ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.31K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
📖“ድርሳን ዘሄርማን ነቢይ ንባብና ትርጓሜው”

ተወዳጆች ‎ከዚህ ቀደም "መጽሐፈ ምሥጢር ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ" በተሰኘ የትርጉም ሥራቸው የምናውቃቸው ➮‎ ‎አባ ኅሩይ ኤርምያስ (ዶ/ር) ከዚህ በፊት ያዘጋጇቸው መጻሕፍት እና የምርምር ሥራዎች መካከል መዝገበ ታሪክ ቁጥር 1፣መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2፣መልካም ዜጋ ማነው?፣ገድለ ቂርቆስ ትርጉም ፣ገድለ ፋሲለደስ - ትርጉም፣ ገድለ አቡነ ቀውስጦስ - ትርጉም፣ ገድለ አቡነ ታዴዎስ - ትርጉም፣ ገድለ አቡነ አፍጼ - ትርጉም፣ መጻሕፍትን መርምሩ፣መርኆ ምሥጢር፣ መጽሐፈ ምሥጢር ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ- ትርጉም፣ቅዳሴ ወቁርባን፣ እንዲኹም መዐዛ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው - አንድምታ........ ተጠቃሽ ናቸው።

👉አኹንም ይህን “ድርሳን ዘሄርማን ነቢይ ንባብና ትርጓሜው”፡ ከተዘጋጀ ቢቆይም ሀገር ውስጥ ማግኘት አለመቻላችንን ከግምት በማስገባት እዚኹ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል....
💧መጽሐፉንም እኛው ዘንድ ያገኙታል ....!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏2🕊2
📖📖📖
#የቅዱስ_ጳውሎስ_14ቱ_መልእክታት

..፲፱ወይትዐወቅ ምግባሩ ለሥጋ
የሥጋም ሥራው ይህ ነው፤
ዝሙት፡ዝሙት፤፳ርኲስ፡ኃጢአት ወምርዓት፡መዳራት፤አጣዕዎ፡በጣኦት ማምለክ ፤ሥራይ፡ሥራይ ማድረግ ፤ ጸልእ፡ፀብዕ፤ትዝኅርት፡ትዕቢት፤ትውዝፍት፡የምንዝር ጌጥ፤ቅንአት፡ቅንአት፤መዓት፡በቁሙቁጣ፤ኑፋቄ፡ጥርጥር፤ተቃሕዎ፡ፉክክር፤ተሓምሞ፡ምቀኝነት፤ተቃትሎ፡ነፍስመ መግደል፤ ስክረት፡ያለመጠን ጠጥቶ መስከር

  ፳፪/ ወፍሬሁሰ ለመንፈስ ቅዱስ
የነፍስ የሠራ ግን
#ተፋቅሮ፤ ፍቅር፤#ፍሥሓ፤ተስፋ ደስታ ልጅነት#ሰላም፤አንድነት #ትዕግሥት ፡በነገር በመከራ መታገሥ፤
#ምጽዋት፣ መስጠት፣#ኂሩት፤ ቸርነት #ሃይማኖት ሃይማኖት፤ #የውሃት ኃዲገ በቀል፤ #ኢዘምዎትንጽሕና 】ነው፡፡

፳፫/ #አልቦ ዘይኄይስ እምዝ ሕግ፡፡
ከዚህ ሥራ የሚበልጥ የለም፤
  ፳፬/ ወእለሰ በኢየሱስ ክርስቶስ ስቀሉ ሥጋሆሙ ምስለ ፍትወት ወምስለ ኃጢአት፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ከ፲፭ቱፈቃዳተ ሥጋ  ጋር ከፍትወት ከኃጢአት ሰውነታቸውን የለዩ ሰዎች ይገብሩ ፱ኙን ፈቃዳተ ነፍስ ይሠራሉ፡፡
#አንድም በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ፱ኙን ፈቃደተ ነፍስ የሚሠሩ ሰዎች ከፍትወት ከኃጢአት ጋር ከ፲፭ቱ ፈቃዳተ ሥጋ ሰውነታቸውን ይለያሉ፡፡
፳፭/ ወይእዜሰ በመንፈስ ንሕየው
አሆንም በፈቃደ ነፍስ እንኑር፤
ወዘመንፈስ ንግበር፡፡
ፈቃደ ነፍሳችነን እንሥራ፡፡
፳፮/ ወኢንኩን ዝኁራነ፤
ትዕቢተኞች አንሁን፡፡

[ከገላትያ ምዕራፍ ፭ የተቀነጨበ ]

መሰል ብስል ተግሳጻትን ብሎም ህግጋትን ኸረ ምኑ......ያጨቀውን የምርጥ እቃው የጳውሎስን 14ቱን መልእክታት አንድምታ ብቻ ሳይኾን ማብራሪያም ጭምር የያዘው በሊቁ #መጋቤ ሐዲስ ቃለ ሕይወት በዛ  የተዘጋጀልንን ይህን ግሩም ክታብ እነኾ።

📚ግዮን መጻሕፍት

📱ይደውሉልን ፦0913083816
5🕊4🙏3
📖"ነገረ ማርያም"
[በሶርያ አባቶች እና ሌሎች ]


መነሻው #የመንፈስ_ቅዱስ_ዋሽንት በተሰኘው በተወዳጁ #ቅዱስ_ኤፍሬም ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጻፋቸው ድርሳናት ነው ፥ ከዚም መለስ ሲባል እያንዳንዱ ገጽ ሕይወት ያለው ነው!-መምህር ዲያቆን ሽመልስ መርጊያ በርካታ የትርጉም ሥራ አበርክተውልናል... ግን እመኑኝ ይኽኛው እጅግ ልዩ ነው ልዩ ስለኾነችዋ ስለ #ድንግሏ_እመቤት -ከጽንሰቷ እስከ እርገቷ ጥፍጥ ባለ መልኩ ስለጌታም አስተዳደግ በመጠኑ የሚያትት ስለሐዋርያቱና -እመቤታችን የጠበቀ ወዳጅነት በተለይ በሶርያ ቤተክርስቲያን እዴት እንደምትከበር ሲተነትን አንዳንድ የእመቤታችን ክብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፈጠረችው እንጂ በሌሎች ኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስያናት የማትከበር ለሚመስላቸው መናፍቃን የማያዳግም ምላሽ የሚሰጥ የሚሉትም ኹሉ የእነርሱ ተረት እና እሳቤ እንደኾነ የሚያስረዳ..ነው። በጥቅሉ እጅግ ተወዳጅ መጽሐፍ ነው! -ስታነቡት እንደምትጋሩኝ አልጠራጠርም ...!
💧ሱባኤውን በንባብ ለማሳለጥ ደግሞ አይነተኛ ምርጫም ነው!

መጽሐፉን ለማግኘት ደግሞ ምንም መጨነቅ አይጠበቅም #በግዮን_መጻሕፍት በተለመዱት የሥራ ቀናት እና እኹድ ደግሞ ከቅዳሴ ሰዓት በኋላ ተሰናድቶ ይቆያችኋል!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏3🥰2🕊2
💧እንኳን ደስ አለን ድጋሚ ታተመልን .....

📖ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት


...✍️#በእውነት ከመጻሕፍት ተዋውቆ፡ መምህራንን ጠይቆ ምሥጢርን ከምሥጢር አራቆ፣ በብዕር አግዝፎ፡ በትዕግሥት ጽፎ ለትውልድ ማቅረብ ልዩ ዕድል /ስጦታ/ ነው:: ይህ መጽሐፍ ለአእምሮ ረቆ፣ ለአንደበት ርቆ ዕፁብ ለተነግሮ የሆነውን ነገረ ድንግል ማርያምን ከነገረ ድኅነት ጋር በማገናዘብ ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንትና ከሌሎችም መጻሕፍት ለቅሞ በምሥጢር አጣጥሞ፣ በጥሩ አቀራረብ ቀምሞ እንደ ቅብዐ ዘይት ጨምቆ ይዞ ቀርባል፡፡ ስለሆነም በጥርጥር የጠወለገ ባለማወቅ የደረቀና ከጠለ ምሥጢር የራቀ ልብን ያለሰልሳል፤

መጋቤ ሐዲስ ደጉ ዓለም ካሣ

[በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ መምህር]


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏4🕊2👏1
#የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ቋንቋ የምትመሰክረው ከራሷ ማንነት (Identity) ጋር የሚመሳሰል እምነት እያላት እንደ ሌላት በመቊጠር የገዛ ልጆቿን ከጉያዋ እየነጠቁ እየወሰዱ በእርሷ እንዲነሡባት የጥላቻን ትምህርት የሚያስተምሩ አያሌ ናቸው:: ታዲያ ይህ ተንኮል ያልገባው የእኔ አገር ልጅ እውነት የሚናገሩ እየመሰለው እንደ ጠፍ ከብት ወደ ነዱት ይሔዳል፡፡ እነርሱ ግን ዓላማቸው የእግዚአብሔር መንግሥት አይደለም፤ የላካቸውም እግዚአብሔር አይደለም፡፡
አምጣ የወለደቻቸው ልጆቿ በመጤ ሃይማኖትና ባህል ሲበከሉ ቤተ ክርስቲያናችን ዝም ብላ መመልከት አይገባትም፡፡ እነርሱ ዛሬ ብዙ የመስበኪያና የመሳቢያ ስልት እንዳላቸው የታወቀ ነው። የእኛም ቤተ ክርስቲያን “እሾህ በእሾህ ይነቀሳል” እንደሚባለው በተመሳሳይ ዘዴ ልጆቿን ከያሉበት መሰብሰብ ይገባታል፤ እነርሱም ቃሏን ሰምተው ነገ ዛሬ ሳይሉ ይመለሱ፤ የሰው ቤት የራስ አይሆንምና፡፡

[ከውስጥ ገጽ የተቆረሰ]

ስለመጽሐፉ አንድ ነገር ብቻ ምለው
'አንብቡት ታተርፉበታላችኹ' !

#ውድ_አፍቃያነ_ንባብ በሥራ ምክንያት #ከሰኞ -ቅዳሜ አንችልም እኹድ ቢመቻችልን ብላችኹ በጠየቃችኹን መሰረት #እኹድ ከቅዳሴ ስዓት 【ከ3-ሰዓት 】በኋላ የምንከፍት መኾኑን ልናሳውቃችኹ እንወዳለን !


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7🥰2🕊2🙏1
#ተወዳጆች....

➮የዕቅበተ እምነቷ ቅመም...
#መድሎተ ጽድቅ ቅጽ-፩
#እነኾ_ለ19ኛ_ጊዜ_ታተመች

''ለሰው ልጆች መዳኛ ትሆን ዘንድ ከእግዚአብሔር የተሰጠችው አንዲቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ክርስትና በሰዎች ግለሰባዊ አስተሳሰብና 'መሰለኝ' በሚል ግምትና መላ ምት የተገኘች ሳትሆን ከራሱ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት፡፡''

[ከውስጥ ገጽ....]


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7🙏5
#ወደ_ላይ_አያዳልጣችሁ#

   /ከዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በጣም በጥቂቱ የተቀነጨበ../

...ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አንድ ጨዋነት የራቀው ሰው ሰደባቸው አሉ። በኋላ ግን ጸጽቶት እግራቸው ላይ ወድቆ “ይማሩኝ፣ አጥፍቻለሁ፣ አድጦኝ ነው” ሲላቸው፣ እርሳቸውም “ታዲያ ወደ ታች ያድጣል እንጂ ወደ ላይ ያድጣል እንዴ?” አሉት ይባላል።

ወደ ላይ የሚያድጣቸውን ብዙ ሰዎች እያየን ነው። ሰሞኑን 👉ዘነበ ወላ የተባለ ግለሰብ፣ ሊነቅፈው ቀርቶ ሊረዳውና ሊያደንቀው እንኳ እጅግ የሚበዛበትን የምናኔ ሕይወት ለመንቀፍ ሲሞክር ሰምተናል (የተነገረው በሕንድኛ ወይም በታይ ቋንቋ አይደለም!)። ይህን የመሰሉ እናውቃለን ከሚሉ አላዋቂዎች ወይም ጭፍን ጥላቻ ካሳወራቸው ሰዎች በኦርቶዶክሳዊነት ላይ በተለያየ መንገድ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እየበዙ መምጣታቸው ጉዳዩን እንደ ቀላል ለማለፍ የማይቻል ያደርገዋል። ዛሬ ካለው የተከማቸ ኦርቶዶክስ-ጠልነት ያደረሱን ከ20ኛው መ/ዓ መጀመሪያ ጀምሮ ኦርቶዶክስ ጠል በነበሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ይሰነዘሩ የነበሩ የጥላቻ ንግግሮችና ጽሑፎች መሆናቸውን ልብ ይሏል።

ምናኔያዊ ሕይወት፣ ከትንሣኤ በኋላ የምናገኘውን እንደ መላእክት የመሆንን ሕይወት፣ በዚህ ዐለም ገንዘብ የማድረግ ሕይወት ነው። “በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ? እንጂ አያገቡም አይጋቡምም” እንዳለ ጌታችን። ማቴ. 22፡30

ምናኔያዊ ሕይወት በክርስትና ውስጥ ያለውን እጅግ የገዘፈና ዘርፈ-ብዙ የሆነ ነገረ-ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ፋይዳ ለጊዜው ብናቆየው እንኳ፣ ክርስቲያናዊ ገዳማት ለሰው ልጆች ያበረከቷቸው ኢኮኖሚያዊ፣ እውቀታዊና ታሪካዊ ጠቀሜታዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው። ጥቂቶቹን እንኳ ብናስታውስ፤ ዩኒቨርሲቲዎችና አዳሪ ት/ቤቶች በዋናነት የተቀዱት ከገዳማት ነው። የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ሲመረቁ የሚለብሱት ጋዋንና የሚደፉት ቆብ የገዳማትን ቀሚስና ሞጣህት እንዲሁም ቆብ የሚመስለው በአጋጣሚ አይደለም።

*ገዳማት ለድሆች፣ ለስደተኞች፣ ለወላጅ አልባ ልጆች፣ ለሕሙማንና ለችግረኞች መጠጊያዎች በመሆን አገለግልዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በ4ኛው መ/ዓ የነበረው ቅዱስ ባስልዮስ የመሠረታቸው ገዳማት ሐኪም ቤቶች፣ የድሆች መመገቢያዎችና የችግረኞች መርጃ ማዕከሎችም ነበሩ። የዘመናዊ ሆስፒታል ጽንሰ-ሐሳብ መሠረቱ ክርስቲያናዊ ገዳማት ናቸው።

መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው። 
   
ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም።

ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። #ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!

   
12🥰3🙏2
📖#ሰፌልያ📖

.....#ቅዱስ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ፣ የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ ፣ የመናንያን አርኣያ ፣ የሰባኪያን መምህር ፣ የአገልጋዮች ሁሉ አርማ ነው:: ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ መጻሕፍትን የጻፈውን ይህንን ሐዋርያ ማወቅ ሐዲስ ኪዳንን ለማወቅ እጅግ ወሳኝ የሆነ ቅድመ ሁኔታ ነው::

#መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን ኆኅተ ሰማይና በመሳሰሉ መጻሕፍቶቻቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመነኛ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ላይ አሻራቸውን ከተዉ ቀደምት ጸሐፍት መካከል አንዱ ናቸው:: በትንታግ አንደበታቸው በሰበኳቸው ድንቅ ትምህርቶቻቸውና "ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ?"ን በመሳሰሉ ውብ የዝማሬ ግጥሞቻቸው ብዙ የተጠቀምንባቸው መልአከ ሰላም ያሬድ አሁን ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ሕይወት የሚዳስስ እና ከመጠራቱ እስከ ዕረፍቱ ድረስ ያለውን ሐዋርያዊ ጉዞ የሚያስቃኝ በደንብ የተደከመበት ሥራ ይዘውልን ብቅ ብለዋል:: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ይናገር ዘንድ ምርጥ ዕቃ እንደነበረ ይህ ሰፌልያ የተሰኘ መጽሐፍም መጽሐፍ ቅዱስ ጥናታዊ ይዘት ያለው ስለ ጳውሎስ ይናገር ዘንድ የተዘጋጀ ምርጥ ዕቃ ነው::

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ

©መጽሐፏም እኛ ዘንድ ውስን ቅጂ ብቻ ያለ ሲኾን እንዳታልቅባችኹ ከወዲኹ ትያዝ......!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
12🙏4
📖#መጽሐፈ_ምስጢር📖

ተወዳጆች.....

#ኢትዮጽያዊው ቄርሎስ መፍቀሬ ድንግል '#ቅዱስ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ'ያበረከቱልን
'
#መጽሐፈ_ምስጢር' መደብራችን ይገኛል!ብቅ በሉ..!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🥰2🕊2
# ከ መምህረ ቤተክርስትያን ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ የተገኙ እንቁ መጻሕፍት
©አነዚኽን ጣፋጭ ምግቦች  ተመግበዋቸው ይኾን...?

📚
#ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ሕይወቱ እና ትምህርቱ
እና
# ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሕይወቱ እና ትምህርቱ

#ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ሕይወቱ እና ትምህርቱ


ከሕይወቱ ቅምሻ
[....አባ እለእስክንድሮስም አትናቴዎስን በመንበረ ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሥርዓት እያስተማረ አሳደገው፤ እርሱም ተወዳጅ ልጅ ሆነው፡፡ ከዚሁም ጋር ሰዋስው፣ ፍልስፍና፣ ክሂሎተ ነቢብና ሌሎች በዘመኑ የነበሩ ትምህርቶችንም በሚገባ ተማረ፡፡ ቆይቶም ለመዓርገ ምንኵስና በቃ᎓᎓ በቅድስናው፣ በሞያውና በግብረ ገብነቱ እንከን የሌለው ወጣቱ አትናቴዎስ በ23 ዓመቱ ....]

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሕይወቱ እና ትምህርቱ


ከሕይወቱ ቅምሻ
[....ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ራሱን ከዚህ ዓለም የበለጠ ለመሰወርና ብቻውን ዘግቶ ለመኖር በመፈለጉ ወደ ዋሻ ውስጥ ገብቶ በብሕትውናና በጽኑ ትኅርምት ለሁለት ዓመት ሲጋደል ኖረ። በዚያም በትጋሃ ሌሊት፣ ለራሱ ዕንቅልፍ በመከልከል፣ በቀዊም፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቃል በማጥናት፣ በጸሎትና በተዘክሮ ኖረ በመቀጠልም ....]

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከውስጥ ገጽ የተቆረሰ
[..ሁሉም የሌሊት ቅዠቶች ኖረዋል፡፡ ሌሊቱ አልፎ ቀኑ በመምጣቱ ከጨለማው ጋር አብረው የጠፉ ህልሞች ብቻ ነበሩ፡፡ ያለ መስሎ ታይቶ እንደጠፋ ጥላ፣ ወደ አየር ተኖ እንደጠፋ ጢስ፣ ሟሙቶ እንዳለቀ አረፋ፣ እንደተበጣጠሰ የሸረሪት ድር ነበሩ፡፡ ስለዚህ ሁል ጊዜ ይህንን መንፈሳዊ መዝሙር እንዘምራለን፡- “ሁሉ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው” የሚለውን፡፡]››

👉መጻሕፍቱን በግዮን መጻሕፍት ያገኙታል !

ይደውሉልን !📞፦0913083816 https://t.me/GhionBookStore1623
10👍3🙏2
📖#ጾመ ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ📖

#የቅዱስ ያሬድ ዋና ሥራ አባቶቻችን በልዩ ትጋትና ጥንቃቄ ባደራጁበት ስልት ተተርጉሞ መቅረቡ ለብዙኃን ግልጋሎት እንዲሰጥ ስለሚያስችል የትርጉም ሥራው አስፈላጊነት አጠያያቂ አይደለም። ድንቅ ሥራ ነው። የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐተ ማኅሌት ምን ያኽል ድንቅና ውስብስብ እንደኾነ ያሳያል። እያንዳንዱ የድጓ ዘር ከየትኛው የቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚጣቀስ፣ ምን እንደሚጨምር፣ ለዝማሬ ስልት ሲባል ምን ቃላት መደበኛ ሥፍራቸውን እንደሚለውጡ፣ ኹነኛ ቃላትን በመደጋገም የዕለቱን ዋና ጭብጥ እንዴት እንደሚያጎሉ፣ በጥቅሉም ቅዱስ ወንጌል በጾም ሳምንታት እንደምን ባለ ክብርና ሞገስ እንደሚሰበክ ለመማር ለሚፈልጉ መጽሓፉ ራሱን ችሎ መማሪያ ይኾናል። የጥንታዊት ኢትዮጵያዊት ርትዕት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነገረ መለኮትም ኾነ ያሬዳዊ ሥርዐተ አምልኮ የተቀረው ክርስቲያናዊ ዓለም ገና ወደፊት እየተሳበ የሚቀርብበት እንጂ የገቡት ሳይቀሩ የሚወጡበት እንዳይኾን በደገኛ ትውፊቶቻችን ላይ በትጋት የሚሠሩ የትርጉም ሥራዎች እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ይኸው ሥራ አንዱ ነው።
መልካም ንባብ!

#ይኩኖ አምላክ መዝገቡ የኢትዮጵያ [ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ዋና ዳይሬክተር]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍3🔥1
📖❖ ሀብታም እና ድሀ📖

...ባለጸጋው ድሀውን በየዕለቱ ደጃፉ ላይ ዓይኑ ስር ወድቆ እያየው ምንም ዓይነት ምጽዋት አልሰጠውም፡፡ ይህ ምስኪን ድሀ በጎዳና ወይም በተሰወረ በጠባብ መተላለፊያ ስላልወደቀ ባለጸጋው አንዴ ወይም ሁለቴ ወይም ብዙ ጊዜ ሲገባና ሲወጣ አይቶታል፡፡ ነገር ግን ሲገባም ሆነ ሲወጣ በውድም ሆነ በግድ ሊያየው በሚችልበት .......

...ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር አሳይቷል፡፡ እግዚአብሔር ስለ መተላለፋችን ከዚህ በኋላ በሚኖረው ሕይወት የሚጠይቀን ቢሆንም የማያዳላውን ዳኛ ሕሊናን ግን በውስጣችን ፈጠረ፡፡ ይህ ዳኛ በዚህ ዓለም ሳለ ይረዳናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ያለው .....

[ከመጽሐፉ የተወሰደ]


ወገን ራስን ለመፈተሽ አይነተኛ መፍትሔ ነው ...! እመነኝ የት ጋር እንዳለህ ይነግርሀል!..ይያዝዝ



ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍2🙏2
📖📚📚📖#አውግስጢኖስ_እና_ኦርቶዶክሳዊ_መንፈሳዊነት

#እነዚህ_የዲያቆን_ሕሊና_በለጠ_ኹለቱ_ሥራዎ_በመደብራችን_ይገኛሉ_..!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍32🙏2
📖📖📖📖📖
#አፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ_እና_ሥራዎቹ

#አፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ መንግሥት አጠቃላይ ቅጥር ግቢው በሁለት ዙር የተከበበ እና የታጠረ ሥፍራ ሲሆን፤ በአጥሩ ዙሪያም በቁጥር አሥራ ሦስት የሚደርሱ የተለያዩ መጠሪያ ሥምና ተግባር(ግብር) ያላቸው በሮች (ዕድሞዎች) እናገኛለን። እነዚህ በሮች እያንዳንዳቸው የተለያየ ተግባር እና ስም ያላቸው ናቸው፡፡ ተግባራቸውን ወደ ኋላ የምናየው ሆኖ በስም ደረጃ ውድነሽ ደጅ፣ ጸር ዋጀት ደጅ፣ መርድ ደጅ፣ መጋረጃ ደጅ፣ መስቀል ደጅ፣ ውላጅ ደጅ፣ ግምጃ ማርያም ደጅ፣ ኢየሱስ ደጅ፣ ቁልፍ ደጅ በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በርካታ ቤቶችና ድንኳኖች የነበሩ ሲሆን፤ የቀኝ በሀልቲሐት ቤት፣ የግራ በሀልቲሐት ቤት፣ የባሀልቲሐት ሽና ቤት፣ የንግሥቷ እናት ቤት፣ የዐቃቢ ሰዓት ቤት፣ የቀኝ ብሕትወደድ ቤት፣ የግራ ብሕትወደድ ቤት፣ የግብፅ ጳጳስ ቤት፣ የንጉሥ ዋና አዳራሽ ቤት፣ የሰቀላ (የጥበቃዎች ቤት፣ የአንበሶች ቤት፣ ከዚህ በተጨማሪ የቀኝ ጀጎላ ሦስት የተለያዩ ድንኳኖች(ደበና)ነበሩት፡፡ በመካከላቸው የተተከለው ድንኳን ዱለት ቤት፣ በቀኝ በኩል ያለው ግምጃ ድንኳን እና በግራ በኩል ያለው አቋት ግምጃ ድንኳን ተብሎ ይጠራ እንደነበረ ተዘግቦ ይገኛል።

      [ከውስጥ ገጽ..]

🌿#ይህ የንጉሡ ዜና መዋዕል እኛ ዘንድ አለ!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4👏2🕊2🤔1
📖ኦሪት ዘፍጥረት 📚

...✍️ኦሪት ዘፍጥረት የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ዋና ትምህርቶች ማለትም የነገረ ድኅነት፣ የነገረ ሰብእ፣ የነገረ ሥነ-ፍጥረት፣ ... መሠረት ነው፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት ብዙ መተርጉማን ትኩረት ሰጥተው በስፋትና በጥልቀት ካብራሯቸውና ከተረጎሟቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡
#እኔ_ያደረግሁት ከእነዚህ የተለያዩ አባቶች፣ ሊቃውንት እና መተርጉማን ሐሳቦች መካከል የተወሰኑትን አሰባስቦ ማቅረብ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በተከታታይ ከቀረበው የኦሪት ዘፍጥረት ማብራሪያ ትምህርት የመጀመሪያዎቹ ዐሥር ምዕራፎች ትምህርት (ከምዕራፍ 1 -10) በዚህ መጽሐፍ ቀርቧል፡፡
በመጻሕፍት ትርጓሜ ውስጥ ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ። ከእነዚህ አንዱ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) እና በመተርጉማን ግላዊ አስተያየቶች መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ለይቶ ማወቅ ነው፡፡

..... በዚህ #መጽሐፍ የቀረቡትን የመተርጉማን ትርጓሜዎችና ማብራሪያዎች በአግባቡ ተረድተን #ለሕይወት እንድንጠቀምበት #የቃሉ ባለቤት #እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

#ኦሪት ዘፍጥረትን ብትን አድርጎ የሚያብራራ ብሎም ገቢውን ለታላቁ ማኅበር #ማኅበረ_ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የተበረከተ ነው።

፨ይህ#መምህረ_መምህራን_ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ አበርክቶት ጥቂት ብቻ ነው የቀረ ሲኾን ይያዝ!!!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
8👍4🙏2🕊1
📖'አባቶችህን፡ እወቅ'📖

'አባቶችህን፡ እወቅ፡ 'በሚል ፡ርዕስ ፡የተዘጋጀው፡ ይህ ፡መጽሐፍ ፡የዚህን [የነገረ ፡አበውን]፡ ትምህርት ፡ዓላማ፡ ለማሳካት፡ በሚረዳ መልኩ፡ ጥሩ ፡ኾኖ ፡የተዘጋጀ ፡መጽሐፍ ፡ነው። #እኔ፡በበኩሌ፡ እንዲዘጋጁ ከምመኛቸው፡መጻሕፍት፡መካከል፡ አንደኛው፡ይህ ፡#መጽሐፍ  ፡ነበር ።ስለኾነም ብዙ ፡ምንጮችን  ፡መመልከት፡ የሚያሻውንና፡ ለይቶ፡ ጨምቆ ፡ለማቅረብ ብዙ ድካም ፡የሚጠይቀውን ፡ሥራ  በመሥራት፡ይህን መጽሐፍ  ፡አዘጋጅቶ ስላቀረበልን ወንድማችን #ዲያቆን_አቤል_ካሳሁንን ፡ከልብ ፡እያመሰገንኩ፡ እኛም፡ አንብበን ፡እንጠቀምበት ፡ዘንድ፡ #እግዚአብሔር ፡ይርዳን ፡እላለሁ ።


#መምህረ_ቤተክርስቲያን_ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

➮ለተወሰነ ጊዜ ጠፍቶ የነበረው ይህ እጅግ ተፈላጊ እንዲኹም አስፈላጊ መጽሐፍ በድጋሚ የታተመ ቢኾንም ጥቂት ኮፒ ብቻ ስለኾነ የታተመው እንዳያመልጠን ..!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍2🕊1
#የዲ/ን አቤል ሌላኛው ሥራው #መላእክት በድጋሚ ታትሟል!ብቅ በሉ..!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4👍2🙏2🕊2
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
#ዜና_መጽሐፍ

በወጉ ያልተዘከሩት ምሁር መጽሐፍ
       ( ዶ/ር ሥርግው ሐብለሥላሴ
)

[ጸጋው ማሞ እንዳሰናዳው]

፨"ሥርግው ምን አልባትም በ20ኛው ክፍለ ዘመን ካሉት ብቸኛው የኢትዮጵያ የጥንታዊ ታሪክ ሊቅ ነው"  ይላሉ ኤርትራዊው የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር "ባህሩ ተፍላ"  ስለ ጥረታቸውና ሀቃዊ የታሪክ ትንተናቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወልተማሪያምም  "በመክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ " መጽሐፋቸው ላይም ምሥክርነታቸውን በአድናቆት ሰጥተዋል። ተቀዳሚ ምሁር ፕሮፌሰር ሥርግው  ሐብለሥላሴ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ተምረው ባካበቱት ሰፊ እውቀት ላይ ተንተርሰው አያሌ የታሪክ ጥናቶችን እንዳካፈሉን ይታወቃል።  ከሁሉም በላይ ግን " የኢትዮጵያ  የብራና ጽሑፎች ማይክሮ ፊልም ድርጅት " ዳይሬክተር ሆነው በሰሩት  ዘመን ተሻጋሪ ሥራ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ሲዘክራቸውም ይኖራል ። #የኢትዮጵያ ሕዝብ የእርሳቸውን  የድካም  ሥራዎች ተገንዝቦ ተገቢውን ክብር ሊቸራቸው ይገባል።

➮ከእርሳቸው የበዙ ሥራዎች መካከል አንዱ  እና ግዙፍ የሆነው "አማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት " ሲሆን ይኸውም በብርቱ ያላሰለሰ ጥረት እና ድካም የተሰራ፤ ዘመን የማይሽረው ከወረት የተሻገረ እጅግ ድንቅ ሥራ ነው። ይኸ ግዙፍ መዝገበ ቃላት በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  ከጥንት ጀምሮ የነበሩ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የታላላቅ  ሊቃውንትን ፣ ቅዱሳንን ፣ ገዳማትን እና አድባራትን ታሪክ በመረጃ የሰነደ ድንቅ ሥራ ነው ። 

#ይኸ ታሪካዊ መዝገበ ቃላት ለታሪክ ተመራማሪዎች ፣ ለሥነ ጽሑፍ ሰዎች ፣ ለሥነ መለኮት አጥኝዎች ፣ ለሥነ ሰብእ መርማሪዎች እንደዚሁም ታሪክ ለሚወዱ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ መጽሐፍ ነው ። ለምሳሌ በገጽ 662 ላይ "ገላኔ"ን እንዲህ ያብራራልናል " /እመት/ በ19ኛው ምእት ዓመት የኖረች የጉድሩ ሴት። ባሉዋ ዋቅጅራ ይባላል። ከእነዚህ አብራክ የተገኘው ወንድ ልጅ  ነገሮ ይባላል...ይኸውም ተክለ ኢየሱስ የተባለው የኢትዮጵያን ታሪክን ጽፎ ያቆየን ነው " በማለት ይገልጽና መረጃውን ከታች ያስቀምጥልናል።

⨳ሌላው  የሚያሳስቱ ተመሳሳይ ስም ያላቸውን የተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን እና የቦታ ስሞች በወጉ እንድንለይም ይጠቀመናል ።ለምሳሌ በዚህ መጽሐፍ ላይ ከ35 በላይ ዮሐንስ የሚባሉ ታላላቅ ታሪካዊ ሰዎች በግልጽ ተብራርተዋል ።  ጀርመኖች ታላቁን  "Encyclopedia of Aethiopica " ከመስራታቸው በፊት የተሰራ ምናልባትም ለዚህ ስራ ታላቅ ግብአት የሆነ መጽሐፍ ነው። 

◆አሁንም የፕሮፌሰር ሥርግው ሐብለሥላሴን የድካም ውጤት "ኢትዮፋጎስ የመጽሐፍ ማእከል"ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ ተመጻሕፍት አገልግሎት " ጋር በመተባበር በእጅ ጽሑፍ የነበረውን 13 ቅጽ አርትኦት በመሥራት በሁለት ግዙፍ መጽሐፍት በማሳተማቸው ከፍተኛ ክብር እና ምሥጋና ይገባቸዋል። ከእኛ የሚጠበቀው በከፍተኛ ልፋት ተጋጅቶ የቀረበልንን ጥሩ  ማዕድ መመገብ ብቻ ነው ።

#ዶ/ር እጓለ ገብረዮሐንስ "ከመጻሕፍት   የሚደገሙት ጥሩዎቹ ናቸው " ይላሉ ።  እንደዚሁም 'ማርክ ትዋይን' የተባለ ሊቅ ደግሞ "ጥሩ መጽሐፍትን የማያነብ ሰው  ማንበብ ከማይችል ሰው አይሻልም " ይላል ። ይኸ መጽሐፍ ደግሞ ከጥሩዎቹ አንዱ ስለሆነ #በእያንዳንዱ ቤተ መጻሕፍት እና መደርደሪያ ውስጥ ሊገኝ የሚገባ ግሩም መጽሐፍ ነው ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6👍2🙏2
#የግዮን_ወንዝ

#በዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ የተጦመረው ይህ ጥዑም መጽሐፍ በድጋሚ ታትሟል! እንደሚታወቀው ደግሞ ሙሉ ገቢው ከምድራችን ቅድስተ ቅዱሳን ክፍሎች ውስጥ አንዱ ለኾነው ለታላቁ #ለደብረ_ሊባኖስ ገዳም ሕንጻ ማሰሪያ እንዲውል የተደረገ ነው ።እኛም ከንባቡ ተጠቅመን ጸኃፊውን እየመረቅን ገዳማችንን እንርዳ ...!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🕊3👍2
#ዶክተር_እጓለ ፦በተውሶ መነጽር እራስንና ማንነትን የማኮሰስ ደዌ #ያላገኛቸው ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው ። -#የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ ያጠኑ፤ የመረመሩ ለነበሩ ጥንታዊ ሀገር በቀል ባህልና እውቀት አክብሮት ያላቸው ሊቅ በመኾናቸው የሀገራቸውን ጽሑፎች ሲያጠኑና ሲመረምሩ መንፈሳቸውና አእምሯቸው ከፍ ወዳለ መራቀቅ ደረጃ ከደረሱት ጥቂት ማሰብ ከሚችሉ ሊቃውንት መካከል እጓለ አንደኛው ናቸው።

[ፍካሬ እጓለ በተመስገን ዋና የቀረበ]


....ከመጽሐፉ ለቅምሻ

#ሰውን ጥቅም፤ ተድላ፣ ደስታ ብቻ ተፈላላጊ አድርጐ በመመልከት ፤ ይህንኑ ምኞቱን የሚያረካበት ትምህርት ብናቀርብለት የሚጐዳ፣ የሚበደል እንጂ የሚጠቀም አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰዎች በመላ ለዚህ ነገር ብቻ ቢሰለፉ በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ያለው ውድድር መልኩን ለውጦ ያለመጠን አስቸጋሪና የሚያፋጅ ሊሆን ይችላል። በተለይም ይኸ እንዲህ ያለ ጥቅምን ብቻ የሚመለከት ትምህርት የሚያስገኘው ጠባይ ከሥልጣን ጋር የተገናኘ እንደሆን ነገር ጨርሶ ሊበላሽ ይችላል ለኔ ማለት ይሰፍናል።
----
የሰው ልጅና ማድጋ ጆሮውን ካልያዙት አሟልጮ ይወድቃል!❞[እዝነ-ልቡናን ያጠይቃል]

#በርግጥ ይህ መጽሐፍ በዓይነቱ እስካሁን በአማርኛ ከተጻፉ መጻሕፍት ሁሉ ብቸኛና ዘላቂ ይዞታ ያላቸው ድርሰተቶች ከምንላቸው ተቀዳሚው ነው! እንግዲያ ብቅ በሉና ደጋግማችኹ ሸምቱት ቅርስ ነውና!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
7👍2🙏2