የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.61K subscribers
6.21K photos
67 videos
79 files
1.71K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" ማቴ 19 ÷6

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም ጋብቻችሁን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸማችሁት የሰንበት ትምህርት ቤታችን የፍኖተ ብርሃን አገልጋይ እህታችን ሣራ ተዘራ  እና ወንድማችን ሱራፌል መዝገበ የአብርሃምን እና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ ጋብቻችሁን ይባርክላችሁ። 

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ከልሎ በፍቅርና በጤና ይጠብቃችሁ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!

    እንኳን ደስ አላችሁ  የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት



ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
https://youtu.be/89NGmkNBgX4?si=ZbCkLomEs6Jq_Vwq

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሳችሁ!!!

የበዓለ ጰራቅሊጦስ  ዝማሬ

(በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅ/ ሚካኤል ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት)

የስሙ ምስክር

የስሙ ምስክር ያደረጋችሁ
ሐዋርያት ድንቅ ነው ግብራችሁ
ሐዋርያት ተገልጧል ክብራችሁ

ሑሩ ወመሀሩ ተብላችኋልና
እንዲሰማ ቃሉ የመንግሥቱ ዜና
አይታችኋልና የእጆቹን ተአምራት
ሰበካችሁ ለዓለም የመዳንን ብሥራት

መከራ መስቀሉን እንድትታገሱ
በበዓለ ሃምሳ ቃኝቷችሁ መንፈሱ
በአምሳለ እሳት ልሳናት ተከፍተው
አሕዛብ ተመለሱ በወንጌሉ አምነው

በዓለም ተነቦ ፊደል ሕይወታችሁ
በአንድ ቃል በአንድ ሐሳብ ታትሞ ልባችሁ
መሞት መነሣቱን ማረጉን ክርስቶስ
በበዓለ ሃምሳ ተሰብኳል በጴጥሮስ

የወንጌልን መረብ በእምነት ጥላችሁ
ለተጨነቀች ነፍስ ሰላምን ሰብካችሁ
የክርስቲያኖች ቤት በዓለም ተተክላ
ይኸው ታበራለች በክርስቶስ አምና
ጰራቅሊጦስ

'' ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ዘሠረጸ እም አብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት''

    በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው።

መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ
ጰራቅሊጦስ:- ናዛዚ ፣ መጽንዒ፣ መስተፍሥሒ ፣ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው።

ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ''እናንተ  ግን  ከላይ ኃይል እስክትለብሱ  ድረስ  በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ'' ብሎ ለሐዋርያቱ በሰጣቸው ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ ድንገት እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት መላው የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በሁሉም ላይ አረፉባቸው በዚህ ጊዜ ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በተለያዩ በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎለመሱ፤ ጥቡዓን ሆኑ፣ ፍርሃት ከውስጣቸው ተወግዶ መንፈሳዊ ድፍረት አግኝተዋል፤  ጽኑዓን ኾነዋል፤ ሰማያዊ ሀብት ዕውቀትና ጸጋን ታድለዋል።

በዚህ ዕለት ሐዋርያት በተገለጠላቸው ቋንቋ ሲያስተምሩ ተቃዋሚ አይሁዳውያን  ''ጉሽ  ጠጅ  ጠጥተው  ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ''  እያሉ ሐዋርያትን አሟቸው ቅዱስ ጴጥሮስም  ሰክረዋል  የምትሉ  እናንተ እንደምትሉት  አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ  ሰዓቱም ገና ጠዋት  ሦስት  ሰዓት  ነው   
ይልቁኑ እናንተ በተንኮል ሰቅላችሁ የገደላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን  በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ከክፋታቸው ተመልሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመኑ በዚያች ብቻ ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ተመልሰዋል ዕለቱም የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ይባላል።
 
ከሶስቱ አካላት አንዱ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ጠብቆት አይለየን የቅዱሳን ሐዋርያት ረድኤታቸው በረከታቸው ይደርብን አሜን።