የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤” (ሐዋ. 6÷3)

የፍኖተ ብርሃን አባላት ወንድምና እህቶች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሰ/ት/ቤታችንን በአመራርት ቢያገለግሉ መልካም ናቸው ብላችሁ ከምታስቧቸው አባላት ውስጥ በልምድ ከካበቱት: በመካከል እንደ ሰንሰለት ሊያስተሳስሩ ከሚችሉትና ልምድ ቢወስዱ ለወደፊት በመልካም ሥነ ምግባርና አመራራቸው ሰ/ት/ቤታችንን በጥሩ ያገለግላሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን አባላት ትጠቁሙን ዘንድ በአምላከ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን።

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አስመራጭ ኮሚቴ

https://forms.gle/tQbQgAknuDCo79Ee8
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ
———————————————


እሑድ ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም

  ከ5:00- 7:00

ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።

            የባለትዳር ጉባኤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤” (ሐዋ. 6÷3)

የፍኖተ ብርሃን አባላት ወንድምና እህቶች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሰ/ት/ቤታችንን በአመራርት ቢያገለግሉ መልካም ናቸው ብላችሁ ከምታስቧቸው አባላት ውስጥ በልምድ ከካበቱት: በመካከል እንደ ሰንሰለት ሊያስተሳስሩ ከሚችሉትና ልምድ ቢወስዱ ለወደፊት በመልካም ሥነ ምግባርና አመራራቸው ሰ/ት/ቤታችንን በጥሩ ያገለግላሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን አባላት ትጠቁሙን ዘንድ በአምላከ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን።

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አስመራጭ ኮሚቴ

https://forms.gle/tQbQgAknuDCo79Ee8
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

ሐመረ ኖኅ፣ ሰላማዊት ርግብ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ የሲና ሐመልማል (ዕፀ ጳጦስ)፣ ጽላተ ሙሴ፣ የኢያሱ የምስክርነት ሐውልት፣ የኤልያስ የወርቅ መሶብ፣ በትረ አሮን፣ ፀምር ዘጌዴዎን፣ ደብር ነዋኂት ዘዳንኤል (የዳንኤል ረጅም ተራራ)፣ የኖኅ የቃል ኪዳኑ ምልክት (ቀስተ ደመና)፣ ዕፀ ሳቤቅ፣ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት መሰላል፣ የኤልሳዕ ማሰሮ፣ የታጠረች ተክል የታተመች የውኃ ምንጭ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመስቀል ሥር ልዩ ስጦታችን እናታችን እመቤታችን ቅድስት ንጽሕት ድንግል ማርያም በጸሎቷ አማልዳ ከልጇ ከወዳጇ ታስታርቀን። አሜን!!!
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ
———————————————


እሑድ ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም

  ከ5:00- 7:00

ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።

            የባለትዳር ጉባኤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤” (ሐዋ. 6÷3)

የፍኖተ ብርሃን አባላት ወንድምና እህቶች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሰ/ት/ቤታችንን በአመራርት ቢያገለግሉ መልካም ናቸው ብላችሁ ከምታስቧቸው አባላት ውስጥ በልምድ ከካበቱት: በመካከል እንደ ሰንሰለት ሊያስተሳስሩ ከሚችሉትና ልምድ ቢወስዱ ለወደፊት በመልካም ሥነ ምግባርና አመራራቸው ሰ/ት/ቤታችንን በጥሩ ያገለግላሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን አባላት ትጠቁሙን ዘንድ በአምላከ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን።

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አስመራጭ ኮሚቴ

https://forms.gle/tQbQgAknuDCo79Ee8
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ብሩክ ተክለሃይማኖት እናት አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸውን ክፍለ ሐገር ፈጽመው የተመለሱ በመሆኑ መኖሪያ ቤታቸው ጎላ በታችኛው በር ድልድዩ አካባቢ በመገኘት እንዲሁም በ 0965561047 መደወል እንድናጽናናቸው  ይሁን።  የእናታችንን ነፍስ  ይማርልን ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
የ2018 ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ በትላንትናው እለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በጸሎት ተጀመረ።

©EOTC_TV
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ አምላክ አሜን!

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦
ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አደረሰን አደረሳችሁ!
“እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ ኣናኅስዮ ኃጢኣቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሃበነ መልእክተ ሣህሉ፡- እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን ኣይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል ኣኖረ” (2ቆሮ. 5፥19)።
የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሰብእነት ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሓፍ ይነግረናል፤ እሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና ኣንድ ማድረግ ነበረ፤
ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየው ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና ኣምጦ የወለደው በደልና እሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት የገባው ሞት ደግሞ የቅጣቱ ማሳያ ፍርድ ነበረ።
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በፈጸሙት ስሕተት መነሻነት ምድርንና ምድራውያንን ለከባድ ቅጣትና መርገም የዳረገው ይህ መለያየት ለሰማያውያኑም ተርፎኣል፤
ምክንያቱም መለያየቱ በእግዚአብሔርና በሰው፣ በመላእክትና በሰው፣ በሰውና በሰው፣ በነፍስና በሥጋ ጭምር የጥል ግድግዳን ገንብቶ እስከ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መዝለቁን በቅዱስ መጽሓፍ የምናውቀው ስለሆነ ማለት ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!

ቀዳማዊና ዘላለማዊ የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብእናችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም የተገለጸው ሰማያውያንንና ምድራውያንን የለያየው  የጥል ግድግዳን ለማፈራረስ ነው፤
ለመለያየት ምክንያት የሆነችውን ኃጢኣት በሰውነቱ በመቅጣት የሕግን ትእዛዝ ከፈጸመ በኋላ የዕርቁን ተግባር በወሳኝ መልኩ ኣከናውኖታል፤
በክርስቶስ ቤዛነት የሆነው ይህ ዕርቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነበረና እሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ኣስታረቀ፤
ለዚህም ነው ተበዳይ እሱ፣ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እሱ፣ ኣስታራቂ እሱ፣ ታራቂ እሱ ሆኖ የምናገኘው፤ ለሱ የሚሳነው ነገር የለምና ለኛ ግር የሚል ቢመስልም ለሱ ቀላል ነበረ።
በዚህ የዕርቅ ተግባር ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሰውና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ ታርቀው በይፋ ተገናኙ፤ በኅብረትና በኣንድነትም መኖር ቻሉ፤ በቀኙ ለተሰቀለው ሽፍታ “ዛሬውኑ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” የሚለው ቃለ ምሕረትና “ኣባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ ኣደራ እሰጣለሁ” የሚለው ቃለ አማሕፅኖ የዕርቁ፣ የግንኙነቱና የኣንድነቱ ማሳያ ኣስረጅ ናቸው።
ስቅለተ ክርስቶስ ነፍሶቻችን ወደ ግዞት ቤት ሳይሆን ወደ ገነት እንዲገቡ፣ የሚቀበላቸውም ራሱ እግዚአብሔር እንዲሆን ያስቻለ ታላቅ መለኮታዊ ፍጻሜ ነው፤
እኛ “ክርስቶስ መድኃኒታችን ነው፤ አድኖናል” ብለን በልበ ሙሉነት የምንመሰክረው፣ እሱም “ሰላሜን ሰጠኋችሁ” ብሎ የሚያረጋጋን በመሰቀሉ ይህንን ውጤት ስላስገኘልን ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!
የድኅነታችንና የሰላማችን መሠረት የሆኑትን የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ለዓለም ማኅበረ ሰብ የማብሰርና የማሥረጽ ተግባር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቍጥር አንድ ተልእኮ ነው፤
ነገረ ሞቱና ነገረ ትንሣኤው በአስተውሎት፣ በጥልቀትና በተመሥጦ ስናስተምር በውስጡ የምናገኘው የዕርቅ፣ የሰላምና የአንድነት ምስጢር ነው፤
እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን በሚጠበቀው መጠን ተልእኮኣችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ አሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት ኣይኖርም ነበር፤
ችግሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባንችልም በእጅጉ መቀነስና ዓቅሙን ማዳከም እንችል ነበር፤ ነገር ግን ተልእኮኣችንን በኣግባቡ ኣለመወጣት ኣንድ ነገር ሆኖ የዓለሙ መሳሪያ ሆነን መገኘታችን “በዕንቅርት ላይ…” ሆኖ ይስተዋላል።
ይሁንና ኣሁንም ሕዝቡን ወደ ኣንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ዘላቂ የጋራ ጥቅምና ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባኤያችን ዓቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ እነዚህ ካሉ የምናጣውም ሆነ የሚያመልጠን የለምና ነው፤ ሃገርን በኃላፊነት ተረክባችሁ በላዕላዊ፣ በማእከላዊና በታሕታዊ መዋቅር የምትገኙ፣ እንደዚሁም ኣማራጭ ሓሳብ ኣለን ብላችሁ የምትንቀሳቀሱ ልኂቃነ ሃገር ፣ ሁላችሁም እግዚአብሔርን ከሚያውቅ፣ ከሚያመልክና ከሚፈራ ሕዝብ የተገኛችሁ ናችሁና በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ፤ የሱ ገንዘብ በሆኑ ፍጡራንም ኣትጨክኑ፤ ሰውን መያዝ የሚቻለው ኅሊናን በመርታት እንጂ በሌላ ኣይደለምና፣
የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ ኣዳምጡ፤ ሕዝቡ የሚፈልገው በኣንድነትና በእኩልነት መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ፍትሕን ማስፈን፣ ለኑሮው የሚበቃ ምጣኔ ሃብትን ማግኘት፣ የእምነት ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው።
ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው፤ ከተደመጠ ደግሞ እሱም በበኩሉ ያደምጣል፤ ይከተላልም፤
ስለሆነም ለሁሉም ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው ወቅታዊ ጥሪ  ሁሉንም ችግሮቻችን በሰላምና በሰላም ብቻ ለመፍታት ተባበሩ የሚል ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረገው ኣማራጭ ሁሉ ለዘላቂ ሰላማችን አይበጅም እንላለን።

           በመጨረሻም፦
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበስራለን!!!
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
አሜን!!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤

ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ ኣበባ - ኢትዮጵያ
በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት መመረጣቸው ተገለጸ

በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የመግቢያ ንግግር ተጀምሯል።

ጉባኤው በይፋ መጀመሩን ተከትሎ የቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት ለምልዓተ ጉባኤው የቀረበ ሲሆን
በመቀጠልም የሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚወያይባቸውን አጀንዳዎች የሚያቀርብ አርቃቂ ኮሚቴ አባላት ተመረጠዋል።

የኮሚቴ አባላቱም

1. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ (ዶ/ር) ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ሊቀ ጳጳስ
4.ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳስ
5. ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ
6. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ
7.ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጳጳስ መሆናቸው ተገልጿል።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤” (ሐዋ. 6÷3)

የፍኖተ ብርሃን አባላት ወንድምና እህቶች በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሰ/ት/ቤታችንን በአመራርት ቢያገለግሉ መልካም ናቸው ብላችሁ ከምታስቧቸው አባላት ውስጥ በልምድ ከካበቱት: በመካከል እንደ ሰንሰለት ሊያስተሳስሩ ከሚችሉትና ልምድ ቢወስዱ ለወደፊት በመልካም ሥነ ምግባርና አመራራቸው ሰ/ት/ቤታችንን በጥሩ ያገለግላሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን አባላት ትጠቁሙን ዘንድ በአምላከ ሚካኤል ስም እንጠይቃለን።

ጥቆማ መስጠት የሚቻለው እስከ ግንቦት 6/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ በመሆኑ አስቀድማችሁ በአመራርነት ያገለግላሉ ብላችሁ የምታስቧቸውን እንድትጠቁሙ በድጋሚ ለማሳሰብ እንወድዳለን።

ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን!!

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አስመራጭ ኮሚቴ

https://forms.gle/tQbQgAknuDCo79Ee8
ልደታ ለማርያም 

አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በግንቦት አንድ ቀን ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ።  “ወክልኤሆሙ ኄራን ወሥሙራን እሙንቱ ወየሐውሩ በሕገ እግዚአብሔር እስመ እግዚአብሔር ኀረዮሙ ወአፍቀሮሙ ትካት” ይላቸዋል እግዚአብሔርን የሚወድዱ በሕጉ የሚኖሩ ደጋጎችና አምላክም የመረጣቸው ነበሩ።  ልጅ ስላልነበራቸው ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና።

እነርሱም ለዓይናቸው ማረፊያ ለልባቸው ተስፋ የሚሆን እንዲሁም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሃሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

“ከሰው የበለጠች ከመላእክት ኹሉ የከበረች ልጅ ትወልዳላችኊ" ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሐና ነግሯት በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን ነሐሴ ሰባት ተጸነሰች፤ በእናቷ ማሕፀን ሳለችም “መንፈስ ቅዱስ ዐቀባ እምከርሠ እማ” እንዲል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥንተ አብሶ ባመጣው መርገም እንዳትያዝ ጠብቋታል፡፡

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን ወንድ ከሆነ በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ሴትም ብትሆን እግዚአብሔርን  ታገለግል ዘንድ ብጽአት አድርጋ እንደምትሰጥ ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ በግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ(በሊባኖስ ተራራ ስር) ወለደች። ስሟንም ማርያም ብላ ጠራቻት። ጠቢቡ ሰሎሞን አስቀድሞ በመንፈሰ እግዚአብሔር ተቃኝቶ  “መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሓይ” (ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) በማለት እንደ ፀሓይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ ንጽሕናዋና ቅድስናዋ የመልኳ ደም ግባት በነቢያት ትንቢት አስቀድሞ የተጐበኘላት የእውነት ፀሓይ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብርና ደም ግባቷን እንደተናገረ በሊባኖስ ተራራ በግንቦት አንድ በተወለደች ጊዜ ፊቷ በእጅጉ ያበራ ነበር፤ መዐዛዋም ከሽቱ ኹሉ ይበልጥ ነበር፡፡

የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን “ልደታ ለማርያም” በማለት ከጥንት ጀምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በቅዳሴ፣ በማሕሌት ታከብረዋለች። ምክንያቱም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሁላችንም ልደታችን ነውና።
 
እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ልደት (ልደታ ለማርያም)  አደረሳችሁ። የእናታችን ረድኤት በረከት አማላጅነቷ በሁላችንም ላይ ለዘለዓለሙ ጸንቶ ይኑር አሜን።