የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.6K subscribers
6.21K photos
67 videos
79 files
1.71K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
በሰንበት ትምህርት ቤታችን የተልዕኮ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ከ350 በላይ የ5 ኛ ዙር የተልዕኮ ት/ት ተማሪዎች የነገረ ቅዱሳን ትምህርት በመስጠት በትናንትናው ዕለት እሑድ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ጉባኤ ተከናወነ።
በሰ/ት/ቤታችን የተልዕኮ ት/ት ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ  በቅርቡ የሚመረቁ ከ250 በላይ የሚሆኑ  ተማሪዎች  በትላንትናው እለት ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ጥናታዊ ጽሑፍ  አቀረቡ። ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ ርዕሰ ጉዳይ በጥቂቱ

➡️ የእህቶች አገልግሎት
➡️  ወጣቶች እና የቤተክርስቲያን አገልግሎት እና
➡️ የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ንን እና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮችንም በተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ ዲፌንስ ያደረጉ ሲሆን አቅራቢዎች በአራት ቡድን ተከፍለው በአራቱ ወንጌላውያን ስያሜ በመሰየም የማቴዎስ ምድብ ፣የማርቆስ ምድብ፣ የሉቃስ ምድብ፣ እና የዮሐንስ ምድብ በመባል ተከፍለው ጥናታቸውን አቅርበዋል።
ልጄ ሆይ፥ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፤ "
                   ሩት 3 : 10


እግዚአብሔር ለምን ወንድ እና ሴት  
     አድርጎ ፈጠረን?
ሴት ማለት?
መንፈሳዊ ሴት ማን ናት? ከእግዚአብሔር
     ጋር የሚኖራት ግኑኝነት
መንፈሳዊት ሴት በእጮኝነት ህይወት 
መንፈሳዊት ሴት በትዳር ህይወት
መንፈሳዊት ሴት በልጅ አስተዳደግ   
     ህይወት
መንፈሳዊት ሴት በማህበራዊ ህይወት ....እና          ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች የምንዳስስበት

      
የእህቶች ጉባኤ


እነሆ ተዘጋጀ!!!


የዚህ ወር ጉባኤያችን:-
👉      እሁድ ሰኔ 7
👉      ከጠዋቱ 3:30
👉      በሰንበት ት/ት ቤቱ ህንፃ


እህቴ ሆይ እህትሽን ይዘሽ ነይ!!!

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን (ቅዱስፍሬምናጦስ)


አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በ245 ዓ.ም በቅድስት ሐገር ኢየሩሳሌም ኅዳር 26 ቀን ተወለዱ።

አቡነ ሰላማ ሲወለዱ ታላቅ ብርሃን ከሰማይ ወርዶ ለ7 ቀናት አብርቷል፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ወደ ምድር ወርደው በመወለዳቸው ታላቅ ደስታን አድርገዋል፡፡

በተወለዱም ጊዜ ‹‹ለአብ ፣ ለወልድ፣  ለመንፈስ ቅዱስ ስግደት ይገባል፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጡኝ ቅድመ ዓለም ለነበሩ ዛሬም ላሉ ዓለምን አሳልፈው ለሚኖሩ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ብለው ዳግመኛም አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ብለው ፈጣሪያቸውን በአንድነት በሦስትነት አመስግነዋል፡፡

ቅዱስ አባታችን አባ ሰላማ በሌላኛው ስማቸው ፍሬምናጦስ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ በ40 ቀናቸው ጌታ በተጠመቀበት በዮርዳኖስ ያጠመቋቸውና ስመ ክርስትና የሰጧቸው ሊቀ ጳጳስ ‹‹ይህ ሕፃን ለኢትዮጵያውን ሁሉ ብርሃን ይሆንላቸዋል›› በማለት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ በሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ አትናቴዎስ በሚገባ ተምረው ካደጉ በኋላ በ257 ዓ.ም ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ስሙ ሜርጵዮስ ከሚባል ከአንድ ነጋዴ ጋር መጡ፡፡ ከእነሱም ጋር አድስዮስ የሚባል ልጅ ነበር፡፡ ወደ ሀገራችንም ሊመጡ የቻሉት መጀመሪያ ለሰባት ወራት በአንድ ሌላ አገር ኖረው ወደ ኢየሩሳሌም ሊመለሱ ሲሉ የበረሃ ሽፍቶች ሜርጵዮስንና ሌሎች መንገደኞችን ገደሏቸውና ሁለቱን ልጆች ማርከው ወስደው ስሙ አልአሜዳ ለሚባል ለአክሱም ንጉሥ ሰጡት፡፡ እርሱም አድስዮስን የቤተክርስቲያን የአልባሳትና የዕቃ ቤት ጠባቂ አድርጎ ሲሾመው ፍሬምናጦስን ደግሞ የቤተክርስቲያንና የሕግ ጠባቂ አደረገው የቤተክርስቲያንን ሥርዓቷንና አገልግሎቷን ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና፡፡

በአክሱምም በተጋድሎና በትጋት ኖረ፡፡ ቅዳሜና እሑድ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ አይቀምስም ነበር፡፡ በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግድ ነበር፡፡ በእርሱም የተጋድሎ ዘመን ደጋግ የሆኑ ነገሥታት አብርሃና አጽብሓ ነገሡ፡፡ እነርሱም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍሬምናጦስን በጣም ይወዱት ነበር፡፡ አንድ ቀን ፍሬምናጦስ የአክሱሙን ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ሚናስን ‹‹ግዝረትና እምነት በእናንተ ዘንድ አለ ነገር ግን ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ መቀበል በእናንተ ዘንድ የለም›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚናስም ‹‹ግዝረትንስ አባቶቻችን ሌዋውያን አመጡ፣ በክርስቶስ ማመንን ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ጃንደረባ አመጣልን፡፡ ስለ ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ ሐዋርያ ወደ እኛ አልተላከም ነገር ግን ያልከውን ሁሉ የሚያደርግልን የሚባርከንና የሚቀድሰን ጳጳስን ታመጣልን ዘንድ ሊቀ ጳጳሱ ወዳለበት ወደ እስክንድሪያ አገር አንተ ሂድ›› አለው፡፡ ጥምቀትስ በጃንደረባው በኩል አገራችን ገብቶ ነበር ነገር ግን ገና ስላልተጠናከረ ብዙ ሕዝብም አልተጠመቀም ነበርና አባታችን ፍሬምናጦስ አጠናክሮ ያልተጠመቀውን ሁሉ አጥምቆአል፡፡

ፍሬምናጦስም ወደ እስክንድሪያ ለመሄድ አስቦ ሳለ እንደተኛ ድንግል ማርያም ተገልጣለት ‹‹ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥቶሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ›› አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ወደ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አትናቴዎስ ሄደህ ከፍ ያችውን ማዕረግ ተቀብለህ የኢትዮጵያን ሰዎች አጥምቅልኝ፣ ነቢዩ ዳዊት ስለ እነርሱ ‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች› ብሎ ተናግሯልና›› አለው፡፡ እርሱም ቅዱሳኑን ነገሥታት አብርሃንና አጽብሓን አግኝቶ ከእነርሱም ጋር ተማክሮ ወደ እስክንድሪያ ሄዶ በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ታኅሳስ 18 ቀን ተሾመ፡፡ ስሙንም ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አለው፡፡ ሰላማ ማለት እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስታርቅ ማለት ነው፡፡ ከሣቴ ብርሃን ማለትም ሃይማኖትን ገልጦ የሚያስተምር ማለት ነው፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም ከሾመው በኋላ ታቦትን በጣም ብዙ ንዋያተ ቅድሳትንና መገልገያ ዕቃዎችን ሰጥቶ መርቆ በሰላም ወደ ኢትዮጵያ ላከው፡፡  አባታችን በ330 ዓ.ም ታኅሣሥ 18 በሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ እጅ ጵጵስና ተሹሟል ፡፡

የአባታችን የአባ ሰላማ በረከት አይለየን አሜን!!