የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.75K subscribers
6.74K photos
70 videos
82 files
1.75K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ነሐሴ 13 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትን በዓል ምክንያት በማድረግ የሰንበት ት/ቤታችን ማእከላውያን ክፍል አባላት በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የበዓሉን ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ በመጨረሻም በደብራችን በርካታ ምዕመናን በተገኙበት፤ ስለ በዓሉ ቃለ እግዚአብሔር ከተሰጠ በኋላ በችቦ ማብራት እና በዝማሬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል። የማእከላውያን ክፍል አባላት በየዓመቱ ለምናካሂደው ጉዞ ከፍለው መጓዝ ለማይችሉ አባሎቻችን፤ ከቡሄ ዝማሬ የሚያገኙትን ገቢ ሙሉ በሙሉ ለጉዞ ኮሚቴ በማስረከብ ለጉዞው ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን፣ ለዚህ በጎ አገልግሎታቸው አምላከ ሚካኤል ዋጋቸውን ይክፈልልን ለማለት እንወዳለን።

እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ!
3