ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው?
Anonymous Poll
5%
ሀ. ያለና የሚኖር
87%
ለ.አሁን አድን አሁን አቅና
5%
ሐ. ማን እንደ እግዚአብሔር
2%
መ.ዘለዓለማዊ
ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና ማለት ቃሉ ሆሼዕና ከሚለው ከዕብራይስጥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ መድኃኒት፣ አቤቱ አሁን አድን ፣አቤቱ አሁን አቅና ማለት ነው፡፡
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ሊቅ በሰየመው የዐቢይ ፆም ሳምንታት ስያሜ ስምንተኛ ሳምንት ሆኖ ተሰይሟል።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱን በማሰብ ዛሬም ድረስ በታላቅ ክብር ቤተክርስቲያን በዓሉን ታከብራለች። ጌታችንም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ያን ጊዜም የታሰረች አህያ ከውርንጭላዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፍቱና አምጡልኝ” አላቸው፡፡
ደቀ መዛሙርቱም እንዴት የሰው ንብረት ዘርፈን እናመጣለን? ብለው ፈሩ ያንጊዜ “ምን ታደርጋላችሁ? የሚላችሁ ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በሉ፤ ያን ጊዜ ይሰዱአችኋል” አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ጌታችን ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡
“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ፤ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡” ትን.ዘካርያስ 9፥9
ተብሎ በነቢያት የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችንም በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በሚገባ ጊዜ ሕዝቡም ልብሶቻቸውን በመንገድ ላይ እያነጠፉ ፤ ዘንባባ ይዘው የዛፎችንም ጫፍ ጫፍ እየቆረጡ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ ያን ጊዜ የሕዝቡና የሕጻናቱ የደስታ ጩኸትና ምስጋና ያስቆጣቸው ፈሪሳዊያን ዝም እንዲያሰኛቸው ጌታችንን ጠየቁት እርሱም መልሶ “እነርሱ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል” ብሎ መለሰላቸው።
''እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላዒ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ
፡ ከህፃናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ
የጠላት ዲቢሎስ ምክሩን ታፈርስበት ዘንድ''
ጌታችን በአህያ ላይ ለምን ተቀመጠ?
• ትህትናን ለማስተማር
• የሰላም ዘመን ነው ሲል
• ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው
“ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’
በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብ እስከ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመስጠት እንዲሁም በአራቱም ማዕዘናት ከአራቱም የወንጌል ክፍል ዕለቱን የሚመለከቱ ምንባባት እየተነበበ በዓሉ ይከበራል፡፡
በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይፈጸም በዚሁ እለት ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

በዓለ ሆሣዕና በደብራችን ጽ/ጽ/ሐ/ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያና ውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ በገባ ጊዜ ሕዝቡ ሲዘምሩና ሲያመሰግኑ የአይሁድ አለቆች በመቆጣታቸው አመስጋኙ ሕዝብ ዝም ሲሉ ሕጻናቱ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘዉ ''ሆሣዕና በአርያም'' እያሉ በደስታ ያመሰገኑበት እነዚህ ሕጻናት ዝም ቢሉ እነዚህ አፍ የሌላቸው ድንጋዮች ያመሰግኑኛል ብሎ የተናገረበት ''እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ በእንተ ጸላዒ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ
ከህፃናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ
የጠላት ዲያቢሎስ ምክሩን ታፈርስበት ዘንድ'' ተብሎ የተነገረበት ታላቁ የሆሣዕና በዓል
የደብራችን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃን አዕምሮ ምስጋናው ፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሰንበት ቤታችን ሕጻናት አባላት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

Telegram
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)