የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.6K subscribers
6.21K photos
67 videos
79 files
1.71K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
የሰንበት ትምህርት ቤታችን የበጎ አድራጎት ክፍል ባደረገው አገልግሎት ባለፈው ሰንበት

1. ለ250 ነዳያን መርሐግብር የተደረገ ሲሆን በመርሐግብሩ ዝማሬ ፣ትምህርት እና ምገባ ተደርጓል በዚህም ቀን ሁለት በሌላ ቤተ እምነት የነበሩ ወገኖቻችንን ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መመለስ እንፈልጋለን በማለት በራሳቸው ፈቃድ የጠየቁ በመሆኑ ክፍሉክፍሉ  ከንስሐ አባት ጋር አገናኝቷቸዋል ክትትልም እያደረገ ይገኛል ሰዎቹን ማገዝ የሚችል/የሚፈልግ ከታች በተቀመጡት ስልኮች መደወል ይቻላል።

2. ለ25 ነዳያን ለወንዶች ንጽህናቸውን የመጠበቅ እና የልብስ ልገሳ የተከናወነ ሲሆን በተጨማሪ፣ ለ25 ነዳያን ለሴቶች የልብስ ልገሳ ተከናውኗል።

እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይቀበልልን!!

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት በጎ አድራጎት ክፍል

አገልግሎቱን ለመደገፍ

0931 144444
0911 091598
0912 419772

የበጎ አድራጎት ክፍል
ሚካኤል ማለት የስሙ ትርጓሜ “መኑ ከመ አምላክ፥ ማን እንደ እግዚአብሔር” ማለት ነው።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከወርሐዊ በዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ ጥበቃውና አማላጅነቱ አይለየን፡፡ አሜን፡፡

ሰላም ለአዕይንቲከ እለ ኀበ ልዑል ያንቃዐድዋ
ለውሉደ ሰብእ ሣህለ እንዘ ይሴፈዋ
ሚካኤል ቀዋሚ ለደቂቀ ጼዋ
ለምክረ ጸርየ በትንባሌከ ዕልዋ
ምዕቅብና ነፍስየ ወሥጋየ ወሀብኩከ ነዋ


ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ዛሬ በቤተክርስቲያናችን የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና የሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዓመታዊ ክብረ በዓል ሲሆን ቅዱሳንን እና እኛን የሚረዳን የቅዱስ ሚካኤል ወራዊ በዓል ነው በድጋሚ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በዓለ ዕርገት

"ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን"

"አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር
በመለከት ድምጽ ዐረገ"
መዝ 46፡5


ዕርገት ከዘጠኙ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት አንዱ ነው፡፡

ዕርገት ማለት ዐረገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ወደ ላይ መውጣት ፣ ከምድር ከፍ ከፍ ማለት ፣ እስከ ሰማየ ሰማያት መመጠቅ ማለት ነው።

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን
ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
ጰራቅሊጦስ

 ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ  ግን  ከላይ ኃይል እስክትለብሱ  ድረስ  በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ››

ግንቦት 23/2018 ዓ.ም በእለተ ሰንበት በዓለ ጰራቅሊጦስ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበት ቀን በአዲስ አበባ የመንፈስ ቅዱስ በሆነው ደብራችን በታላቅ ድምቀት ይከበራል!!

  አድራሻ:- ከኢሚግሬሽን ወደ ላይ ከፍ ብሎ

- ከቴዎድሮስ አደባባይ ሲመጡ ኤክስትሪም ሆቴል ገባ ብሎ
ዛሬ በሰንበት ትምህርትን ቤታችን ግንቦት 16/2018 ዓ.ም በሚደረገው ምርጫ ላይ የደብራችን አስተዳደር ፣የስብከተ ወንጌል ተወካዮች ፣ የክፍለ ከተማ ሰ/ት/ቤት ተወካዮች፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤቶች ተወካዮች ስለሚመገኙና የሰንበት ት/ቤታችን ደረጃም የሚለካበት በመሆኑ የአባላት ቁጥር መስፈርት አንዱ ስለሆነም በዕለቱ እንድትገኙ ይሁን።

    ማሳሰቢያ :- ጸሎተ ኪዳን የሚደርስ በመሆኑ በጊዜ በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳስባለን!!
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን አምሐ ክፍሉ ወላጅ አባት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ከቀኑ 6:00  የሚፈጸም በመሆኑ በቀብሩ ላይ መገኘት  የምትችሉ ተገኝተን እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው አያት -አራብሳ ሠላም ሰፈር በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የአባታችንን ነፍስ  ይማርልን ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com