የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
በዓለ ሆሣዕና በደብራችን ጽ/ጽ/ሐ/ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።

ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያና ውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ በገባ ጊዜ ሕዝቡ ሲዘምሩና ሲያመሰግኑ የአይሁድ አለቆች በመቆጣታቸው አመስጋኙ ሕዝብ ዝም ሲሉ ሕጻናቱ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘዉ ''ሆሣዕና በአርያም'' እያሉ  በደስታ ያመሰገኑበት እነዚህ ሕጻናት ዝም ቢሉ እነዚህ አፍ የሌላቸው ድንጋዮች ያመሰግኑኛል ብሎ የተናገረበት  ''እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላዒ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ
ከህፃናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ
የጠላት ዲያቢሎስ ምክሩን ታፈርስበት ዘንድ'' ተብሎ የተነገረበት ታላቁ የሆሣዕና በዓል 
የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አዕምሮ ምስጋናው ፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሰንበት ቤታችን ሕጻናት አባላት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።


ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com