የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ዕለተ ረቡዕ
የምክር ቀን (ምክረ አይሁድ)

-የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ ምክር የጀመሩበት ቀን ነው።

- መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል። ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ ዕፍረት (ባለ ሽቱዋ ማርያም) ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በፀጕሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው።

- የዕንባ_ቀንም ይባላል። ይህም ስያሜ የተሰጠበት ምክንያት ይህችው ማርያም እንተ ዕፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲልላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፤ በፀጕሯም በዕንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። በፀጕሯም ማበሷ  አክሊሌ_ነህ ስትል ነው።

ይህን ሳምንት ፀሐይ እስክትጠልቅ በመጾም በጸሎት በስግደት የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሳምንት ነው።

መልካም የሕማማት ሳምንት ይሁንልን።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
ሐሙስ

  1.ጸሎተ ሐሙስ ይባላል

ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ  ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።

  2.ሕጽበተ ሐሙስ

ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑ  ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

 3.የምስጢር ቀን ይባላል

ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የሆነው የቅዱስ ቁርባን ምስጢር  በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

4. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል

መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ  የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

 5.የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ  የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

6.አረንጓዴ ሐሙስ ይባላል።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኔ በአረንጓዴው የአትክልት ስፍራ ስለጸለየ አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥነ ስርዓት በደብራችን ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ የደብራችን አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት አዕምሮ ምስጋናው በተገኙበት ተከናወነ ።

እኔ እግርህን ካላጠብኩህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም›› (ዮሐ.፲፫፥፰)

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ
ወአስተዩኒ ብሒአ ለፅምየ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ቅንዋተ መስቀል

1. ሳዶር
2. አላዶር
3. ዳናት
4. አዴራ
5. ሮዳስ
ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል

፩. ፀሐይ ጨለመ
፪. ጨረቃ ደም ኾነ
፫. ከዋክብት ረገፉ
፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ
፭. አለቶች ተፈረካከሱ
፮. መቃብራት ተከፈቱ
፯. ሙታን ተነሡ።
ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

፩. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?

፪. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››

፫. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››

፬.እመቤታችንን ‹‹ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን ‹‹ እነኋት እናትህ›› 

፭. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ››

፮. ‹‹ተጠማሁ››

፯. ‹ሁሉ ተፈጸመ› 
በሰሙነ ሕማማት በስቀለት ማግስት የሚውለው ቅዳሜ ቀዳም ሥዑር በመባል ይጠራል፡፡ በዚህ ዕለት ከድሮው በተለየ መልኩ ጌታችን መድኂታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ አገዛዝና እስራት ነጻ ለማውጣት የተቀበለውን መከራ፣ እንዲሁም ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ማደሩን በማሰብ በጾም ታስቦ ስለሚውል ቀዳም ስዑር ወይም የተሻረው ቅዳሜ ተብሏል፡፡ የማይጾመው ቅዳሜ ስለሚጾም ስዑር /የተሻረ/ ተብሏል፡፡
ቀዳም ሰዑር ሌሎችም ስያሜዎች ያሉት ሲሆን እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ለምለም ቅዳሜ፡–

ካህናቱ ሌሊት ለምእመናን ለምለም ቄጤማ ስለሚያድሉ ዕለቲቱ በዚህ ስያሜ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ ዓዋዲ/ እየመቱ “ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ” የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቄጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡

ቅዱስ ቅዳሜ

ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

©Mk
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሠላም

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ ዲያብሎስን አሰረው፤ አዳምን ነጻ አወጣው፡፡ ሰላም! ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ኾነ፡፡”


ትንሣኤ፡- ትንሣኤ ተንሥአ ተነሣ ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙ መነሣት ማለት ነው፡፡
 «እግዚአብሔር ምከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ÷ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፤» ።መዝ ፸፯፥፷፭።

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ!!

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የሰንበት ትምህርት ቤታችን በጎ አድራጎት ክፍል የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ አቅም ለሌላቸው102 ወገኖች ያደረገው ድጋፍ በዓይነት
-ዶሮ
-ሽንኩርት
-በርበሬ
-ዘይት
-እንቁላል እና
-የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

" ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል። " ምሳ 19 : 17

በጎ አድራጎት ክፍሉን

🔹በገንዘብ
🔹አልባሳት በመስጠትና በተለያዩ የዓይነት ድጋፎች አሁንም ወደፊትም ለመሳተፍ ቢፈልጉ ⤵️⤵️

CBE: 1000658532921
(Tesefaye teshome & mulugeta seman & shewangzaw habte)

ለበለጠ መረጃ:-
+2519-31-14-44-44
+2519-11-09-15-98
+2519-12-48-65-04 ይደውሉልን።
✞የፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት በጎ አድራጎት ክፍል✞