ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
3.32K subscribers
327 photos
1 video
282 links
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

t.me/FinoteBooks1623
Download Telegram
📚#የበርሃ_ምንጮች📚
[ማላንካራውያን]

.....ኢትዮጵያውያን ወላጆችም ልክ እንደ ማላንካራውያን የዛሬ ሕፃናት የነ አባቶች፣ የዛሬ ሕፃናት የነገ ሀገር መሪዎች፣ የዛሬ ሕፃናት የነገ ካህናት ጳጳሳት መሆናቸውን ተረድተን ልጆቻችን እንዲሆኑ የምንመኘውን የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ እና ቤተክርስቲያንን ለማየት እንድንችል ዛሬ ላይ ሆነን ነገን በጋራ ለልጆቻችን እንሥራላቸው፡፡ ሥራችንን ከቤታችን እንጀምር። ቢያንስ የወለድናቸውን ልጆች የእግዚአብሔር እንዲሆኑ እናድርጋቸው እኔ ካየሁት እውነት በመነሳት ይህንን የማትጊያ መጽሐፍ ለነገይቱ ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ ይጠቅማል ብዬ ሳበረክት እንደመነሻ ይሆን ዘንድ እንጂ ከዚህ የተሻለ ሥራ ይዘው የሚቀርቡ ወንድሞችና እህቶች እንደሚኖሩ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡ የተወደዳችሁ አንባብያን መጽሐፉን ስታነቡት የአጻጸፍ ግድፈትም ሆነ ሌላ ክፍተቶችን ካገኛችሁ የእኔ የጸሓፊው ድክመት እንጂ የማንም አለመሆኑን በቅንነት እንድትረዱኝ እጠይቃለሁ ።

[✍️ ጸሐፊው]

➲ማሳሰቢያ የመጽሐፉ ሙሉ ገቢ ለቤተክርስቲያን የተደረገ ሲኾን በኹለት ወገን የምንጠቀምበት መጽሐፍ ነው..!

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5👍3
📜ወይቤሉ በበይናቲሆሙ ፥ አኮኑ ይነድደነ ልብነ ፥ ዘከመ ይነግረነ በፍኖት ፥ ወይፌክር ለነ መጻሕፍተ!📖

«እርስ በርሳቸውም፦ “በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን?” ተባባሉ»
[ሉቃ ፳፬፥፴፪]
15
📚#ሳይንስ_እና_ሃይማኖት

...ተፈጥሯዊ የሆነውን የአጽናፈ ዐለም ምስጢር በገለጥን ቁጥር የእግዚአብሔርን እጅ እየገለጥን ነው፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ የዚህን ዐለም ጥበብ የሚመረምርበትንና የሚረዳበትን እውቀት የሰጠው እግዚአብሔር ነውና። ስለዚህ ሳይንስ ከክርስትና እምነት ጋር ይጋጫል ብሎ ማሰብ እግዚአብሔርን ከመተቸት ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ምክንያቱም በሳይንስ የምንረዳውን ነገር አስቀድሞ የፈጥረው እርሱ ነውና። በሳይንስ እና በእምነት መካከል በተከፋፈለ ዐለም ውስጥ፣ “ሳይንስ እና ሃይማኖት” ተለምዷዊ ድንበሮችን በመሞገት አንባቢዎች የእውነትን መንገድ እንደገና እንዲያጤኑት ይጋብዛል። ሳይንቲዝምን እንጂ ሳይንስን ባልተቃውመ መልኩ፣ መምህር ያረጋል አበጋዝ ጥልቅ ሐሳቦችን እንዲመረምሩ ይጋብዛል።በአጠቃላይ፣ በሳይንስ እና በእምነት መካከል ያለውን ጥልቅ ግኑኝነት የሚዳስስ አእምሯዊ አነቃቂና በመንፈሳዊ የበለጸገ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ስለ ህልውና ምስጢር ለማወቅ ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው በጣም ይመከራል።

✍️ዲያቆን ክብረት መኳንንት

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]


ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
🙏52
💧አዲስ መጽሐፍ
📚#መልክአ_ሥዕል_ንባቡና_ትርጓሜው

➥ይኽ የቅዱሳት ሥዕላትን ክብር በግጥም ስንኝ ቋጥሮ የሚያወድስ“መልክአ ሥዕል” አስደናቂ ድርሰት ሲኾን በውስጡም፡-

❖ ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ታሪክ
❖ ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ሠዓሊዎች
❖ ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ክብር
❖ ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ዓይነቶች (የጌታችን እና የእመቤታችን ሥዕላት)
❖ ከመላእክት ሥዕላት ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል፣ የቅዱስ ገብርኤል፣ የቅዱስ ሩፋኤልን ሥዕላት
❖ ከሰማዕታት የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥዕል
❖ በተለያዩ ሀገራት ስለሚገኙ ቅዱሳት ሥዕላት
❖ በቅዱሳት ሥዕላት ስለተደረጉ ተአምራት በግጥም መልኩ በውስጡ ተጽፈዋል፡፡ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ክብር የተደረሰው የዚኽ የመልክአ ሥዕል ደራሲ ማነው? ለሚለው ጥያቄ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በአታ የአቋቋም ምስክር ጉባኤ ቤት መምህር የነበሩት መጋቤ አእላፍ ሔኖክ ወልደ ሚካኤል ባሳተሙት “መልክአ ጉባኤ” ላይ የግል ምንጭ ኅሩይን በመጥቀስ በገጽ ፫፻፲፰ ላይ ዐጼ ገላውዴዎስ እንደኾኑ ጽፈዋል፡፡
◈አንባብያን ሆይ መጽሐፉን ሳዘጋጅ ምናልባት በኮምፒውተር ጽሕፈት ጊዜ የሚያጋጥም የፊደልና የቍጥር ግድፈት ካገኛችኍ መልታችኍ እንድታነቡት በአክብሮት እጠይቃለኊ፡፡

✍️[መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ]

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]


ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4🕊3🥰2
«ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወለሥዕለ ወልድኪ እገኒ ማርያም ድንግል ማርያም እመ አዶኒ ማዕበለ ጌጋይ ጽኑዕ ሶበ ለአስጥሞ በጽሐኒ ሐመርየኒ ማዕዶትየኒ ሃይማኖትየኒ ማርያም እግዝእትየ ወእንበሌኪ አልብየ ምንትኒ::"
   ትርጉም:-
"በሥዕልሽ ፊት ልስገድ ለልጅሽም ሥዕል ልገዛ
ድንግል ማርያም እናቱ  የአዶናይ የዓለሙ ቤዛ
ነፍሴን ሊያሰጥማት ደርሶ የበደሌ ማዕበል ሲበዛ
ሃይማኖቴ አንቺ ነሽ መርከቤ መሻገሪያ ምሽግ ታዛ
ማን አለኝ ያላንቺ እመቤቴ ማርያም የንግግሬ ለዛ::"
          "አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መልክአ ሥዕል"

"እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ"ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልጂን ሰላም አንድነት ፍቅር ስጭን በመንገዳችን በሕይወታችን ሁሉ አትለይን ዘመናችንን ባርኪልን ርስት ሀገርሽን ኢትዮጵያን ጠብቂልን፥ ከሐሰተኞች መምህራን ጠብቂን ::»
10
Forwarded from Tekle H
📚#መጽሐፈ_አርጋኖን

«እምኵሉ ድርሳናት ዘተናገርክዎሙ ይጥዕም ወይትሌዓል፤ ልቦናዬን መንፈስ ቅዱስ አነሣስቶኝ ከተናገርኋቸው ውዳሴያት ኹሉ መጽሐፈ አርጋኖን ጥዑም ነው...» ሲል ታላቁ ሊቅ #ጻድቁ_አባ_ጊዮርጊስ የተናገረውን በከበረ መጽሐፈ ገድሉ ምዕራፍ አምስት አንቀጽ ዐሥራ አንድ ላይ እንመለከታለን ፡፡እነሆ ገቢው ለደብረ ባሕርይ ጻድቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና ለቅዱስ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል አንድነት ገዳም ይውል ዘንድ በገዳሙ ፈቃድ ይኽ መጽሐፈ አርጋኖን ኢትዮጵያውያን የጻድቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና የቅዱስ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ወዳጆች ኹሉ ለብዙ ዘመናት ረድኤተ እግዚአብሔርን ለማግኘት የእመቤታቸንን አማላጅነት ሲማፀኑበት ከጠላ ቶቻቸው እጅ ሲጠበቁበትና ሀብተ ሥጋ ሀብተ ነፍስን ሲቀበሉበት ይልቁንም ጸሎቱን ደግመው እየተጠመቁ ሲፈወሱበት ኖረዋል ።-ስለዚህ እመቤታችን ለጻድቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በገለጠችላቸው በዚህ በከበረ መጽሐፈ አርጋኖን ድኅነተ ሥጋ፣ድኅነተ ነፍ ስን እናገኝ ዘንድ ልቦናችን በምስጋና ይመላ ዘንድ አዘውትረንም ወደፈጣሪያችን እንጸልይበት ። " የጻድቁ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች : ታድናለችምና "

[የጻድቁ አባታችንአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና
የቅዱስ አባ በጸሎተ ሚካኤስ አንድነት ገዳም
]


📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]


ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
🕊32
🍂🍂🍂🍀🍂🍂🍂🍂
....ክቡር ኃያል መስተጋድል #ሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ማር_ጊዮርጊስ እጅግ ደስ ብሎት #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ የማይገባኝን እጅግ አክብረኸኛልና አመሰግንሀለሁ አለ :: ከዚኽ በኋላም #ጌታችን የተመሰገነ #ሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስን ባርኮት ከእርሱ ተሠወረ #ቅዱስ_ማር_ጊዮርጊስም ወታደሮችን ቀስቅሶ ወንድሞቼ ኑ የታዘዛች ሁትን ፈጽሙ አላቸው ፡፡ ፊቱንም ወደ ምሥራቅ መልሶ #በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስቅዱስ ብሎ በመስቀል ምልክት አማትቦ አንገቱን አቀረበ ፡፡ ያን ጊዜም የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ማር ጊዮርጊስን የከበረች ራሱን ቈረጡት ደምና ውኃ ወተትም ፈሰሰው ፡፡ ጌታም ደሙን በብርሃን ልብስ እንዲቀበለው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘለት ፡፡#ጌታችንና መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኀያሉ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ነፍስ በእጁ ተቀብሎ ሳማት በሰማያዊ ልብስም አጐናጽፎ ከእርሱ ጋራ ወደ ሰማይ አሳረጋት፡፡
ሰላም ለከ በእንተ #ሃይማኖት_ርትዕት ነፍስ ዚአከ ትሜጡ፣#ጊዮርጊስ ዕፍረት ዘዕፁብ ሤጡ ፣ ገበርተ አፈው እምይጽዕጡ ፡፡
ትርጉም
ሽቱን የሚቀምሙ ከሚያጣፍጡት ሽቱ ይልቅ ዋጋህእጅግ ድንቅ የኾነ ስለቀናች ሃይማኖት ነፍስህን የሰጠህ #ሊቀ_ሰማዕታት_ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሆይ ምስጋና ይድረስህ ፡፡

🍂ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት በዓል እንኳን አደረሰን! ክብርት ጸሎቱ ትድረሰን ፥ እንደእርሱ የእውነት ምስክርም እንድንኾን ምልጃው ትደግፈን!
6🙏4
📚#ሕይወተ_ማርያም_ድንግል

.....እንግዲህ ምን እንላለን ሕዝቅኤል ያያትን አዳራሽ ቁራዎች ቢከቧት ምን አደረጉ፤ እንዲያው እነሱ እየታጨዱ ወደቁ እንጅ ፤ ዛሬም #የእመቤታችንን ክብር ያቃለልን መስሏቸው ተረፈ ቁራዎች ዙሪያዋን ከበው መጽሐፍ ይጽፋሉ፣ንግግር ያደርጋሉ ግን በአዳራሷ ላይ ቅንጣት ታክል ነውር መጨመር እንደማይችሉ የምናገርበት አጋጣሚ ቢሆነኝ ብዬ እኔም አባቶቼ #ስለእመቤታችን ከተናገሩት የውዳሴ ውቅያኖስ ቀድቼ እንደ ክብሯ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በረዳኝ መጠን በማብዛት ያይደለ በማሳነስ፤ በማስረዘም ያይደለ በማሳጠር ጥቂት ቃላትን ተናግሬአለሁና አንብበን እንጠቀም ዘንድ ‹‹በእንተ ስማ ለማርያም›› እላለሁ።

✍️ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መላክ

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]


ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
7
#ተወዳጆች....

➮የዕቅበተ እምነቷ ቅመም ባለማወቅ ለተነጠቁት ዓይነተኛ መፍትሔ (መድኃኒት) በመኾን የጠቀመ በእውር ድንብር ለሚመሩት ደግሞ ከዳተኝነታቸው የተነሳ የሚፈሩት የ*መ*ና*ፍ*ቃ*ን 🔨 በጉምቱ መምህራችን በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ የተቀመመው ድንቁ መጽሐፋችን #መድሎተ ጽድቅ ቅጽ-፩ #ለ20ኛ_ጊዜ_ታትሟል!!


''ለሰው ልጆች መዳኛ ትሆን ዘንድ ከእግዚአብሔር የተሰጠችው አንዲቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ክርስትና  በሰዎች ግለሰባዊ አስተሳሰብና 'መሰለኝ' በሚል ግምትና መላ ምት የተገኘች ሳትሆን ከራሱ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናት፡፡''

           [ከውስጥ ገጽ....]


📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞
0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5
📚#ዝክረ ቅዱሳን አንስት ዘተዋሕዶ ፩

...#የጣማፍ_ኄራኒ አኗኗር ገዳማዊነትን በትክክል ላየ ሰማያዊ ሰው ወይም ምድራዊ መልአክ የሚያሰኝ ነው። በዚህ የተቀደሰ ኑርዋ ውስጥ የጥንታውያኑን ገዳማውያን አበውና እማት አኗኗር እንድናይ አድርጋናለች። ሥርዓቱን ከሕይወቷ ጋር እያናበበች ወይም እየኖረች በማሳየት አዲሱ ትውልዳችን የጥንታውያኑን ክርስ ቲያኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሕይወትና ፍቅረ እግዚአብሔርን ገንዘብ ያደርግ ዘንድ፥ እንደ መጽሐፍ የሚነበብ አገልግሎቷንና ተጋድሎዋን ማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ ተግባሯ ነው᎓᎓ ከባሕር የወጣ ዐሣና ከገዳሙ የወጣ መነኰስ አንድ ናቸው እንደሚባለው ሁሉ፡ ከወንጌል የራቀ ክርስቲያንም የነፍስ ድኅነት የለውምና፥ ወንጌል ከሆነው የቅዱሳን አበውና እማት ሕይወት እንማር።በአጠቃላይ የመጽሐፉ ዐላማ ሴቶች በመንፈሳዊ ጉዞአቸው ከወንዶቹ በምንም እንደማይተናነሱና ይህንንም በተለያዩ ዘመናት የነበሩ አንስት በገድል እየኖሩ ያሳዩ መሆ ናቸውን ማሳወቅና መልካም አርአያነታቸውንም መግለጽ ነው።

Ⓒለረዥም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ የነበረው ይህ መጽሐፍ በጥሩ ኅትመት በድጋሚ ወደ ገበያ መጥቷል።

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
4
…... ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የተጻፈላቸውን ደብዳቤ ይዘው ቤተ ክህነት ሲደርሱ፤ የቤተክህነቱ ባለሥልጣናት ‘እንዴት ለአንድ መምህር ደመወዝ አንድ መቶ ብር ይከፈላል? ለእርስዎ ሃያ ብር ይበቃዎታል’ ብለው ቀነሱት፡፡

ሆኖም በሁኔታው ያዘኑ የእርሳቸው የሆኑ ሰዎች ‘ንጉሡ የፈቀዱትን እዚህ ያሉት ሠራተኞች ሊቀንሱ ስለማይችሉ አሁንም ሄደው ያመልክቱ’ ይሏቸዋል፡፡
እሳቸውም ‘ሄጄ የማመለክተው እዳ ለምን ተቀነሰልኝ ብዬ ነው? ይኼውም ሲበዛብኝ ነው’ ብለው ያንን ሃያ ብር ደመወዝ ተቀበሉ፡፡

ታዲያ አዲስ አበባ ሄደው በነበሩበት ጊዜ ….. ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ይሄዳሉ፡፡ ቀደም ሲል ጎንደር አብረዋቸው ይማሩ የነበሩት አለቃ የማነብርሃን የሚባሉ ዳር ሀገር እየተባለ ከሚጠራው ቦታ የሚኖሩ በአጋጣሚ ለጉዳያቸው አዲስ አበባ መጥተው ኖሮ እዚሁ አራዳ ቅዱሰ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ድንገት ይገናኛሉ፡፡

መንፈሳዊ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ስለኑሯቸው ሲወያዩ፡-
‘አዬ ጥበቡ! ለእኛ ትበጃለህ ብለን የምናምንብህ እዚያ ከገጠር ተሸጉጠህ ቀረህ፡፡ እኔን እንኳ እስኪ ተመልከተኝ’ ብለው በኑሯቸው የደላቸው መሆናቸውን ለማስረዳት ሲሞክሩ፡-

‘አዬ የማነብርሃን! እኔም እኮ የጠላሁት እንዳንተ መሆኑን ነው’ አሏቸው…..”

ከውስጥ ገጽ

«#የማምሻ_ዕድሜ_ወግ»»

📚ፍኖተ መጻሕፍት
t.me/FinoteBooks1623
5👍5
🌹 ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ :
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ ::

" ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን(አስገኘችልን) "

◉እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:5)


‹‹ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌዉ በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል#ይህ_መቅደሱን_የሰራበት_ዕለት_ነዉ፡፡ ይህዕለት ትልቅ ህንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነዉ፡፡››
[የቀርጤሱ ቅ/እንድርያስ]

 
#ማርያም ማርያም ይላል ምጥም እንዳያቄም
     
#በማን_ስም? ወለዱሽ ሐና እና ኢያቄም

ዮም ፍስሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም
!
       
12
📚#አንቀጸ_ብርሃን
አንድምታ ትርጓሜ

#አንቀጸ_ብርሃን ፦ የብርሃን ደጃፍ ፤ የብርሃን መስኮት፤ የብርሃን በር፤ አለ፦ ከሌሎች አናቅጽ ሲለያት አንቀጸ ብርሃን አላት። መስታዎት ሲላት ነው። በሌሎቹ አናቅጽ ግዙፋኑ ግሡሳኑ ፍጥረታት ይገቡባቸዋል ይወጡባቸዋል። በዚህ መስታዋት ግን ከብርሃን በቀር ሌላ ነገር አይገባባትም አይወጣባት። እመቤታችንም ብርሃን ዘበአማን ከሚባል ከጌታ በቀር ሌላ ልጅ የላትምና።አንድም ሌሎቹ አናቅጽ ካልተከፈቱ አያስገቡም ካልተዘጉ አይከለክሉም። መስታዋት ግን በዝግነት ሳላ ብርሃንን ያሳልፋል ብርሃንን ሲያስገባ ግዙፋኑን ፍጥረታት ነፋሳትን ማያትን ሳይቀር ይከለክላል። አንድም..

***ይነበብ...

📚 ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
5🙏4
📚#ሰማዕትነት_አያምልጣችኹ
በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ



«የኅሊና ዳኛ»
#እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ኅሊና ውስጥ፣ ኹል ጊዜ ንቁና ትጉ የኾነ ዳኛ ያስቀመጠው ስለ ምንድን ነው ብለኅ ብትጠይቀኝ፣ ከሰው ወገን ይኽን የ'ኅሊና ዳኛ'ን የመሰለ፣ እንቅልፍ የለሽ ዳኛ ስለሌለ ነው ብዬ እመልስልሃለኹ፤ ዳግመኛም፣ የውጪ ዳኞች በገንዘብ፣ በውሸት በመደለል፣ የሐሰት ፍርድ እንዲሰጡ በማስፈራራት፣ እንዲኹም በሌሎች መጠነ ብዙ ምክንያቶች፣ ርቱዕ የኾነ (ያልተዛባ) ውሳኔአቸውን ሊያጣምሙ ይችላሉ፤ የ'ኅሊና ዳኛ'ን ግን በእነዚኽ በገለጽናቸው ምክንያቶች በምንም መንገድ የሚደለል አይደለም፤ ጉቦ ብንሰጠው፣ ልንዋሸው ብንሞክር፣ ብናስፈራራው፣ ሌላ ሌላም ብናደርግ እንኳ፣ ይኽ የ'ኅሊና ዳኛ' ለምናስበውና ለምንሠራው ኀጢአት ምንም ሳይጠመዝዝ እውነተኛ ፍርድን ይሰጣል፤ ኀጢአት የሠራ ሰው፣ ሌላ ሰው ባይወቅሰውም እንኳ፣ ርሱ ራሱ ራሱን ይወቅሳል፤ አንዴ ወይም ኹለቴ ብቻ አይደለም፣ መላ ዘመኑን እየደጋገመ ኅሊናው ይወቅሰዋል፤ ኅጢአት የሠራነው ከረዥም ዘመናት በፊት ሊኾን ይችላል፤ የኅሊናችን ዳኛ ግን ያን የሠራነው ጥፋት ፈጽሞ አይረሳውም።

📚ፍኖተ መጻሕፍት
t.me/FinoteBooks1623
4🥰2👏1🙏1🕊1
📚 #ፍና_ቅዱሳን

‹‹እግዚአብሔር በአንድም መንገድ በሌላም ይናገራል››

ደቀመዝሙር ለመምህር፤ ምዕመንም ለካህን መመለስ ምክንያት ቢሆን አይደንቅም፡፡ ለበለዓም መመለስ አህያን፣ #ለቅዱስ_ጴጥሮስ ንስሐም ዶሮን እግዚአብሔር ተጠቅሟል፡፡ መስማት መቻል የእኛ ፋንታ ነውእውነተኛ ማንነታችን በስም፣ በማዕረግ፣ በእውቀት፣ በዕድሜ ወዘተ... ተሸፍኖ ሊኖር ይችላል፡፡ ዛሬ ብዙዎቻችን ጋር ያለው ከልብ ያልሆነ የማስመሰል ክርስትና ነው፡፡ መማር፣ መቀደስ ማስቀደስ፣ መዘመር፣ መስበክ ወዘተ... ብቻ ክርስትና መስሎን የምንኖር ብዙዎች ነን፡፡ ይኸውም እንኳ የልማድ እንጂ ከውስጥ ያልሆነ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሥርዓተ አምልኮ ክፍል እንጂ በራሱ ብቻውን የክርስቲያናዊ ሕይወት መገለጫ አይደለም፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያን ሔደን ስለተማርን፣ ስላስቀደስን፣ ስለዘመርን ወይም አገልጋዮችም ስላስተማርን፣ ስለቀደስን፣ ስላስተዳደርን ብቻ ክርስትናን እየኖርን ከመሰለን ተሳስተናል፡፡ ተክል ፍሬ እንዲያፈራ ውሃ፣ ማዕድን፣ የፀሐይ ብርሃን ወዘተ... እንደሚያስፈልገው እኒህም መንፈሳዊ ፍሬ እንድናፈራ የሚያደርጉን ናቸው፡፡ አብዛኞቻችን ግን በእነዚህ ብቻ ታጥረን ቆመናል፡፡👉🏿 የክርስትና ሕይወት መገለጫ ፍቅር፣ ቅድስና፣ ንጽሕና፣ ትኅትና፣ ትዕግሥት፣ ቅንነት፣ ይቅር ባይነት፣ በሌላ አለመፍረድ.... እኒህንም የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በመመላለሳችን ሁሉ እኒህ ከሌሉ የክርስትናን ጭምብል አጥልቀን እየተወንን እንጂ ክርስትናን አይደለም፡፡ ብርሃን ከጨለማ በቀላሉ እንደሚለይ ክርስቲያንም በግብሩ ከአሕዛብ በቀላሉ ይለያል፡፡ መለያው ደግሞ ሕይወቱ እንጂ የአገልግሎት ተሳትፎው አይደለም፡፡

📚ፍኖተ መጻሕፍት
t.me/FinoteBooks1623
7🕊4
📚#አምስቱ_የንስሐ_መንገዶች
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

“ጠላቶቼ ኹሉ ይፈሩ፥ እጅግም ይጐስቁሉ”  (መዝ.6፥10)

ይህ ጸሎት ታላቅ የኾነ ጥቅም አለው - ጠላቶች ሲያፍሩና ወደ ኋላ ሲሉ! ምን ማለት ነው? በክፉዎች መንገድ የሚኼዱ ሰዎች ሲያፍሩና ወደ ኋላቸው ሲያፈገፍጉ ከክፋታቸው ይመለሳሉና፡፡

አንድ ሰው በፊቱ ወዳለው ገደል ለመውደቅ እየተንደረደረ እንደ ኾነ ስናየው፡- “ወንድሜ ሆይ! የምትሮጠው ወዴት ነው? በፊትህ ያለው’ኮ ገደል ነው” እንደምንለው ኹሉ፥ ክቡር ዳዊትም “ጠላቶቼ ኹሉ ይፈሩ፥ እጅግም ይጐስቁሉ” ሲልም እነዚህ ሰዎች ከክፉና እነርሱን ከሚያጠፋቸው መንገዳቸው እንዲመለሱ እየጸለየ ነው፡፡

📚 ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞፦0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
3🙏3
📚#ተንከተም📚

👉ይህ መጽሐፍ፥ ጸሎተ ሃይማኖትን እየጸለዩ የይዘቱን ጥልቀት የማያወቁትን ሁሉ ከአምስት ደቂቃ ላልበለጠ ጊዜ የሚጸልዩት ጸሎት ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ የሚያመላክት ግሩም መጽሐፍ ነው። እንግዲያውስ ከ፲፪ቱ አበው የተቀበሉትን፣ ሊቃውንት በ፲፪ አንቀጾች የቀመሙትንና ፲፪ በሮች ወዳሏት መንግሥተ ስማያት የሚያስገባንን ጸሎተ ሃይማኖት በ፲፪ ምዕራፎች ላቀረቡልን ሊቀ ሊቃውንት፥ ዕድሜ፣ ጤና እንዲሰጥልኝ እየተመኘሁ፡ ባለ፲፪ የሆናችሁት እንድታነቡት በ፲፪ቱ ሐዋርያት ስም እጋብዛለሁ፡፡ ሊቀ ሊቃውንትን ስምዐኮነን እና ሌሎች ሊቃውንትንም ልክ እንደዚህ የተቋጠሩትን እንድታፍታቱልን በዚሁ አጋጣሚ አሳስባለሁ፡፡

✍️ከዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።

[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]

ይደውሉልን!📞
0913083816

Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
9🙏2