የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
'' ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ''
     
            ክፍል ሁለት

   በመ/ር ዲ/ን ዳንኤል ታደለ

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ዛሬ  ቅዳሜ  ጥር 23/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  12:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ጥር ሃያ አራት በዚህች ዕለት ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ ጻድቅ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ይከበራል።

ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ብርሃን ዘኢትዮጵያ ተብለዋል፡፡

አባ ተክለሃይማኖት ከበዓታቸው ሳይወጡ በጸሎት ተጠምደው ሌሊትና ቀን ይቆሙ ነበር። ከተጋድሎ የተነሳ ቁመትንም ካበዙ ወዲህ አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግራቸው ሰባት ዓመትን ቆሙ። በዚህ ቀንም ቤተክርስቲያን በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ለስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ታከብራለች።

የጻድቁ አባታችን በረከታቸው ይደርብን!!
የተልዕኮ ተማሪዎች ጉባኤ ተከናወነ የዕለቱ ትምህርት በመ/ር አቤል ካሣሁን የተሰጠ ሲሆን የበገና ዝማሬ ቀርቦ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።
ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡

በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው መሆኑን እንዲነግራቸውና ቸርነትና ምሕረት ወደማያልቅበት  ወደ  እግዚአብሔር  እንዲመለሱ ንስሐ እንዲገቡ እንዲነግራቸው ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው።
ነቢዩ ዮናስ ግን  ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ሰዎችም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ 
ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ 

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል ።

የጾሙ በረከት በሁላችንም ይደር!!
በደብራችን በዛሬው እለት የተጀመረው የነነዌ የሶስት ቀን ጉባኤ በጸሎተ ምሕላ የተጀመረ ሲሆን ትምህርተ ወንጌል በቆሞስ አባ ወልደ ገብርኤል(ፕሮፌሰር) የተሰጠ ሲሆን ያሬዳዊ ዝማሬ በደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ጎልማሶች ማኅበር እና በበኩረ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ ቀርቦ የመጀመሪያ ቀን ጉባኤ ተጠናቅቋል
ነገ ሁለተኛ ቀን ጉባኤ ይቀጥላል