የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.59K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው              የወንድማችን የዲ/ን ቸርነት ድንቁ ወላጅ አባት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ታኅሣሥ 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ቀጨኔ መድኀኔዓለም ቤ/ክ የሚፈጸም በመሆኑ መገኘት የምትችሉ አባላት በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ጎላ በላይኛው በር መግቢያ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የአባታችንን ነፍስ  ይማርልን ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ለሰ/ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

በተለያዩ ጊዜያት ለአገልግሎት ልብሰ ስብሐት ወስዳችሁ ነገር ግን ለመመለስ ያልቻላችሁ አባላት አሁን ለአገልግሎቱ እጥረት እንዳያጋጥመን በየቤታችሁ ያለ ያልመለሳችሁትን ልብሰ ስብሐት እንድትመልሱ በትህትና እንጠይቃለን!!

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን


የሒሳብና ንብረት አስተዳደር
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ

ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ሆነ።

ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ ሀገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ከጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ።

ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረሰው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና።

ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብሮኮ ሮስም አጣቢ ሆነ ያቺ ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጉሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ለእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።

ከዚህም በኃላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑንም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ።

ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው አንተስ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት አይዞሽ አትዘኝ አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት። በዚያንም ጊዜ ያ ሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም ወዮልኝ እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን አለች። እርሱም አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።

ከሀገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የሀገሩ ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ። ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን እግዚአብሔር ጠበቃቸው።

የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት። የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል። እርሱም ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኃላ ከእስያ በዙርያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ እግዙአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው።ይህም የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም። ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለም ሲስ የሙባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው።ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው።

ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው።

ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው ።

የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ።ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጉድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና።

ሁለተኛም እንዲህ አላቸው እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም።

ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የቅዱስ ዩሐንስ ረድኤት በረከት አይለየን!!
እንኳን ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

ሁላችንም እንደምናውቀው  የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በቃና ዘገሊላ እለት የሰ/ት/ቤታችን ባለትዳር ጉባኤ ክፍል  በየዓመቱ የምሳ ዝግጅት ለአገልጋዮች እንደሚያደርግ ይታወቃል ።
ስለዚህ እርስዎም ከእዚህ ታላቅ በረከት ለመሳተፍ አቅምዎ የፈቀደውን በገንዘብ ፣ በማቴርያል ..... በማንኛውም ነገር  ለዝግጅት ክፍሉ እገዛ (ድጋፍ ) እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
   ለሚደረገው ማንኛውም እገዛ ( ድጋፍ ) የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ ።🙏🙏🙏

         የፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት
           የባለ ትዳር ጉባኤ ንዑስ ክፍል   
                    
                             
በገንዘብ ፣ በማቴሪያል እንዲሁም በተለያየ ነገሮች መርዳት (ማገዝ ) ለምትፈልጉ
09 11 14 76 34  አቶ እስጢፋኖስ ብርሃኑ 
 09 11 36 74 46  ወ/ሮ ቀለሟ ባደግ በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ ።

 
"ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።" ማቴ 19 ÷6

በትላንትናው እለት ጥር 03 /2018ዓ.ም ጋብቻችሁን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸማችሁት የሰንበት ትምህርት ቤታችን የፍኖተ ብርሃን አገልጋዮች ወንድማችን ይድነቃቸው እና እህታችን ትዕግሥት የአብርሃምን እና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ ጋብቻችሁን ይባርክላችሁ። 

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፉ ከልሎ በፍቅርና በጤና ይጠብቃችሁ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!

     እንኳን ደስ አላችሁ  ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት



ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት በሙሉ

እንኳን ለበዓለ ሥላሴ በሰላም አደረሳችሁ እያልን የጥምቀት በዓል የደረሰ በመሆኑ አገልግሎታችንን እግዚአብሔር ይቀበልልን ዘንድ በዓሉም የሰላም በዓል እንዲሆንልን አስቀድመን ከዛሬ ሐሙስ ጥር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት የጸሎት መርሐግብር ስለሚኖረን በጸሎቱ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን።

        የመዝሙር አገልግሎት እና የዜማ 
          ትምህርቶች ሥልጠና ክፍል
                  
ለሰ/ት/ቤታችን አባላት በሙሉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

በተለያዩ ጊዜያት ለአገልግሎት ልብሰ ስብሐት ወስዳችሁ ነገር ግን ለመመለስ ያልቻላችሁ አባላት አሁን ለአገልግሎቱ እጥረት ስላጋጠመን በየቤታችሁ ያለ ያልመለሳችሁትን ልብሰ ስብሐት እንድትመልሱ በትህትና እንጠይቃለን!!


ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን

 
        የሒሳብና ንብረት አስተዳደር
💧💧💧💧💧💧

           እንኳን አደረሳችሁ

💧💧በዓለ ኤጲፋንያ 💧💧

ለሰንበት ት/ቤታችን የጥምቀት ዘማርያን እና አገልጋዮች በሙሉ

የጥምቀት በዓል ላይ ከጥምቀት ዘማርያን ምን ይጠበቃል?


ቅድመ በዓል

👉 በተነጋገርንው  መሠረት ጸጉር መስተካከል፤ ጥፍር መቆረጥ፤ የእጅና የጆሮ ጌጥ አለማድረግ፤ ከህክምና መነጽር ወጪ የዓይን እና ሌሎች  ማስዋቢያዎችን አለመጠቀም የግል ንጽህናን መጠበቅ (ሰውነትን መታጠብ)፤ ከውኃ ውጭ አለመጠጣት! የሚረብሸንን ምግብ አለመመገብ

👉ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አለባበስ መልበስ
👉አግባብነት ያለው የሚመች ጫማ መጫማት
👉ልብሰ ስብሐቱ ካጠረን ከረዘመው ጋር ከረዘመን ካጠረው ጋር መቀያየር
👉ልብሰ ስብሐቱን ከመልበሳችን በፊት  ጸሎት ማድረግ
👉የእኛን ልብሰ ስብሐት ለሌላ ሰው ሰጥተን ማዘመር አይቻልም። መዘመር ካልቻልን ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቅ እና መመለስ ይገባል።

ጊዜ በዓል

👉በሥርዓት ሆኖ መዘመር
👉ያለ አስተባባሪው ፈቃድ በዝማሬ የጀመሩበትን ቦታ አለመቀየር እና አቋርጦ አለመውጣት

👉  የተለየ ድካም የህመም ስሜት ሲኖር ለአስተባባሪዎች መንገር                           👉 ከአስተባባሪዎች የሚሰጠንን መመሪያ መቀበል

ድኅረ በዓል

👉መንገድ ላይ እየተራመዱ ልብሰ ስብሐት ማውለቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

👉 ጸበል ጸዲቅ ከተዘጋጀበት ቦታ ምግብ ከበላን በኋላ ንግግራችንን መጠን አድርገን፣  ያለ ግርግር  በረከታችንን ወደ ቤታችን ይዘን መሔድ ይገባናል።

👉ከዝማሬ በኋላ ልብሰ ስብሐት ይዞ አላስፈላጊ ቦታ መገኘት ፣ ግጭት ውስጥ መግባት ፣ ያልተገባ ንግግር መናገር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

👉ስንቀመጥም፣ ስንነሳም፣ ስንሄድም፣ ስናስቀምጥም ልብሰ ስብሐቱን በተቻለን አቅም እናክብረው።

👉 በከተራ ጥምቀት እና በቃና ዘገሊላ ዕለት ልብሰ ስብሐቱን ለብሶ ካፌ እና ልዩ ልዩ ቦታዎች መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው !!!     

👉 በማንኛውም የአገልግሎት ጉዳይ ላይ የስራ አመራር አባላትን እና ጽ/ቤቱን ማናገር ይቻላል

ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ ስንት ሰዓት ይንቀሳቀሳል?

ጥር 10፦ በዓለ ከተራ  7:00 ሰዓት ስለሚወጣ 6:00 ሰዓት በደብራችን እንገኝ።

ጥር 11፦ 4:00 ሰዓት ስለሚወጣ 3:00 ሰዓት ታቦት ማደሪያ እንገኝ።

ጥር 12፦ 4:00 ሰዓት ስለሚወጣ 3:00 ሰዓት ታቦት ማደሪያ እንድንገኝ ይሁን ። 

የጌታችን  የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት አንድነት  የእናታችን የቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ምልጃ የአሳዳጊያችን የቅዱስ ሚካኤል ጥባቆት የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ምልጃ እና ጸሎት ከዅላችን ጋራ ይኹን አገልግሎታችንን አምላከ ቅዱሳን ይቀበልልን የበረከት በዓል ያድርግልን በዓሉን በሰላም ያስፈጽመን አሜን!!!               

    የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጽህፈት ቤት  
በዓለ ከተራ

ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል