የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.11K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።” መዝሙር 22፥4
በጋራ መታሰቢያቸውን ለማድረግ የተዘጋጀ ዝክረ ካህናት ወአባላት ልዩ ጉባኤ ይታደሙ አበረዋችሁ ያገለገሉትን አባላትና የምታውቋቸውን አባቶች ፎቶ ይላኩልን በዕለቱም በጉባኤው ይታደሙ
አቡነ ተክለሃይማኖት    

ታኅሣሥ ሃያ አራት በዚህች ዕለት ጌታችን በቃሉ ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደታቸው ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን ነው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ለአባታችን ተገልጦ ከዚህ በኋላ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው›› አላቸው፡፡

ጻድቁ ተክለሃይማኖት ፈጣሪያቸውን ለማገልገል ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ›› ብለው ቤታቸውን እንደተከፈተ ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል።

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት በረከት አይለየን!!
“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።” መዝሙር 22፥4
በጋራ መታሰቢያቸውን ለማድረግ የተዘጋጀ ዝክረ ካህናት ወአባላት ልዩ ጉባኤ ይታደሙ አበረዋችሁ ያገለገሉትን አባላትና የምታውቋቸውን አባቶች ፎቶ ይላኩልን በዕለቱም በጉባኤው ይታደሙ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ

  ''መንፈሳዊና ሕይወትና የጠባይ ለውጥ''

ክፍል ሁለት

እሑድ ታኅሣሥ 26/2018 ዓ.ም

  ከ5:00- 7:00

ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።

            የባለትዳር ጉባኤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!


"ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ ለዘተወልደ እምቅድስት ድንግል ርእይዎ ኖሎት አእኰትዎ መላእክት፤
እነሆ ዛሬ ሰማያዊውን በበረት የተኛውንና ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት።"

 
እነሆ አራቱም ክፍላት
   📌ሕፃናት ክፍል
   📌ማዕከላውያን ክፍል
   📌ወጣት ክፍል
   📌ባለ ትዳር ክፍል የሚገኙበት
      
ልዩ የዝማሬ ቀን
በልደተ ክርስቶስ
ታኅሣሥ 29/2018 ዓ.ም



ቦታ፦ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ
ሰዓት፦ ከ 10-12 ሰዓት


ይህንን የመዳኛችን መጀመሪያ ቀን ሁላችንም በበዓሉ ቀን በቤተክርስትያን በመገኘት አምላካችንን በማመስገን እናክብረው።

ሲመጡ 2 ጧፍ አንዱ መባዐችን ይሆንና ሌላኛውን እናበራው ዘንድ ይዛችሁ ተገኙ።

ማስታወሻ፦ ከርቀት ቦታ የሚመጡ አባላት ስለሚኖሩና ሲመለሱ ትራንስፖርት ሊቸገሩ ስለሚችሉ በተባለው ሰዓት እንጀምር ዘንድ ሰዓት አክብረን እንምጣ።

     የመዝሙር አገልግሎት እና የዜማ     
          ትምህርቶች ሥልጠና ክፍል
እንኳን አደረሳችሁ ነገ በበዓለ ልደቱ ታኅሣሥ 29 ከቀኑ 10:00-12:00 ድረስ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ ልዩ የዝማሬ ቀን አይቀርም!!
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ  ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመት ምሕረት፤

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!


+  በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
+  ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
+  የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
+  በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
+  እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣

እኛ በሕይወት እንኖር ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም የላከ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓስራ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ልደቱ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

“ወበዝንቱ ተዓውቀ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር ላዕሌነ እስመ ለወልዱ ዋሕድ ፈነዎ ውስተ ዓለም ከመ ንሕየው በእንቲኣሁ፤ ወዝንቱ ውእቱ ፍቅሩ ለእግዚአብሔር፡- የእግዚአብሔር ፍቅሩ በእኛ ዘንድ ተገለጠ፤ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነው፤ (፩ዮሓ. ፬፥፱)

በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው እኛ ምሥራቃውያን ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት የምናከብረው በዓል፣ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ነው፤ በዓለ ልደት የእግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ለሰው ልጆች ሁሉ የታወጀበት ዕለት ነው፤ በዚህ ዕለት የሆነው የእግዚአብሔር ፍቅርና ሰላም ቃላዊ ወይም ተምኔታዊ ኣልነበረም፤ ወይም ደግሞ በርቀት በመልእክት የተላለፈ ኣልነበረም፤
ከዚህ ይልቅ ሰብእናችንን በመዋሐድ፣ በተግባር ሆኖ በመገኘት፣ እንዲሁም ለመሰጠት ዝግጁ በመሆን የተገለጠና የታየ ሰላምና ፍቅር ነው፤ እግዚአብሔር የኛን ሰላምና ፍቅር በእጅጉ የሚሻው መሆኑን ለመረዳት፣ የኛን ሰብአዊ ክዋኔ በምልአት ተዋሕዶ በመካከላችን ከመገኘት የተሻለ ሌላ ማረጋገጫ ሊኖር ኣይችልም፤ እኛ ሰዎች ለእግዚአብሔር ጠላቶቹ ተብለን በቅዱስ መጽሐፍ የተገለጽን ነን:: እግዚአብሔር ጠላቶቹን የራሱ አካል አደረጋቸው ሲባል ከመስማት የበለጠ አስደናቂ ነገር በዚህ ዓለም ምን ሊኖር ይችላል?

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እግዚአብሔር ሰብኣዊነታችንን በምልአት ተዋሕዶ በዓለማችን እንዲገለጥ የሆነበት ዋና ምክንያት እሱ እንዳስረዳን እኛ በሕይወት እንድንኖር ነው፤ ይህንንም ያደረገው ከሁሉ በላይ የሆነ ሌላ ገፊ ኃይል ገፋፍቶት ሳይሆን ድንበር የለሽና ፍጹም ፍቅሩ አነሣሥቶት እንደሆነ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንረዳለን፤ የእግዚአብሔር ፍቅር እኛ ከምናውቀው ፍቅር ሁሉ በላይ መሆኑንም በዚህ እናስተውላለን፤ ለጠላቶቹ ሕይወት ፍቅርና ሰላም ሲል እነሱን ከመሆን አልፎ እስከ ቤዛዊ መሥዋዕት የሚዘልቅ ፍቅር እጅግ በጣም ታላቅ ነው፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፈቃድ እኛ በሕይወት በሰላምና በፍቅር እንድንኖርለት ከሆነ የእኛ ግብረ መልስም ከዚህ የተለየ ሊሆን ኣይገባም፤ እግዚአብሔር ጠላቶቹን ለማዳን እንጂ ለማጥፋት አልመጣም፤ የእኛም ሕይወት የሚጠበቀው ኣንዱ ሌላውን በማዳን እንጂ በማጥፋት እንዳልሆነ ጌታችን በቃልም በተግባርም በአጽንዖት ነግሮናል፤ በዚህ አስተሳሰብና እምነት እንድንኖርም አዞናል፡፡
ታድያ በቃሉ ለመኖርና ለእሱ ለመታዘዝ ቃል የገባን እኛ ክርስቲያኖች ይህን ሁሉ እርግፍ ኣድርገን በመተው እርስ በእርስ ለመጠፋፋት መሽቀዳደም ምን ይሉታል? ይህስ ለማን ይበጃል?
የአንድ ሀገር ሕዝቦች ይመካከራሉ፣ ይቻቻላሉ፣ ይታገሣሉ፣ ጊዜ ሰጥተው ያስቡና መፍትሔ ያበጃሉ እንጂ ማን በማን ላይ ይነሣል? ይህ ለማንኛችንም አይበጀንምና ወደ ኣእምሮኣችን እንመለስ የሚል ጥሪ የወቅቱ የቤተ ክርስቲያናችን መልእክት ነው፤

በመጨረሻም፤

ይህንን የተቀደሰ በዓል ስለ ሃገራችን ዘላቂ ሰላም በመጸለይና በማሰብ እንዲሁም በልዩ ልዩ  ምክንያት የምግብ፣ የልብስና የመጠለያ እጥረት ያጋጠማቸው ወገኖቻችንን በመደገፍና በመርዳት ለእግዚአብሔር ክብር ብለን ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ፍጹም ሰላም መስፈን ከልብ በመነሣሣት በዓሉን እንድናከብር አባታዊ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን!!

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን!!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የዓለም መድኃኒት ዛሬ ተወለደ

   
     ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት፤ ወአብ በዲበ ምድር፣ በሰማይ ያለእናት ከአብ መወለዱን፣ በምድርም ያለ አባት ከድንግል ማርያም መወለዱን እናምናለን።
      
ቤዛ ኵሉ ዓለም ዮም ተወልደ  (ለዓለም ቤዛ  የሆነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ተወለደልን) የጌታችን መወለድ ለዓለም ሁሉ ደስታ ነው ምክንያቱም ጌታ የሚወለደው በዲያብሎስ ባርነት ይኖር የነበረውን የአዳምን ዘር ዓለምን ሁሉ ለማዳን ነውና ተለያይተው የነበሩ ሰውና መላእክትን ሕዝብና አህዛብን አንድ ለማድረግ ለአዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ ብሎ በገባለት ቃልኪዳን መሰረት በእመቤታችን ማኅጸን አደረ የሰውን ልጅ ለማዳን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ።  ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስም በወንጌሉ ላይ እንዲህ አሰፈረው

''በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው ፤ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ ፤ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ ፤ መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ ፤ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ  ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ'' ሉቃ.  2፥6
ነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ በትንቢት መነጽር ተመልክቶ እንዲህ ብሎ ነበር

" ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።"  ትን. ኢሳ.7፥14

 እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!!


     የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት 
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው              የወንድማችን የዲ/ን ቸርነት ድንቁ ወላጅ አባት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ታኅሣሥ 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ቀጨኔ መድኀኔዓለም ቤ/ክ የሚፈጸም በመሆኑ መገኘት የምትችሉ አባላት በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ጎላ በላይኛው በር መግቢያ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የአባታችንን ነፍስ  ይማርልን ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com