https://youtu.be/89NGmkNBgX4?si=ZbCkLomEs6Jq_Vwq
እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ!!!
የበዓለ ጰራቅሊጦስ ዝማሬ
(በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅ/ ሚካኤል ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት)
የስሙ ምስክር
የስሙ ምስክር ያደረጋችሁ
ሐዋርያት ድንቅ ነው ግብራችሁ
ሐዋርያት ተገልጧል ክብራችሁ
ሑሩ ወመሀሩ ተብላችኋልና
እንዲሰማ ቃሉ የመንግሥቱ ዜና
አይታችኋልና የእጆቹን ተአምራት
ሰበካችሁ ለዓለም የመዳንን ብሥራት
መከራ መስቀሉን እንድትታገሱ
በበዓለ ሃምሳ ቃኝቷችሁ መንፈሱ
በአምሳለ እሳት ልሳናት ተከፍተው
አሕዛብ ተመለሱ በወንጌሉ አምነው
በዓለም ተነቦ ፊደል ሕይወታችሁ
በአንድ ቃል በአንድ ሐሳብ ታትሞ ልባችሁ
መሞት መነሣቱን ማረጉን ክርስቶስ
በበዓለ ሃምሳ ተሰብኳል በጴጥሮስ
የወንጌልን መረብ በእምነት ጥላችሁ
ለተጨነቀች ነፍስ ሰላምን ሰብካችሁ
የክርስቲያኖች ቤት በዓለም ተተክላ
ይኸው ታበራለች በክርስቶስ አምና

YouTube
" የስሙ ምስክር " | አዲስ ዝማሬ | ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት መዘምራን #mezemur
የሰንበት ት/ቤታችንን አገልግሎት ለመደገፍ እባክዎን #ሰብስክራይብ_ያድርጉ ያድርጉ ቪድዮውን #ላይክ በማድረግ ይጀምሩ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
Facebook page:- / @fbirhan
Telegram Channel:-https://t.me/finotebirhan12
Website:-https:…

ጰራቅሊጦስ
'' ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ዘሠረጸ እም አብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት''
በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው።
መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ
ጰራቅሊጦስ:- ናዛዚ ፣ መጽንዒ፣ መስተፍሥሒ ፣ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው።
ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ''እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ'' ብሎ ለሐዋርያቱ በሰጣቸው ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ ድንገት እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት መላው የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በሁሉም ላይ አረፉባቸው በዚህ ጊዜ ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በተለያዩ በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎለመሱ፤ ጥቡዓን ሆኑ፣ ፍርሃት ከውስጣቸው ተወግዶ መንፈሳዊ ድፍረት አግኝተዋል፤ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ሰማያዊ ሀብት ዕውቀትና ጸጋን ታድለዋል።
በዚህ ዕለት ሐዋርያት በተገለጠላቸው ቋንቋ ሲያስተምሩ ተቃዋሚ አይሁዳውያን ''ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ'' እያሉ ሐዋርያትን አሟቸው ቅዱስ ጴጥሮስም ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትሉት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ ሰዓቱም ገና ጠዋት ሦስት ሰዓት ነው
ይልቁኑ እናንተ በተንኮል ሰቅላችሁ የገደላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ከክፋታቸው ተመልሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመኑ በዚያች ብቻ ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ተመልሰዋል ዕለቱም የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ይባላል።
ከሶስቱ አካላት አንዱ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ጠብቆት አይለየን የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤታቸው በረከታቸው ይደርብን አሜን።