የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
በዓለ ኤጲፋንያ


   ‛‛ ያመነ የተጠመቀ ይድናል ፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል’’ ማር. 16፥16

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ለሰው ልጆች አርአያ ሊሆነን ትህትናን ሊያስተምረን በዲያብሎስ ለግዞት የተጻፈውን የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ እና የአንድነት የሦስትነት ምስጢርን ለመግለጥ ተጠመቀ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያውኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀመጠ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት።

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።