አርፈው የድል አድራጊነት አክሊል የደፉትን ቅዱሳን የአሸናፊነት ታሪክ በያዘው ቅዱስ ጽሕፈት (ገድል) ሁለንተናዊ ይዘት ጀምረን በዘመናዊት ኢትዮጵያ ዋዜማ ቤተ ክርስቲያናቸውን በክብር ለማቆየት ተገቢውንና ዘመኑ የሚጠይቀውን ተጋድሎ ቢፈጽሙም በቅጡ ባልተዘከሩት፣ ታሪካቸው በተጻራሪዎቻቸው ተለባብሶ ተጽፎ በተዳፈነው ሊቃውንት የተጋድለ ሒደት እንቋጫለን፡፡ መልካም የንባብ ጉዞ ከመዋዕያኑ ጋራ!
✍️በአማን ነጸረ

➯ይህንና መሰል ጥዑምና ብስለት ያላቸው መጻሕፍት ለማግኘት #ጎራ_በሉ..!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🙏4👍1