ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.3K subscribers
337 photos
1 video
288 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
#ቅምሻ

"እማሆይ ወ/ሚካኤል የተኛች መስላ ሁኔታውን ስትከታተል ነበርና እንዳልሰማች እንቅልፍ እንደ ያዘው ሰው ዝም አለች። ሰሚ ያጣችው እማሆይ [ማየ ገነት] ያለ' ኃይሏን አጠራቅማ ቀና ብላ 'ወለቴ ኧረ ወለቴ' አለች በጩኸት። 'እ... ጠራሽኝ?' በማለት ቀና ብላ አየቻት። 'ኧረ መሞቴ ነው፥ እምነት ስጪኝ' ብላ መኝታዋ ላይ ተዘረረች። እማሆይ ወ/ሚካኤል ፈጠን ብላ ከቤቷ ይዛ የመጣችውን ዘንቢል ከፍታ የሆነ የተጠቀለለ ነገር አውጥታ ቆንጥራ ብርጭቆ ውስጥ ጨምራ በጥብጣ 'ከቤት ያመጣሁት እምነት ነው ጠጪው' አለቻት። እማሆይ ማየ ገነት የምትናገረውን ሁሉ ባይኗ ትከታተላት ነበርና 'እቤት ውስጥ ያለው እምነት እያለ ለምን ሌላ?' ብላ የሆነ ነገር ጠረጠረች። ግን ውጋቱ ፋታ ስለ ነሳት 'እምነት እምነት ነው' ብላ የግዷን ተቀበለቻትና ቀመስ ስታደርገው መረራት። የያዘችውን ብርጭቆ ወረወረችውና የቀመሰችው ካፏ ተፍታው መልሳ መኝታዋ ላይ ድፍት አለች።

"ምን መሆንሽ ነው የምታፈሺው? ግዴታ መጠጣት አለብሽ እኮ። ይሄ የማይገኝ እምነት ነው። የአባቴ ጓደኞች ከትልቅ ዘግተው ከሚኖሩ አባት ያመጡለት ነው'ኮ። ሰው 'በየት ባገኘነው?' ይላል። አንቺ ትደፊዋለሽ እንዴ? ወይስ ፀላኤ ያዘሽ? አባቴ ሲነግረኝ 'ሰይጣን ያለበት እንኳን ሊጠጣት እሱ የገባበት ቤት አይገባም' ብሎኛል። ስለዚህ በሽታሽን ንቅል እንዲያደርገው በግድ መጠጣት አለብሽ' ብላ ድጋሚ በጥብጣ በግድ ልታጠጣት ስትሞክር ከውጪ ቤቶች ክፈቱ የሚል ድምፅና በር መንኳኳት ተሰማ። ቶሎ ብላ ወደ አልጋው ውስጥ አስገባችውና 'ማነው? ይግቡ' ብላ በሩን ከፈተች።"

"እማሆይ ማየ ገነት መናገር አቅቷት በላብ ተዘፍቃ ወደላይ ወደላይ ትቃስታለች። ዓይኗ ብቻ ይንከራተታል። በሩን የመቱት"

© ገድለ ምንኩስና ገጽ 170-171

t.me/FinoteBooks1623
12👏2
ወንጌል እስከ መጨረሻው ዘመን ድረስ በአለሙ ሁሉ እንደሚሰበክ የተነገረው ትንቢት

ጌታችን "ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዐለም ሁሉ ይሰበካል" ብሏል።ማቴ. 24: 14 ይህ ጌታችን ስለ ወንጌል በዐለም ሁሉ እስከመጨረሻው ዘመን ድረስ መሰበክ የተናገረው ትንቢት በተነገረበት ግዜ ፣ በመሆን ዕድል ደረጃ ሲያስቡት ለመቀበል ቀላል ጉዳይ አልነበረም። ዐሥራ ሁለት የሆኑ ሐዋርያት፣ ከገሊላ ምድር ወጥተው የማያውቁና ከገሊላ ውጭ ወደ ሌላ አገር ሄደው ለማስተማር ይቅርና ሌላ አገር ስለ መኖሩም ምንም የማያውቁ የነበሩ ዓሳ አጥማጆች ከጣዖት አምላኪዎችና ራሳቸውን ማስመለክ ከለመዱ ከክፉ ነገሥታትና መኳንት እንዲሁም በመጥፎ ሰይጣናዊ ልማድ የተበላሸ ሕዝብ ጋር ባዶ እጃቸውን ታግለው፣ከምርኩዝ በቀር በትር እንኳ ሳይኖራቸው ዞረው ወንጌልን መስበክና ክርስትናን ማስፋፋት መቻላቸው በራሱ ልዩ ተአምር ነው።

ሳይንስ እና ሃይማኖት ገጽ 329


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4👏2
በአማን ነጸረ ስለ መጽሐፉ የሰጡት አስተያየት፦

የመጽሐፍ ሥራ የትሩፋት ሥራ ነው ብዬ አምናለሁ። ለጉባኤ ቤት ሰዎች ሲሆን ቸርነትም ነው። በዚህ ትውልድ  ያሉ መምህራን በመጽሐፍ በኩል ደጋግ ናቸው። እንጠቀምባቸው። ይህ መጽሐፍ ምግባረ ሠናይን፣ የምስጋና ሕይወትን፣ ለተፈጠሩለት ዐላማ መኖርን፣ ራስን አሳልፎ መስጠትን፣ ወዘተ. በፍጥረት መስታወትነት በረቂቅ እይታ ይሰብካል። መጽሐፍና ፍጥረት ድንቅ ሥራውን ሊመሰክሩ በጸሐፊው ብርዕ አካል ነሥተው ከፊታችን ቆመዋል።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍43
“ኃጢአቷን የቀበረችው ማርያም” መጽሐፍ በድጋሚ ታተመ

-በመ/ር ሥሙር አላምረው የተዘጋጀው “ኃጢአቷን የቀበረችው ማርያም” የተሰኘ መጽሐፍ ጌታን ሽቶ ስለቀቡት ማርያም ኀጥእት ብዙ ኃጢአቷን ቀብራ ብዙ ጸጋ ስላገኘችውና ማርያም እኀተ አልዓዛር ልዩነት ያስረዳል፡፡ መምህሩ “ከዚኽ በኋላ ጌታችንን ሽቱ የቀቡት ሴቶች እንዴት ሥስት ናቸው ተባለ የጋራ የቤት ሥራ ይኾነናል እንጅ አንዲት ሴት ብቻ ቀባችው ብለን የጨለማ ገልማጭ አንኾንም” ይሉናል፡፡

የመጽሐፉ አላማዎች

1) በእኅተ አልአዛር ማርያም ስም ማርያም ኃጥእት ተሠውራ እንዳትቀር ማድረግ

2)ስለ ባለሽቱ ሴቶች የግብጽ ቤ/ንና ሌሎች ተቋማት ምን አይነት ትምህርት እንዳላቸው ማሳየት

3)የተለያዩ የሊቃውንት ትርጓሜ ስለ ኃጢአተኛዋ ማርያም ምን እንደሚሉ ማስረዳት

4) የማርያም ኀጥእትን ገድል መሠረት በማድረግ የንስሐ ለቅሶዋን፣ ያጋጠማትን ፈተና እንዲሁም ገድሉ ያሉበትን የስምና የታሪክ ቅደም ተከተል ዝንፈትን መጠቆም፡፡

5)መጽሐፈ ስንክሳር የካቲት 6 የእኅተ አልዓዛር መታሰቢያ እንዳልሆነና የማርያም ዘሀገረ ናይን መታሰቢያ እንደሆነ ማስረዳት 

መጽሐፉን እኛ ዘንድ ያገኙታል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍43
የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ አቡነ አትናስዮስ እስክንድር ይህን መጽሐፋቸውን ወደ አማርኛ እንድተረጉመው ፣ ‹መንፈሳዊነት› የሚል ርእስ ያላቸው ብዙ መጻሕፍት በመኖራቸው የመጽሐፉን ርእስ በቀጥታ ተግባራዊ መንፈሳዊነት (Practical Sprituality) ብሎ በመተርጎም _ ፈንታ ተግባራዊ ክርስትና (Practical Christianity) ብዬ እንድተረጕመው በመፍቀድ፣ ፎቶአቸውንና የመጽሐፉን አዲስ ኅትም በመላክ ቀና ትብብር ስላደረጉልኝ አመሰግናቸዋለሁ፡፡ በዚህ የአማርኛ ትርጕም ላይ ለኢትዮጵያውያን ምእመናን ልጆቻቸው መልእክት እንዲጽፉ ስጠይቃቸውም‹‹እኔ ካህን ሆኜ ሳለ በኢትዮጵያ ላሉ እኅቶቼ እና ወንድሞቼ መጻፍን እንደ ድፍረት እቆጥረዋለሁ፡፡ በእኔ ፈቃድ የታተመ መሆኑ ከገለጽህ ይበቃል፡፡›› ብለዋል፡፡ ይህም ሌላ ተግባራዊ ክርስትና ስለሆነ በፈቃዳቸው ይህንን አሳብም አካትቼዋለሁ፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5👍2
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ3 ግዜ ታትማ ወታለች።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
6👍3
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት

ዘመናችን ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እጅጉን ፈተና ላይ የወደቀበት, የቤተ ክርስቲያን ሥርዐቷ ባለቤት ያጣበት ጊዜ መሆኑን መናገር ለቀባሪ የማርዳት ያህል ነው፡፡ ነገሩ ሲከፋ ደግሞ የቤተ ጉባኤና የቤተ ክርስቲያንን የሥርዐት መጻሕፍት ጠቅሶ ማስተማር የሚያሳፍር : የሚመስልበት ደረጃ ላይ ደርስናል። "ጸሐፊ" እና "ሰባኪ" የሚል ስም ተሸክመው ፍትሐ ነገሥትን የመሰሉ የሥርዐት መጻሕፍትን ለመጥቀስ እንኳ ፍላጎት የሌላቸው "አገልጋዮች" እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ምእመናንን (በተለይም በከተሞችና በውጭ ሀገራት የሚኖሩትን) ለእግዚአብሔር ሥርዐት ግዴለሽ እንዲሆኑ አድርጓል። በውጤቱም ክርስትና ከተግባር ቅድስና ይልቅ ስብከትና ጽሑፍ ብቻ እንዲሆን አስገድዷል። ስለዚህም እንደዚህ ያሉ የሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በእጅጉ ያስፈልጉናል። ይህ መጽሐፍ ኹሉንም የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዐቶች ለማካተት ይዘቱ፤ መጠኑ ባይፈቅድም ወሳኝ የሚባሉትን ነጥቦች በጥያቄና መልስ እያሰናሰለ ይዟል፡፡ ትኩረቱን ደግሞ በተለይ የዘመናችን የሥርዐት ክፍተት የሚታይባቸው የቅዳሴ፤ የቤተ ክርስቲያን ዙሪያና መሰል ጉዳዮች ላይ አድርጓል። ጸሐፊው፦ መምህር አብርሃም ከልጅነታቸው ተምረው በዜማ፤ በቅኔና በመጻሕፍተ ትርጓሜ የበሰለ አእምሮ ከጥሩ ብዕር ጋር ያላቸው ናቸውና ለዚህ የመጀመሪያ የጽሑፍ ሥራቸው መርቀናቸዋል። ቀጥሎም መሰል መጻሕፍትን ከመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የተነሣ ከትበው ያበረክቱልናል የሚል ተስፋ አለን፡፡

ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816
t.me/FinoteBooks1623
8👍2
ቃና ዘገሊላ መጽሐፍ ለ11ኛ ጊዜ ታተመ።

"የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ሁለትን የመጀመሪያ አንቀጽ መነሻ ያደረገችውና በሰርግ ቤቱ ስም ቃና ዘገሊላ በማለት የተሰየመ ይህ መጽሐፍ፥ እንደ ሰርግ ቤቱ ስድስት ጋኖች በስድስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው። ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዝ እንደነበሩት እንደ ቃና ጋኖችም እነዚህ ምዕራፎች እያንዳንዳቸው ሦስት ወይም አራት የንዑስ ርዕስ እንስራን የያዙ ናቸው፡፡ ...

"ይህ መጽሐፍ በስድስቱ ጋኖች /ምዕራፎች/ ውስጥ በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ትርጓሜ መነሻነት በሰርግ ቤቱ ውስጥ ጥቂት እንድንቆይ ለማድረግ ይተጋል፡፡ .….

"እንኪያስ እኛም በኄኖክ መሪነት በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ውስጥ እንድንመላለስ፣ ከጌታችንና ከሐዋርያቱ ጋር ወደ ሰርግ ቤቱ እንድንገባ፣ ወደ ጓዳ ዘልቀን የወይኑን ማለቅ አስበን እንድንጨነቅ፣ እመቤታችን ስታማልድ ልጇም ሲማለድ እንድናይ፣ ከአገልጋዮቹ ጋር ውኃ ልንቀዳ ወንዝ እንድንወርድ፣ አብረን ውኃውን እስከአፉ ሞልተን ጌታችን የሚያደርገውን እንድንመለከት፣ ከታዳሚዎች ጋር ወይን የሆነውን ውኃ ቀምሰን እንድናደንቅ፣ መልካሙ የወይን ጠጅ ምነው እስካሁን ቆየ? ብለን ከአሳዳሪው ጋር አብረን እንድንቆጭ፣ ከዚያም ከሐዋርያቱ ጋር በስሙ አምነን ከሰርግ ቤቱ እንድንወጣ፣ ከምድራዊው ሰርግ ቤት ወጥተንም ወደ የቤታችን ሳንገባ ወደ ሌላ ሰማያዊ ሰርግ እንድንታደም ይህን ግሩም መጽሐፍ እናንብብ፡፡...
____
ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
12👍6
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት

አሁኑ ጊዜ ‹‹ሃይማኖት እንጂ ሥርዓት አያድንም! በሚል ፈሊጥ እምነቱን ፍጻሜ የሚሰጠውና በሥራ የሚያስተረገመው ሥርዓትና ቀኖና በምን አለበት» አዘናጊ ብሂል ፈተና ሲገጥመው ይታያል፡፡ እውነታው እንዲህ እንዳልሆነና በእንዴት ያሉ ደጋግ አበው፣ በመቼ ጊዜና ቦታ፣ በምን ምክንያትና ምን ዐላማን ለማሳካት እንደ ተጻፈ በዚህ መጽሐፍ እንረዳለን፡፡ መጽሐፉ ብሔራውያን ምንጮች ከውጭ ቅጂዎች በማስተናበር የተጻፈ በመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችንን ያልተፋለሰና ያልተቋረጠ የእምነትና የሥርዓተ አምልኮ ጥንታዊነት በውስጥም በአፍአም ማስረጃ ያረጋግጥልናል። እያንዳንዱ ጉባኤ የተደረገበትን፣ የእያንዳንዱን ጉባኤ አናቅጽ ይዘት፣ የድንጋጌያቸውን ምክንያት፣ በጉባኤያቱ የነበሩ ተሳታፊዎችን ማንነትና ከጉባኤው በኋላ የነበረውን የአፈጻጸም ሁኔታ፣ በጉባኤው ሂደትና አፈጻጸም ያጋጠመውን ፈተና፣ የጉባኤያቱ ዓይነት፣ ያነጋገሩትን ጭብጦች፡ ያላስማሙትን ቁልፍ ቃላትና ሌሎችም ተያያዥ ሃይማኖታውያንና ታሪካውያን ሁነቶች መጥኖ አቅርቧል፡፡ እንደዚህ ያለ ታሪክንና ዐውድን ያገናዘበ አቀራረብ፡- ቃለ ሃይማኖትንና ሥርዓትን ቀዳምያኑ ሠሪዎች (ሐጋጊዎች) ባፀደቁበት ዐውድና በእኛ የዛሬ መረዳት መካከል የሚኖረውን ክፍተት በመሙላት ረገድ ዐቢይ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ የምንጩ ልሳነ ብዙኅ መሆን የቲዎሎጂ መምህራንና ተማሪዎች ከአብነቶቹ ያላቸውን ተዋሥኦ ያዳብራል፡፡ የወንድማችን የዲያቆን አዶንያስ ብርሃነ ‹የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች» መጽሐፍ ለዚህ ተዋሥኦና ጥናት ብዙ ርቀት የሚያስጉዝ ስንቅ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ከኢየሩሳሌሙ የሐዋርያት ጉባኤ እስከ ቊስጥንጥንያ የነበሩትን ጉባኤያት በግሩም አቀራረብ ቃኝቶ በመልካም ትርጓሜ አቅርቦልናል፡፡ መልካም ንባብ!

በአማን ነጸረ
ደብተራና የሕግ ባለሙያ

t.me/FinoteBooks1623
11👍6
#ዜና_ድጋሚ_ኅትመት

"ዮሐንስ ዘሰዋስው በምሥራቁ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ እንዲያውም በገዳማዊ ሕይወት ውስጥ ከወንጌል ቀጥሎ ተጠቃሹና ተሰሚነት ያለው መጽሐፍ ይህ መጽሐፍ መሆኑ በስፋት የተነገረለት ነው፡፡ እስከ ዛሬ ወደ እኛ ባለመምጣቱ የቀረብንን ይኸው ዛሬ መጽሐፉ ተተርጉሞ በመቅረቡ አንድ ጉድለት ተሸፍኗል፡፡ መጽሐፉ የክርስትና ሕይወትን ምንነት በአግባቡ ለመረዳትና ለመኖር በሚሹ ዘንድ ሁሉ የሚፈለግና የሚጠቅም መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ በተለይ ደግሞ እግዚአብሔር አምላካቸውን በገዳማዊ ሕይወት ለሚያገለግሉ ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው፡፡"
            ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

ይህ ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረውና ግሩም የሆነ መጽሐፍ አሁን በድጋሚ ታትሞ  ለገበያ ቀርቧል።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
16👍7
#ዜና-ድጋሚ-ኅትመት
አሐቲ ድንግል ለ4ኛ ግዜ ታትማለች!

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7👍4
ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
Photo
#ይህ የዲያቆን ታደሰ ወርቁ “ጽዋዔ" የተሰኘውን መጽሐፍ በርካታ ታዳሚ ፅንሰ ሐሳባት የታደሙበት ታላቅ የእልፍኝ አዳራሽ ይመስላል፡፡ መጽሐፉን ለማዘጋጀት በርካታና ጠቃሚ ዋቤ፣ ማጣቀሻ መጻሕፍትን መጠቀሙን ከመጽሐፉ የኅዳግ ክፍል ውስጥ መረዳት እንችላለን፡፡ የመጽሐፉም ዝግጅት በዋቤ መጻሕፍት ላይ ብቻ የተደገፈ የዕውቀትና የምርምር ጽሑፍ ብቻ ሳይሆን የአንባብያንን ኅሊና የሚሞግትና በሰው የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ የማኀበራዊ ፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ ምን መምሰል እንዳለበት የሚያስገነዝብ ኃይል ያለው ነው፡፡ መጽሐፉ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን የትውልድ ዘመን፣ የፍልስፍናና የሥነ መለኮት ትምህርት፣ የሥነ ልቦና ውቅር፣ ስለሰው ያለው ጥልቅ ፍቅር፤ እንዲሁም ለነፍሳት የሚያሳየው ፍጹም ርኅራኄ፣ በአንጾኪያ የነበረው የክህነት አገልግሎትና አስተምህሮ፣ በማኅበራዊ እኩልነትና በምጣኔ ሀብት ፍትሐዊ ክፍፍልነት ላይ ያለው ሙግት በጥልቀት የሚያነሣ በመሆኑ፤ መጽሐፉን አነበብኩት ብቻ ሳይሆን አጠናሁት ለማለት እችላለሁ፡፡ አንባብያንም ሆንን በዚህ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያየ የሥራ ዘርፍ የምንገኝ ሁሉ ስለ ማኅበራዊ ፍትሕ ፅንሰ ሐሳብ በይበልጥ የምንማርበት ስለሆነ ሁሉም ሰው መጽሐፉን አንብቦ እንዲጠቀምበት ግብዣዬ ነው፡፡
አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ (ዶ/ር)

በአሜሪካን ሀገር በትምህርት አገልግሎት ተቋም ውስጥ የትምህርት ሥራ ባለሙያና ተመራማሪ

"ጽዋዔ" በሚል ርእስ የተጻፈው የዲያቆን ታደሰ ወርቁ መጽሐፍ፣ ቃለ እግዚአብሔርን በሚገርም ጸጋ በማስተማርና በመስበክ የሚታወቀውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ጥሪ እና አገልግሎት ድንቅ በሆነ መልኩ ያስቃኘናል፡፡ ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ሳይሆን፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በእውነትና በኃይል በመስበክ፣ በሀብታቸው የሚመኩ ባለጸጎችን እየገሠጸ፣ ለድኾች ጥብቅና በመቆም ዮሐንስ አፈ ወርቅን የሚያክል አባት እስካሁን አልተነሣም፡፡ ዲያቆን ታዴ የዚህን ኦርቶዶክሳዊ ቅዱስ አባት ጥሪና እስከ ሊቀ ጵጵስና የደረሰ አገልግሎት፣ ከታሪክ ጸሐፊዎቹ ከእነ ሶቅራጥስ፣ ፓላዲየስ፣ አውሳብዮስ ዘቂሣርያ ወዘተ... አንደበት የሰማ እስኪመስል ድረስ ተነብቦ በማይጠገብ ሥነ ጽሑፍ (የአጻጻፍ ውበት) አቅርቦልናል፡፡ የታሪኩ ፍሰት፣ በየገጹ የሚታዩት ማራኪ ንኡሳን አርእስት እና የተወሳሰበው ታሪክ ተብራርቶ የቀረበበት መንገድ መጽሐፉን ተወዳጅም ያደርገዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት ለነገረ መለኮት (theology) ተማሪዎችና መምህራን፣ ለሰባክያን፣ እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያናቸው ታሪክ አካል የሆነውን የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ሕይወት አጽንኦት ሰጥተው እንዲያጠኑት በማድረግ ታላቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ራሳቸውን ልሂቃን (elites) አድርገው የሚቆጥሩ ወገኖቻችንም የተሰጣቸውን ሓላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ከዚህ መጽሐፍ ብዙ የሚማሩት ነገር ያለ ይመስለኛል፡፡

ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (ዶ/ር) የቀድሞ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዋና ዲን እና የ“አኰቴተ ቊርባን“ መጽሐፍ ደራሲ

ጽዋዔን ሳነብ ሀገሬ ትዝ አለችኝ፡፡ከአንድ ሺሕ ስምንት መቶ ዓመት በፊት አንጾኪያና አንጾኪያውያን የገቡበትን ሁለንተናዊ አረንቋ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ዛሬ ገብተንበታል፡፡ በርግጥም ከልብ አንብቦ ለተረዳው ለትንሣኤያችን መነሻ አሳብ አበርካች መጥሐፍ ነው። የጳጳሳቱ፣ የካህናቱ፣ የምእመናኑ፣ የመለካውያኑን ጠባያት በገሐድ ያሳያል። ኢትዮጵያውያን ከአዚማችን ከአልነቃን እንደ አንጾኪያ የሰዓታት ሳይሆን የዓመታት ዐመፅ አይቀሬ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ሀገሬ ዛሬም ዮሐንስ አፈ ወርቅን ታስሳለች፡፡ ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ምቀኝነት፣ መጠፋፋት፣ አሳልፎ መሰጣጣት ሁሉ በሚከወንባት ሀገሬ ከመጥፋቷ፤ እኛም ከመጥፋታችን በፊት መድኃኒት የሚሆን መጽሐፍ ነው፡፡ የታዴ የቃላት አመራረጡ፣ ክብደቱና አዋሐዱ የዐሥራ አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀገሬን ጠሐፍት አባቶቸን አስታወሰኝ፡፡ የቃላት ድርቅ ለመታንና በአማርኛ ጽሑፎቻችን እንግሊዝኛ ቃላትን ለምናዘወትረው “ተመየጡ ሀበ ዘቀዳሚ ፊደልክሙ" ይለናል። መጽሐፉን ብዙ ተመራምሮ አጣቅሶ የጣፈው እንደሆነ ከኅዳጎቹና ከጥቅሶቹ መረዳት ይቻላል፡፡

ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኅን አገልግሎት ሥርጭት ድርጀት ዋና ሥራ አስኪያጅ


ታላቁ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ አንጾኪያ በነበረበት ወቅት የአደረጋቸው ነገሮችና የአስተማራቸው ትምህርቶች ቤተ ክርስቲያን እና ሀገር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ሕዝብን እንዴት ማገልገልና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ማሻገር እንደሚቻል በተግባር ያስተምሩናል፡፡ ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ሰፊ ጥናትና ዳሰሳ በማድረግ የአዘጋጀው ይኽ መጽሐፍ፤ በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የአንጾኪያ የተጋድሎ ሕይወት አንጻር ካህናት ሕዝባቸውን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት መምራትና ማሻገር እንደሚገባቸው ያሳየናል፡፡ ተግባራዊ ትምህርት የሚሰጥ የሆነውን ይህን መጽሐፍ በመጻፉም ሊመሰገን ይገባዋል፡፡

መምህር ያረጋል አበጋዝ
ጸሐፊና ሰባኬ ወንጌል
💯54
“በዚህ መጽሐፍ ለማድረግ
የሞከርኩት አበው (አባቶቻችን) ያቆዩልንን የባሕረ ሐሳብ ትምህርት በትውልዳችን ቋንቋ ማቅረብ ሲሆን  ዓላማዬ ለማንም የአራት መደብ የቍጥር ትምህርት ለተማረ ሰው (ከልሂቅ እስከ ደቂቅ) ባሕረ ሐሳብ የማውጣት ችሎታን ማስተማር
ነው” (ገጽ 14)።

“የዛሬው ትውልድ ታሪክ ሲጠቅስ ብዙ ጊዜ ከአፄ ቴዎድሮስ ወደኋላ ሲሄድ ስለማልሰማ ከመጻሕፍቱ ጋራ በመስማማት ከሳቸው በፊት ያሉትን ዘመናት ለማስተዋወቅ ብዙ ገጾች ወስጃለሁ።
አፄ  ተከታዮቻቸው ቴዎድሮስና ነገሥታት
ኢትዮጵያን ከወደቀችበት እናንሣ ሲሉ አገራችን ያሸበረቀችበትና የወደቀችበት ዘመን ነበረ ማለታቸው ነው” (ገጽ 229)።

  “በምዕራፍ ፭ የተመዘገበው በዓውደ
ሰማዕ(ታ)ት መጀመሪያ ጀምሮ በዓመተ ምሕረት (ዓ.ም.) እና በዓመተ እግዚእ (A.D.) መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳየው (ሠንጠረዥ) ( በኛ
ዘመንቈጠራዎች የተመዘገበን
የታሪክ ድርጊት ወደ እነሱ የዘመን ቈጠራ (ወደ ዓመተ እግዚእ A.D.)፣ በነሱ (በዓመተ እግዚእ) የዘመን ቈጠራ የተመዘገበን  የታሪክ ድርጊት ወደኛ (ወደ ዓመተ ቈጠራ ምሕረት) የዘመን ለማዞር
ነው” (ገጽ 17)።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍63💯2
ገድለ አቡነ ጸጋ ዘአብ ወእምነ እግዚእኀረያወገድለ አቡነ ታዴዎስ ጽላልሽ
....ገድላት ኹሉን አቀፍ የመረጃ ምንጮች ናቸው። ዘመን፤ በአንድ አካባቢ፤ በአንድ ተመሳሳይ ሁኔታ የሚጓዙ አለመሆናቸው፤ በተለያዩ የዓለም ክፍል በተለያዩ ዘመናትና ጊዜያት የተነሡ የቅዱሳንን ሕይወት የተመለከቱ፤ ከምእመናን እስከ መዐርገ ጵጵስና ድረስ በተራ ዜግነት ከተሰለፉት እስከ ንጉሥነትና ንግሥትነት ደረጃ እስከ ደረሱት ድረስ ምእመናንንና ምእመናትን በእኩልነት የያዘ በመኾኑ ከሃይማኖት ጥቅሙ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰዎችን እኩልነት በማሳየቱ የበለጠ አጎልቶ ይሳያል።
  ❞ስለዚኽ ይኸ የካህኑ ጸጋ ዘአብ፣የብፅዕት እግዚእ ኀረያ እና የአቡነ ታዴዎስ ገድል የነፍስና የሥጋ በረከት የምንቀበልበት፤ ኹሉን አቀፍ መረጃ የምናገኝበት በመኾኑ በ፯ቱ ዕለታት በመክፈል በግዕዝና በአማርኛ በመተርጎም ቀርቧል።

❞ይኸም ቅዱሳኑ በሕይወተ ሥጋ እያሉም ኾነ ከዕረፍታቸው በኋላ በዐጸደ ነፍስ ሳሉ ያደረጓቸውን ልዩ ልዩ ድንቅ ተኣምራትን መልክዐቸውንም  አካቶ የያዘ የካህኑ ጸጋ ዘአብን፣ የብፅዕት እግዚእ ኀረያንና አቡነ ታዴዎስን ዝክረ ስም የሚናገር የምስጋናጸሎት ስለኾነ በዚኸ የጸሎት መጽሐፍ ተጠቅመን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እናገኝ ዘንድ ይህን ገድል   ኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም እነሆ  ይለናል ።

ይኽን የቅዱሳን ተጋድሎ እና ምስጋና የያዘ ገድል ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
4👍3🕊3🥰2
…………ለ8ተኛ ጊዜ የታተመ

"እንደ ኦርቶዶክሳውያን ወላጆች፥ ዓላማችን ፍጹማን ወላጆች መኾን አይደለም። ይህ የማይቻል ነውና። ... ልጆች የሚፈልጉት [እና የሚያስፈልጋቸው] እንደ እነርሱ የሚሳሳቱና [ከስሕተታቸው እየተማሩ] የሚያድጉ ወላጆችን ነው።"

#ትንሿ_ቤተክርስቲያን፥ ገጽ 447


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8🕊3👍2
.....አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ ሆነህ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#ከኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ_መጽሐፍ

❝ከ ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅወርቃማ ትምህርቶች አንዱ የሆነውን ይህን መጽሐፍ በግዮን መጻሕፍት የሚያገኙት   ሲሆን ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ለምትገኙ ውድ አንባቢያን በDHL እና በEMS  እንዲሁም የ delivery
አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ለአንባብያን ተደራሽ እናደርጋለን።❞

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
12👍4🕊3
💥ሰፌልያ🩸

"ሰፌልያ" የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወትን የሚተርክ እስከ ዛሬ ያልሰማናቸውን ዕውቀቶች እየተደመምን የምንጠጣበትና ጽናት የምናግኝበት ልዩ መጽሐፍ ነው።

በሰባኪ ወንጌል ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን ተደርሶ ለአንባቢያን የቀረበው ይህ አዳዲስ መረጃዎችን የሸከፈው መጽሐፍ፥ የዓለም ብርሃን ንዋይ ኅሩይ ስለ ተባለው የአገልግሎት ውጣ ውረድን የሚዳስስ ሥራ ነው።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
👍54🕊2
#ንስሓና_ምጽዋት_ታተመ!

በዚህ መጽሐፍ የተካተቱት ዓሥር ድርሳናት፥ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በ386 እና በ387 ዓ.ም. በአንጾኪያ ያስተማራቸው ሲኾኑ፥

👉  ኃጥአንም ጻድቃንም ንስሓ እንደሚያሻቸው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ካለው ወደር የለሽ ፍቅሩ የተነሣ አንድ ዓይነት የንስሓ መንገድ እንዳልሰጠ፣

👉 በዚህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓምድ ትምህርት በኾነው በንስሓ አማካኝነት ኃጥአን ያሳደፉትን ልጅነታቸውን የሚያድሱበትና ሕይወት ወደ ኾነው ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚመልሳቸው መንገድ መኾኑን፣

👉 ወደ ቅዱስ ቁርባን መድረሻ መንገድ ብቻ ሳይኾን ከላይ እንደ ተገለጠው በተለያየ መንገድ ማለትም በጸጸት፥ በምጽዋት፣ በጸሎት፣ በፆም፥ በትሕትና፥ ቅዳሴውንና አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮን በመሳተፍ፥ በአጠቃላይ ምግባር ትሩፋትን በመሥራት ያሸበረቀ ቤተ ክርስቲያናዊ ሕይወትን በመኖር የሚገለጥ ምሥጢር መኾኑን፣

👉 የአምላክን መጠን አለፍ ቸርነት ስጦታ መኾኑን ከብዙ ማሳያዎች ጋር ያስተማረባቸው ናቸው፡፡

መጽሐፉ በ200 ገጾች፣ በሚማርክ ኅትመትና በ300 ብር የሽፋን ዋጋ ለሦስተኛ ጊዜ ታትሞ ለአንባቢያን ቀርቧል።


ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5👍3🥰3🕊2
ዜና ድጋሚ ኅትመት !

ሳይንስ እና ሃይማኖት

..ሳይንስ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን አዕምሮ ተጠቅሞ ያስገኘውና በዚህ ዓለም ያለውን የኑሮ ድካም ማቅለያው የዕውቀት ዘርፍ ሲሆን ሃይማኖት ደግሞ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘው መንገድ ነው። ነገር ግን የሳይንስን ውሱንነት ያልተረዱ ሰዎች ሃይማኖትን በሳይንሳዊ ዕውቀት ለመተንተን ሲሞክሩና ወደ ተሳሳተ ግንዛቤ ሲያመሩ ይስተዋላል። በሌላ መልኩ ደግሞ ሳይንስ ለመንፈሳዊ ሰዎች እርባና የሌለው ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።
ይህንን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ፍልስፍናዊ አስተያየቶች፣ ጸሐፊው መምህር ያረጋል አበጋዝ፣ በዚህ መጽሐፉ ከሳይንስና ከሃይማኖት ጋር በተገናኙ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦች ዙሪያ ሰፊ ጥናት በማድረግ ከጥልቅ ትንታኔ ጋር አቅርቦልናል። ስለሆነም መጽሐፉን አንብበን የተሻለ ግንዛቤ እንድናገኝና እንድንጠቀምበት እየጠየቅኩ፣ ለመምህር ያረጋል ዕድሜና ጤናን ለእናንተ ለአንባብያን ደግሞ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ቀሲስ ሰሙ ምትኩ (ፕሮፌሰር)
ቦትስዋና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ




ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
8👍4🕊3
ጥቂት የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች
ሁ?ከተሰኘው


አባታችን አብርሃም ኑሮውን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግ የጀመረው አገሩንና ቤተ ሰዎቹን በተወ ጊዜ ነበር፡፡ አባቶቻችን ሐዋርያት ተመሳሳይ ነገር ነው ያደረጉት፡፡ እነርሱ ሲጠሩ ዓሣ አጥማጆች ሆነው ሳሉ የተዉት መረቦቻቸውንና ታንኳዎቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተከትለውትም ሄደዋል፤ማቴ 4፡20እና22፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው ከሆነማ ያላቸውን ነገር ሁሉ ትተው ነው የከተሉት፤ ማቴ 19፡27፡፡ እናንተስ? ስለ እግዚአብሔር ስትሉ የተዋችሁት ነገር ምንድር ነው? እናንተ ኃጢአተኛ ሕይወታችሁን በመተው ንስሐ ገብታችኋል?...
***
ያዕቆብመልእክት
ከተሰኘው

‹ብዙ ሰዎች እኔን በሀብታም ሰዎች ላይ ያለህ አቋም በጣም ጥብቅ ነው እያሉ ይናገሩኛል፡፡ በእርግጥም እንዲህ በማለታችሁ እውነት ብላችኋል፤ይሁን እንጂ እኔ በሀብታም ሰዎች ላይ ጥብቅ የሆንኩት ገንዘባቸውን ለመሳደቢያ አድርገው ለተጠቀሙበት ሀብታሞች ነው፡፡ እኔ እነርሱን የማጠቃቸው በግል አይደለም፤ነገር ግን የማጠቃው ስስታቸውን ነው፡፡ ........

  ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

...በተለይ በተለይ በትርጉም ስራ ረገድ ለኛ [ለኢትዮጵያውያን ] አባት ልጁን ለመመገብ  እንደሚጨነቅ እና እንደሚፋጠን ኹሉ በልዩ እና በተረዳ እንዲሁም በማይጠገብ መልኩ የሚያዘጋጁልን ፦
#አያሌው ዘኢየሱስን ያቆይልን እያልን ፦

💥አሁንም እነዚህን ሁለት ግሩማን፤  ሐሳቦችን የተሞሉ ፤መጻሕፍት እነኾ ያሉን ሲሆን በፍኖተ መጻሕፍት ያገኟቸዋል ።

ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦091308381
6

t.me/FinoteBooks1623
👍76🕊3🥰2