የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
🔴 ስንክሳር #ታኅሣሥ_30

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ታኅሣሥ 30 በዚች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ አበ ምኔት የሆነ የከበረ አባት #አባ_ዮሐንስ አረፈ፣ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው የተመሰገነ #የአባ_ዮሐንስ_ብጹዕ አረፈ፣ #ቅዱሳን_ኮርዮንና_ፊልሞና ከእነርሱም ጋር አርባ ወታደሮች በሰማዕትነት ሞቱ፣ ተጋዳይ የሆነ #አባ_ዘካርያስ_ገዳማዊ አረፈ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ዮሐንስ_አበ_ምኔት

ታኅሣሥ ሠላሳ በዚህች ቀን በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ አበ ምኔት የሆነ የከበረ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ።

ይህም አባት በተሾመ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በራች ለብዙ ቅዱሳንም አባት ሆነ ከእርሳቸውም ውስጥ ታላላቅ ከዋክብት የሆኑ አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም የሀገረ ተሙዝ ኤጲስቆጶስ አባ ሚናስ የሀገረ ስሐ አባ ዘካርያስ ለብዙ ሰዎች ነፍሳት ወደብ የሆኑ እነርሱን የመሰሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ። ለሕዝቡ ቅዱስ ቊርባንን በሚያቈርብ ጊዜ ኃጢአተኛውና ጻድቁ ይገለጥለታል ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስንም በመሠዊያው ላይ ብዙ ጊዜ አየው።

በአንዲትም ዕለት ሥራው የከፋ አንዱን ቄስ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር ያሉ ብዙዎች ርኩሳን የረቀቁ አጋንንት ከበውት አፉ ውስጥ ልጓም አድርገዋል ወደ ቤተ ክርስቲያንም ከመግባቱ በፊት የእግዚአብሔር መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ በእሳት ሰይፍ ከእርሱ ከቄሱ መናፍስትን አሳደዳቸው ቄሱም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ መቀደሻውን የክህነት ልብስ ለበሰ ሁለመናውም እንደ እሳት ሆነ ቀድሶም ለሕዝቡ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው።
ልብሰ ተክህኖውንና የመቀደሻውን ሽልማት ከላዩ አውልቆ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜ እንዚያ የጠቆሩ መናፍስት ርኩሳን ተቀብለው እንደቀድሞው አደረጉበት።

አባ ዮሐንስም ይህን ነገር ለመነኰሳቱ ሲያስረዳ እንዲህ አላቸው በቅዳሴ አገልግሎት ጊዜ ለኃጢአተኛውና ለጻድቁ ቄስ ልዩነት የለም ስለ ሕዝቡ እምነት ያ ኅብስት ተለውጦ የክርስቶስን ሥጋ ይሆናልና ወይኑም የከበረ ደሙን ይሆናልና።

ዳግመኛ በምሳሌ እንዲህ አላቸው በብረት በወርቅና በብር ላይ እንደሚቀረጽ እንደ ንጉሥ ማኅተም ነው። ማኅተሙም አይለወጥም እንዲሁ ከካህናትም የክህነት ጸጋ አይለወጥም እርሱ እግዚአብሔር በጊዜው ጊዜ ለሁሉም ለየአንዳንዱ እንደሠራው ይከፈለዋል እንጂ።

ይህንም የከበረ ዮሐንስ ታላቅ መከራ ደርሶበታል አረማውያን በርበር ማረከው ወደ አገራቸወደ ወስደውታልና እያሠቃዩትም በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመን ታሥሮ ኖረ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ገዳሙ መለሰው።

ከመሞቱ በፊት የሚሞትበትን ጊዜ አውቆ መነኰሳቱን ሰበሰባቸውና የወንጌልን ትዕዛዝ ይጠብቁ ዘንድ በሰማያዊ መንግሥት በጎ ዕድልን ርስትንም ከእርሳቸው ጋር ይቀበሉ ዘንድ እንደ ቅዱሳን አባቶች አካሄድ እንዲጓዙ አዘዛቸው።

ከዚህም በኋላ ጥቂት ታመመ ነፍሱን ሊቀበሉ የቅዱሳንን አንድነት ሲመጡ አያቸውና ፈጽሞ ደስ አለው ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ መነኰሳቱ ወደ ከበረች ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወስደው በመዘመርና በታላቅ ምስጋና ገንዘው ቀበሩት እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ከተገነዘበት ልብስ ቆርጠው በእነርሱ ዘንድ አኖሩት ለሚታመም ሁሉ የሚፈውስ ሆነ የዚህም አባት ዕድሜ ዘጠና ዓመት ሆነ በግቢግ የሚልዋት መኖሪያው እስከ ዛሬ አለች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ)
https://t.me/finotebirhan12
ይህ የሰንበት ት/ቤታችን የመዝሙር ክፍል ቴሌግራም ቻናል ነው ይቀላቀሉን መዝሙሮችን፣ ወረቦችን በድምፅና በጽሑፍ ያገኛሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 https://t.me/finotewereb 👈
👉 https://t.me/finotewereb 👈
👉 https://t.me/finotewereb 👈
👉 https://t.me/finotewereb 👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
🔴 ስንክሳር#ጥር_2

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ጥር ሁለት በዚች ቀን ደሙ በግፍ የፈሰሰ #ጻድቁ_አቤል አረፈ፣ የከበረ አባት #ቅዱስ_አላኒቆስ ኤጲስቆጶስ በሰማዕትነት ሞተ፣ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት #ቅዱስ_ቴዎናስ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አቤል_ጻድቅ

ጥር ሁለት በዚች ቀን ደሙ በግፍ የፈሰሰ ጻድቁ አቤል አረፈ እርሱም ወንድሙ ቃየል የገደለው የሙታን በኵር የሆነ ነው።

ምክንያቱም አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ተላልፎ እንዳይበላው የታዘዘውን ዕፅ በላ ያን ጊዜ በእርሱና በልጆቹ ላይ ሞት ሠለጠነ ለኃጢአትም ተገዥ ሆነ። ሰይጣንም ሰውን ለማሳት ሠለጠነ ከዚህም በኋላ አዳም ከገነት ወጥቶ ወደታችኛዋ ምድር ወረደ ስለ በደሉና የፈጣሪውንም ትእዛዝ በመተላለፉ ፈጽሞ እያዘነና እያለቀሰ መቶ ዓመት ኖረ።

ከዚህም በኋላ አዳም ሔዋንን በግብር አወቃት ፀንሳ ቃየልንና እኅቱን ኤልዩድን ወለደች ሁለተኛም ዐወቃት አቤልንና እኅቱን አቅሌማን ወለደቻቸው አዳምም ሔዋንን እነሆ ልጆችሽ አካለ መጠን አደረሱ ጐለመሱ ቃየል የአቤልን እኅት አቅሌማን ያግባት አቤልም የቃየልን እኅት ኤልዩድን ያግባት አለ።

ቃየልም እናቱን ሔዋንን እንዲህ አላት ለእኔ ከእኔ ጋር የተወለደች እኅቴን ማግባት ይገባኛል አቤልም ከእርሱ ጋር የተወለደች እኅቱን ያግባ ቃየል ከእርሷ ጋር የተወለደ ኤልዮድም እናቷ ሔዋንን የምትመስል እጅግ የምታምር መልከ መልካም ናትና።

አዳምም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ ጭንቅ ሆነበት ቃየልንም አብራህ የተወለደች እኅትህን ታገባት ዘንድ አይገባህም አለዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቅርቡና መሥዋዕቱን ለተቀበለው ይሁን አለው።

መሥዋዕትንም በአቀረቡ ጊዜ የአቤልን መሥዋዕት እግዚአብሔር ተቀበለ የቃየልን ግን አልተቀበለም ስለዚህም ቃየል ፈጽሞ አዘነ ሰይጣንም ተገናኘውና ምን ያሳዝንሃል አለው ቃየልም ለወንድሜ ለአቤል እኅቴን እተውለት ዘንድ አባቴ አዘዘኝ አለው። ሰይጣንም ምክርን ከኔ ስማ ወንድምህን ወደ ውኃ ምንጭ ይዘኸው ሒድ ውኃንም ሲጣጣ ራሱን በደንጊያ ምታው በሞተ ጊዜ ሁለቱንም ታገባቸዋለህ የሚከለክልህ ማነው አለው ለቃየልም የሰይጣን ምክር ደስ አሰኘው ልቡም በዝሙት እሳትነት ነደደ ሰይጣን እንዳስተማረውም ወንድሙን አቤልን ገደለው ለሴት ስለ መቅናትም ጻድቁ አቤል በወንድሙ እጅ ሞተ እንዲህም ሞት ወደ ዓለም ገባ።

እግዚአብሔርም ቃየልን ወንድምህ አቤል ወዴት ነው አለው። ቃየልም አላውቅም በውኑ እኔ የአቤል ጠባቂው ነኝን አለው። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው ቃየል ምን አድርገሃል የወንድምህ የአቤል ደም ጩኸት ከምድር ወደኔ ደርሷል። አሁንም በእጅህ የፈሰሰውን የወንድምህን ደም ትጠጣ ዘንድ አፍዋን የከፈተች ምድር የተረገመች ትሁን አንተ ታርሳታለህና በረከቷን ትሰጥህ ዘንድ አትጨምርም በምድር ላይ ፈሪ ተቅበዝባዥ ሁን።

ይህም መርገም ዘሩ በጥፋት ውኃ ከምድር ገጽ እስከ ሚደመሰስ በቃየል ላይ የበዛ ሆነ። የክብር ባለቤት ጌታችንም ጸሐፍት ፈሪሳውያንን ሲዘልፋቸው እንዲህ አላቸው ስለዚህ ነቢያትን ሊቃውንትን ጥበበኞችን ወደናንተ እልካለሁ ከነርሱ የምትገድሉት አለ የምትሰቅሉትም አለ በምኵራባችሁ የምትገርፉት አለ ካንድ አገር ወዳንድ አገር ታሳድዷቸዋላችሁ።

ከጻድቁ ከአቤል ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በዓለም የፈሰሰው የጻድቃን ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርስ ዘንድ።

ጳውሎስም አለ ቃየል ካቀረበው መሥዋዕት ይልቅ አቤል በሃይማኖት ለእግዚአብሔር ያቀረበው መሥዋዕት ተሻለ ስለ እርሱም ደግ እንደሆነ መሰከረለት መሥዋዕቱንም በመቀበሉ ምስክሩ እግዚአብሔር ነው ደግ እንደሆነም ከሞተ በኋላ ተናገረ።

ከዚህም በኋላ አዳም ልጁን በአጣው ጊዜ ወንድምህ አቤል ወዴት አለ ብሎ ቃየልን ጠየቀው ቃየልም በቁጣ አላውቅም እኔ የአቤል ጠባቂው ነውኝን ብሎ መለሰ አዳምም ልጁን ይፈልግ ዘንድ ወደ ዱር ሮጠ በወንዝ ዳርም በድኑን አገኘና አንገቱን አቅፎ ማን ገደለህ አለው ከበድኑም ወንድሜ ቃየል ገደለኝ የሚል ቃል ወጣ። አዳምና ሔዋንም በልጃቸው በአቤል ሞት ሃያ ስምንት ዓመት ያህል ሲያለቅሱ ኖሩ።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ አዳም መጥተው የዓለሙ ሁሉ አባቶች አባት አዳም የምሥራች እነሆ ልጅህ አቤል የገነትን ዛፎች ተሳለመ ነፍሱም እንደ ተወደደ መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር ዐረገች አሉት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
https://t.me/finotebirhan12
🔴 ስንክሳር#ጥር_3

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥር 3በዚች ቀን #የቤተልሔም_ሕፃናት በኄሮድስ ተገደሉ፣ የከበረ አባት #የአባ_ሊባኖስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ኄሮድስ_ያስገደላቸው_ሕፃናት

ጥር ሦስት በዚች ቀን ኄሮድስ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸው ከዚያም በታች የሆኑ በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ ሁሉ ያሉ ሕፃናት ተገደሉ። ቊጥራቸውም ዐሥራ አራት እልፍ ከአራት ሺህ ነው እነርሱም ከሴቶች እንደ ተወለዱ ንጹሐን የሆኑ ናቸው።

በከበረ ወንጌል እንደተነገረ ሰብአ ሰገልም ከሔዱ በኋላ እነሆ ኄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ ተመለስ ብዬ እስከምነግርህም ከዚያ ኑር ብሎ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ነገረው። እርሱም በሌሊት ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብጽ ሔደ ኄሮድስ እስቲሞት ድረስም በዚያ ኖረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ልጄን ከግብጽ ጠራሁት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ።

ከእነዚህ ውስጥ የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስ አንዱ እንደሚሆን ኄሮድስ አስቧልና። ጌታችንም ሥራውን ሁሉ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር ሠራ በረቀቀ ጥበቡም ከኄሮድስ ፊት ሸሸ ኄሮድስ አግኝቶት ሊገድለው ቢአስብ ያለ ጊዜው መግደል ባለተቻለውም ነበርና ሰነፎች ሰዎች ሰው መሆኑን ምትሐት ነው ብለው በአሰቡ ነበር ስለዚህ የክብር ባለቤት ጌታችን ሸሸ ሁለተኛም እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብጽ ይወርዳል ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ዳግመኛም ከክፉ ነገር እንድንሸሽ ለእኛ ሊአስተምረን የግብጽንም ጣዖታት ያጠፋቸው ዘንድ ነው።

ይህን ያህል ብዛት ያላቸውን ሕፃናት መሰብሰብና መግደል ለኄሮድስ እንዴት ተቻለው ተንኰለኛ ኄሮድስ ምክንያት ፈጥሮ የሁለት ዓመትና ከዚያም ያነሱ ሕፃናትን አሳድገን ጭፍራ እንሠራለት ዘንድ የሚያዝ የንጉሠ ነገሥት ቄሣር ደብዳቤ ከእኔ ዘንድ ደርሷል ወርቅ ብር ቀለብ ልብስም እንሰጣለን ብሎ ወደ ሀገሩ ሁሉ ላከ። ስለዚህም ከእናቶቻቸው ጋር ተሰበሰቡ ያን ጊዜ ከእርሱ ዘንድ አንድ ሽህ ሁለት መቶ ወታደሮችን አውጥቶ በተራራ ላይ አረዱአቸው። ነቢይ ኤርምያስም የተናገረው ተፈጸመ ራኄል ስለ ልጆቿ ስታለቅስ ብዙ መከራ ጩኸት ሙሾ ልቅሶ ዋይታ በራማ ተሰማ ልቅሶ መተውን መጽናናትን እምቢ አለች ልጆቿ ልጆችን አልሆኗትምና።

ዮሐንስም በራእዩ እንዲህ አለ በታላቅ ቃል ጮኹ የተመሰገንህ እውነተኛ አቤቱ እስከ መቼ ነው ስለ ደማችን ተበቅለህ በምድር ላይ በሚኖሩ ሰዎች አትፈርድባቸውምን አሉ። ከእነርሱም ወገን ለየአንዳዱ ብሩህ ልብስ ሰጥተው እንግዲህ ጥቂት ቀን ዕረፉ አሉዋቸው። እንደነርሱ ላሉ ለእግዚአብሔር ባለሟሎች እንደነርሱ ይሞቱ ዘንድ ያላቸው ወንድሞቻቸው እስከሚፈጸሙበት ቀን ድረስ እንዲህ የእሊህን ሕፃናት ነፍሳቸውን አይቷልና።

ዳግመኛም እንዲህ አለ በዙፋኑ ፊት በአራቱ እንስሶችና በሃያ አራቱ አለቆች ፊት አዲስ ምስጋና ያመሰግናሉ ከግብጽ ምድር ከተዋጁ ከዐሥራ አራት እልፍ አራት ሽህ ሕፃናት በቀር ያቺን ምስጋና ሊያውቃት የሚቻለው የለም። እነርሱም ከሴቶች እንደ ተወለዱ ንጹሐን የሆኑ ናቸው።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር እና #ከገድላት_አንደበት)
https://t.me/finotebirhan12
🔴 ስንክሳር#ጥር_4

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ሆነ።

ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ ሀገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ከጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ።

ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረሰው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና።

ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብሮኮ ሮስም አጣቢ ሆነ ያቺ ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጉሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ለእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።

ከዚህም በኃላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑንም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ።

ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው አንተስ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት አይዞሽ አትዘኝ አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት።በዚያንም ጊዜ ያ ሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም ወዮልኝ እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን አለች።እርሱም አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።

ከሀገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የሀገሩ ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ።ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን እግዚአብሔር ጠበቃቸው።

የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት።የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል።እርሱም ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው።ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኃላ ከእስያ በዙርያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ እግዙአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው።ይህም የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም።ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለም ሲስ የሙባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው።ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው።

ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው።

ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው ።

የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ።ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጐድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም።እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና።

ሁለተኛም እንዲህ አላቸው እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም።

ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት በሐዋርያ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
https://t.me/finotebirhan12
🌑 ሀዘን ..የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የመምህር ኢዮብ ይመኑ እናት ስላረፉ ቀብር ዛሬ አርብ ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት በሽሮሜዳ ጉስቋም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል ሁላችንም የመምህራችን ሀዘን ተካፋይ እንድንሆን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ለመምህራችን መጽናናቱን ይስጥልን
🔴#ስንክሳር_ጥር 7
በዚች ቀን #በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ ሕንጻ ሰናዖርን ያፈረሱበትና ቅዳሴ ቤታቸው ነው፣ የከበረ አባት የሮሜ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ሶል_ጴጥሮስ አረፈ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ

ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት
ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
https://t.me/finotebirhan12
🔴 ስንክሳር#ጥር_9

#አባ_አብርሃም_ገዳማዊ

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ጥር ዘጠኝ በዚህች ቀን የከበረ አባት አባ አብርሃም ዐረፈ፡፡ የዚህም ቅዱስ ሰው አባቱ ድኆችን የሚወዳቸውና የሚራራላቸው ነው። በዘመኑም በግብጽ አገር ታላቅ ረሀብ ሆነ እጅግ ባለጸጋ ነበርና ከደግነቱና ከታማኝነቱ ብዛት የተነሣ እርሱ በአለበት አገር ዙሪያ ያሉ አገሮች ሁሉም የምድራቸው ፍሬ በእርሱ ዘንድ አደራ ያስቀምጡ ነበር ረሀቡም በጸና ጊዜ በእርሱ ዘንድ በአደራ የተቀመጠውን እህል ሁሉንም ለድኆች ሰጠ እግዚአብሔርም ስለ ምድራቸው ፍሬ ሁሉንም ክፉ ቃልን እንዳይናገሩት አደረጋቸው። በእርሱ ዘንድ ያኖሩትን የምድራቸውን ፍሬ ሽተው ወደርሱ በሚልኩ ጊዜ ተነሥቶ ወደርሳቸው ይሔዳል እነርሱም በየራሳቸው ለያንዳንዱ የምድራቸው ፍሬ እንደደረሳቸው አድርገው ይጽፉለታል እንጂ ምንም ምን አይናገሩትም።

የዚህም ቅዱስ እናት እግዚአብሔርን የምትፈራ ምእመን ናት ሰይጣንም ቀናባት በአንድ ክፉ ሰው ልቡና አድሮ በፋርስ ሰዎች ዘንድ ነገር ሠራባት እነርሱም ማርከው ወደ አገራቸው ወሰድዋት በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየች ያ ነገር የሠራባት ሰው በሲኦል ውስጥ በእሳት ሰንሰለት ታሥሮ "እግዚአብሔር ያደረገልሽን ተመለከትሽን ነገር የሠራብሽን ያንን ሰው ተበቅሎታልና" ይላታል እርሷ ግን "ጌታዬ ሆይ መከራና ሥቃይ በርሱ ላይ እንዲደርስ አልሻም" ትላለች ያ የሚያሳያትም "አንቺ ግን ወደ አገርሽ ተመልሰሽ በቤትሽ ትኖሪ ዘንድ አለሽ" ይላታል እንዲሁም ሆነ።

ባሏም በሞተ ጊዜ አብርሃም ድኃ አደግ ሆነ እርሷም እናቱ ሚስት ልታጋባው አሰበች እርሱ ግን ይህን አልወደደም እናቱም እጅግ ደስ ተሰኘችበት። ወደ ገዳም ሒዶ ሊመነኵስ በፈለገ ጊዜ እናቱ ልትሸኘው ወጣች እጆቿንም ወደ ሰማይ አንሥታ በመጸለይ ልጇን ወደ እግዚአብሔር አደራ አስጠበቀች። "አቤቱ ጌታዬ ይህን ቊርባንን አድርገህ ተቀበለኝ" አለች።

በዚያንም ጊዜ አባ አብርሃም ሔደ በአስቄጥስ በረሀ ውስጥ ተጒዞ በአባ ዮሐንስ አበ ምኔትነት ዘመን ወደ አባ መቃርስ ገዳም ደረሰ ወደርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ገባ ተወዳጅ ልጅንም ሆነለት። በጎ ተጋድሎንም ጀመረ በአንዲት ሌሊትም ራዕይን አየ የበዓቱ ጣሪያ ተሰነጠቀ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጦ ወደርሱ ሲወርድ አየው ኪሩቤልም ያመሰግኑት ነበር እርሱም ፈርቶ ተንቀጠቀጠ ፈጥኖም ሰገደ ጌታችንም ባረከውና በታላቅ ክብር ወደ ሰማይ ዐረገ። ጌታችንም የወረደባት በቤቱ ጣሪያ የተሠነጠቀችው ምልክት ሁና እስከ ዛሬ በመታሰቢያነት አለች እርሷም ለመንፈሳዊ አባቱ ለአበ ምኔቱ አባ ዮሐንስ መኖሪያ ቅርብ ናት እርሷም በግቢግ ትባላለች። የእግዚአብሔርም መልአክ ሁል ጊዜ ይጐበኘዋል ብዙ ምሥጢራትንም ይገልጥለታል ያስገነዝበዋልም።

ከዚህም በኋላ አባ አብርሃም ወደ ደብረ ኀርዮን ሔደ በዚያም አባ ገዐርጊን አግኝቶት ወደ አስቄጥስ ገዳም ከእርሱ ጋር ወሰደውና እስከ ዕረፍታቸው ጊዜ በዚያች በዓት ኖሩ።

አበ ምኔቱ አባ ዮሐንስም በዐረፈ ጊዜ በአባ አብርሃም ላይ ሰይጣን ታላቅ ደዌ አምጥቶበት ዐሥራ ስምንት ዓመት በዚያ ደዌ ውስጥ ኖረ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የጌታችንን ሥጋና ደም ያቀብሉት ዘንድ ወንድሞችን ለመናቸው ከተቀበለም በኋላ መንፈሳዊ አባቱ አባ ዮሐንስ ወደርሱ መጥቶ "እነሆ ወደ ታላቅ ሠርግ እግዚአብሔር ጠርቶሃል" አለው። ከዚህም በኋላ ዕድሜው ሰማንያ ዓመት ሁኖት በሰላም ዐረፈ፡፡ በዓታቸውም እስከ ዛሬ የታወቀች ሁና ትኖራለች።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
https://t.me/finotebirhan12
ነገ የከተራ በዓል ለበዓሉ ተመርጣችሁ ዝማሬ የምታቀርቡ ወጣት፣ ማዕከላውያንና ሕጻናተ አባላቶቻችን ከቀኑ 6:30 የሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ ሁላችንም እንገኝ ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ በግዜ ተነስቶ ወደ ጥምቀተ ባሕሩ በግዜ እንዲደርስ ስለታሰበ ላልሰሙት በማሰማት ከቀኑ 6:30 እንድንገኝ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን
መልካም ዜና ለሰንበት ት/ቤታችን አባላት በሙሉ.... በከተራ ክብረ በዓል ፈሸቶ የተነሳችሁ እንዲሁም በጋራ እና በግል ለመነሳት የምትፈልጉ አባላት በጥምቀትና በቃና ዘገሊላ እለት ፍቶ መነሳት የምትፈልጉ ለ1ፎቶ 10 ብር ብቻ በመክፈል ሶፍት ኮፒ መውሰድ ትችላላችሁ
ጥር 12 እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኝው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው መነሻነት ነው።

የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው። ነገር ግን አባቶቻችን የውሃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል። ይኽም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሳሰር ነው።

በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ይከበራል
#መልካም_በዓል
የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ እንደጻፈው...

ምዕራፍ ፪÷፩-፲፩


በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤


ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።


የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፦ የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።


ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።


እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።


አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።


ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።


አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።


አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦


ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።

፲፩
ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።