የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ልዩ የባለትዳር አባላት ጉባኤ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
      በየዓመቱ ከጥር እስከ ጥር ያገቡ የሰንበት ት/ቤታችን አባላት መልስ የምንጠራበት ልዩ መርሐግብር እሑድ የካቲት 01/2018ዓ.ም  ሁላችንም ባለትዳር አባላት መልስ የምንጠራቸውን ሙሽሮች በክብር ለመቀበል በእለቱ ሌላ መርሐግብር እንዳትይዙ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳን።

    እሑድ  የካቲት 01/2018 ዓ.ም
        ከረፋዱ 5:30

   እግዚአብሔር ማኅበራችንን ይባርክ


                   የባለትዳር ጉባኤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የሦስት ቀናት ልዩ ጉባኤ እና ጸሎተ ምሕላ

የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በየዓመቱ ልዩ የነነዌ ልዩ ጉባኤና ጸሎተ ምሕላ እንደሚያደርግ ይታወቃል የዚህ ዓመትም ከጥር 25- 27/2018 ዓ.ም ይከናወናል። ስለዚህ ከቀኑ 10:00 ጀምሮ በመገኘት የበረከቱ ተሣታፊ ይሁኑ።
'' ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ''
     
            ክፍል ሁለት

   በመ/ር ዲ/ን ዳንኤል ታደለ

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ዛሬ  ቅዳሜ  ጥር 23/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  12:00 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ጥር ሃያ አራት በዚህች ዕለት ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ ጻድቅ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ይከበራል።

ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ብርሃን ዘኢትዮጵያ ተብለዋል፡፡

አባ ተክለሃይማኖት ከበዓታቸው ሳይወጡ በጸሎት ተጠምደው ሌሊትና ቀን ይቆሙ ነበር። ከተጋድሎ የተነሳ ቁመትንም ካበዙ ወዲህ አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግራቸው ሰባት ዓመትን ቆሙ። በዚህ ቀንም ቤተክርስቲያን በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ የተሰበረበትን (ለስብረተ አፅማቸው) መታሰቢያ ታከብራለች።

የጻድቁ አባታችን በረከታቸው ይደርብን!!
የተልዕኮ ተማሪዎች ጉባኤ ተከናወነ የዕለቱ ትምህርት በመ/ር አቤል ካሣሁን የተሰጠ ሲሆን የበገና ዝማሬ ቀርቦ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል።