ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.31K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
ዜና ድጋሚ ኅትመት

       📖ተንከተም📖    

ይህ መጽሐፍ፥ ይህን በተግባር የሚያሳይ፣ ጸሎተ ሃይማኖትን እየጸለዩ የይዘቱን ጥልቀት የማያወቁትን ሁሉ ከአምስት ደቂቃ ላልበለጠ ጊዜ የሚጸልዩት ጸሎት ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ የሚያመላክት ግሩም መጽሐፍ ነው። እንግዲያውስ ከ፲፪ቱ አበው የተቀበሉትን፣ ሊቃውንት በ፲፬ አንቀጾች የቀመሙትንና ፲፬ በሮች ወዳሏት መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባንን ጸሎተ ሃይማኖት በ፲፪ ምዕራፎች ላቀረቡልን ሊቀ ሊቃውንት፥ ዕድሜ፣ ጤና እንዲሰጥልኝ እየተመኘሁ ባለ፲፪ የሆናችሁት እንድታነቡት በ፲፪ቱ ሐዋርያት ስም እጋብዛለሁ። ሊቀ ሊቃውንትን ስምዐኮነን እና ሌሎች ሊቃውንትንም ልክ እንደዚህ የተቋጠሩትን እንድታፍታቱልን በዚሁ አጋጣሚ አሳስባለሁ።

#ዲያቆን_ብርሃኑ_አድማስ


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍94🕊3
#ውድ_ግዮናውያን ለተወሰነ ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረው ይህ #ዓምደ_ሃይማኖት የተሰኘው መጽሐፍ እነኾ ድጋሚ ታትሟል በርግጥም ነገረ ሃይማኖት ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ከሚያስጨብጡን ዐበይት መጻሕፍት መካከል በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው ። አናም ሳያልቅብን ከወዲሁ በመሸመት ተቃሚ እነኹን እያልን ጋብዘናል ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🥰4👍3🕊2
#ቅዳሴ_ ዐዲስ መጽሐፍ

-በቀሲስ መብራቱ ኪሮስ(ዶ/ር) የተዘጋጀ "ቅዳሴ" የተሰኘ ዐዲስ መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት ያገኙታል።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍7🥰2
📖#የሐዋርያው_የቅዱስ_ጳውሎስ_መለእክታት_ከሮሜ_እስከ_ገላትያ

#በሃይማኖት ላይ የሚጨምረውን ደፋር የሚቀንሰውን ሌባ ልንለው ይገባል እንዳለ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሣጹ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትም አባቶቻቸው ባስረከቧቸው ሃይማኖታዊ ምሥጢር ላይ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ ቅዱስ መጽሐፍን ንባቡ ለጆሮ ምሥጢሩ ለአእምሮ እንዲስማማ አድርገው ሲተረጉሙ ኖረዋል፡፡ #መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤም ሃይማኖት ያላቸው ወደ ምግባር፣ ምግባር የሌላቸው ወደ ሃይማኖት እንዲቀርቡ በማሰብ ሃይማኖት ከምግባር የታረቀበትን ሕግ ከጸጋ የተስማማበትን የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት ተንትነው እና አብራርተው አቅርበውልናል ።

❝በዚህ መሠረት ያላነበበ ክርስቲያን የሰይጣን ጉዳይ አስፈጻሚና የብልጣብልጥ መናፍቃን የሐሳብ መስጫ ሳጥን ይሆናልና ሃይማኖታዊ ዐይኑን ገልጦ መንፈሳዊ ጆሮውን ከፍቶ ውድ ጊዜውን ሠውቶ ቢያነበው እንደጠንቋይ የገመቱትን ከሚያወሩ ሐሰተኞች ሰባክያን ይጠብቀዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

#መልካም_ንባብ!

#መጋቤ_ሐዲስ_እሸቱ_ዓለማየሁ
በሰዋሰወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር



፨ ይህ ግሩም መጽሐፍ በድጋሚ የታተመ ሲኾን #በፍኖተ መጻሕፍት ያገኙታል።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍3🙏2
#ዜና ድጋሚ ኅትመት

       📖ኆኅተ ስብከት📖


ቅዱስ ያሬድ በምድር ስንኖር ሊኖረን ስለሚገባን ሥነ ምግባርና ማኅበራዊ ትስስር፤ በዚህች ምድር ስለሚያስፈልጉን ነገሮች፤ በዙሪያችን ስላሉ ድንቅ ተፈጥሮዎች ተቀኝቷል፡፡ ለምሳሌ ስለመረጋጋት፣ ስለፍቅርና ስለሰብአዊ እኩልነት ካዜመው ውስጥ ለምሳሌ ቁም በዘሀሎከ ኢታንቀልቅል ወኢትትሐወክ ለዓለመ ዓለም፤ ወዘሰ ሕኑፅ በመሠረተ እግዚአብሔር አልቦቱ ዘተኀጕለ ወኢያፍቱከ ምክሮሙ ለረሲዓን ተዘከር ሠናያተ ዘገብረ ለከ እግዚአብሔር። ወንድሞቼ ሆይ ሰውን መጥላት ምን ይጠቅመናል? ወንድምን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነውና፡፡ ባለህበት ጸንተህ ቁም፤ ተረጋጋ፤ አትነዋወጥ አትጨነቅ፤ ለዘለዓለምም አትታወክ፤ በእግዚአብሔር መሠረት ላይ የታነጸ ሰው ጥፋትና ጉስቁልና የለበትምና፤ የክፎዎች ምክራቸውና ሥራቸው አያስጎምጅህ፤ አንተ ግን እግዚአብሔር በጎ በጎ ነገር ያደረገልህን ብቻ አስብ›› በማለት በኑሮ ሒደት ማኅበራዊ ቀውስ ገጥሟቸው የተጨነቁትን አካላት በዜማው ሲያረጋጋ እናገኘዋለን፡፡

የዝማሬ፣ የፍልስፍና፤ የስነ ከዋክብት፤ የሕግ፤ የታሪክ፣ የመልክዐ ምድርና የቋንቋ ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ዛሬ ዓለም ለደረሰበት የዜማ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሕይወት ፍልስፍናም መሠረት ነው ሊያስብል የሚያስችሉ ሰማያዊ ሰነዶችን ትቶልን አልፏል፡፡ የተፈጥሮን ሁኔታ ያስቃኘናል፡፡

ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ

-ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን ደምፀ ያዘጋጁት "ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ" የተሰኘ  መጽሐፍ ለ4ኛ ጊዜ ስለታተመ በግዮን መጻሕት ያገኙታል።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
5🙏3👍2
📖#ምሥጢረ_ሥነ_ፍጥረት📖

እግዚአብሔር የሥራው ሁሉ መጀመሪያ ያደረገው ፍጥረትን መፍጠር ነው ስለዚህም የዕውቀት መጀመሪያው አምላክ በ፩ ቀን የፈጠረውን ፳፪ ፍጥረት ማወቅ ስለሚቀድም መ/ር ዲበኵሉ በዚህ መጽሐፍ አምላክ በከሀሊነቱ ፍጥረትን እንዴት እንደ ፈጠረ የፈጠረው ፍጥረትም ለያንዳንዱ የረቀቀ ምሥጢር እንዴት እንዳለው እንዲሁም ፬ ባሕርያትና ጠባያት አንድ የሚሆኑበትንና የሚለዩበትን እንዴት እንደተነተኑት አስደናቂ ምሥጢር ሁኖ አግኝቼዋለሁ።

፪ኛ በሌላ በኩል ይህ መጽሐፍ ለስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ሳይንቲስቶች ለአዲስ ምርምር በር ከፋች ነው፤ የዓለም ሳይንቲስቶች ሁል ጊዜም ስለሚመራመሩት የፍጥረታት ምሥጢር ስለፀሐይና ጨረቃ ክዋክብት, ካልዕ ፍጥረት ስለሚባሉም ሥውራን ፍጡራን በሚገርም ሁኔታ ያስረዳል፣ በተለይ እንዳንድ የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች ባለማወቅ ሳይንስ ቀዳማዊ ነው እምነት ደኅራዊ ነው እያሉ ለሚያስቡት መልሱ ይህ ነው:: ምክንያቱም አምላክ ዓለምን ካለመኖር አምጥቶ ከፈጠረ በኋላ ዓለም ላይ በተፈጠሩ ፍጥረታት ምርምር ተጀምሯልና፡፡

፫ኛ የዚህ መጽሐፍ ይዘቱ ሁሉንም አንባቢዎች ከመንፈሳውያን እስክዓለማውያን ለሳይንንቲስቶች ተመራማሪዎች ሁሉ ማዕከል ያደረገ በመሆኑ የፍጥረታትንም ረቂቅ ምሥጢር አጕልቶ አስፍቶ የያዘ በመሆኑ ሁሉም ሰው ቢያነበውና ቢማርበት ትውልድን የሚቀርፅ እጅግ በጣም ጥሩ መጽሐፍ ነው ብዬ አምናለሁ

መ/ር ቸሬ ሲሳይ መኰንን

የወልድያ የዩንቨርስቲ መምህርና ተመራማሪ


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816


t.me/FinoteBooks1623
5👍4🙏4
"ማርያም ሆይ! ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን፤ እውነተኛ የጽድቅ መብል እና እውነተኛ የሕይወት መጠጥ የሆነውን ወልደሽልናልና።"
***
ቅዳሴ ማርያም
32🥰4🙏4🕊3
"የክርስቶስ ቤዛነት ይህ ነው፦ እርሱ ስለተሸከማቸው ዘግናኝ ሕማሞች እና ኃጢኣቶች እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ይናገራል። ኃጢኣት የማያውቀውን እርሱን እግዚአብሔር አብ ስለእኛ ሲል 'ኃጢኣት እንዲሆን' አደረገው። አመንዝራው፣ ስድ ሆኖ የሚበድለው፣ ቆሻሻ በሆኑ ተግባራት አረንቋ ውስጥ የሚዛቅጠው እና ኃፍረት አልባ በሆኑ ተግባራት የሚበላሸው ሁሉ ከክርስቶስ ሲሸሽ ድምጹ በኋላው ይከተለዋል። ይኸውም 'የተወደድህ ልጅ ሆይ፥ ና! ኃጢኣቶችህ ከእኔ ጋር ናቸው፤' እያለ የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ደም ነው! ገና የሠራሃቸው ዕለት ነው በምልዓት የተሸከምኳቸው። ካሣውን ከፍያለሁ፦ ሐፍረት ተጭኖብኛል፤ ተገርፌያለሁ፤ ደቅቄያለሁ፤ ተሰቅያለሁ፤ እንዲሁም መርገምን ተሸክሜያለሁ። ለአንተ የይቅርታ እና የንጽሕና ተግባራትን እንዲሁም ይገባኛል የምትልበትን ጸጋ አዘጋጅቼልሃለሁ። ና! ለአንተ መከራ የተቀበልኩትን ያህል በአንተ ደስ ይለኝ ዘንድ ና! የመዳንን ዘውድ እደፋልህ ዘንድ፣ ፍቅሬን እና መንፈስ ቅዱስን በአንተ ላይ አፈስስ ዘንድ፣ እንዲህ አድርጌ ወደ አባቴ አቀርብህ ዘንድ ና! አንተ ከበጎቼ ሁሉ እጅግ ውዱ ነህ፤ እኔ ደሜን እስከመክፈል ደርሼ ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥቼሃለሁና።"
***
የክርስቶስ ስሞች፣ ገጽ 135-36።

ይህን ምሥጢር የሆነ መሐፍ እንድታነቡት ግብዣችን ነው።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍53🙏2
አዲሱን #ብርህት_ዓይን የተሰኘውን መጽሐፍ አስገብተናል

ስለ መጽሐፉ የተሰጠ አስተያየት

#ብርህት_ዐይንየተሰኘው መጽሐፍ ጊዜ የማይገድበው የነገረ መለኮት ማስተዋሎችን በማቅረብ በቅዱስ ኤፍሬም አእምሮ /ልቡና/ እና በዚህ ዘመን በሚገኙ አማኞች መካከል እንዳለ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።

... ስከዚህ፡ የብርህት ዐይን፣ መጽሐፍ ወደ አማርኛ ቋኝቋ መተርጎሙ ፡ በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ ካሉት ምእመናን፡ የቤተ ክርስቲያ፣ አባቶች መፈሳዊ እይታ ለማስተዋወቅ የሚረዳ ፡ #በዲያቆን_ሕሊና_በለጠ የተበረከተ ጉልህ የኾነ አስተዋጽዖ ነው :: ለዚህ ድካሙም እውነተኛና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባዋ ።

#ቀሲስ ዶክተር ጆሊ ኮብ

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍52🙏1
ውድ አንባብያን በጥያቄያችኩ መሰረት እነኾ.....

📖 #888

✍️.......የ አ ፣ በ ፣ ገ ፣ ደ  ቀመረ ፊደልን፣ በተመከተ ይኽ፣ መጽሐፍ ያዘጋጁ #መጋቢ_ሐዲስ_ዶክተር_ሮዳስ ታደሰ ፤ ጠለቅ ያለ ጥናት፣ መሠት ባደርገ ጽሑፋዊ ዝግጅታቸው መሮነት ፤ የአንባብያንን ሕዋስ አእምሮ እየፈለፈሉ፤ የጥናታዊ አጻጻፍ ጥበብ በኣት ለማድረግ አዘውትረው እየጣሩ እደኾነ ከዝግጅታቸው ምስጢራዊ ትንታኔ ለመገንዘብ ችያለኹ።

#መምህር_ዐምደወርቅ_እስጢፋኖስ

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍63🔥2🥰2
📖ኆኅተ ስብከት ፩እና ፪

የግድ ሊኖረን የሚገባ መጽሐፍ
እስኪ በወፍ በረር ላስቃኛችኹ..

‹‹ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ›› ሲባል
➮አንድም ዐይነ ልቡናችሁን ወደ ወንጌል እግረ ነፍሳችሁን ወደ መንግሥተ ሰማያት አቅኑ ማለት ነው።
➮አንድም#ወደ_እመቤታችን_ተመለሱ_ሲል_ነው፦#እመቤታችን_አማናዊት ኢየሩሳሌም ትባላለች፤ አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹ዛቲ ይእቲ ኢየሩሳሌም ሀገሮሙ ለነቢያት ወማኅደረ ፍሥሐሆሙ ለኵሎሙ ቅዱሳን᎓᎓ ደስ ብሏቸው የሚኖሩ የቅዱሳን የነቢያት የሐዋርያት የጻድቃን የሰማዕታት የመላእክት የማደሪያቸው ማደሪያ የኾነች የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ይህቺ ኢየሩሳሌም እመቤታችን ናት::›› ሲል መስክሯል፡፡ ኢየሩሳሌም ማለት ሀገረ ሰላም ማለት ነው᎓᎓ ቅዱስ ያሬድ #እመቤታችንን ሀገረ ሰላም ይላታል ‹‹ይትፌሣሕ ልብኪ ኦ ድንግል ወይትሌዓል ቀርንኪ በክብር ሰማይ ዳግሚት ብኪ ድኅነ ዓለም ወበወልድኪ ኮነ ሰላም:: ድንግል ሆይ ልብሽ ደስ ይበለው፤ መንግሥትነትሽም በክብር ከፍ ከፍ ይበል፤ ሁለተኛ ሰማይ ሆይ ባንቺ ዓለም ዳነ በልጅሽም ሰላም ሆነ።›› በማለት የዓለም ድኅነት የሰላም መገኛ ምክንያት መሆኗን ሊቁ መስክሯል። ዳግመኛም ‹‹እምጽዮን ነበበ እምኢየሩሳሌም ቃሎ ወሀበ ከመ ይመጽእ ንጉሥ ዘስሙ አማኑኤል ዘውእቱ አምላክ ቡሩክ ለዓለም አስተርአየ ገሃደ በማኅበረ ቅዱሳን፡፡ ስሙ አማኑኤል የሆነ ንጉሥ እንደሚመጣ ከጽዮን ሆኖ ተናገረ፤ ከኢየሩሳሌምም ቃሉን ሰጠ፤ ይኸውም ለዘለዓለም የተመሰገነ አምላክ በቅዱሳን ማኅበር ተገለጠ ተመሰገነ፡፡›› ሲል ከአማናዊቷ ኢየሩሳሌም ከእመቤታችን አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ተወልዶ ሰላምን እንደሰጠን ተናግሯል:: የሐዋ ፫ ፲ ፳

#ከመጽሐፉ_የተቀነጨበ

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
👍5🥰3🕊31
💦#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት
📖📖📖
#ውዳሴ_ጳውሎስ
#መግቦተ_እግዚአብሔር

.......በእርግጥ የሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ የግድ ሊኖረን እንደሚገባ ግልጽ ነው። #ታድያ ለረጅም ጊዜ ገበያ ላይ ጠፍተው የነበሩ እነዚህ ግሩማን መጻሕፍት እነኾ በድጋሚ የታተሙ መኾናቸውን እያበሰርን ለእናንተ ለውድ አፍቃርያነ ንባብ ቤተሰቦቻችን በልዩ ቅናሽ አቅርበናልና ሳያልቅ ተቋደሷት እያልን እናሳስባለን ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍5🥰21👏1
💦#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት

📖📖📖📖📖
#በእንተ_ክህነት

......መንጋው በደኅና ኹኔታ እያለና በጥሩ ምግብና ላይ ሳለ የጥበቃውን ኃላፊነት ብወስድና ከዚያ በኋላ ግን በእኔ【ካህን ኾኜ በራሴ 】 አላዋቂነትና ጥበብ የለሽነት ምክንያት ባጠፋቸው እነርሱን ለማዳንና ለመቤዠት ሲል ራሱን የሰጠላቸውን እግዚአብሔርን በራሌ ላይ አነሣሣዋለሁ ብዬ እፈራለሁ፡፡

➮ከመጽሐፉ የተወሰደ


#ስለመጋቢ /ስለ ካህን በጥልቀት የሚያትተው ይህ ግሩም መጽሐፍ በድጋሚ በውብ ኹኔታ ታትሟል!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4👏2👍1
📖#ትምህርት_በእንተ_ምክንያተ_ሐውልታት📖

.....ገብረ እግዚአብሔር ኪደን የማመሰግነው ይህን ሊቅ በራሳችን ቋንቋና ዘይቤ ዳግም እንዳውቀው ስላደረገኝ ነው፡፡ የትርጓሜው ወደረኛ ቋንቋና ውበት ሊቁን የራሳችን ትውፊትና የሕይወት ዘይቤ አካል አድርገን እንድንቈጥር ይጠቁመናል ሳይኾን ያስገድደናል፤ እኔ ተገድጄበታለሁ!
ይህን መጽሐፍ አንብቦ ትውፊቱን ከጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ለማነጻጸር፣ ሕይወቱን፣ ነባራዊውን የአገራችንን አኗኗር፣ የአገሩን ካህናት አገራዊ ሚና፣ ክርስቲያናዊ ምግባሩን ... ለመፈተሸ የማይገደድ አንባቢ ካለ ከሸንጎ ፊት ያቅርበኝ!በማለት የመጽሐፉን ግሩምነት የመሰከሩት #ደብተራና የሕግ ባለሞያ የኾኑት በአማን ነጸረ እኛም አንብበን ተጠቃሚዎች እነኾን ዘንድ ብሎም ራሳችንን እንድንፈትሽበት ያሳሰቡ ሲኾን #በግዮን_መጻሕፍት ደግሞ በልዩ ቅናሽ የተዘጋጀ ሲሆን ግዜ ሳንሰጥ መጽፏን ገዝተን ብንመገባት መልካም ነው እንላለን!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍3🙏32🔥1
📖#ሐተታ_ዘቅዱስ_አትናቴዎስ

#ያለሀሰት ቅዱስ አትናቴዎስ ለቤተክርስትያን አምድ ከምንላቸው ቅዱሳን አባቶቻችን አንዱና ዋነኛው መኾኑ አያጠያይቅም ታድድያ ከእርሱ ግሩማን አበርክቶዎች መካከል "ተስእሎተ አንትያኮስ" የተሰኘውን መጽሐፍ #መምህር_ቃለ ጽድቅ_ሕግነህ በተዋበ እና ለንባብ ምቹ አድርገው የተረጎሙት ሲኾን ➱ቅዱስ አትናቴዎስ በዚህ መጽሐፍ ከሚመልሳቸው ጥያቄዎች .....

አንትያኮስ፡ ርኩሳን መናፍስት የሆኑ አጋንንት ከቅዱሳት መጻሕፍት የሚፈሩት የጸሎት ዐይነት የቱ ነው?
ጥያቄ ፦ በውኑ ለኃጥአን ነፍሳት በዚህ ዓለም ዘመዶቻቸው የመታሰቢያ(ተዝካር) ቍርባን፣ ጸሎትና ምጽዋት ቢያደርጉላቸው በዚያኛው ዓለም ይጠቅማቸዋልን?
➮ጥያቄ ፦ ለሰው እጅ ሥራዎች እንዳንሰግድ እግዚአብሔር በነቢያቱ አዝዞናልና ለምን የሰው እጅ ለሠራው ለቅዱሳን ሥዕልና ለቅዱስ መስቀሉ እንሰግዳለን?
➮አንትያኮስ፡- ከኃጢአት ሁሉ የሚበልጠው ኃጢአት የቱ ነው?
➮አንትያኮስ፡- ብዙ በደልንና ኃጢአትን የሠራ ሰው ቢኖር ከዚያም በኋላ ንስሓ ቢገባ፤ እንደገና ተመልሶ ኃጢአት ቢሠራ እግዚአብሔር ንስሓውን ይቀበለዋልን ወይስ አይቀበለውም?

#ይህንና መሰል ጥያቄዎችን ከነ መልሶቻቸው የያዘ ልዩ መጽሐፍ በመኾኑ እንድታነቡት ግብዣችን ነው!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
9👍3👏2
#አሐቲ_ድንግል
【ለ5ተኛ ጊዜ ታትማለች】

#ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን እመቤታችን ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትውልድ" ብላ ከተናገረችላቸው አንዱ ናቸው። ይሄ መጽሐፍ በትውፊት የምናወርሰው፥ ነገር ግን እያየነው የተደረሰ አዲሱ አርጋኖን ነው። ከእኔ ጋራ የተወለደውን የመጻሕፍት ንጉሥ ታዩ ዘንድ ኑ!

#ሊቀ_ሊቃውንት_ስምዐ_ኮነ_መልአክ_የ፬ቱ_ጉባኤያተ_መጻሕፍት_ምስክር_መምህር

#አሐቲ_ድንግል" የተባለው ይህ የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያናችን ስለእመቤታችን ያላትን አስተምህሮ በሥርዓተ አምልኮዋ ውስጥ እመቤታችን ያላትን ቦታ እና ቅዱሳን ስለእርሷ እንዴት እንዳስተማሩ እና እንዴት እንዳመሰገኗት ማወቅ የሚፈልግ ሁሉ ይህ መጽሐፍ በእጂጉ ያስፈልገዋል።

#ዲያቆን_ብርሃኑ_አድማስ

#ይህች አሐቲ ድንግል የተሰኘችው መጽሐፍ ስለ ብቸኛዋ ድንግል የተጻፈች ብቸኛዋ የመጽሐፍት ንግስት ናት!#አንባቢን ከንባብ ጸሐፊን ከክታብ አያናውጽብን እያልን እጅግ አስፈላጊ መኾኑ እርግጥ ስለኾነ ይህች ብቸኛዋ መጽሐፍ #ለ5ተኛ ጊዜ ታትማለችና እነኾ ሳታልቅ እንቃመሳት።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍54🕊4🙏3🥰1
📖#ራእየ_ኒፎን📖

#በምድራዊ አሠራር አንድ ንጉሥ ለእርሱ ጠንክረው ስለተዋጉ የሚያከብራቸው አሉ፤ ብዙ ስጦታን አምጥተው ስላከበሩት የሚያከብራቸውም ይኖራሉ፡፡ ሌሎችን ደግሞ ምንም ባያደርጉለትም በፊቱ ሞገስ የሚያ ይኖራሉ፡፡ በእግዚአብሔርም ዘንድ እንዲሁ ነው፡፡ ስለ ተጋድሏቸው የሚያከብራቸው አሉ፡፡ አገልግሎታቸው የሚያከብራቸው አሉ፡፡ ከልባቸው ተፀፀተው ንስሐ ስለመግባታቸው የሚያከብራቸው ይኖራሉ፡፡ ከርኅራኄውና ከቸርነቱ ብዛት የቅዱሳኑን ጸሎትና ምልጃ ተቀብሎ የሚያከብራቸውም አሉ፡፡ በሌላም መልኩ በዚህ ነገር በሕይወታቸው የደረሰባቸውን ነገር ሁሉ ሳያማርሩ በምስጋና ስለ መቀበላቸው በመንግሥቱ መጽናናትን የሚያገኙ ይኖራሉ፡፡”

....የአገልግሎት ሹመት ፍቅረ እግዚአበሔር አሳድዳ ለያዘችው ሲሆን ደግ ነው፤ ፍሬም ይገኝበታል፡፡ ደጅ ጠንተው መማለጃ ሰጥተው የያዙት ሹመት ግን በተራው ሌላውን ደጅ ጥኑኝ መማለጃ አምጡልኝ ከሚል ውጪ መንፈሳዊ ሥራ ለመሥራት አያበቃም፡፡”

#ወንድምህ ከቆመበት ትቢያ ሥር ባለው ጥልቅ ውስጥ ራስህን በትሕትና ማቆየት ካልቻልክ፤ በኅሊናህ ራስህን በእግሩ ላይ ጣል፡፡

ከመጽሐፉ የተወሰዱ

💦...ለተወሰነ ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረውን ይህን #የመናኙ_ጳጳስ_የቅዱስ_ኒፎን የተጋድሎ ሕይወት አስተምህሮት እንዲኹም በራዕዩ አይቶ በተግሳጽ መልክ የጻፈልንን እጹብብብብ የሚያሰኝ መጽሐፍ ለእኛ በሚስማማ መልኩ በውብ አተረጓጎም #ቀሲስ_ታምራት_ውቤ ያዘጋጁት ሲኾን
ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
12👍4🥰2🙏1
📖📖📖
#የቅዱስ_ጳውሎስ_14ቱ_መልእክታት

..፲፱ወይትዐወቅ ምግባሩ ለሥጋ
የሥጋም ሥራው ይህ ነው፤
ዝሙት፡ዝሙት፤፳ርኲስ፡ኃጢአት ወምርዓት፡መዳራት፤አጣዕዎ፡በጣኦት ማምለክ ፤ሥራይ፡ሥራይ ማድረግ ፤ ጸልእ፡ፀብዕ፤ትዝኅርት፡ትዕቢት፤ትውዝፍት፡የምንዝር ጌጥ፤ቅንአት፡ቅንአት፤መዓት፡በቁሙቁጣ፤ኑፋቄ፡ጥርጥር፤ተቃሕዎ፡ፉክክር፤ተሓምሞ፡ምቀኝነት፤ተቃትሎ፡ነፍስመ መግደል፤ ስክረት፡ያለመጠን ጠጥቶ መስከር

  ፳፪/ ወፍሬሁሰ ለመንፈስ ቅዱስ
የነፍስ የሠራ ግን
#ተፋቅሮ፤ ፍቅር፤#ፍሥሓ፤ተስፋ ደስታ ልጅነት#ሰላም፤አንድነት #ትዕግሥት ፡በነገር በመከራ መታገሥ፤
#ምጽዋት፣ መስጠት፣#ኂሩት፤ ቸርነት #ሃይማኖት ሃይማኖት፤ #የውሃት ኃዲገ በቀል፤ #ኢዘምዎትንጽሕና 】ነው፡፡

፳፫/ #አልቦ ዘይኄይስ እምዝ ሕግ፡፡
ከዚህ ሥራ የሚበልጥ የለም፤
  ፳፬/ ወእለሰ በኢየሱስ ክርስቶስ ስቀሉ ሥጋሆሙ ምስለ ፍትወት ወምስለ ኃጢአት፡፡
በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ከ፲፭ቱፈቃዳተ ሥጋ  ጋር ከፍትወት ከኃጢአት ሰውነታቸውን የለዩ ሰዎች ይገብሩ ፱ኙን ፈቃዳተ ነፍስ ይሠራሉ፡፡
#አንድም በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ፱ኙን ፈቃደተ ነፍስ የሚሠሩ ሰዎች ከፍትወት ከኃጢአት ጋር ከ፲፭ቱ ፈቃዳተ ሥጋ ሰውነታቸውን ይለያሉ፡፡
፳፭/ ወይእዜሰ በመንፈስ ንሕየው
አሆንም በፈቃደ ነፍስ እንኑር፤
ወዘመንፈስ ንግበር፡፡
ፈቃደ ነፍሳችነን እንሥራ፡፡
፳፮/ ወኢንኩን ዝኁራነ፤
ትዕቢተኞች አንሁን፡፡

[ከገላትያ ምዕራፍ ፭ የተቀነጨበ ]

መሰል ብስል ተግሳጻትን ብሎም ህግጋትን ኸረ ምኑ......ያጨቀውን የምርጥ እቃው የጳውሎስን 14ቱን መልእክታት አንድምታ ብቻ ሳይኾን ማብራሪያም ጭምር የያዘው በሊቁ #መጋቤ ሐዲስ ቃለ ሕይወት በዛ  የተዘጋጀልንን ይህን ግሩም ክታብ እነኾ።

ይደውሉልን!📞፦0913083816


t.me/FinoteBooks1623
🙏52👍2🥰2👏1
📖#ገድለ_ቅዱስ _ፊቅጦር📖

✍️ #እርሱ ባለቤቱ የሠራዊት ጌታ አምካችን እግዚአብሔር በዐወቀ ለወዳጆቹ ቅዱሳን የሰጣቸው ሌላም ትንቢታዊ ዕሤተ ጸጋ አለ ። እውነት ነው :: የእርሱ ቸርነታዊ ጸጋ እጅግ ብዙ ነው።

ቅዱስ መጽሐፍም ይኽንኑ ሲያረጋግጥ “ወብክሙ ጸጋ

<"እግዚአብሔር--------ከአምላካችሁ እግዚአብሔር የተሰጣችሁ ልዩ ልዩ ጸጋ አላችሁ...">ይላል ።
#ከእነዚኽም ጸጋዎች አንዱ ሀብተ ትንቢት #ለሰማዕቱ_ቅዱስ_ፊቅጦር ተሰጥቶት ከአንፆኪያ እስከ እለእስክንድርያ ምድር ይልቁንም ባርቆን ድረስ በስደት ተግዞ በተቀበለው ፀዋትወ መከራ ውስጥ ሳለ በዚኽ የመጨረሻው ዘመን ስለሚከሠተውና ስለሚኾነው ነገር ስለ #ኢትዮጵያም ኹሉ ግልጥ ትንቢትን ተናግሯል፡፡

➮ይኽን ትንቢቱንም በዚኹ መጽሐፈገድል ውስጥ እንደምናነበው በዚኽ በአለንበት ዘመን እየታየ ያለውን አስከፊና አስደንጋጭ
የጭንቅ ኩነትና በመጨረሻም መልካም ዘመን እንደሚመጣ ደግ ንጉሥ ቴዎድሮስ እንደሚነሣ ይናገራል ፡፡ በተጨማሪም “...በዚያ ዘመን ሰዎች እርስ በእርሳቸው ይጠላላሉ ። አንዱ አንዱን ለሞት አሳልፎ ይሰጠዋል ይገድለዋል ። ሐሰተኞች ነቢያትና ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ ፡ ብዙ ሰዎችን ያስታሉ.........እያለ በዚህ ገድል ሰፋ አድርጎ የተገለጸለትን ያትተዋል።

#ገድላትን በማንበብ ከበረከታቸው ሱቱፋን እንኾን ዘንድ ይገባናል !ታድያ ጽሩይይይ በኾነ መልኩ ተተርጉሞና ተሻሽሎ እንዲኹም ለአይን ምቹ ይኾን ዘንድ ሽሮ ከለር ኾኖ ቀደሞ ከ88 በላይ ገድላት እና ድርሳናትን ከግእዝ ወደ አማርኛ በመተርጎም ያበረከቱልን ሊቁ አኹን ደግሞ የዚህን #ታላቅ_ሰማእት_ማር_ቅዱስ_ፊቅጦር ገድል አበርክተውልናል!


ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
6👍2🔥2🥰2
ሸሽተህ አምልጥ

«ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አለው ራስህን አድን ወደ ኋላህ አትይ በዚህም ዙሪያ ሁሉ ኣትቁም እንዳትጠፋ ወደ ተራራው ሸሽተህ አመልጥ» /ዘፍ.19፥17/

አንዳንድ ሰዎች ባለማወቅ ብቻ ሳይሆን ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል እያወቁ እንኳ ጉዳት ከሚያስከትልባቸው ነገር ሽሽቶ ማምለጥ ያቅታቸዋል፡፡ ሽሽት ራስን የማዳኛ መንገድ ነው:: አንድ ክርስቲያን በሕይወቱ ኃጢአትን በሁለት መንገድ ሊያሽንፍ ይችላል። ይህም ሊከናወን የሚችለው ከኃጢአቱ ባሕርይ ኣኳያ ተነሥተን እንጂ እንዲያው በደፈናው አይደለም:: ምክንያቱም በትግል የምናሽነፈው ኃጢኣት እንዳለ ሁሉ በሽሽትም የምና ሽንፈው ኃጢአት አለ:: በሽሽት ማመለጥ ያለብን ኃጢአት ራሴን አውቃለሁ አልሽነፍም በሚል ትምክህት ለምታገል መሞከር ያለብን ኃጢአት ራሴን አውቃለሁ ውጤቱ አደገኛ ሊሆን ይችላል ።ለምሳሌ በአንድ ትልቅ ፓርቲ ላይ ተገኝቶ ብዙዎች እየበሉና እየጠጡ ተነሥተውም እየጨፈሩና እየደነሱ ባሉበት ሁኔታ ይህን ከመሸሽ ይልቅ በመካከላቸው በታዛቢነት ተቀምጬ አያቸዋለሁ እንጂ ምንም አልሆንም በአይኔ የማየው ዳንሳቸው በጆሮዬ የምሰማው ዘፈናቸው በዙሪያዬ የሚከናወነው ትርምሳቸው ሁሉ ለእኔ የሚታየኝ እንደ ምንም ነው ማለቱ ከከንቱ ትምክህት የሚመነጭ ነው ከዚህ ይልቅ ውጤታማ የሚያደርግ በዚያ ዙሪያ ሁሉ አለመቆሙ የሕሊናና የመንፈስ መሰረቅ እንዳያጋጥመን ሸሽቶ ማምለጡ አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡

ለቅዱስ ቁርባን እንድንበቃ ምን ላድርግ ገጽ 84


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
9🔥3🙏3👍2