የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.76K subscribers
6.74K photos
70 videos
82 files
1.75K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ነሐሴ 13 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በዓል ምክንያት በማድረግ የሰንበት ት/ቤታችን ማእከላውያን ክፍል አባላት በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የበዓሉን ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ በመጨረሻም በደብራችን በርካታ ምዕመናን በተገኙበት፤ ስለ በዓሉ ቃለ እግዚአብሔር ከተሰጠ በኋላ በችቦ ማብራት እና በዝማሬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል። የማእከላውያን ክፍል አባላት በየዓመቱ ለምናካሂደው ጉዞ ከፍለው መጓዝ ለማይችሉ አባሎቻችን፤ ከቡሄ ዝማሬ የሚያገኙትን ገቢ ሙሉ በሙሉ ለጉዞ ኮሚቴ በማስረከብ ለጉዞው ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ለዚህ በጎ አገልግሎታቸው አምላከ ሚካኤል ዋጋቸውን ይክፈልልን ለማለት እንወዳለን።

እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ!
3
በዛሬ ዕለትን የእናታችን የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ዓመታዊ የትንሣኤ እና የዕርገት በዓል የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ጸሐይ ቆሞስ አባ ብርሃነ ሥላሴ አስፋው፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል። ወቅቱ ክርምት እንደመሆኑ ዝናብ ቢጥልም፣ ምዕመናን ዝናቡን ታግሰው በዓሉን በታላቅ መንፈሳዊ ስነ ሥርዓት አክብረው ውለዋል።

የእናታችን የኪዳነ ምሕረት ጸሎት በረከቷ፣ ምልጃ ቃል ኪዳኗ፤ የልጇ ቸርነት አይለየን!
🕊2