ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.3K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት

"ዮሐንስ ዘሰዋስው በምሥራቁ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ እንዲያውም በገዳማዊ ሕይወት ውስጥ ከወንጌል ቀጥሎ ተጠቃሹና ተሰሚነት ያለው መጽሐፍ ይህ መጽሐፍ መሆኑ በስፋት የተነገረለት ነው፡፡ እስከ ዛሬ ወደ እኛ ባለመምጣቱ የቀረብንን ይኸው ዛሬ መጽሐፉ ተተርጉሞ በመቅረቡ አንድ ጉድለት ተሸፍኗል፡፡ መጽሐፉ የክርስትና ሕይወትን ምንነት በአግባቡ ለመረዳትና ለመኖር በሚሹ ዘንድ ሁሉ የሚፈለግና የሚጠቅም መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በተለይ ደግሞ እግዚአብሔር አምላካቸውን በገዳማዊ ሕይወት ለሚያገለግሉ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡"
            ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ይህ ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረውና ግሩም የሆነ መጽሐፍ አሁን በድጋሚ ታትሞ  ለገበያ ቀርቧል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
16👍7
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ4ኛ ግዜ ታትማለች!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍4
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
#ይህ የዲያቆን ታደሰ ወርቁ “ጽዋዔ" የተሰኘውን መጽሐፍ በርካታ ታዳሚ ፅንሰ ሐሳባት የታደሙበት ታላቅ የእልፍኝ አዳራሽ ይመስላል፡፡ መጽሐፉን ለማዘጋጀት በርካታና ጠቃሚ ዋቤ፣ ማጣቀሻ መጻሕፍትን መጠቀሙን ከመጽሐፉ የኅዳግ ክፍል ውስጥ መረዳት እንችላለን፡፡ የመጽሐፉም ዝግጅት በዋቤ መጻሕፍት ላይ ብቻ የተደገፈ የዕውቀትና የምርምር ጽሑፍ ብቻ ሳይሆን የአንባብያንን ኅሊና የሚሞግትና በሰው የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ የማኀበራዊ ፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ ምን መምሰል እንዳለበት የሚያስገነዝብ ኃይል ያለው ነው፡፡ መጽሐፉ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን የትውልድ ዘመን፣ የፍልስፍናና የሥነ መለኮት ትምህርት፣ የሥነ ልቦና ውቅር፣ ስለሰው ያለው ጥልቅ ፍቅር፤ እንዲሁም ለነፍሳት የሚያሳየው ፍጹም ርኅራኄ፣ በአንጾኪያ የነበረው የክህነት አገልግሎትና አስተምህሮ፣ በማኅበራዊ እኩልነትና በምጣኔ ሀብት ፍትሐዊ ክፍፍልነት ላይ ያለው ሙግት በጥልቀት የሚያነሣ በመሆኑ፤ መጽሐፉን አነበብኩት ብቻ ሳይሆን አጠናሁት ለማለት እችላለሁ፡፡ አንባብያንም ሆንን በዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያየ የሥራ ዘርፍ የምንገኝ ሁሉ ስለ ማኅበራዊ ፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ በይበልጥ የምንማርበት ስለሆነ ሁሉም ሰው መጽሐፉን አንብቦ እንዲጠቀምበት ግብዣዬ ነው፡፡
አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ (ዶ/ር)

በአሜሪካን ሀገር በትምህርት አገልግሎት ተቋም ውስጥ የትምህርት ሥራ ባለሙያና ተመራማሪ

"ጽዋዔ" በሚል ርእስ የተጻፈው የዲያቆን ታደሰ ወርቁ መጽሐፍ፣ ቃለ እግዚአብሔርን በሚገርም ጸጋ በማስተማርና በመስበክ የሚታወቀውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ጥሪ እና አገልግሎት ድንቅ በሆነ መልኩ ያስቃኘናል፡፡ ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ሳይሆን፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእውነትና በኃይል በመስበክ፣ በሀብታቸው የሚመኩ ባለጸጎችን እየገሠጸ፣ ለድኾች ጥብቅና በመቆም ዮሐንስ አፈ ወርቅን የሚያክል አባት እስካሁን አልተነሣም፡፡ ዲያቆን ታዴ የዚህን ኦርቶዶክሳዊ ቅዱስ አባት ጥሪና እስከ ሊቀ ጵጵስና የደረሰ አገልግሎት፣ ከታሪክ ጸሐፊዎቹ ከእነ ሶቅራጥስ፣ ፓላዲየስ፣ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ ወዘተ... አንደበት የሰማ እስኪመስል ድረስ ተነብቦ በማይጠገብ ሥነ ጽሑፍ (የአጻጻፍ ውበት) አቅርቦልናል፡፡ የታሪኩ ፍሰት፣ በየገጹ የሚታዩት ማራኪ ንኡሳን አርእስት እና የተወሳሰበው ታሪክ ተብራርቶ የቀረበበት መንገድ መጽሐፉን ተወዳጅም ያደርገዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት ለነገረ መለኮት (theology) ተማሪዎችና መምህራን፣ ለሰባክያን፣ እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያናቸው ታሪክ አካል የሆነውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ሕይወት አጽንኦት ሰጥተው እንዲያጠኑት በማድረግ ታላቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ራሳቸውን ልሂቃን (elites) አድርገው የሚቆጥሩ ወገኖቻችንም የተሰጣቸውን ሓላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ከዚህ መጽሐፍ ብዙ የሚማሩት ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡

ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (ዶ/ር) የቀድሞ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዋና ዲን እና የ“አኰቴተ ቊርባን“ መጽሐፍ ደራሲ

ጽዋዔን ሳነብ ሀገሬ ትዝ አለችኝ፡፡ከአንድ ሺሕ ስምንት መቶ ዓመት በፊት አንጾኪያና አንጾኪያውያን የገቡበትን ሁለንተናዊ አረንቋ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ዛሬ ገብተንበታል፡፡ በርግጥም ከልብ አንብቦ ለተረዳው ለትንሣኤያችን መነሻ አሳብ አበርካች መጥሐፍ ነው። የጳጳሳቱ፣ የካህናቱ፣ የምእመናኑ፣ የመለካውያኑን ጠባያት በገሐድ ያሳያል። ኢትዮጵያውያን ከአዚማችን ከአልነቃን እንደ አንጾኪያ የሰዓታት ሳይሆን የዓመታት ዐመፅ አይቀሬ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ሀገሬ ዛሬም ዮሐንስ አፈ ወርቅን ታስሳለች፡፡ ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ምቀኝነት፣ መጠፋፋት፣ አሳልፎ መሰጣጣት ሁሉ በሚከወንባት ሀገሬ ከመጥፋቷ፤ እኛም ከመጥፋታችን በፊት መድኃኒት የሚሆን መጽሐፍ ነው፡፡ የታዴ የቃላት አመራረጡ፣ ክብደቱና አዋሐዱ የዐሥራ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀገሬን ጠሐፍት አባቶቸን አስታወሰኝ፡፡ የቃላት ድርቅ ለመታንና በአማርኛ ጽሑፎቻችን እንግሊዝኛ ቃላትን ለምናዘወትረው “ተመየጡ ሀበ ዘቀዳሚ ፊደልክሙ" ይለናል። መጽሐፉን ብዙ ተመራምሮ አጣቅሶ የጣፈው እንደሆነ ከኅዳጎቹና ከጥቅሶቹ መረዳት ይቻላል፡፡

ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኅን አገልግሎት ሥርጭት ድርጀት ዋና ሥራ አስኪያጅ


ታላቁ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ አንጾኪያ በነበረበት ወቅት የአደረጋቸው ነገሮችና የአስተማራቸው ትምህርቶች ቤተ ክርስቲያን እና ሀገር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ሕዝብን እንዴት ማገልገልና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ማሻገር እንደሚቻል በተግባር ያስተምሩናል፡፡ ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ሰፊ ጥናትና ዳሰሳ በማድረግ የአዘጋጀው ይኽ መጽሐፍ፤ በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የአንጾኪያ የተጋድሎ ሕይወት አንጻር ካህናት ሕዝባቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት መምራትና ማሻገር እንደሚገባቸው ያሳየናል፡፡ ተግባራዊ ትምህርት የሚሰጥ የሆነውን ይህን መጽሐፍ በመጻፉም ሊመሰገን ይገባዋል፡፡

መምህር ያረጋል አበጋዝ
ጸሐፊና ሰባኬ ወንጌል
💯54
“በዚህ መጽሐፍ ለማድረግ
የሞከርኩት አበው (አባቶቻችን) ያቆዩልንን የባሕረ ሐሳብ ትምህርት በትውልዳችን ቋንቋ ማቅረብ ሲሆን  ዓላማዬ ለማንም የአራት መደብ የቍጥር ትምህርት ለተማረ ሰው (ከልሂቅ እስከ ደቂቅ) ባሕረ ሐሳብ የማውጣት ችሎታን ማስተማር
ነው” (ገጽ 14)።

“የዛሬው ትውልድ ታሪክ ሲጠቅስ ብዙ ጊዜ ከአፄ ቴዎድሮስ ወደኋላ ሲሄድ ስለማልሰማ ከመጻሕፍቱ ጋራ በመስማማት ከሳቸው በፊት ያሉትን ዘመናት ለማስተዋወቅ ብዙ ገጾች ወስጃለሁ።
አፄ  ተከታዮቻቸው ቴዎድሮስና ነገሥታት
ኢትዮጵያን ከወደቀችበት እናንሣ ሲሉ አገራችን ያሸበረቀችበትና የወደቀችበት ዘመን ነበረ ማለታቸው ነው” (ገጽ 229)።

  “በምዕራፍ ፭ የተመዘገበው በዓውደ
ሰማዕ(ታ)ት መጀመሪያ ጀምሮ በዓመተ ምሕረት (ዓ.ም.) እና በዓመተ እግዚእ (A.D.) መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳየው (ሠንጠረዥ) ( በኛ
ዘመንቈጠራዎች የተመዘገበን
የታሪክ ድርጊት ወደ እነሱ የዘመን ቈጠራ (ወደ ዓመተ እግዚእ A.D.)፣ በነሱ (በዓመተ እግዚእ) የዘመን ቈጠራ የተመዘገበን  የታሪክ ድርጊት ወደኛ (ወደ ዓመተ ቈጠራ ምሕረት) የዘመን ለማዞር
ነው” (ገጽ 17)።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍63💯2
ገድለ አቡነ ጸጋ ዘአብ ወእምነ እግዚእኀረያወገድለ አቡነ ታዴዎስ ጽላልሽ
....ገድላት ኹሉን አቀፍ የመረጃ ምንጮች ናቸው። ዘመን፤ በአንድ አካባቢ፤ በአንድ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚጓዙ አለመሆናቸው፤ በተለያዩ የዓለም ክፍል በተለያዩ ዘመናትና ጊዜያት የተነሡ የቅዱሳንን ሕይወት የተመለከቱ፤ ከምእመናን እስከ መዐርገ ጵጵስና ድረስ በተራ ዜግነት ከተሰለፉት እስከ ንጉሥነትና ንግሥትነት ደረጃ እስከ ደረሱት ድረስ ምእመናንንና ምእመናትን በእኩልነት የያዘ በመኾኑ ከሃይማኖት ጥቅሙ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰዎችን እኩልነት በማሳየቱ የበለጠ አጎልቶ ይሳያል።
  ❞ስለዚኽ ይኸ የካህኑ ጸጋ ዘአብ፣የብፅዕት እግዚእ ኀረያ እና የአቡነ ታዴዎስ ገድል የነፍስና የሥጋ በረከት የምንቀበልበት፤ ኹሉን አቀፍ መረጃ የምናገኝበት በመኾኑ በ፯ቱ ዕለታት በመክፈል በግዕዝና በአማርኛ በመተርጎም ቀርቧል።

❞ይኸም ቅዱሳኑ በሕይወተ ሥጋ እያሉም ኾነ ከዕረፍታቸው በኋላ በዐጸደ ነፍስ ሳሉ ያደረጓቸውን ልዩ ልዩ ድንቅ ተኣምራትን መልክዐቸውንም  አካቶ የያዘ የካህኑ ጸጋ ዘአብን፣ የብፅዕት እግዚእ ኀረያንና አቡነ ታዴዎስን ዝክረ ስም የሚናገር የምስጋናጸሎት ስለኾነ በዚኸ የጸሎት መጽሐፍ ተጠቅመን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እናገኝ ዘንድ ይህን ገድል   ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም እነሆ  ይለናል ።

ይኽን የቅዱሳን ተጋድሎ እና ምስጋና የያዘ ገድል ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
4👍3🕊3🥰2
…………ለ8ተኛ ጊዜ የታተመ

"እንደ ኦርቶዶክሳውያን ወላጆች፥ ዓላማችን ፍጹማን ወላጆች መኾን አይደለም። ይህ የማይቻል ነውና። ... ልጆች የሚፈልጉት [እና የሚያስፈልጋቸው] እንደ እነርሱ የሚሳሳቱና [ከስሕተታቸው እየተማሩ] የሚያድጉ ወላጆችን ነው።"

#ትንሿ_ቤተክርስቲያን፥ ገጽ 447


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🕊3👍2
.....አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ ሆነህ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ከኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ_መጽሐፍ

❝ከ ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅወርቃማ ትምህርቶች አንዱ የሆነውን ይህን መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት የሚያገኙት   ሲሆን ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ውድ አንባቢያን በDHL እና በEMS  እንዲሁም የ delivery
አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ለአንባብያን ተደራሽ እናደርጋለን።❞

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
12👍4🕊3
💥ሰፌልያ🩸

"ሰፌልያ" የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወትን የሚተርክ እስከ ዛሬ ያልሰማናቸውን ዕውቀቶች እየተደመምን የምንጠጣበትና ጽናት የምናግኝበት ልዩ መጽሐፍ ነው።

በሰባኪ ወንጌል ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን ተደርሶ ለአንባቢያን የቀረበው ይህ አዳዲስ መረጃዎችን የሸከፈው መጽሐፍ፥ የዓለም ብርሃን ንዋይ ኅሩይ ስለ ተባለው የአገልግሎት ውጣ ውረድን የሚዳስስ ሥራ ነው።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍54🕊2
#ንስሓና_ምጽዋት_ታተመ!

በዚህ መጽሐፍ የተካተቱት ዓሥር ድርሳናት፥ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በ386 እና በ387 ዓ.ም. በአንጾኪያ ያስተማራቸው ሲኾኑ፥

👉  ኃጥአንም ጻድቃንም ንስሓ እንደሚያሻቸው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ካለው ወደር የለሽ ፍቅሩ የተነሣ አንድ ዓይነት የንስሓ መንገድ እንዳልሰጠ፣

👉 በዚህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓምድ ትምህርት በኾነው በንስሓ አማካኝነት ኃጥአን ያሳደፉትን ልጅነታቸውን የሚያድሱበትና ሕይወት ወደ ኾነው ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚመልሳቸው መንገድ መኾኑን፣

👉 ወደ ቅዱስ ቁርባን መድረሻ መንገድ ብቻ ሳይኾን ከላይ እንደ ተገለጠው በተለያየ መንገድ ማለትም በጸጸት፥ በምጽዋት፣ በጸሎት፣ በፆም፥ በትሕትና፥ ቅዳሴውንና አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮን በመሳተፍ፥ በአጠቃላይ ምግባር ትሩፋትን በመሥራት ያሸበረቀ ቤተ ክርስቲያናዊ ሕይወትን በመኖር የሚገለጥ ምሥጢር መኾኑን፣

👉 የአምላክን መጠን አለፍ ቸርነት ስጦታ መኾኑን ከብዙ ማሳያዎች ጋር ያስተማረባቸው ናቸው፡፡

መጽሐፉ በ200 ገጾች፣ በሚማርክ ኅትመትና በ300 ብር የሽፋን ዋጋ ለሦስተኛ ጊዜ ታትሞ ለአንባቢያን ቀርቧል።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5👍3🥰3🕊2
ዜና ድጋሚ ኅትመት !

ሳይንስ እና ሃይማኖት

..ሳይንስ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን አዕምሮ ተጠቅሞ ያስገኘውና በዚህ ዓለም ያለውን የኑሮ ድካም ማቅለያው የዕውቀት ዘርፍ ሲሆን ሃይማኖት ደግሞ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘው መንገድ ነው። ነገር ግን የሳይንስን ውሱንነት ያልተረዱ ሰዎች ሃይማኖትን በሳይንሳዊ ዕውቀት ለመተንተን ሲሞክሩና ወደ ተሳሳተ ግንዛቤ ሲያመሩ ይስተዋላል። በሌላ መልኩ ደግሞ ሳይንስ ለመንፈሳዊ ሰዎች እርባና የሌለው ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።
ይህንን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ፍልስፍናዊ አስተያየቶች፣ ጸሐፊው መምህር ያረጋል አበጋዝ፣ በዚህ መጽሐፉ ከሳይንስና ከሃይማኖት ጋር በተገናኙ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦች ዙሪያ ሰፊ ጥናት በማድረግ ከጥልቅ ትንታኔ ጋር አቅርቦልናል። ስለሆነም መጽሐፉን አንብበን የተሻለ ግንዛቤ እንድናገኝና እንድንጠቀምበት እየጠየቅኩ፣ ለመምህር ያረጋል ዕድሜና ጤናን ለእናንተ ለአንባብያን ደግሞ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ቀሲስ ሰሙ ምትኩ (ፕሮፌሰር)
ቦትስዋና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ




ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍4🕊3
ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች
ሁ?ከተሰኘው


አባታችን አብርሃም ኑሮውን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ የጀመረው አገሩንና ቤተ ሰዎቹን በተወ ጊዜ ነበር፡፡ አባቶቻችን ሐዋርያት ተመሳሳይ ነገር ነው ያደረጉት፡፡ እነርሱ ሲጠሩ ዓሣ አጥማጆች ሆነው ሳሉ የተዉት መረቦቻቸውንና ታንኳዎቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተከትለውትም ሄደዋል፤ማቴ 4፡20እና22፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው ከሆነማ ያላቸውን ነገር ሁሉ ትተው ነው የከተሉት፤ ማቴ 19፡27፡፡ እናንተስ? ስለ እግዚአብሔር ስትሉ የተዋችሁት ነገር ምንድር ነው? እናንተ ኃጢአተኛ ሕይወታችሁን በመተው ንስሐ ገብታችኋል?...
***
ያዕቆብመልእክት
ከተሰኘው

‹ብዙ ሰዎች እኔን በሀብታም ሰዎች ላይ ያለህ አቋም በጣም ጥብቅ ነው እያሉ ይናገሩኛል፡፡ በእርግጥም እንዲህ በማለታችሁ እውነት ብላችኋል፤ይሁን እንጂ እኔ በሀብታም ሰዎች ላይ ጥብቅ የሆንኩት ገንዘባቸውን ለመሳደቢያ አድርገው ለተጠቀሙበት ሀብታሞች ነው፡፡ እኔ እነርሱን የማጠቃቸው በግል አይደለም፤ነገር ግን የማጠቃው ስስታቸውን ነው፡፡ ........

  ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

...በተለይ በተለይ በትርጉም ስራ ረገድ ለኛ [ለኢትዮጵያውያን ] አባት ልጁን ለመመገብ  እንደሚጨነቅ እና እንደሚፋጠን ኹሉ በልዩ እና በተረዳ እንዲሁም በማይጠገብ መልኩ የሚያዘጋጁልን ፦
#አያሌው ዘኢየሱስን ያቆይልን እያልን ፦

💥አሁንም እነዚህን ሁለት ግሩማን፤  ሐሳቦችን የተሞሉ ፤መጻሕፍት እነኾ ያሉን ሲሆን በፍኖተ መጻሕፍት ያገኟቸዋል ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦091308381
6

t.me/FinoteBooks1623
👍76🕊3🥰2
ቅዱስ ጳውሎስ ዕቅበተ እምነትን በአጭር ቃል ሲገልጸው "ወንጌልንም መመከቻና መጽኛ ማድረግ " ይለዋል:: (ፊልጵ. 1:7) አንዲቱ ወንጌል ለተቃዋሚዎች "መመከቻ" ስትሆን በውስጥ ላሉ ምእመናን ደግሞ "መጽኛ" ትሆናለች:: "ለምእመናን ተስፋ ለመ^#ቃን ዘለፋ" እንዲል ትርጓሜው::

የጳውሎስ አቻው ቅዱስ ጴጥሮስ ደግሞ :- "ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመሥጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ" ብሎአል:: ልብ አድርጉ "ለሚሰድቧችሁ" አላለምና እምነታችንን ለሚሳደቡ መልስ አንሠጥም:: ለጥያቄ ግን እንመልሳለን::

ይህንን እውነት ከተረዱ ወንድሞች አንዱ የሆነው የዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ዳጎስ ያለ ዕቅበተ እምነታዊ መጽሐፍ አቅርቦልናል:: ለራሳችን መጽኛ ለሌላው መመከቻ የሚሆነው መጽሐፉ እጅግ ብዙ ጥያቄዎች በጥንቃቄ የተመለሱበት የተደከመበት ስራ እንደሆነ በወፍ በረር ቅኝቴና መጽሐፉን አይተው አስተያየታቸውን ካሠፈሩ ምስክሮች ተረድቼያለሁ:: በብዙ ድካም የሠራውን መጽሐፍ ከአንድ ኪሎ ሥጋ መሸጫ ባነሰ ዋጋ አበርክቶልናል:: አይለፈን!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍2👏1🙏1
የብርሃን እናት ለ10 ግዜ ታትማለች

"እግዚአብሔር የሰው ልጅን ያዳነበት መንገድ በዕለተ ዐርብ በመሰቀሉና መከራን በመቀበሉ ብቻ የሚመስለውና ከነገረ መስቀሉ ውጪ ያለው ጉዳይ የሚጠቅም የማይመስለው ሰው ካለ ነገረ ድኅነትን ጨርሶ አልተረዳም፡፡

እንደዚያ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በድንግል ማርያም ተፀንሶ ተወልዶ ሠላሳ ዓመታትን መቆየት ሳያስፈልገው ልክ የመጀመሪያውን አዳም እንደፈጠረው የሠላሳ ዓመት የሆነ ሥጋንና ነፍስን ለራሱ ፈጥሮ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው መሆን ይችል ነበር፡፡ ይህንን ቢያደርግም ሦስት ዓመታት በምድር ላይ አስተምሮ በጊዜው ተሰቅሎ የማዳን ሥራውን መፈጸም ይችል ነበር፡፡

እርሱ ግን ማዳኑን የጀመረው በማሕፀን ከመፀነስ ነበር፡፡
አረጋዊው ስምዖን ‘ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋል’ እንዳለ ማዳኑንም የጀመረው ሕፃን ሆኖ በመታቀፉ ነው፡፡ ሉቃ. ፪፥፴

አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ላለው ክርስቶስ በምድር ላይ በቆየበት መዋዕለ ሥጋዌው አልፋው ድንግል ማርያም ስትሆን ኦሜጋው መስቀል ነበር፡፡ የተሰቀለ ቀን ብቻ አይተህ ልታውቀው አትችልም፡፡ ሁለተኛ አዳምነቱ ዘልቆ የሚሰማህ ወደ ልደቱ ስትመለስ ነው፡፡ የሰው ልጅ ቁስልም የሻረው ጌታ ሊወለድ ካለበት ቅፅበት ጀምሮ ነው"

የብርሃን እናት ገጽ 97


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
10👍6🕊4🎉1
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
#ገድለ ሐዋርያት

"በሐዋርያት ና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል"ኤፌ፪÷፴

...." ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ለተሰጠች ሃይማኖት ተጋደሉ” ተብለናልና፡፡ ይሁ ፩፡፡ የተጠራነውም ልናምን ብቻ ሳይሆን መስቀሉን ልንሸከም መከራ ልንቀበል ጭምር ነው። ስለ እርሱ መከራ ልትቀበሉ እንጂ ልታምነ ብቻ አይደለም” እንዲል። ፊል ፪፡፳፬

❞የቅዱሳን ሐዋርያትን ታሪካዊ ሕይወት ማወቅ #ቅዱስ እግዚአብሔርን ለሚያመልኩ ምእመናን ጥቅሙ የጎላ ነው፡፡ ለሃይማኖታዊ ጉዟቸው መንገድ መሪዎች ናቸውና፡፡

"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፤ የእምነታቸውንም
ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሏቸው” በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ምእመናን
የመከረውም ለዚህ ነው፡፡ ዕብ ፲፫፥፯


ስለሆነም ምእመናን በሃይማኖት ዋኖቻቸው የሚሆኑ የሐዋርያትን ታሪክ በተገቢው መንገድ ማወቅና መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ቅዱሳኑ ለሃይማኖታቸው የከፈሉትን ዋጋ ካወቁና ከተረዱ ‹‹እኔስ ለሃይማኖቴ ምን ማድረግ አለብኝ? ፈጣሪዬንስ እንዴት ላስደስተው?›› የሚለውንና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ለመወሰን ይችላሉ፡፡

ቤተ-ክርስቲያን ምእመናኖቿ የዚህ አማናዊና አምላካዊ ቃል ኪዳን ተሳታፊዎች ይሆን ዘንድም ‹‹ዛሬ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ ዛሬ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው፡፡›› ወዘተ እያለች ገድላቸውን ጽፋ፣ ያልተተረጎመውን ተርጉማ ስለእግዚአብሔር ወዳጆች ቅዱሳን ለምእመናን ታስተምራለች፡፡ በዚህም ምእመናን የበረከት ሰዎች ይሆናሉ፡፡ ”በረከት በጻድቅ ራስ ነውና” ምሳ ፲፮፡፡ መታሰቢያቸው ዘመን የማይሽረው በመሆኑም ምእመናን ለዘለዓለሙ ተጠብቀውበት ይኖራሉ፡፡

#እነዚህና የመሳሰሉት ጉዳዮች ተግባራዊ ይሆኑ ዘንድም ገድለ ሐዋርያት መተርጎም አስፈላጊነቱ ለዚህ ነው፡፡
#በመሆኑም በሐዋርያት መሠረትነት ላይ የተመሠረተ ምእመን እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት በሃይማኖቱ ለመጽናትና ታሪካቸውን ተገንዝቦ የቃል ኪዳናቸው ተሳታፊ ለመሆን መጽሐፉን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡ በማለት
#መምህር ተስፋሚካኤል ታከለ 
የተዘጋጀውን ይህን የቅዱሳኑን ዜና ሕይወት [ገድል ]#በፍኖተ መጽፍት ያገኙታል ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7🕊4👍3
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
#ኹለቱ ኪዳናት

"ሌላ መሠረት እንዳትሹ ዕወቁ፤"ዕብ፮÷
አንዳንድ ሰዎች ግን የንስሓን /የመናዘዝንና ቀኖና የመቀበልን ምሥጢር ረብህ የሌለው አድርገው ከማስተማራቸው የተነሣ ከእግዚአብሔር መንግሥት ይለያሉ። ትምህርታቸው ቀድሞ ምግባርን በኋላም የምግባርን እናት ሃይማኖትን ያስተዋቸዋልና።

#ኃጢአታችን ይቅር ሊለንና ከዓመፃም ኹሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው። 1ኛዮሐ:19

ስለዚኽ ንስሓ ኃጢአትን ኹሉ የምታስተሠርይ የእግዚአብሔር በር ናት።
❝ቅዱስ ጳውሎስ ንስሓን የሚቃወም ትምህርት ከሞት የማያድን ነውና መሠረትን ደግመን እንመሥርት አለን። “... ይኽን እወቁት
" ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።" ኤፌ.53 13
በማለት አንዳንዶች “ከንቱ ንግግር” በተባለ የውሸት ትምህርታቸው ብዙዎችን የኃጢአት አበጋዝ : አድርገው : ነበርና : ከዚኽ መጠበቅ እንደሚገባ ያስተምረናል።

❞በአኹኑም ጊዜ “እግዚአብሔር ፍጹም መሐሪ ነው" በሚል ፈሊጥ የሰውን ኹሉ ኃጢአት ዝም ብሎ ይቅር እንደሚል የሚያስተምሩና ሰውን ወደ ኃጢአት የሚጋብዙ መኖራቸውን አውቆ ራስን መጠበቅ ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ምሕረት ለተነሣሕያን እንጂ ክሳደ ልቡናቸውን አደንድነው በኃጢአት ለሚተጉት ኹሉ _ አይደለም፤
“እግዚአብሔር የሚያጠፋ እሳት ነው።" ዕብ.12፥29፡፡
.................

ደግሞስ ስለ ቅብዐትና ጸጋ
አመጣጥና ታሪካቸውን በወፍ በረር ቃኘት አድርጎ እግረ መንገዱን አጠር ብላ የማታዳግም ምላሽ ሲሰጡ ወቸው ጉድ ሳያስብለን አይቀርም !
🤔የቀረውንማ ምን ከቃሉ አገባብ በብዙ መንገድ ካለው ፍቺ  እኛ ካለንበት አኹናዊ ኹናቴ ኸረ .....በብዙ መንገድ #ዕብራውያን14ቱ መልእክታት ትርጓሜ ላይ ተመስርቶ በደንብ እየተነተነ ልብን በላይኛው ሀገር ይዞ የሚከንፍ #በመሪጌታ ኃይሎም በርሄ ተዘጋጅቶ #ዲያቆን ብርሃኑ አድማስን ደግሞ አርታዒ በማድረግ የቀረበ ይኽ ግሩም መጽሐፍ #በፍኖተ መጻሕፍት ያገኙታል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🕊5👍3🙏1
📖“ወልታ ጽድቅ”

❝... የዚህ መጽሐፍ “ወልታ ጽድቅ” አዘጋጅ (በብዕር ስሙ በአማን ነጸረ) ደግሞ ከይዘት አንጻር የሚራራቁ የሚመስሉ ነገር ግን ከላይ ከጠቀስኩት እሳቤና ሁለቱም እመቤታችን ማዕከል ከማድረጋቸውም አንጻር የሚገናኙትን እነዚህን ሁለት ጉዳዮች እንደ ብልህ ገበሬ አንድ ላይ ጠምዶ አቅርቦልናል፡፡ ምንም እንኳ ሁለቱም[ታሪክና ሃይማኖት ]ጉዳዮች በየራሳቸው ገና ብዙ ሊጠኑ፤ ሊጻፍባቸውና ሊብራሩ የሚችሉ ቢሆኑም በእነ ንባብ መሠረት ከሆነ ለዘመኑ ትውልድ በጥሩና በተሻለ መንገድ ሲቀርቡ “ወልታ ጽድቅ” የመጀመሪያ መጽሐፍ ይመስለኛል፡፡ በእኔ እምነት በአማን በእነዚህ ሁለት እጅግ አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ካቀራረቡ ጀምሮ አዲስ ነገሮችን ይዞ ብቅ ብሏል። ስለዚህም በጉዳዩ ላይ ማወቅ፣ ማጥናት፣ መመራመር፣ መሞገት መረዳትና መጻፍ ብቻ ሳይሆን መታዘብ የሚፈልግ እንኳ ቢሆን ወልታ ጽድቅን እንዲያነብብ በልበ ሙሉነት እጠቁመዋለሁ፡፡ ታሪካዊ ግንዛቤን እንደ እምነት ፤ እምነትን እንደ ዐለማዊ ዕውቀት ይዞ ነገር ለተገላበጠበትም ወደ ፍጹሙ መድኃኒትና ድኅነት የምታደርሰው የስቃይ ማስታገሻ (ant pain) ልትሆንለት የምትችል ምርጥ ቅመማ ናት፤ ወልታ ጽድቅ፡፡❞

#ብርሃኑ አድማስ (ዲን፣ በሥነ ድርሣን ሁለተኛ ዲግሪ)

#ይህን ጥዑም መጽሐፍ በፍኖተ መጻሕፍት ያገኙታል ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍5🕊2
📖#ታኦዶኮስ

©በመምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ

  ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

❝.....በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የዐራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት የትርጓሜ መምህር የሆኑት የሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ደቀ መዝሙርና የጉባኤ ቤቱ ምክትል መምህር በሆኑት በመምህር በጽሐ ዐለሙ ታኦዶኮስ በሚል ርእስ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ አማኞችን ሳይቀር ለሚያነታርከው እመቤታችን ጥንተ አብሶ አለባት የለባትም ለሚለው ጥያቄ ከቤተ ክርስቲያናችን ነባር ኣስተምህሮ አንጻር መልስ የሚሰጥ ግሩም መጽሐፍ ነው፡፡
 

.... ወደፊት በጽሑፍ ልትጠቅሙን የምትመኙ ሁሉ ወደፊት ለምትሠሩት ሥራ ቢያንስ እንደ አንድ መክፈቻ የሆነውንና ሌሎቹንም ጥያቄዎች በአስተማማኝነት ለመመለስ ብልሃትንና መንገድን የሚያሳየውን ይህን ድንቅ መጽሐፍ አንብባችሁ እንድትጠቀሙ በታላቅ ትሕትና ስጋብዛችሁ ከአነበባችሁ በኋላ በምታገኙት ትንሽ የማይባል ጥቅም የምትደሰቱት ደስታ እንደሚኖር በመተማመን ጭምር ነው፡፡

#ብርሃኑ አድማስ (ዲያቆን፣ በሥነ ድርሳን ሁለተኛ ዲግሪ)

⩩እንደ እውነቱ የእናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነገር የማይሸነቁጠው አማኝ [ኦርቶዶክሳዊ ] አለ ለማለት ያስቸግራል ለዚህም የልብን የሚያደርስ መጽሐፍ እነሆ ያሉንን የኔታ በጽሐ አለሙን  ያኑርልንንን እያልን   መጽሐፏን ሁላችንም አንብበን እናተርፍበት ዘንድ መጽሐፉን   #በፍኖተ መጻሕፍት ያገኙታል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
👍6🕊53
📖 " ማስያስ "

❝...ማስያስ የመጻሕፍት ሁሉ ማዕከላዊ የመጽሐፍ ራስ ሆኖ ቀርቦልናል። ስለዚህም በዲያቆን ሚክያስ አስረስ የተዘጋጀልንንና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዘመናት ሁሉ ለነበሩ አማኞቿ ስትመግበው የነበረውን ይህንን ምሥጢራዊ ትምህርት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በጥሩ መንገድ ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን። ዲያቆን ሚክያስ ከቤተ ክርስቲያን መምህራን ፍጻሜ፣ የሐዋርያት ስብከት ራስ፣ የሰማዕታት የሰማዕትነት አክሊል፣ ከተማረውና ሰፊ ሽፋን ካለው ንባቡ አዋሕዶ የነቢያት ትንቢት የጻድቃንም የምናኔያቸው ምሥጢርና የምድረ በዳ ተጋድሏቸው የምእመናንም እረኛቸው የካህናትም አለቃቸው፣ የአምልኮታቸው መዳረሻ፣ የቅዳሴያቸው ሊቀ ካህናት የመሥዋዕታቸውም ቊርባን የሆነውን ጌታ “ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን” እያልን በሰሙነ ሕማማት ስግደታችንን በምናቀርብለት ስሙ ይዞልን መምጣቱ እጅግ ደስ ያሰኛል።
መጽሐፉ ለኦርቶዶክሳዊ የዶክትሪን አስተምህሮ እንደ መነሻ ወይም መግቢያ በሚመስል አቀራረብ ለሁሉም አንባብያን እንዲሆኑ በተዘጋጁ መጻሕፍት ላይ እስካሁን ያላነበብኳቸውን አዳዲስ ምሥጢራት አካትቶ ቀርቦልናል። ስለዚህም ይህን ግሩም መጽሐፍ በማንበብ ጌታችን እንደመለሳቸው ደቀ መዛሙርት ልቡናችንን በሚያቃጥሉ የትርጓሜ ምሥጢራት መግበን ምዕራብ ወደተባለ ዐለምና ኃጢአት ከምናደርገው ጉዞ እንድንመለስና እንደ እንድርያስም ማስያስን/መሲሑን አግኝተናል ብለን ሌሎችን ወደ እውነተኛው መሲሕ ልንጠራበት ይገባናል።❞

#ብርሃኑ አድማስ



ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
7👍5🕊5🤔1