የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.08K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
60 የጥቁር አንበሳ ግቢ ገባኤ የሕክምና ተማሪዎች ተመረቁ።

በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ  ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል መንፈሳዊ ተከታታይ ትምህርታቸውን ሲያስተምራቸው የቆዩ የጥቁር አንበሳ ግቢ ገባኤ ተማሪዎችን ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስመርቋል።

በምትሄዱበት፣በምትሠማሩበት  የሥራ መስክ ሁሉ የዳር ተመልካቾች ሳትሆኑ በንቃትና በጥንቃቄ  ቅድስት ቤተክርስቲያንን እና ሀገራችሁን እንዲሁም ያስተማራችሁን ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳንን በቅንነት፣ በታማኝነት እንድታገለግሉ ሲሉ በማኅበሩ የአዲስ አበባ  ማእከል የሕዝብ ግንኙነት ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ኅላፊ አቶ አማረ ምትኩ  ለዕለቱ ተመራቂዎች መልእክታቸውን  አስተላልፈዋል።

በዕለቱ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ፣ ተመራቂ ፣የተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ወ/ሮ ታየች አለሙ ወንድሟ አርፎ ሥርዓተ ቀብሩ በትላንትናው እለት ተፈጽሟል። በመሆኑም መገኘት የምትችሉ አባላት መኖሪያ ቤቱ ለገዳዲ መድኀኔዓለም ቄራ ፊት ለፊት በመገኘት እንዲሁም በ0913257351 በመደወል እንድናጽናናቸው ይሁን።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የወንድማችንን ነፍስ  በአጸደ ገነት ያሳርፍልን ።

        የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ
———————————————

    በእለተ ኒቆዲሞስ


እሑድ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም

  ከ5:00- 7:00

ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።

            የባለትዳር ጉባኤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ
¯¯ ¯¯ ¯¯ ¯¯¯ ¯¯ ¯¯¯¯ ¯ ¯ ¯ ¯¯¯ ¯¯

እንደ እግዚአብሔር አምላክ መልካም ፈቃድ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ እሑድ መጋቢት 20/2018 ዓ.ም የሚከናወን በመሆኑ ከ11:30 ጀምሮ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክንን ይጠብቅልን።

     የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ሰላም እብል ለዘይቀድም ፆታሁ
እምእለ ቅውማን ገጻት ለብሉየ መዋዕል ታሕተ ክነፊሁ፤
ሚካኤል ካህን ለመልእክተ ዲያቆን በአምሳሊሁ ፤
ያትክል ዕድወ ነፍስየ እኂዞ በእዴሁ፤
ከመ ርእዮሙ ካልዓን ይፍርሑ።

ለተልዕኮ በሚፋጠን አገልጋይ አምሳል የነፍሳችንን ጠላት ሰይጣንን ፈጥኖ ያጠፋልን ዘንድ፤ ሌሎችም አይተው ይፈሩ ዘን፤ ዘመን በማይቆጠርለት በአምላክ ፊት ቆመው ከሚያመሰግኑ መላእክት ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሰላም እላለሁ።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሐገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿንና ቅድስት ቤተክርስቲያንን በክንፈ ረድኤትህ ጠብቅልን በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዘው የሚጨነቁትን ማርልን።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የነበረው (ነፍሱን ይማርልን) የወንድማችን ሠይፉ አማረ ወላጅ እናት አርፈዋል ሥርዓተ ቀብራቸው በዛሬው እለት መጋቢት 12/2018 ዓ.ም ክፍለ ሃገር ይፈጸማል ።  በመሆኑም መኖሪያ ቤታቸው ዘርዓይ ደረስ ት/ቤት ገባ ብሎ በመገኘት ቤተሰቦቻቸውን እንድናጽናናቸው ይሁን።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የእናታችንን ነፍስ  በአጸደ ገነት ያሳርፍልን ።

        የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
ለፍኖት መረዳጃ ዕድር አባላት በሙሉ
--------------------------------------------
ነገ እሑድ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም ከቀኑ 5:00-7:00 ጠቅላላ ጉባኤ ስላለ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
ገብርኄር

ገብርኄር ማለት ቸር መልካም ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ታማኝ አገልጋይነትን ሲያስተምር

  "ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ ሰጣቸው ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው  ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ መክሊት ሰጠና ወደ ሌላ አገር ሄደ።
      አምስት መክሊት የተቀበለው ሰው ሄዶ ነገደበት ሌላም ተጨማሪ አምስት መክሊት አተረፈ፤  ሁለት መክሊት  የተቀበለውም ሰው ነግዶ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈበት።  አንድ መክሊት  የተቀበለው ሰው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና ከጌታው የተቀበለውን መክሊት ቀበረው።

ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ጌታ ሆይ፥ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

ጌታውም መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ  ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

ሁለት መክሊት የተቀበለውም ባሪያ ቀርቦ ጌታ ሆይ፥ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ፥ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ።

  ጌታውም  መልካም፥ አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

አንድ መክሊት የተቀበለው ባሪያ ቀርቦ ጌታ ሆይ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ፈራሁ ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ ክፉና ሃኬተኛ ባሪያ፥ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥.....እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አሥር መክሊትም ላለው ስጡት ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
   ይህ መልዕክት ለሰው ልጆች በሙሉ ነው ለሁላችንም እንደየአቅማችን መክሊት ከጌታ ዘንድ ተሰጥቶናል በዚህ በተሰጠን መክሊት መጥተን ወርደን ለፍተን እግዚአብሔርን አገልግለን በተሰጠን ጸጋ ልናተርፍበት ጌታ በመጣ በተጠየቅን ጊዜ ይሄው አገልግሎቴ ያተረፍኩት ብለን የምናቀርበው የምንሰጠውን ዋጋ ይዞ መገኘት ያስፈልጋል።
   ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን በተሰጠን መክሊት አትርፈን ገብርኄር የምንባል ያድርገን።