የሐዘን መግለጫ
የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ተክሌ ወንድም አርፏል። የቀብር ሥነ ስርዓት የሚፈጸመው ዛሬ መጋቢት 23/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 በሰዓሊተ ምሕረት ቤ/ክ በመሆኑ የምትችሉ አባላት በመገኘት ወንድማችንንና ቤተሰቦቻቸውን እንድናጽናናቸው እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።
አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን ።
የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com

Telegram
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
የመጽሐፉ ስም "ሳምራዊቷ ሴት"
የመጽሐፉ አዘጋጅ ✍️ - ኢዮብ በቀለ ዘገነተ ጽጌ
የመጽሐፉ ገጽ - 350
የምዕራፍ ብዛት - 27
የመጽሐፉ ይዘት - በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ አራት ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማርያ ሲካር መንደር በያዕቆብ ጉድጓድ አጠገብ አግኝቶ ቅዱስ ቃሉን አስተምሮ ወደ ድኅነት ያመጣትና ለማኅበረሰቧ መዳን ምክንያት ስለሆነችው የሰማርያዋ ሴት ላይ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ነው፡፡
መጽሐፉ በውስጡ ጌታችን ሴቲቱን ለማግኘት ከመጣበት ስድስት ሰዓት ጀምሮ ለመንደሯ ሰዎች ምስክር እስከ ምትሆንበት ድረስ ያለውን የዮሐንስ ወንጌል (ምዕራፍ አራት) ላይ የተጻፈውን ከርሷ ሕይወት ፣ ከሰማርያ ከተማ እና ከሰው ልጅ ድኅነት ጋር በማያያዝ በስፋት ተብራርቶበታል ፡፡ ጌታችንን ካገኘችና በወንጌል ከተጻፈላት ታሪክ በኋላ ስለ ስሞቿ፣ በዘመነ ሐዋርያት ስለነበራት ተጋድሎ ከአምስት እኅቶቿና ከሁለት ልጆቿ ጋር ስለተቀበለችው መከራ እና ስቃይ ፣ በመጨረሻም ስለ ሰማዕትነቷ ተጽፎ የምናገኝበት መጽሐፍ ነው፡፡
የመጽሐፉ ዋና አከፋፋይ - ሰርዲኖን የመጽሐፍ መደብር
አድራሻ - ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ሕንጻ Ground ላይ

ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው?
Anonymous Poll
5%
ሀ. ያለና የሚኖር
87%
ለ.አሁን አድን አሁን አቅና
5%
ሐ. ማን እንደ እግዚአብሔር
2%
መ.ዘለዓለማዊ
ሆሳዕና በአርያም
ሆሳዕና ማለት ቃሉ ሆሼዕና ከሚለው ከዕብራይስጥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ መድኃኒት፣ አቤቱ አሁን አድን ፣አቤቱ አሁን አቅና ማለት ነው፡፡
ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊው ሊቅ በሰየመው የዐቢይ ፆም ሳምንታት ስያሜ ስምንተኛ ሳምንት ሆኖ ተሰይሟል።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቤተ ፋጌ ወደ ኢየሩሳሌም በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱን በማሰብ ዛሬም ድረስ በታላቅ ክብር ቤተክርስቲያን በዓሉን ታከብራለች። ጌታችንም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ያን ጊዜም የታሰረች አህያ ከውርንጭላዋ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፍቱና አምጡልኝ” አላቸው፡፡
ደቀ መዛሙርቱም እንዴት የሰው ንብረት ዘርፈን እናመጣለን? ብለው ፈሩ ያንጊዜ “ምን ታደርጋላችሁ? የሚላችሁ ቢኖር ጌታቸው ይሻቸዋል በሉ፤ ያን ጊዜ ይሰዱአችኋል” አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ጌታችን ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡
“አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ፤ እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያ በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡” ትን.ዘካርያስ 9፥9
ተብሎ በነቢያት የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችንም በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም በሚገባ ጊዜ ሕዝቡም ልብሶቻቸውን በመንገድ ላይ እያነጠፉ ፤ ዘንባባ ይዘው የዛፎችንም ጫፍ ጫፍ እየቆረጡ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም” እያሉ ይጮሁ ነበር፡፡ ያን ጊዜ የሕዝቡና የሕጻናቱ የደስታ ጩኸትና ምስጋና ያስቆጣቸው ፈሪሳዊያን ዝም እንዲያሰኛቸው ጌታችንን ጠየቁት እርሱም መልሶ “እነርሱ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል” ብሎ መለሰላቸው።
''እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላዒ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ
፡ ከህፃናት አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ
የጠላት ዲቢሎስ ምክሩን ታፈርስበት ዘንድ''
ጌታችን በአህያ ላይ ለምን ተቀመጠ?
• ትህትናን ለማስተማር
• የሰላም ዘመን ነው ሲል
• ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል ነው
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ሕዝቡ ዘንባባ ይዘው
“ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረክ ነው።’’
በማለት ስለተቀበሉት ይህን በማሰብ እስከ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን ዘንባባ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በመስጠት እንዲሁም በአራቱም ማዕዘናት ከአራቱም የወንጌል ክፍል ዕለቱን የሚመለከቱ ምንባባት እየተነበበ በዓሉ ይከበራል፡፡
በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሐት ስለማይፈጸም በዚሁ እለት ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር