የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ለፍኖት መረዳጃ ዕድር አባላት በሙሉ
--------------------------------------------
ነገ እሑድ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:00-7:00 ጠቅላላ ጉባኤ ስላለ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
ገብርኄር

ገብርኄር ማለት ቸር መልካም ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ታማኝ አገልጋይነትን ሲያስተምር

  "ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ ሰጣቸው ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው  ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ መክሊት ሰጠና ወደ ሌላ አገር ሄደ።
      አምስት መክሊት የተቀበለው ሰው ሄዶ ነገደበት ሌላም ተጨማሪ አምስት መክሊት አተረፈ፤  ሁለት መክሊት  የተቀበለውም ሰው ነግዶ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈበት።  አንድ መክሊት  የተቀበለው ሰው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና ከጌታው የተቀበለውን መክሊት ቀበረው።

ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

ጌታውም መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ  ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

ሁለት መክሊት የተቀበለውም ባሪያ ቀርቦ ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

  ጌታውም  መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

አንድ መክሊት የተቀበለው ባሪያ ቀርቦ ጌታ ሆይ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ፈራሁ ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥.....እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
   ይህ መልዕክት ለሰው ልጆች በሙሉ ነው ለሁላችንም እንደየአቅማችን መክሊት ከጌታ ዘንድ ተሰጥቶናል በዚህ በተሰጠን መክሊት መጥተን ወርደን ለፍተን እግዚአብሔርን አገልግለን በተሰጠን ጸጋ ልናተርፍበት ጌታ በመጣ በተጠየቅን ጊዜ ይሄው አገልግሎቴ ያተረፍኩት ብለን የምናቀርበው የምንሰጠውን ዋጋ ይዞ መገኘት ያስፈልጋል።
   ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን በተሰጠን መክሊት አትርፈን ገብርኄር የምንባል ያድርገን።
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ
¯¯ ¯¯ ¯¯ ¯¯¯ ¯¯ ¯¯¯¯ ¯ ¯ ¯ ¯¯¯ ¯¯

እንደ እግዚአብሔር አምላክ መልካም ፈቃድ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ እሑድ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም የሚከናወን በመሆኑ ከ11:30 ጀምሮ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክንን ይጠብቅልን።

     የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
'' የፍቅርና የትህትና ሕይወት ''
     
         

   በመጋቢ ሃይማኖት መ/ር  ኢዮብ ይመኑ

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ቅዳሜ   መጋቢት 19/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com/
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ወይንሸት አሰፋ ወላጅ እናት አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ።  ስለሆነም አባላት በስልክ ቁጥር 0913137171 በመደወል እንድናጽናናቸው ይሁን።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የእናታችንን ነፍስ  በአጸደ ገነት ያሳርፍልን ።

        የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ
¯¯ ¯¯ ¯¯ ¯¯¯ ¯¯ ¯¯¯¯ ¯ ¯ ¯ ¯¯¯ ¯¯

እንደ እግዚአብሔር አምላክ መልካም ፈቃድ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ የፊታችን እሑድ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም የሚከናወን በመሆኑ ከ11:30 ጀምሮ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክንን ይጠብቅልን።

     የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ_አሜን

ለፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤ አባላት በሙሉ!

ሰንበት ት/ቤት የመንፈሳዊ ሕይወት መማሪያ ተቋም ናት!

በሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ብዙዎቻችን ስላደግንባትና ስለተማርንባት፣ #ፍኖተ_ብርሃን ሰንበት ት/ቤታችን የውለታዋን ያህል ባይሆንም ጥቂት መመስከር እንችላለን። በፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የዛሬው ማንነታችን በእምነት፣ በእውቀት፣ በጥበብ፣ በማስተዋል፣ በበረከት...በብዙ ነገር ተቀርጾ በሕይወታችን ላይ ትልቁን አሻራ ያስቀመጠችልን መሆኑን የምንዘነጋው ሀቅ አይደለም። የቅዱስ ሚካኤል ፍቅር በልባችን እንዲሳል፣ የሐዋርያት ረድኤት አብሮን እንዲኖር፣ የቅዱሳንን ቃልኪዳን በሕይወታችን እንድንጠቀምበት፤ በአምላካችን #በመንፈስ_ቅዱስ ሕግ እየተመራን እንድንመላለስ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት የመንፈሳዊ የትምህርት ተቋም ሆና ትልቅ አሻራ በማሳረፍ አገልግላናለች።

ዛሬ ስለ ሰንበት ት/ቤታችን ይህንን ማሳሰቢያ እንድናስተላልፍ ምክንያት የሆነን ነገር፤ አጠቃላይ ቅድስት ቤተክርስቲያንናችንም ሆነች የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት በብዙ ፈተናዎች በተከበቡበት ጊዜ ላይ እንደመገኘታችን መጠን የልጅነታችንን ግዴታ እንደ አቅማችን እንድንወጣ አጭር መልእክት ለማስተላለፍ ነው።

1. የፊታችን እሑድ #መጋቢት_20/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ ለቀጣይ ሦስት ዓመት ሰንበት ት/ቤትን በመሪነት የሚያገለግሉ አመራሮችን ለመምረጥ #የአስመራጭ_ኮሚቴ_ምርጫ ይካሄዳል። በመሆኑም የሩቅ ተመልካች ከመሆን ወጥተን በንቃት ላሳደገችን ሰንበት ት/ቤት አገልግሎትም ሆነ በአጠቃላይ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የድርሻቸውን የሚወጡ አገልጋዮችን የሚመለምሉልንን አስመራጭ ኮሚቴዎችን በመምረጥ እና ራሳችንንም ለዚህ አገልግሎት በማዘጋጀት ብንሳተፍ አንድ ሻማ ለፍኖተ ብርሃን ማዋጣት ይሆናልና፤ የቀድሞ ሥራ አመራር በመሆን በተለያዩ ክፍል ያገለገላችሁ ታላላቅ ወንድምና እሕቶች በጸሎት፣ በሐሳብ፣ በምክር፣ እንዲሁም በማገልገል ብትሳተፉ መልካም ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።

2. የፊታችን እሑድ የሚመረጡት አስመራጭ ኮሚቴዎች በሚሰጡት መመሪያና አካሄድ በንቃት በመሳተፍ የሰንበት ት/ቤታችንን ቀጣይ አመራር በመምረጥ የአገልግሎት ዘመኑ የፍሬ እንዲያደርግልን ሁላችንም የድርሻችንን ለመወጣት ፈቃዳችን ቢሆን መልካም እንደሆነ ለማሳሰብ።

3. ዛሬ የምናደርገው እያንዳንዷ ነገር የነገ ፍሬ መሆኗን አውቀን፣ ድክመትም ይሁን መልካም ጎናችን የሁላችንም ውጤት መሆኑን ተረድተን፤ ለነገ መልካም ፍሬ ዛሬን በጽናት እንድንጠቀምበት በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ስም ለሁላችንም ማሳሰብ እንፈልጋለን።

4. የምርጫ አካሄዳችንን በተመለከተ

በቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ አገልግሎት ምርጫ ዙሪያ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ባወቀ በእኛ ምርጫ ውስጥ እርሱ አምላካችን በጎውን፣ የሚበጀንን አገልጋይ እንዲመርጥልን ስለ ሰንበት ት/ቤታችን በአንድነት በቅንነትና በፍቅር ሆነን የምንወስነው እንጂ፤ በጓሮ ተቧድኖ መጥቶ የምናካሂደው ምርጫ ከዓለማዊ ስጋዊ አስተሳሰብ ስለሚመነጭ በጎ ስራ ከሚያሰራን ከእግዚአብሔር ጋር ሊለያየን ይችላል። ይህም ፍሬ የሌለው ከንቱ የድካም አገልግሎት ውስጥ እንዳይከተን፣ በጸሎት ከቡድንተኝነትና ከመከፋፈል ስሜት የጸዳ የአንድነትና የፍቅር ምርጫ  እንድናደርግ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ይርዳን።

#እግዚአብሔር አምላካችን በጎውን ያጽናልን!
ክፉውን ያርቅልን!
ሰንበት ት/ቤታችንን ይባርክልን!
ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን!

ወስብሐት #ለእግዚአብሔር