የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.75K subscribers
6.74K photos
70 videos
82 files
1.75K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ሰላም እንደምን አመሻችሁ
ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ

ውድ የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ የፊታችን ማግሰኞ ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም Calendar ዝግ የሆነ በመሆኑ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሰ/ት/ቤታችን በጀትና ንብረት አስተዳደር አስተባባሪነት ለአገልግሎት የምንጠቀምበትን ልብሰ ስብሐት ለማጠብ መርሐግብር ይዘናል በመሆኑም በዕለቱ መምጣት የምንችል አባላት በሙሉ በመገኘት ይህን የትሩፋት ሥራ በመሥራት ከበረከቱ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም በአክብሮት ጠርተኖታል።
 
እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ!

    
  ከበጀትና ንብረት አስተዳደር ክፍል
12
የእለቱ የአገልግሎት ዜና
ነሐሴ ፲፯/፳፻፲፰


በዛሬው ዕለት የሰንበት ት/ቤታችን አዳጊ-ሀ ሕጻናል ክፍል በርዕሰ አድባራት መንበረ ጸሐይ እንጦጦ ማርያም እና በእንጦጦ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ አብያተ ክርስቲያናት ዓመታዊ የአንድነት ጉዞዋቸውን አከናውነዋል።

ለጉዞው መሳካት የትራንስፖርት ወጪያቸውን በማዕከላውያን ክፍል አባላት ከቡሄ ዝማሬ ያገኙትን ገቢ ለታናናሾቻቸው ወጪውን በመሸፈን ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፤ በቀጣይ ነሐሴ 30 የአዳጊ-ለ ሕጻናት ክፍልና የማዕከላውያን ክፍል የአንድነት ጉዞ የሚያደረግ በመሆኑ፤ ይህንንም ጉዞ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ አባላትን በማስተባበር ከፍለው መሄድ የማይችሉ ወንድምና እሕቶቻችንን ለማገዝ የጉዞ ኮሚቴ ጥሪ እያደረገ ስለሚገኝ፤ አባላት እንደ አቅማቸሁ የተዘጋጀውን የድጋፍ ኩፖን በመግዛት እንድንተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክልን!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተከፈቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ናቸው። ቤተሰብ በመሆንና ለሌሎች በማጋራት አብረውን ያገልግሉ። 

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
3