ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.31K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
📖❖ ሀብታም እና ድሀ📖

...ባለጸጋው ድሀውን በየዕለቱ ደጃፉ ላይ ዓይኑ ስር ወድቆ እያየው ምንም ዓይነት ምጽዋት አልሰጠውም፡፡ ይህ ምስኪን ድሀ በጎዳና ወይም በተሰወረ በጠባብ መተላለፊያ ስላልወደቀ ባለጸጋው አንዴ ወይም ሁለቴ ወይም ብዙ ጊዜ ሲገባና ሲወጣ አይቶታል፡፡ ነገር ግን ሲገባም ሆነ ሲወጣ በውድም ሆነ በግድ ሊያየው በሚችልበት .......

...ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አሳይቷል፡፡ እግዚአብሔር ስለ መተላለፋችን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚጠይቀን ቢሆንም የማያዳላውን ዳኛ ሕሊናን ግን በውስጣችን ፈጠረ፡፡ ይህ ዳኛ በዚህ ዓለም ሳለ ይረዳናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ያለው .....

[ከመጽሐፉ የተወሰደ]


ወገን ራስን ለመፈተሽ አይነተኛ መፍትሔ ነው ...! እመነኝ የት ጋር እንዳለህ ይነግርሀል!..ይያዝዝ



ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍2🙏2
📖📚📚📖#አውግስጢኖስ_እና_ኦርቶዶክሳዊ_መንፈሳዊነት

#እነዚህ_የዲያቆን_ሕሊና_በለጠ_ኹለቱ_ሥራዎ_በመደብራችን_ይገኛሉ_..!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍32🙏2
📖📖📖📖📖
#አፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_እና_ሥራዎቹ

#አፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ መንግሥት አጠቃላይ ቅጥር ግቢው በሁለት ዙር የተከበበ እና የታጠረ ሥፍራ ሲሆን፤ በአጥሩ ዙሪያም በቁጥር አሥራ ሦስት የሚደርሱ የተለያዩ መጠሪያ ሥምና ተግባር(ግብር) ያላቸው በሮች (ዕድሞዎች) እናገኛለን። እነዚህ በሮች እያንዳንዳቸው የተለያየ ተግባር እና ስም ያላቸው ናቸው፡፡ ተግባራቸውን ወደ ኋላ የምናየው ሆኖ በስም ደረጃ ውድነሽ ደጅ፣ ጸር ዋጀት ደጅ፣ መርድ ደጅ፣ መጋረጃ ደጅ፣ መስቀል ደጅ፣ ውላጅ ደጅ፣ ግምጃ ማርያም ደጅ፣ ኢየሱስ ደጅ፣ ቁልፍ ደጅ በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በርካታ ቤቶችና ድንኳኖች የነበሩ ሲሆን፤ የቀኝ በሀልቲሐት ቤት፣ የግራ በሀልቲሐት ቤት፣ የባሀልቲሐት ሽና ቤት፣ የንግሥቷ እናት ቤት፣ የዐቃቢ ሰዓት ቤት፣ የቀኝ ብሕትወደድ ቤት፣ የግራ ብሕትወደድ ቤት፣ የግብፅ ጳጳስ ቤት፣ የንጉሥ ዋና አዳራሽ ቤት፣ የሰቀላ (የጥበቃዎች ቤት፣ የአንበሶች ቤት፣ ከዚህ በተጨማሪ የቀኝ ጀጎላ ሦስት የተለያዩ ድንኳኖች(ደበና)ነበሩት፡፡ በመካከላቸው የተተከለው ድንኳን ዱለት ቤት፣ በቀኝ በኩል ያለው ግምጃ ድንኳን እና በግራ በኩል ያለው አቋት ግምጃ ድንኳን ተብሎ ይጠራ እንደነበረ ተዘግቦ ይገኛል።

      [ከውስጥ ገጽ..]

🌿#ይህ የንጉሡ ዜና መዋዕል እኛ ዘንድ አለ!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4👏2🕊2🤔1
📖ኦሪት ዘፍጥረት 📚

...✍️ኦሪት ዘፍጥረት የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ዋና ትምህርቶች ማለትም የነገረ ድኅነት፣ የነገረ ሰብእ፣ የነገረ ሥነ-ፍጥረት፣ ... መሠረት ነው፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት ብዙ መተርጉማን ትኩረት ሰጥተው በስፋትና በጥልቀት ካብራሯቸውና ከተረጎሟቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡
#እኔ_ያደረግሁት ከእነዚህ የተለያዩ አባቶች፣ ሊቃውንት እና መተርጉማን ሐሳቦች መካከል የተወሰኑትን አሰባስቦ ማቅረብ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በተከታታይ ከቀረበው የኦሪት ዘፍጥረት ማብራሪያ ትምህርት የመጀመሪያዎቹ ዐሥር ምዕራፎች ትምህርት (ከምዕራፍ 1 -10) በዚህ መጽሐፍ ቀርቧል፡፡
በመጻሕፍት ትርጓሜ ውስጥ ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ። ከእነዚህ አንዱ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) እና በመተርጉማን ግላዊ አስተያየቶች መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ለይቶ ማወቅ ነው፡፡

..... በዚህ #መጽሐፍ የቀረቡትን የመተርጉማን ትርጓሜዎችና ማብራሪያዎች በአግባቡ ተረድተን #ለሕይወት እንድንጠቀምበት #የቃሉ ባለቤት #እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

#ኦሪት ዘፍጥረትን ብትን አድርጎ የሚያብራራ ብሎም ገቢውን ለታላቁ ማኅበር #ማኅበረ_ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የተበረከተ ነው።

፨ይህ#መምህረ_መምህራን_ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ አበርክቶት ጥቂት ብቻ ነው የቀረ ሲኾን ይያዝ!!!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
8👍4🙏2🕊1
📖'አባቶችህን፡ እወቅ'📖

'አባቶችህን፡ እወቅ፡ 'በሚል ፡ርዕስ ፡የተዘጋጀው፡ ይህ ፡መጽሐፍ ፡የዚህን [የነገረ ፡አበውን]፡ ትምህርት ፡ዓላማ፡ ለማሳካት፡ በሚረዳ መልኩ፡ ጥሩ ፡ኾኖ ፡የተዘጋጀ ፡መጽሐፍ ፡ነው። #እኔ፡በበኩሌ፡ እንዲዘጋጁ ከምመኛቸው፡መጻሕፍት፡መካከል፡ አንደኛው፡ይህ ፡#መጽሐፍ  ፡ነበር ።ስለኾነም ብዙ ፡ምንጮችን  ፡መመልከት፡ የሚያሻውንና፡ ለይቶ፡ ጨምቆ ፡ለማቅረብ ብዙ ድካም ፡የሚጠይቀውን ፡ሥራ  በመሥራት፡ይህን መጽሐፍ  ፡አዘጋጅቶ ስላቀረበልን ወንድማችን #ዲያቆን_አቤል_ካሳሁንን ፡ከልብ ፡እያመሰገንኩ፡ እኛም፡ አንብበን ፡እንጠቀምበት ፡ዘንድ፡ #እግዚአብሔር ፡ይርዳን ፡እላለሁ ።


#መምህረ_ቤተክርስቲያን_ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

➮ለተወሰነ ጊዜ ጠፍቶ የነበረው ይህ እጅግ ተፈላጊ እንዲኹም አስፈላጊ መጽሐፍ በድጋሚ የታተመ ቢኾንም ጥቂት ኮፒ ብቻ ስለኾነ የታተመው እንዳያመልጠን ..!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍2🕊1
#የዲ/ን አቤል ሌላኛው ሥራው #መላእክት በድጋሚ ታትሟል!ብቅ በሉ..!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4👍2🙏2🕊2
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
#ዜና_መጽሐፍ

በወጉ ያልተዘከሩት ምሁር መጽሐፍ
       ( ዶ/ር ሥርግው ሐብለሥላሴ
)

[ጸጋው ማሞ እንዳሰናዳው]

፨"ሥርግው ምን አልባትም በ20ኛው ክፍለ ዘመን ካሉት ብቸኛው የኢትዮጵያ የጥንታዊ ታሪክ ሊቅ ነው"  ይላሉ ኤርትራዊው የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር "ባህሩ ተፍላ"  ስለ ጥረታቸውና ሀቃዊ የታሪክ ትንተናቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልተማሪያምም  "በመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ " መጽሐፋቸው ላይም ምሥክርነታቸውን በአድናቆት ሰጥተዋል። ተቀዳሚ ምሁር ፕሮፌሰር ሥርግው  ሐብለሥላሴ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ተምረው ባካበቱት ሰፊ እውቀት ላይ ተንተርሰው አያሌ የታሪክ ጥናቶችን እንዳካፈሉን ይታወቃል።  ከሁሉም በላይ ግን " የኢትዮጵያ  የብራና ጽሑፎች ማይክሮ ፊልም ድርጅት " ዳይሬክተር ሆነው በሰሩት  ዘመን ተሻጋሪ ሥራ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ሲዘክራቸውም ይኖራል ። #የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርሳቸውን  የድካም  ሥራዎች ተገንዝቦ ተገቢውን ክብር ሊቸራቸው ይገባል።

➮ከእርሳቸው የበዙ ሥራዎች መካከል አንዱ  እና ግዙፍ የሆነው "አማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት " ሲሆን ይኸውም በብርቱ ያላሰለሰ ጥረት እና ድካም የተሰራ፤ ዘመን የማይሽረው ከወረት የተሻገረ እጅግ ድንቅ ሥራ ነው። ይኸ ግዙፍ መዝገበ ቃላት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የታላላቅ  ሊቃውንትን ፣ ቅዱሳንን ፣ ገዳማትን እና አድባራትን ታሪክ በመረጃ የሰነደ ድንቅ ሥራ ነው ። 

#ይኸ ታሪካዊ መዝገበ ቃላት ለታሪክ ተመራማሪዎች ፣ ለሥነ ጽሑፍ ሰዎች ፣ ለሥነ መለኮት አጥኝዎች ፣ ለሥነ ሰብእ መርማሪዎች እንደዚሁም ታሪክ ለሚወዱ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፍ ነው ። ለምሳሌ በገጽ 662 ላይ "ገላኔ"ን እንዲህ ያብራራልናል " /እመት/ በ19ኛው ምእት ዓመት የኖረች የጉድሩ ሴት። ባሉዋ ዋቅጅራ ይባላል። ከእነዚህ አብራክ የተገኘው ወንድ ልጅ  ነገሮ ይባላል...ይኸውም ተክለ ኢየሱስ የተባለው የኢትዮጵያን ታሪክን ጽፎ ያቆየን ነው " በማለት ይገልጽና መረጃውን ከታች ያስቀምጥልናል።

⨳ሌላው  የሚያሳስቱ ተመሳሳይ ስም ያላቸውን የተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን እና የቦታ ስሞች በወጉ እንድንለይም ይጠቀመናል ።ለምሳሌ በዚህ መጽሐፍ ላይ ከ35 በላይ ዮሐንስ የሚባሉ ታላላቅ ታሪካዊ ሰዎች በግልጽ ተብራርተዋል ።  ጀርመኖች ታላቁን  "Encyclopedia of Aethiopica " ከመስራታቸው በፊት የተሰራ ምናልባትም ለዚህ ስራ ታላቅ ግብአት የሆነ መጽሐፍ ነው። 

◆አሁንም የፕሮፌሰር ሥርግው ሐብለሥላሴን የድካም ውጤት "ኢትዮፋጎስ የመጽሐፍ ማእከል"ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ ተመጻሕፍት አገልግሎት " ጋር በመተባበር በእጅ ጽሑፍ የነበረውን 13 ቅጽ አርትኦት በመሥራት በሁለት ግዙፍ መጽሐፍት በማሳተማቸው ከፍተኛ ክብር እና ምሥጋና ይገባቸዋል። ከእኛ የሚጠበቀው በከፍተኛ ልፋት ተጋጅቶ የቀረበልንን ጥሩ  ማዕድ መመገብ ብቻ ነው ።

#ዶ/ር እጓለ ገብረዮሐንስ "ከመጻሕፍት   የሚደገሙት ጥሩዎቹ ናቸው " ይላሉ ።  እንደዚሁም 'ማርክ ትዋይን' የተባለ ሊቅ ደግሞ "ጥሩ መጽሐፍትን የማያነብ ሰው  ማንበብ ከማይችል ሰው አይሻልም " ይላል ። ይኸ መጽሐፍ ደግሞ ከጥሩዎቹ አንዱ ስለሆነ #በእያንዳንዱ ቤተ መጻሕፍት እና መደርደሪያ ውስጥ ሊገኝ የሚገባ ግሩም መጽሐፍ ነው ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6👍2🙏2
#የግዮን_ወንዝ

#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ የተጦመረው ይህ ጥዑም መጽሐፍ በድጋሚ ታትሟል! እንደሚታወቀው ደግሞ ሙሉ ገቢው ከምድራችን ቅድስተ ቅዱሳን ክፍሎች ውስጥ አንዱ ለኾነው ለታላቁ #ለደብረ_ሊባኖስ ገዳም ሕንጻ ማሰሪያ እንዲውል የተደረገ ነው ።እኛም ከንባቡ ተጠቅመን ጸኃፊውን እየመረቅን ገዳማችንን እንርዳ ...!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🕊3👍2
#ዶክተር_እጓለ ፦በተውሶ መነጽር እራስንና ማንነትን የማኮሰስ ደዌ #ያላገኛቸው ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው ። -#የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ ያጠኑ፤ የመረመሩ ለነበሩ ጥንታዊ ሀገር በቀል ባህልና እውቀት አክብሮት ያላቸው ሊቅ በመኾናቸው የሀገራቸውን ጽሑፎች ሲያጠኑና ሲመረምሩ መንፈሳቸውና አእምሯቸው ከፍ ወዳለ መራቀቅ ደረጃ ከደረሱት ጥቂት ማሰብ ከሚችሉ ሊቃውንት መካከል እጓለ አንደኛው ናቸው።

[ፍካሬ እጓለ በተመስገን ዋና የቀረበ]


....ከመጽሐፉ ለቅምሻ

#ሰውን ጥቅም፤ ተድላ፣ ደስታ ብቻ ተፈላላጊ አድርጐ በመመልከት ፤ ይህንኑ ምኞቱን የሚያረካበት ትምህርት ብናቀርብለት የሚጐዳ፣ የሚበደል እንጂ የሚጠቀም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በመላ ለዚህ ነገር ብቻ ቢሰለፉ በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ያለው ውድድር መልኩን ለውጦ ያለመጠን አስቸጋሪና የሚያፋጅ ሊሆን ይችላል። በተለይም ይኸ እንዲህ ያለ ጥቅምን ብቻ የሚመለከት ትምህርት የሚያስገኘው ጠባይ ከሥልጣን ጋር የተገናኘ እንደሆን ነገር ጨርሶ ሊበላሽ ይችላል ለኔ ማለት ይሰፍናል።
----
የሰው ልጅና ማድጋ ጆሮውን ካልያዙት አሟልጮ ይወድቃል!❞[እዝነ-ልቡናን ያጠይቃል]

#በርግጥ ይህ መጽሐፍ በዓይነቱ እስካሁን በአማርኛ ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ብቸኛና ዘላቂ ይዞታ ያላቸው ድርሰተቶች ከምንላቸው ተቀዳሚው ነው! እንግዲያ ብቅ በሉና ደጋግማችኹ ሸምቱት ቅርስ ነውና!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
7👍2🙏2
📖 #ወንጌል_ቅዱስ 📖


.....፱/ ወእመኒ ዐይንከ ታስሕተከ ምልሓ ወግድፋ እምላዕሌከ፤
ዓይንህ ብታስትህ አውጥተህ ጣላት፡፡

እስመ ይኄይሰከ ነቋረከ ትባእ ውስተ ሕይወት   እምእንዘ ክልኤ ዐይን ብከ ትትወደይ ውስተ እሳተ ገሃነም፡፡

➮ዛሬ በዚህ _ ዓለም ሁነህ ኑረህ፤ ኋላ ገሃነም ከምት ወርድ፤ ዛሬ በዚህ ዓለም አንድ ": ዓይን ሁነህ ኑረህ ኋላ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ይሻለሃልና፡፡
#አንድም ወእመኒ ዓይንከ ብለህ ሁሉ ንም አንብብ፡፡➮#የነቀፍከውን ኤጲስ
ቆጶስ ሹመህ ኑረህ ኋላ ገሃነም ከምትወርድ ፤
ዛሬ በዚህ ዓለምየነቀፍከውን ኤጲስ ቆጶስ ሽረህ ያልነቀፍከውን ኤጲስ ቆጶስ ሹመህ ኑረህ ኋላ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ይሻልሃልና፡፡

ዑቁ ኢታስተሐቅርዎ ለአሐዱ እምእሉ ንዑሳን፤
#በእኔ ካመኑ ከምእመናን አንዱን አትናቁ አታቃሉ እንዳትንቁእንዳታቃልሉ አስተውሉ፡፡

#የማቴዎስ_ወንጌል_ከምዕራፍ_፲፰

ወንጌላችንን እንዲህ አንድ በአንድ እስከ ትርጓሜው ማወቅ ግድ ነው !ከቀድሞ አባቶች ሲተረጎም የመጣው ንባቡና ትርጓሜው በአንድምታ አድርገው  ለአይን ጎላ ባለ ና ለንባብ ደግሞ በቀለም የተለየ ና በምቹ  ኹኔታ ያቀረቡልልን #መጋቢ ሐዲስ ቃለ ሕይወትን እያመሰገንን እጅግ ወሳኝ  በመኾኑ ባያመልጠን መልካም ነው እንላለን!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🕊3🙏2
📖#ሐተታ_ዘቅዱስ_አትናቴዎስ

#ያለሀሰት ቅዱስ አትናቴዎስ ለቤተክርስትያን አምድ ከምንላቸው ቅዱሳን አባቶቻችን አንዱና ዋነኛው መኾኑ አያጠያይቅም ታድድያ ከእርሱ ግሩማን አበርክቶዎች መካከል "ተስእሎተ አንትያኮስ" የተሰኘውን መጽሐፍ #መምህር_ቃለ ጽድቅ_ሕግነህ በተዋበ እና ለንባብ ምቹ አድርገው የተረጎሙት ሲኾን ➱ቅዱስ አትናቴዎስ በዚህ መጽሐፍ ከሚመልሳቸው ጥያቄዎች .....

አንትያኮስ፡ ርኩሳን መናፍስት የሆኑ አጋንንት ከቅዱሳት መጻሕፍት የሚፈሩት የጸሎት ዐይነት የቱ ነው?
ጥያቄ ፦ በውኑ ለኃጥአን ነፍሳት በዚህ ዓለም ዘመዶቻቸው የመታሰቢያ(ተዝካር) ቍርባን፣ ጸሎትና ምጽዋት ቢያደርጉላቸው በዚያኛው ዓለም ይጠቅማቸዋልን?
➮ጥያቄ ፦ ለሰው እጅ ሥራዎች እንዳንሰግድ እግዚአብሔር በነቢያቱ አዝዞናልና ለምን የሰው እጅ ለሠራው ለቅዱሳን ሥዕልና ለቅዱስ መስቀሉ እንሰግዳለን?
➮አንትያኮስ፡- ከኃጢአት ሁሉ የሚበልጠው ኃጢአት የቱ ነው?
➮አንትያኮስ፡- ብዙ በደልንና ኃጢአትን የሠራ ሰው ቢኖር ከዚያም በኋላ ንስሓ ቢገባ፤ እንደገና ተመልሶ ኃጢአት ቢሠራ እግዚአብሔር ንስሓውን ይቀበለዋልን ወይስ አይቀበለውም?

#ይህንና መሰል ጥያቄዎችን ከነ መልሶቻቸው የያዘ ልዩ መጽሐፍ በመኾኑ እንድታነቡት ግብዣችን ነው!

📚ግዮን መጻሕፍት ለውድ አንባብያን  በDHL ,በEMS እንዲሁም የ delivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

📱ይደውሉልን ፦0913083816

Telegram
https://t.me/GhionBookStore1623
7👍3
📖#አንድሮሜዳ📖

#የዶክተር_ሮዳስ አንድሮሜዳ የተሰኘው መጽሐፍ የጥንት ኢትዮጵያውያን የሕዋ ሥልጣኔ ከዘመናዊው ሳይንስ አንጻር በደንብ ፍንትው አድርጎ የሚያብራራ እንዲሁም ከሕጻናት እስከ አዋቂ እንዲረዳው ተቀምሞ የተዘጋጀ ለልጆች ደግሞ ንቃተ ሕሊናን የሚያስጎነጭ ጥዑም ጦማር ነው ። ለዚህ ሳምንት ለልዩ ቅናሽ የመረጥነው መጽሐፍ ነው ። ቻናሉን #ሼር በማድረግ ወዳጆቻችሁን ተጠቃሚ አድርጉ!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍3
#ገድለ_አቡነ_ሐራ_ድንግል


#ማኅቶተ ቤተክርስቲያን ጳውሎስ ከመዠመሪያ አንሥቶ የነበሩ የቅዱሳንን ስም እየጠራ ገድላቸውን እየጠቀሰ በቃልም በመልእክትም ያስተምር ነበር፡፡ ዕብ. ፲፩፥፴፪

“እንግዲህ ምን እላለሁ፤ የጌዴዎንን፣ የባርቅን፣ የዮፍታሔን፣ የሶምሶንን፣ የዳዊትን፣ የሳሙኤልን የሌሎችንም ነቢያት ነገር ልነግራችሁ ቀን ያጥርብኛልና፡፡ በሃይማኖት የተጋደሉትን ነገሥታትን ድል የነሡትን ዋጋቸውን ያገኙትን ትሩፋት የሠሩትን ተስፋቸውን ያገኙትን የአንበሶችን አፍ የዘጉትን ዋዕየ እሳትን ያጠፉትን፣ ከጦር ስለት የዳኑትን፣ በመከራቸው የፀኑትን በሰልፍ ጊዜ የበረቱትን፣ የጠላቶቻቸውን ጭፍራ ያሳደዱትን ነገር እንዳልነግራችሁ ቀን ያጥረኛል፡፡” “ከመከራ እንዲድኑ አልወደዱምና፤ የገረፏቸው የዘበቱባቸው፣ አስረው ያጋዟቸውም አሉ፤ በመጋዝ የሰነጠቋቸው፣ በድንጊያ የደበደቧቸው፣ በሰይፍ ስለት የገደሏቸው አሉ፤ ማቅ የተልባ እግር የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፣ ተቸገሩ፣ መከራ ተቀበሉ፣ ተራቡ፣ ተጠሙ፡፡” ዕብ. ፲፩፥፴፪


#ገድላቸውን አንብበን ከበረከታቸው የምንሳተፍ ያድርገን!
👉#ማሳሰቢያ የቀረን የተወሰነ ፍሬ ነውና እንዳያመልጥዎ

[አንብበው ሲጨርሱ ቻናሉን ሼርማድረግ አይርሱ!]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🙏3👍2
#የመጽሐፍ_ቅዱስ_ታሪኮች_ለልጆች

#የልጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አስገብተናል! #በመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር የታተመ ውስጡ ከለርድ ልጆችን በሚማርክ መልኩ የተዘጋጀ ነው። ልጆቻችንን የነገ የቤተክርስቲያን ተረካቢ እንደመኾናቸው በሃይማኖትና በወንጌል ኮትኩተን በማሳደግ ኃላፊነታችን እንወጣ ዘንድ እንዲያስፈልግ ልብ ይሏል !

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🕊3👍1
#ዜና_መጽሐፍ

📖#አንጋረ_ሊቃውንት📖

#ትናንት የሌለው ዛሬ፣ መነሻ የሌለው መድረሻ የለውም፡፡ የእኛ ዛሬነት የትናንት መነሻነት ሲኾን፤ የዛሬው ማንነታችን ደግሞ ለነገዎቹ መነሻ ነው፡፡ “በቃል ያለ ይረሳል፣ በመጽሐፍ ያለ ይወረሳል” እንዲሉ፤ የዛሬ እኛዎች የትናንት ዛሬዎች፣ የነገ ትናንቶች እንደ መኾናችን መጠን፤ ከቀድሞ ጀምሮ ቃል በቃል ሲነገር የመጣውን የአባቶቻችን ብሂል ለዛሬ ተጠቅመንበት ቀጣይ ትውልድም እንዲጠቀምበት ለማስቻል መ/ር ሐዲስ ደከመኝና ስለቸኝ ሳይሉ ከአበው ቃል በቃል የመጣውንና ከመጻሕፍት ያገኙትን አሰባስበው ያቀረቡልን በመኾናቸው የአባቶች በረከት አይለይዎት በማለት ልባዊ ምኞቴን እገልጻለሁ። በዚሁ አጋጣሚ ቀደምት አባቶቻችን እንኳን ፍቅራቸውን፤ ሊያስተላልፉ የፈለጉትን መልዕክት ለጆሮ በማይጎረብጥ፣ ልብን በሚመስጥ ኹኔታ ይገልጹ እንደ ነበር መረዳት ችያለሁ፡፡

#መምህር_ዳግማዊ_ሙሴ
[የመጽሐፈ ምንኃር አዘጋጅ]

#አንብበው_ሲጨርሱ_ሼር_ማድረግ_አይርሱ!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🙏2🕊2
📖#ዜና_አበው 📖
[ዘውእቱ መጽሐፈ ገነት ካልዕ]


#የአባቶች ንግግር የመንፈሳዊ ሕይወት ትርጉም ነው፡፡ በቅድስና አኗኗር ውስጥ የሚነገሩ ቃላቶች የመንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ፍሬዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር የባሕርይ መገለጫዎቹን ማደሪያዎቹ በሆኑ በቅዱሳን ኑሮ ላይ እናገኛቸዋለን፡፡ ያ የመንፈስ ፍሬም ነገረ እግዚአብሔር ይባላል፡፡ ቢሰሙት የማይሰለቹት ቢያወሩት የማይጠግቡት ሁልጊዜ መንፈስን የሚያድስ ህሊናን የሚያለመልም ንግግር ነው። #በመምህር_አብርሃም_ፈቃዴ ተተርጉሞ የቀረበልን ዜና አበዊነ ቅዱሳን የሚለው መጽሐፍም ይሄው የአባቶች ጥልቅ ድንቅ የሕይወት ጣዕመ ንግግር ነው᎓᎓ በዘመናቸው ደርሰን በአካለ ሥጋ የማናያቸው አባቶቻችን ዕለት ዕለት እንዲመክሩን የሕይወት ጣዕማቸው ይሄው ደርሶናል፡፡ ወንጌል በሕይወት ስትገለጥ ምን እንደምትመስል ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡በጣዕመ መንፈስ ቅዱስ ከታሹ አባቶች ጋራ ማውራት ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ለመረዳት እስከ መጨረሻው ማንበብ ነው።

#የኔታ_ገብረ_መድኅን_እንየው


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🕊3🙏2
#ውድ_የግዮን_ቤተሰቦች_እንኳን_ለሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ወርኃዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችኹ ፤ እያልን
#ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ (ወንጌላዊ) መጥቷልና ብቅ በሉ..!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🙏2🕊1
📚#መዝሙረ፡ዳዊት፡ንባቡና፡ትርጓሜው

#መዝሙረ፡ዳዊት፡ መነኮሳት፡ካህናት፡መዘምራንም፡በዜማ፡ በንባብ ፡ በቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ በመዓልትም ፡ በሌሊትም ፡ ሳያቋርጡ ፡ እን ዲጸልዩበት፤ ምእመናንም ፡ ከሌላው ፡ ጸሎት፡ይልቅ፡እሱን፡መላልሰው፡ እንዲጸልዩ ፡ የታዘዙ ፤ ኤፌ ፡ ፭ ፡ ፲፱ ። መዝሙር ፡ ፴፫ ፡ ፩ ። በሰማይና በምድር ፡ ያሉ ፡ ሁሉ ፡ በዳዊት ፡ ቃል ፡ ይዘምራሉ ፡ ተብሎ ፡ የተነገረለት፡ በመሆኑ ፡ ከሁሉ ፡ ይበልጥ ፡ ተፈላጊ ፡ መሆኑ ፡ ሲታወቅ ፡ የትርጓሜውም ፡ ዋና ፡ ጥቅሙ፡ ምስጢሩን ፡ ሳያውቁ ፡ የሚጸልዩበት ምእመናን ፡ ምስጢሩን ፡ ዐውቀው ፡ እንዲጸልዩ ፡ ማድረግ ፡ ነው ።-ስለዚህ ፡ ይኸ ፡ መዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ ከጥንት ፡ አባቶች ፡ እንደ ፡ ተረ ጐሙትና ፡ ሲወርድ ፡ ሲዋረድ ፡ እንደ ፡ መጣው ፡ ንባቡና ፡ ትርጓሜው ፡ ተጽፎና ፡ ታርሞ ፡ በግርማዊ ፡ ጃንሆይ ፡ ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ትእ ዛዝ ፡ በብፁዕ ፡ አቡነ ፡ ባስልዮስ ፡ ፈቃድ ፡ ባ፲፱፻፶ (1950)፡ ዓ ∙ ም ፡ ታተመ

[''አባ ፡ ቴዎፍሎስ ፡
የሐረር ፡ ጳጳስና ፡ የኢትዮጵያ ፡ ሊቀ ፡ ጳጳሳት ፡ ዋና ፡ እንደራሴ "]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6👍3🙏2
📖#የበገና መማሪያ ተሻሻሽሎ የቀረበ📖

ከዚህ መጽሐፍ ላይ ያለው የማስተማር ዘዴ መምህሬ መምህር ሲሳይ እኔን ያስተማረበትና እኔ የማውቀው ብቻ ከ750 በላይ በገና ደርዳሪዎች ያፈሩበት /የተገኙበት/ ነው፡፡ በተጨማሪም መጽሐፉ ተማሪዎች ለብዙ ዓመታት ሲገጥማቸው የነበረውን የበገና አደራደር መለማመጃና መማሪያ መጽሐፍ ችግር የሚፈታ ሲሆን ይህን መጽሐፍ በትክክል አንብቦና ተረድቶ ለሚለማመድ ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በገና መደርደር ይችላል የሚል እምነት አለኝ።

ቀለል ባለ ዘዴ በገናን የመማሪያ መጽሐፍ ችግር ባለበት በአሁኑ ወቅት ይህ መጽሐፍ አንዲዘጋጅ የረዳን እግዚአብሔር አምላካችን የተመሰገነ ይሁን፡፡

አቤል ተክዑ ኢንጂነር የበገና መምህር


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍3🔥1
#ራእየ_ኒፎን

የይቅርታ ፏፏቴ የርኅራኄ ባለጠጋ የሆንክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ማረኝ፤ ይቅርም በለኝ፡፡

ጌታ ሆይ “አላውቅህም አትበለኝ!' ጌታ ሆይ እስከዛሬ የት ነበርክ?' ብለህም አትቆጣብኝ፡፡ በኃጢአት የቆሸሽሁ፧ በበደል እንደ ጢስ የጠቆርሁ፤ ሕግህን በመተላለፍ የበሰበስሁ፤ ፍቅርህን በመርሳት የተዋረድሁ፤ በርኵሰት የሽተትሁ፤ በዲያብሎስ ምክር የጠፋሁ፤ ሰዎች በሚሠሩት አስነዋሪ ሥራም ዋነኛ የሆንኩ የማልጠቅም ትቢያና ጉድፍ ልጅህን አትናቀኝ፤ ከፊትህም አፍሬ አልመለስ፡፡

መምህሬ ሆይ! ከእኔ አትራቅ፤ ራራልኝ፤ አድነኝም፡፡ ሰው ወዳጅ ሆይ “አንተ የኃጢአተኛን በንስሐ ከክፉ መንገዱ መመለሱን እንጂ መጥፋቱን እንደማትሻ' አውቃለሁና ተመልሰህ እስክትረዳኝና ምሕረትህን እስካገኝ አላርፍም፡፡"

(ራእየ ኒፎን ገጽ 59)


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
15🙏3