ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ
እንኳን ለበዓለ ሥላሴ በሰላም አደረሳችሁ እያልን የጥምቀት በዓል የደረሰ በመሆኑ አገልግሎታችንን እግዚአብሔር ይቀበልልን ዘንድ በዓሉም የሰላም በዓል እንዲሆንልን አስቀድመን ከዛሬ ሐሙስ ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት የጸሎት መርሐግብር ስለሚኖረን በጸሎቱ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን።
የመዝሙር አገልግሎት እና የዜማ
ትምህርቶች ሥልጠና ክፍል

ለሰ/ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
በተለያዩ ጊዜያት ለአገልግሎት ልብሰ ስብሐት ወስዳችሁ ነገር ግን ለመመለስ ያልቻላችሁ አባላት አሁን ለአገልግሎቱ እጥረት ስላጋጠመን በየቤታችሁ ያለ ያልመለሳችሁትን ልብሰ ስብሐት እንድትመልሱ በትህትና እንጠይቃለን!!
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን
የሒሳብና ንብረት አስተዳደር

💧✨💧✨💧✨💧✨💧✨💧
እንኳን አደረሳችሁ
💧✨💧በዓለ ኤጲፋንያ 💧✨💧
ለሰንበት ት/ቤታችን የጥምቀት ዘማርያን እና አገልጋዮች በሙሉ
የጥምቀት በዓል ላይ ከጥምቀት ዘማርያን ምን ይጠበቃል?
ቅድመ በዓል
👉 በተነጋገርንው መሠረት ጸጉር መስተካከል፤ ጥፍር መቆረጥ፤ የእጅና የጆሮ ጌጥ አለማድረግ፤ ከህክምና መነጽር ወጪ የዓይን እና ሌሎች ማስዋቢያዎችን አለመጠቀም የግል ንጽህናን መጠበቅ (ሰውነትን መታጠብ)፤ ከውኃ ውጭ አለመጠጣት! የሚረብሸንን ምግብ አለመመገብ
👉ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አለባበስ መልበስ
👉አግባብነት ያለው የሚመች ጫማ መጫማት
👉ልብሰ ስብሐቱ ካጠረን ከረዘመው ጋር ከረዘመን ካጠረው ጋር መቀያየር
👉ልብሰ ስብሐቱን ከመልበሳችን በፊት ጸሎት ማድረግ
👉የእኛን ልብሰ ስብሐት ለሌላ ሰው ሰጥተን ማዘመር አይቻልም። መዘመር ካልቻልን ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ እና መመለስ ይገባል።
ጊዜ በዓል
👉በሥርዓት ሆኖ መዘመር
👉ያለ አስተባባሪው ፈቃድ በዝማሬ የጀመሩበትን ቦታ አለመቀየር እና አቋርጦ አለመውጣት
👉 የተለየ ድካም የህመም ስሜት ሲኖር ለአስተባባሪዎች መንገር 👉 ከአስተባባሪዎች የሚሰጠንን መመሪያ መቀበል
ድኅረ በዓል
👉መንገድ ላይ እየተራመዱ ልብሰ ስብሐት ማውለቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
👉 ጸበል ጸዲቅ ከተዘጋጀበት ቦታ ምግብ ከበላን በኋላ ንግግራችንን መጠን አድርገን፣ ያለ ግርግር በረከታችንን ወደ ቤታችን ይዘን መሔድ ይገባናል።
👉ከዝማሬ በኋላ ልብሰ ስብሐት ይዞ አላስፈላጊ ቦታ መገኘት ፣ ግጭት ውስጥ መግባት ፣ ያልተገባ ንግግር መናገር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
👉ስንቀመጥም፣ ስንነሳም፣ ስንሄድም፣ ስናስቀምጥም ልብሰ ስብሐቱን በተቻለን አቅም እናክብረው።
👉 በከተራ ጥምቀት እና በቃና ዘገሊላ ዕለት ልብሰ ስብሐቱን ለብሶ ካፌ እና ልዩ ልዩ ቦታዎች መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው !!!
👉 በማንኛውም የአገልግሎት ጉዳይ ላይ የስራ አመራር አባላትን እና ጽ/ቤቱን ማናገር ይቻላል
ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ ስንት ሰዓት ይንቀሳቀሳል?
ጥር 10፦ በዓለ ከተራ 7:00 ሰዓት ስለሚወጣ 6:00 ሰዓት በደብራችን እንገኝ።
ጥር 11፦ 4:00 ሰዓት ስለሚወጣ 3:00 ሰዓት ታቦት ማደሪያ እንገኝ።
ጥር 12፦ 4:00 ሰዓት ስለሚወጣ 3:00 ሰዓት ታቦት ማደሪያ እንድንገኝ ይሁን ።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት አንድነት የእናታችን የቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ምልጃ የአሳዳጊያችን የቅዱስ ሚካኤል ጥባቆት የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ምልጃ እና ጸሎት ከዅላችን ጋራ ይኹን አገልግሎታችንን አምላከ ቅዱሳን ይቀበልልን የበረከት በዓል ያድርግልን በዓሉን በሰላም ያስፈጽመን አሜን!!!
የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጽህፈት ቤት

በዓለ ከተራ
ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
መልካም የከተራ በዓል

የከተራ 2018 ዓ.ም በዓል በሰላም ተከብሮ ዋለ