የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
የመጽሐፉ ስም "ሳምራዊቷ ሴት"
የመጽሐፉ አዘጋጅ ✍️ - ኢዮብ በቀለ ዘገነተ ጽጌ
የመጽሐፉ ገጽ - 350
የምዕራፍ ብዛት - 27
የመጽሐፉ ይዘት - በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማርያ ሲካር መንደር በያዕቆብ ጉድጓድ አጠገብ አግኝቶ ቅዱስ ቃሉን አስተምሮ ወደ ድኅነት ያመጣትና ለማኅበረሰቧ መዳን ምክንያት ስለሆነችው የሰማርያዋ ሴት ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ነው፡፡
       መጽሐፉ በውስጡ ጌታችን ሴቲቱን ለማግኘት ከመጣበት ስድስት ሰዓት ጀምሮ ለመንደሯ ሰዎች ምስክር እስከ ምትሆንበት ድረስ  ያለውን የዮሐንስ ወንጌል (ምዕራፍ አራት) ላይ የተጻፈውን ከርሷ ሕይወት ፣ ከሰማርያ ከተማ እና ከሰው ልጅ ድኅነት ጋር በማያያዝ በስፋት ተብራርቶበታል ፡፡ ጌታችንን ካገኘችና በወንጌል ከተጻፈላት ታሪክ በኋላ ስለ ስሞቿ፣ በዘመነ ሐዋርያት ስለነበራት ተጋድሎ ከአምስት እኅቶቿና ከሁለት ልጆቿ ጋር ስለተቀበለችው መከራ እና ስቃይ ፣ በመጨረሻም ስለ ሰማዕትነቷ ተጽፎ የምናገኝበት መጽሐፍ ነው፡፡

የመጽሐፉ ዋና አከፋፋይ - ሰርዲኖን የመጽሐፍ መደብር

   አድራሻ - ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ሕንጻ Ground ላይ
ሆሳዕና በአርያም

ሆሳዕና ማለት ቃሉ ሆሼዕና ከሚለው ከዕብራይስጥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ  መድኃኒት፣ አቤቱ አሁን አድን ፣አቤቱ አሁን አቅና ማለት ነው፡፡

ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ሊቅ በሰየመው የዐቢይ ፆም ሳምንታት ስያሜ  ስምንተኛ ሳምንት ሆኖ ተሰይሟል።

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱን በማሰብ ዛሬም ድረስ በታላቅ ክብር ቤተክርስቲያን በዓሉን ታከብራለች። ጌታችንም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው  “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ያን ጊዜም የታሰረች አህያ ከውርንጭላዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፍቱና አምጡልኝ” አላቸው፡፡

ደቀ መዛሙርቱም እንዴት የሰው ንብረት ዘርፈን  እናመጣለን? ብለው ፈሩ ያንጊዜ  “ምን ታደርጋላችሁ? የሚላችሁ ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በሉ፤ ያን ጊዜ ይሰዱአችኋል” አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ጌታችን ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡

“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ፤ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡” ትን.ዘካርያስ 9፥9
ተብሎ በነቢያት የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችንም በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በሚገባ ጊዜ ሕዝቡም ልብሶቻቸውን በመንገድ ላይ እያነጠፉ ፤ ዘንባባ ይዘው የዛፎችንም ጫፍ ጫፍ እየቆረጡ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ ያን ጊዜ የሕዝቡና የሕጻናቱ የደስታ ጩኸትና ምስጋና ያስቆጣቸው ፈሪሳዊያን ዝም እንዲያሰኛቸው ጌታችንን ጠየቁት እርሱም መልሶ “እነርሱ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል” ብሎ መለሰላቸው።

''እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላዒ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ
፡  ከህፃናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ
የጠላት ዲቢሎስ ምክሩን ታፈርስበት ዘንድ''

    ጌታችን በአህያ ላይ ለምን ተቀመጠ?

• ትህትናን ለማስተማር
• የሰላም ዘመን ነው ሲል
• ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል ነው

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው

“ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’

በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብ እስከ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመስጠት እንዲሁም በአራቱም ማዕዘናት ከአራቱም የወንጌል ክፍል ዕለቱን የሚመለከቱ ምንባባት እየተነበበ በዓሉ ይከበራል፡፡

በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይፈጸም በዚሁ እለት ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር