ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.31K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
💥እነኾ አዲስ_ምግብ📚

         📖#ሐመረ_ነፍስ📖

...✍️በተለይም እንዲህ የሚሉት ጥያቄዎች ከብዙ ወጣቶች በተደጋጋሚ ይሰማሉ... ➮እውነት ያለዉ በኦርቶዶክስ ክርስትና ውስጥ መሆኑን እንዴት እርግጠኛ መሆን እንችላለን? ➮ሰው በተወለደበት ማኅበረሰብ ባገኘው እምነት ወደ እውነትና ዘለዓለማዊ ሕይወት መድረስ አይችልምን? ➮በሁሉም ሃይማኖት ውስጥ ያለ አስተምህሮና መዳረሻስ አንድ አይደለምን?➮ በሂንዱይዝም ውስጥ እሉ የሚባሉት ታላላቅ ሰዎች (ጉሩዎች) የሚያደርጓቸው አስገራሚ ነገሮች ከእግዚአብሔር ኃይል የተገኙ አይደሉም ማለት እንዴት ይቻላል?➮ ዮጋ የሚባለው የተመስጦ ልምምድስ ከሃይማኖት ጋር ይገናኛልን? ➮ክርስቲያን ሆኜ ዮጋን ብለማመድ ምን ችግር አለው?

#ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎችም መልስ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ከግሪክ ተነሥቶ ወደ ህንድ አገር ሄዶ በዚያ ካለ የሂንዱይዝም ታላላቅ ጉሪዎች ጋር ተገናኝቶ ያየውንና በራሱ ላይ በተጨባጭ የደረሰበትን ነገር የጻፈው እንደ እርሱ ያለ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች በእርሱ የደረሰው ችግር ይደርስባቸውና ራሳቸውን ለአደጋ ማጋለጥ ሳያስፈልጋቸው ከእርሱ የድካም ፍሬ ትምህርት መውሰድ ይችሉ ዘንድ ነው። ስስዚህ ከዚህ ዓይነቱ ተግባራዊ ሙከራና ውጤት መማር ጠቃሚም ተገቢም ነው። ወንድማችን ዲ/ን ሁነኛው ተሾመም ይህን መጽሐፍ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ስላቀረበልን ከልብ አመሰግነዋለኹ።#እግዚአብሔር ለወንድማችን መልካም ዋጋ ይክፈልልን እኛንም አንብበን ለመጠቀም ይርዳን! በማለት  በዚሕ መልኩ
#ዲ/ን_ያረጋል_አበጋዝ የጋበዙን ሲኾን

#ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816
7👍2🕊2🙏1
💧🥀ዜና መጽሐፍ

📖ከቅዱስ_ጳውሎስ 📖

#በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው መጽሐፍ ወጣ.....
በቀደመ ሥራው «አባቶችህን እወቅ »ብሎን የነበረው ዲያቆን አቤል አኹን አንድ በአንድ ሊያሳውቀን ቆርጦ ሣይነሳ አልቀረም። ይኸው#ከጌታ_ምርጥ_ዕቃ_ከቅዱስ _ጳውሎስ ጀምሮታል እንግዲህ አለማንበብብ ሳይኾን ለማዘግየት ማሰብ ራሱ ግፍ ነው ......

#በእውነቱ መምህራችን ያኑርልን!🙏

ከደረስንበት በወፍ በረር እናድርሳችኹ ,,,,

‹‹ቅዱስ ሉቃስ ሐዋርያው ጳውሎስ በልብሱ ጨርቅ ድውይ የፈወሰበትን፣ በእጆቹም እጅግ የሚያስገርም ተአምራት ያደረገበትን ታሪክ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ እና ክርስቲያኖችን ያሳድድ እንደ ነበር መጻፉ ለእኛ ለኃጥአን መጽናኛ እና ትልቅ የተስፋ ስንቅ ነው፡፡ ንስሐ የማያጥበው ሰውነት፣ የማያነጻው ማንነት የለም፡፡ እኛ የቱንም ያህል ብንበድል እና በኃጢአት ያደፍን ብንሆን፣ የእኛ መቆሸሽ እግዚአብሔር ከሚያጥብበት የንስሐ ሳሙና በላይ ሊጠነክር አይችልም፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ የመጠራት ታሪክ የንስሐን ኃያልነት እና የእግዚአብሔርን ምሕረት ያለ ማቋረጥ የሚያሳይ ዘመን አይሽሬ መስታወት ነው፡፡ ስለዚህም አሳዳጁን ሳውል ወደ ሐዋርያነት ያሸጋገረችውን ንስሐ ከአባ ዮሐንስ ሳባ (አረጋዊ መንፈሳዊ) ጋር በመሆን እንዲህ እያልን እናመስግናት

[ከገጽ 149]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
16🙏4👍2🕊2
💧💧💧💧💧💧💧

📖#የጽድቅ_ሕይወት📖

አልፎ አልፎ አንዳንድ ሰዎች “ለጸሎት ጊዜ የለንም!” በማለት ይቅርታ ሲጠይቁ ይደመጣሉ፡፡ እኔ ምንጊዜም ቢሆን እንደዚህ ያለውን ምክንያት ፈጽሞ አልቀበለውም፡ ዋና ምክንያት አድርጌም አልቆጥረውም፡፡ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች እንዲህ እላቸዋለሁ፡ “ጸሎታችሁንና ተመስጦአችሁን ቅድሚያ ከምትሰጧቸው ፍላጎቶቻችሁ በላይ አድርጋችሁ የምታስቀምጧቸው ከሆነ ለእነርሱ የሚሆነውን ጊዜ ማግኘት ትችላላችሁ በአገልግሎት መስክ ውስጥና ብዛት ባላቸው አገልጋዮች ሕይወት ውስጥ ስላለው ጸሎትም ተመሳሳይ ነገር መናገር እንችላለን ፡፡ እነርሱ ራሳቸውን በመንፈሳዊነት ለማዘጋጀት ከሚወስዱት ጊዜ የበለጠ ትምህርቱን ለማዘጋጀት ለሚወስዱት ጊዜ ነው ትኩረት የሚሰጡት፡፡ እነርሱ የሚጨነቁት ለአገልግሎታቸው ጊዜ፡ ለአገልግሎቱ ለሚደረጉ ስብሰባዎች፡ ለፎቶግራፎች፡ ለስጦታዎች፡ ለቤተመጻሕፍት፡ ለስብከቶች፡ ለጉዞዎችና ለሌሎች ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች ነው፡፡

[ከመጽሐፉ የተወሰደ]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
10👍3🙏2
💦#ዜና_መጽሐፍ

📖የአባ_ዘራስ_ምክር📖
[ከእማኾይ_እኅተ_ማርያም_ይፍሩ_ዘደብረ _ወገግ]

📝ከእማኾይ ጋር ምንም እንኳ-#በገድለ_ምንኲስና ብንተዋወቅም #የበረሃው_ምስጢር በተሰኘው ክታብ ልቡ ተሳፍሮ ከቅዱሳኑ በረሃ ያልገባ #ፍቅረ_እግዚአብሔር እንዲሁም ወደር አልባ ምሕረቱን በማሰብ ድንቂያ ያልወዘወዘው፤ የልቡናውን አውታር በቅዱሳኑ ታሪክ ያላለዘበ የለም ብንል ሐሰት አይመስለኝም! -ታድያ አኹን ደግሞ ከ፬ዓመታት በኋላ #የአባ_ዘራስ_ምክር በተሰኘ አጓጊ መጽሐፍ መተውልናል እነኾ .....!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4🥰3👍2🙏2
#ዜና_መጽሐፍ 💧

📖#የቤተ-ክርስቲያን ታሪክ📖

❝ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ፣ ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው አሱን ማገድ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራው እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሠይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡ የሐሜት ጐርፍ ያስወርድብሃል፡፡ #ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ...❞
[#ብጹዕነታቸው አቡነ ጎርጎርዮስ ]

#ቀ'ደ'ም በኹለት ክፍል ተዘጋጅቶ የነበረው -የቤተክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ እና -የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ #ከብጹዕነታቸው አቡነ ጎርጎርዮስ ጥዑም ታሪክና፤ተግሳጻት ጋር ታጅቦ በአንድ ጥራዝ
 #በመምህር በአማን ነጸረ እና በተመስገን-ዋና #አርትኦትነት ተዘጋጅቶ ብቅ ብሏል እንዳያመልጠን....!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🕊2👍1🙏1
«ሰው የሚፈልገውን ከፈጸመ የሚጠብቀው ሞቱን ነው !»

ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ】

#ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል በመቂ ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለሚገኙ ምእመናን ትምህርተ ወንጌል ለመስጠት ሲሔዱ በዚህች ቀን በድንገተኛ የመኪና አደጋ አለፉ፡፡😭 ገና በ፶ ዓመታቸው! ከጊዜ ጋር የነበራቸው መሽቀዳደም ተገታ፡፡ ጥድፊያው፣ ችኮላው፣ ከሀገር ሀገር መራወጡ፣ ትውልድ ማሰባሰቡ ለዚህ ኖሯል። ያ በርቀት የተያዘ ዕቅድ በአጭር ተቀጨ ያ ዕረፍት አልባ ሩጫ በሞት ተገደበ ፤ #ያ ተወርዋሪ ኮከብ ብልጭ ብሎ ወገግታውን ሰጥቶ ጠፋ፡፡ ለተልዕኮ የመጣ ነውና በተልዕኮ አለፈ፡፡ የዕድሜን፣ የመኖርን፣ አጭር ጊዜ ኖሮ ሕያውና ዘላቂ ሥራ መሥራትን በሕይወቱ ተርጕሞልን ተጠራ፡፡
አባታችን ለሞት የተጠሩበት ዕድሜ በጳጳሳት ደረጃ ሲታይ እጅግ ልብ ሰባሪ የሚባል ነው፡፡ የሞታቸውን ዜና የዘገበው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በፊት ለፊት ገጹ የተጠሩበትን ዕድሜ አጉልቶ “በ፶ ዓመታቸው አርፈዋል” ያለው ጥሪው ቢያሰቅቀው ነው፡፡ ከአባታችን ጋር ለአገልግሎት አብረው ሔደው የነበሩት ዲያቆን ጳውሎስ በቀለና የመኪናው አሽከርካሪ ዲያቆን ኤፍሬም ዘውዴም በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ገና በለጋ ዕድሜያቸው አልፈዋል።

ስምከ ሕያው ዘኢይመውት

[ ከ፲፱፻፴፪ - ፲፱፻፹፪ ዓ.ም  ]


#እኛም እንጂ ታሪካቸውን ብሎም ስራዎቻውን በማንበብ እንዘክራቸው ዘንድ #አዲሱን የብጹዕነታቸውን መጽሐፍ ለዛሬ በልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል!

[ታላቁ አቡነ ጎርጎርዮስ  በዛሬው ዕለት ነው ያረፉት በጸሎታቸው ያስቡን !]

ፍኖተ መጻሕፍት

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816
11🔥4🙏4
🫧መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ

.....🤔እናንተዬ ጊዜው ይነጉዳል የዛሬ 55ዓመት ገደማ መኾኑ ነው...
#መልአከ_ብርሃናት_አድማሱ_ጀንበሬ የኢትዮጵያን ሊቃውንት ታሪካቸውንና ቅኔያቸውን አሰባስበው ለኅትመት እያዘጋጁ በነበሩበት ወቅት በስትሮክ ሕመም በወርኃ ሐምሌ 24 ቀን1962 ዓ.ም ኅልፈት የገታቸው .....

የ20ኛው ክፍለ ዘመን መብራት እንቁ ሊቅ ረቂቅ የሃይማኖት አርበኛ መኾናቸው ዛሬም መጻሕፍቶቻቸውን ያነበበ በሙሉ የዃሊት መለስ ብሎ በአድናቆት የሚመሰክረው እውነታ ነው።
💧 በእቅበተ እምነት ዙሪያም ይኽ ነው የማይባል አሻራ አኑረውልናል ።ከድንቅና ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቻቸው መካከል መድሎተ አሚን[ሰው ኾይ!!] እና ኰኲሐ ሃይማኖት የተሰኙት መጻሕፍት በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው ።
የሚደንቀው እያንዳንዱን መጽሐፍ በትህትና ለብጠው በእውቀት ጠርዘው እንዳዘጋጁት መጻሕፍቱ ምስክር ናቸው ለዚያም በየዘመኑ የሚነሱ ዛሬም ድረስ ያሉ አሉን የምንላቸው እውቅ ጸሐፍት በየክታቦቻቸው የእሳቸውን መጽሐፍ ሳያጣቅሱልን አያልፉም ።
ለእናት ቤተክርስትያንም ግጻዌ እና መሰል መገልገያዎች ያበረከቱ ፤ የቅኔ ማዕበል የኾኑ ታላቅ ሊቅ......!

[በረከታቸው ትድረሰን!]

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
18🕊4🤔2

📖መጽሐፈ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን📖

#ይህ መጽሐፍ ጥንታዊው #ኦርቶዶክሳዊ_የቤተ_ክርስቲያ፣ አስተምህሮ ከዘመነኛው ተግዳሮት (በተለይ እስላማዊው የአስተምህሮ ትችት) አንጻር ቃኝቶ ያዘጋጀው ድርሰቱ ነው:: ምሥጢረ ሥላሴን በአብዛኛው በኩነታት አጓጻር ሲያብራራ እናገኘዋለ። ይህም ለእስላማዊው ትችት የተሻለ የሚሆነው በኩነታት ላይ የተመሠረተው ሐተታ በመሆኑ ነው::

👉ይህ መጽሐፍ በሳዊሮስ እና በሌሎች አረብ~ክርስቲያ፣ ሊቃውንት ድርሳናት በተለመደ መልኩ ጥልቅ እና ረቂቅ የሆኑ ተመስጦአዊ ሐተታዎች፣ የያዘ መጽሐፍ ነው። ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ነገረ~ሃይማኖታዊ ሐተታዎች፣ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የሆኑ የመንፈሳዊ ሕይወት መመሪያዎች፣ እና ተሞክሮዎች የያዘ እጅግ ጠቃሚ መጽሐፍ መሆኑ ነው::
#መምህር_ኤፍሬም ክንዱ ይህን በቀላሉ የማይገኝ ውድ መጽሐፍትን ከግእዝ ወደ አማርኛ ተርጉመው ለአንባብያን ማብቃታቸው በእጅጉ የሚያስመሰግን ነው:: #ለመምህር _ኤፍሬም #እግዚአብሔር ብዙ የሚያገለግሉበት፣ ጸጋ ያድልልኝ!!

ዲ/ን በረከት አዝመራው


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
11🙏2🕊2👏1
#ውድ_የግዮን_ቤተሰቦቻችን
# እንኳን ለጾመ ማርያም [ጾመ ፍልሰታ ለእግዝእትነ]  አደረሰን..!

..ታዲያ ለተወጁ ጾም ማሳለጫ ይኾኑ ዘንድ እኒህን መረጥንላችኹ👇ተጋበዙልን...

📜ነገረ ማርያም በሶርያ አባቶች ፦በጣም ግሩም መጽሐፍ ነው!#በመምህር ሽመልስ መርጊያ ፦ በጥቅሉ ስለ ቅድስቷ ደስ በሚል አጻጻፍ የተዘጋጀ...እንደምትወዱት አልጠራጠርም !

📖ፍና ቅዱሳን  ፦ ቀሲስ ታምራት ውቤ ...እድሜዎትን ያርዝምልን ..!  ይህ ከቅዱሳኑ መንገድ እንዴት እንደምንደርስ ቆንጠጥ እያረገ በግሩማን መካሪ ቃላት የተሰናዳ ብቻ ምን አለፋችኹ ጓደኛ የሚኾን መጽሐፍ !ይያዝ!

🗞ሕይወተ ማርያም ድንግል ፦ከሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የተበረከተ...ስለዚህ  መጽሐፍ ማውራት ይከብዳል ከጥፍጥናው የተነሳ ከእጃችን ባንለየውሳ ያሰኛል....! ለዚህ ጾም ደግሞ የግድድድድ መነበብ አለበት!

📝ከበረሐውያን ሕይወት እና አንደበት ፦መምህረ መምህራን ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ እቅበተ እምነት ብቻ አይደለም እንዲህ ወደ ቅድስና የሚያንደረድር መሳጭ መጽሐፍም አበርክተዋል! አደራ ይነበብ!


👉#እኛም ጥቆማ ብቻ ሳይኾን ጾሙን በማስመልከት ታላቅ ቅናሽ አዘጋጅተናል!


"...እኛስ ወገኖች ጾምን እንጹም ባልንጀራችንን እንውደድ እርስ በእርሳችንም እንዋደድ...."

«ቅዱስ ያሬድ ማሕሌታይ»

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
12🥰3👍2
📖#አንቀጸ_ብርሃን_ትርጓሜ📖

#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲህ ገልጿቸው ነበር ✍️"ቅዱሳት መጻሕፍት ተቀድቶ እንደማያልቅ ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ናቸው፡፡ ማንም : ሰው : የፈለገውንና የቻለውን ያህል ጠጥቶ መርካትና ቀድቶ መውሰድ ይችላል፣ የውኃ ጉድጓዱን ግን አይጨርሰውም። ከእርሱ በኋላ የሚመጡ ሌሎችም እንዲሁ መጠጣትና መቅዳት ይችላሉ፡፡ የቀደመው ለኋለኛው፤ ያም ከእርሱ በኋላ ለሚመጣው አይጨርስበትም፡፡"
.. ይህም ማለት ቅዱሳት መጻሕፍትን ሊቃውንት በየዘመናቱ ይመሰጡባቸዋል፤ ይመገቧቸዋል፤ ይተረጕሟቸዋል፣ ያም ሆኖ ግን እነርሱ የተገለጠላቸውንና የቻሉትን ያህል ተረድተውና አስረድተው ያልፋሉ እንጂ ምሥጢሩን ግን አይጨርሱትም።

#መምህራችን መምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ እስከ ዛሬ ሐሳቡ ሳይፍታታና ሳይተረጐም በገጸ ንባብ ብቻ የነበረውን አንቀጸ ብርሃን የተባለውን የቅዱስ ያሬድን ድርሰት በአንድምታ ትርጓሜ ተርጉመው አቅርበውልናል።

#የኔታ ኃይለ ማርያም ዘውዱ  በዚህ የጀመረው አስተማሪ የሆኑ ሌሎች መጻሕፍትንም ብዕራቸው ወደፊትም እንደሚያስነብበን ተስፋ በማድረግ፤ እርሳቸውን እንዲጠብቅልን እኛንም #አንብበን እንድንጠቀም #እግዚአብሔር ይርዳን እላለሁ፡፡

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🙏2🕊2
📖ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም
ጸሎተ ሃይማኖትና አቡነ ዘበሰማያት
አንድምታ ትርጓሜ

#ውዳሴ ማርያምንና ቅዳሴ ማርያምንና የጸለዩ አባቶች ከፍ ያለ ክብርና ከፈጣሪያቸው ባለሟልነትን ተቀብለዋል። እኛም በጸሎቱ ተጠቅመን ከሰይጣን ሥራ ከሥጋ ፈተና ተጠብቀንበት በአምላካችን ዘንድ ክብር እንድናገኝ ያድርገን፤ ለቅዱስ ኤፍሬምና ለቅዱስ ሕርያቆስ ምሥጢሩን ጥበቡን የገለጠች እመቤት ለእኛም ጥበቡን ማስተዋሉን ትግለጥልን፤ ከነዚህ ቅዱሳን በረከት ረድኤት ያሳትፈን፤ አሜን፡፡

#በታላቁ የበዓታው ሊቅ መጋቤ ሐዲስ ደምጸ አንበርብር የተዘጋጀው ይህ የእመቤታችንን ውዳሴዋን ቅዳሴዋን ከአቡነ ዘበሰማያትናጸሎተ ሃይማኖት ጋር የያዘ አንድምታ ነው! ማብራሪያውና ታሪኩማ ልዩ ነው !!

➮በያዝነው ጾም ደግሞ አስፈላጊነቱ የማያጠያይቅ ነው!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6🥰3🕊3🙏2
📖“ድርሳን ዘሄርማን ነቢይ ንባብና ትርጓሜው”

ተወዳጆች ‎ከዚህ ቀደም "መጽሐፈ ምሥጢር ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ" በተሰኘ የትርጉም ሥራቸው የምናውቃቸው ➮‎ ‎አባ ኅሩይ ኤርምያስ (ዶ/ር) ከዚህ በፊት ያዘጋጇቸው መጻሕፍት እና የምርምር ሥራዎች መካከል መዝገበ ታሪክ ቁጥር 1፣መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2፣መልካም ዜጋ ማነው?፣ገድለ ቂርቆስ ትርጉም ፣ገድለ ፋሲለደስ - ትርጉም፣ ገድለ አቡነ ቀውስጦስ - ትርጉም፣ ገድለ አቡነ ታዴዎስ - ትርጉም፣ ገድለ አቡነ አፍጼ - ትርጉም፣ መጻሕፍትን መርምሩ፣መርኆ ምሥጢር፣ መጽሐፈ ምሥጢር ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ- ትርጉም፣ቅዳሴ ወቁርባን፣ እንዲኹም መዐዛ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው - አንድምታ........ ተጠቃሽ ናቸው።

👉አኹንም ይህን “ድርሳን ዘሄርማን ነቢይ ንባብና ትርጓሜው”፡ ከተዘጋጀ ቢቆይም ሀገር ውስጥ ማግኘት አለመቻላችንን ከግምት በማስገባት እዚኹ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል....
💧መጽሐፉንም እኛው ዘንድ ያገኙታል ....!


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏2🕊2
📖📖📖
#የቅዱስ_ጳውሎስ_14ቱ_መልእክታት

..፲፱ወይትዐወቅ ምግባሩ ለሥጋ
የሥጋም ሥራው ይህ ነው፤
ዝሙት፡ዝሙት፤፳ርኲስ፡ኃጢአት ወምርዓት፡መዳራት፤አጣዕዎ፡በጣኦት ማምለክ ፤ሥራይ፡ሥራይ ማድረግ ፤ ጸልእ፡ፀብዕ፤ትዝኅርት፡ትዕቢት፤ትውዝፍት፡የምንዝር ጌጥ፤ቅንአት፡ቅንአት፤መዓት፡በቁሙቁጣ፤ኑፋቄ፡ጥርጥር፤ተቃሕዎ፡ፉክክር፤ተሓምሞ፡ምቀኝነት፤ተቃትሎ፡ነፍስመ መግደል፤ ስክረት፡ያለመጠን ጠጥቶ መስከር

  ፳፪/ ወፍሬሁሰ ለመንፈስ ቅዱስ
የነፍስ የሠራ ግን
#ተፋቅሮ፤ ፍቅር፤#ፍሥሓ፤ተስፋ ደስታ ልጅነት#ሰላም፤አንድነት #ትዕግሥት ፡በነገር በመከራ መታገሥ፤
#ምጽዋት፣ መስጠት፣#ኂሩት፤ ቸርነት #ሃይማኖት ሃይማኖት፤ #የውሃት ኃዲገ በቀል፤ #ኢዘምዎትንጽሕና 】ነው፡፡

፳፫/ #አልቦ ዘይኄይስ እምዝ ሕግ፡፡
ከዚህ ሥራ የሚበልጥ የለም፤
  ፳፬/ ወእለሰ በኢየሱስ ክርስቶስ ስቀሉ ሥጋሆሙ ምስለ ፍትወት ወምስለ ኃጢአት፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ከ፲፭ቱፈቃዳተ ሥጋ  ጋር ከፍትወት ከኃጢአት ሰውነታቸውን የለዩ ሰዎች ይገብሩ ፱ኙን ፈቃዳተ ነፍስ ይሠራሉ፡፡
#አንድም በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ፱ኙን ፈቃደተ ነፍስ የሚሠሩ ሰዎች ከፍትወት ከኃጢአት ጋር ከ፲፭ቱ ፈቃዳተ ሥጋ ሰውነታቸውን ይለያሉ፡፡
፳፭/ ወይእዜሰ በመንፈስ ንሕየው
አሆንም በፈቃደ ነፍስ እንኑር፤
ወዘመንፈስ ንግበር፡፡
ፈቃደ ነፍሳችነን እንሥራ፡፡
፳፮/ ወኢንኩን ዝኁራነ፤
ትዕቢተኞች አንሁን፡፡

[ከገላትያ ምዕራፍ ፭ የተቀነጨበ ]

መሰል ብስል ተግሳጻትን ብሎም ህግጋትን ኸረ ምኑ......ያጨቀውን የምርጥ እቃው የጳውሎስን 14ቱን መልእክታት አንድምታ ብቻ ሳይኾን ማብራሪያም ጭምር የያዘው በሊቁ #መጋቤ ሐዲስ ቃለ ሕይወት በዛ  የተዘጋጀልንን ይህን ግሩም ክታብ እነኾ።

📚ግዮን መጻሕፍት

📱ይደውሉልን ፦0913083816
5🕊4🙏3
📖"ነገረ ማርያም"
[በሶርያ አባቶች እና ሌሎች ]


መነሻው #የመንፈስ_ቅዱስ_ዋሽንት በተሰኘው በተወዳጁ #ቅዱስ_ኤፍሬም ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጻፋቸው ድርሳናት ነው ፥ ከዚም መለስ ሲባል እያንዳንዱ ገጽ ሕይወት ያለው ነው!-መምህር ዲያቆን ሽመልስ መርጊያ በርካታ የትርጉም ሥራ አበርክተውልናል... ግን እመኑኝ ይኽኛው እጅግ ልዩ ነው ልዩ ስለኾነችዋ ስለ #ድንግሏ_እመቤት -ከጽንሰቷ እስከ እርገቷ ጥፍጥ ባለ መልኩ ስለጌታም አስተዳደግ በመጠኑ የሚያትት ስለሐዋርያቱና -እመቤታችን የጠበቀ ወዳጅነት በተለይ በሶርያ ቤተክርስቲያን እዴት እንደምትከበር ሲተነትን አንዳንድ የእመቤታችን ክብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፈጠረችው እንጂ በሌሎች ኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስያናት የማትከበር ለሚመስላቸው መናፍቃን የማያዳግም ምላሽ የሚሰጥ የሚሉትም ኹሉ የእነርሱ ተረት እና እሳቤ እንደኾነ የሚያስረዳ..ነው። በጥቅሉ እጅግ ተወዳጅ መጽሐፍ ነው! -ስታነቡት እንደምትጋሩኝ አልጠራጠርም ...!
💧ሱባኤውን በንባብ ለማሳለጥ ደግሞ አይነተኛ ምርጫም ነው!

መጽሐፉን ለማግኘት ደግሞ ምንም መጨነቅ አይጠበቅም #በግዮን_መጻሕፍት በተለመዱት የሥራ ቀናት እና እኹድ ደግሞ ከቅዳሴ ሰዓት በኋላ ተሰናድቶ ይቆያችኋል!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏3🥰2🕊2
💧እንኳን ደስ አለን ድጋሚ ታተመልን .....

📖ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት


...✍️#በእውነት ከመጻሕፍት ተዋውቆ፡ መምህራንን ጠይቆ ምሥጢርን ከምሥጢር አራቆ፣ በብዕር አግዝፎ፡ በትዕግሥት ጽፎ ለትውልድ ማቅረብ ልዩ ዕድል /ስጦታ/ ነው:: ይህ መጽሐፍ ለአእምሮ ረቆ፣ ለአንደበት ርቆ ዕፁብ ለተነግሮ የሆነውን ነገረ ድንግል ማርያምን ከነገረ ድኅነት ጋር በማገናዘብ ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንትና ከሌሎችም መጻሕፍት ለቅሞ በምሥጢር አጣጥሞ፣ በጥሩ አቀራረብ ቀምሞ እንደ ቅብዐ ዘይት ጨምቆ ይዞ ቀርባል፡፡ ስለሆነም በጥርጥር የጠወለገ ባለማወቅ የደረቀና ከጠለ ምሥጢር የራቀ ልብን ያለሰልሳል፤

መጋቤ ሐዲስ ደጉ ዓለም ካሣ

[በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ መምህር]


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏4🕊2👏1
#የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በራሷ ቋንቋ የምትመሰክረው ከራሷ ማንነት (Identity) ጋር የሚመሳሰል እምነት እያላት እንደ ሌላት በመቊጠር የገዛ ልጆቿን ከጉያዋ እየነጠቁ እየወሰዱ በእርሷ እንዲነሡባት የጥላቻን ትምህርት የሚያስተምሩ አያሌ ናቸው:: ታዲያ ይህ ተንኮል ያልገባው የእኔ አገር ልጅ እውነት የሚናገሩ እየመሰለው እንደ ጠፍ ከብት ወደ ነዱት ይሔዳል፡፡ እነርሱ ግን ዓላማቸው የእግዚአብሔር መንግሥት አይደለም፤ የላካቸውም እግዚአብሔር አይደለም፡፡
አምጣ የወለደቻቸው ልጆቿ በመጤ ሃይማኖትና ባህል ሲበከሉ ቤተ ክርስቲያናችን ዝም ብላ መመልከት አይገባትም፡፡ እነርሱ ዛሬ ብዙ የመስበኪያና የመሳቢያ ስልት እንዳላቸው የታወቀ ነው። የእኛም ቤተ ክርስቲያን “እሾህ በእሾህ ይነቀሳል” እንደሚባለው በተመሳሳይ ዘዴ ልጆቿን ከያሉበት መሰብሰብ ይገባታል፤ እነርሱም ቃሏን ሰምተው ነገ ዛሬ ሳይሉ ይመለሱ፤ የሰው ቤት የራስ አይሆንምና፡፡

[ከውስጥ ገጽ የተቆረሰ]

ስለመጽሐፉ አንድ ነገር ብቻ ምለው
'አንብቡት ታተርፉበታላችኹ' !

#ውድ_አፍቃያነ_ንባብ በሥራ ምክንያት #ከሰኞ -ቅዳሜ አንችልም እኹድ ቢመቻችልን ብላችኹ በጠየቃችኹን መሰረት #እኹድ ከቅዳሴ ስዓት 【ከ3-ሰዓት 】በኋላ የምንከፍት መኾኑን ልናሳውቃችኹ እንወዳለን !


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7🥰2🕊2🙏1