የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ምስጋና ዘፍኖተ ብርሃን

የከተራ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ በዓልን በመንፈስቅዱስ መሪና ጠባቂነት በሰላም አክብረን አጠናቀናል !!! ተመስገን ከሁሉ አስቀድሞ ለአምላካችን ለቅዱስ እግዚአብሔር ምስጋና አምልኮ እና ውዳሴ ይድረስው እናታችን ድንግል ማርያም አሳዳጊያችን እና ጠባቂያችን ቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ይድረሳችሁ !!!

የሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
ሕፃናት አባላት  (የሰንበት ት/ቤቱ የነገ ተስፋዎች) ማዕከላውያን አባላት ( የሰንበት ት/ቤቱ ተረካቢዎቻችን) ወጣቶች አባላት  (የሰንበት ት/ቤቱ ጠበቃዎች) የባለ ትዳር ጉባኤ አባላት (የሰንበት ት/ቤቱ ጥላዎቻችን )ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍላት ላይ የተሳተፋችሁ አባላት  የልብሰ ስብሐት እጥረት አጋጥሞን በዝማሬ ያላሳተፍናችሁ  አባላት እንዲሁም  ለእኅት ሰንበት/ት/ቤታችን ለደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ምክሐ ለደናግል ሰንበት ት/ቤት ለደብራችን አገልጋዪች በሙሉ  በጠቅላላ ለልዪ ልዩ የጊቢያችን ማኅበራት ለምንወዳችሁ እና ለምናከብራችሁ ይልቁንም ቤተክርስቲያን በስስት ለምታያችሁ እና ጠበቃዋ ለሆናችሁ በሦስቱም መውጫ በር ላይ ላላችሁ የአጥቢያው ወጣቶች እና ምዕመናን              
* ለደብራችን አገልጋዮች በሙሉ 
* ለልደታ ክፍለ ከተማ  አስተዳደር
* ለልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
* ለወረዳ 07 የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት  በሙሉ ጊዜያችሁን ጉልበታችሁን  ገንዘባችሁን ሳትሰስቱ እና ሳትቆጥቡ ስትሰጡ ለበዓሉ ድምቀት ለሆናችሁ ምዕመናን እና ምዕመናት በሙሉ ዋጋ ከፋይ አስራት ተቀባይ የለመነቱን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸሩ መድኃኔዓለም አምላካችን ዋጋቹሁን ይክፈላችሁ!!! ከዓይን ጥቅሻ ይልቅ ፈጥና የምትደርስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሕይወታችሁ በቤታችሁ ትግባ ስሙ ሲጠራ ልባችን ወከክ እግራችን ሸብረክ የሚለው ጠባቂያችን አሳዳጊያችን  ቅዱስ ሚካኤል ከልጅነታችን እስከ ሽምግልናችን በጥባቆቱ አይለየን ከቁጥር ሳያጎድለን አምና ብለን ለማውጋት ያጎደለውን ለመሙላት ያብቃን!!! እንዲህ ማማራችን እና መዋባችን በእርሷ ነውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቅልን!!! ሀገራችንን ኢትዮጵያን በሰላም እና በፍቅር በአንድነቷ አጽንቶ ያቆይልን የዓመት ሰው ይበለን!!!    ....ነጻ በምታወጣ በኢየሩሳሌም   ከተማ     ከጽዮን ልጆች ጋራ መዝሙራችን እንዲሰማ  አንድ ሆነን በቀኝ እንድንቆም ከበኩራት ከበኩራት ማህበር ጋራ አንድ ሆነን ዛሬ እናገልግል አንድ ሆነን ዛሬ እንስራ                                                  
            ጥር 13/2018 ዓ.ም

   የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ /ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ
         የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
               ጽ/ቤት