የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.6K subscribers
6.21K photos
67 videos
79 files
1.71K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
እንኳን ለአባቶቻችን ሐዋርያት ጾም (ጾመ ሐዋርያት) በሰላም አደረሰን!

በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምንጾማቸው ሰባቱ አጽዋማት መካከል ዛሬ የጀመርነው የሐዋርያት ጾም አንዱ ነው። ቅዱሳን አባቶቻችን በጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን በበዓለ ሃምሳ ከተቀበሉ በኋላ የአገልግሎታቸው መጀመሪያ ያደረጉት ጾምን ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በ30 ዘመኑ ለአገልግሎት በወጣ ጊዜ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ተጠምቆ በቀጥታ ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ በመጓዝ ጾምና ጸሎትን የአገልግሎት መጀመሪያ እንድናደርገው በተግባር አስተምሮናል። ሐዋርያትም ይህንን መሰረት አድርገው ጾምና ጸሎትን የአገልግሎታቸው መነሻ አደረጉት።

ሐዋርያዊት የሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህንን የሐዋርያት አሰር በመከተል የእነርሱን ጾም በስማቸው ሰይማ እኛም እንድንጾም ታስተምረናለች።

የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከት በሁላችን ላይ ይደር። መልካም የጾም ወቅት ያድርግልን!! አሜን።