የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.11K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
በትላንትናው ዕለት ታኅሣሥ 05/2018 ዓ.ም የተጠራው የሰንበት ትምህርት ቤታችን ጠቅላላ ጉባኤ ተከናወነ።


ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የደስታ መልእክት

🙏 የተከበራችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በባለቤቴ  ታምራት አሻግሬ  በመጥፋቱ ምክንያት ለተጨነቃችሁ እና  ላዘናችሁ እንዲሁም በአካል መጥታችሁ  ላበረታችሁኝ በሙሉ በፈጣሪ ስም አመሰግናለሁ ።

        ባለቤቴ  ተገኝቷል  ።
    ደውሎ ድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ እንዳለ ነግሮናል ።
    ከክፉ ነገር ጠብቆ በህይወት እንዲኖር ያደረገ  እግዚአብሔር  ይክበር ይመስገን 🙏🙏🙏
      
           እህታችሁ ሙሉ  በርሄ ።
ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት፣ ካህናት እና የአጥቢያችን ምዕመናን በሙሉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በቅርብ ቀን በደብራችንና በሰንበት ትምህርት ቤታችን ሲያገለግሉ የነበሩ አሁን ግን በሕይወት የሌሉ ካህናትና የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችን የምናስብበት ዝክረ ካህናት ወአባላት የተሰኘ ልዩ መርሐግብር እያዘጋጀን በመሆኑ በየትኛውም ጊዜ በደብራችን ሲያገለግሉ የነበሩ (ያረፉ)ካህናትንና የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችን ስም ዝርዝር ፣ ፎቶ ግራፍ እና ዓ.ም የምታውቋቸውን በሙሉ
+251911458862 በዚህ ስልክ በቴሌግራም ገጽ /በሜሴጅ/ እንድትልኩልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

   አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ከሁላችንም ጋር ይሁን
                  
ሰላም ለከ ዐቃቤ ቅዱሳን እምተሀውኮ፤
ወለፀረ ነፍሶሙ ዘሞቃሕኮ፤
አመ መጽአ ወልድ በአፈ ነቢያት ተሰቢኮ፤
ከመ ያስተፋኑ ሐራ መልአኮ፤
እስከ ምጽንዓት ኃምስ ሚካኤል ተለውኮ።

ቅዱሳንን ከልብ መታወክ የምትጠብቃቸው የነፍሳቸውንም ጠላት አስረህ የምታስጨንቀው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ሰላም እልኻለሁ።
    በቅዱሳን ነቢያት አንደበት ትንቢት የተነገረለት እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ ጭፍራ አለቃውን አጅቦ እንዲሸኝ አንተም እስከ አምስቱ ሰማያት ድረስ ተከተልኸው።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ሐገራችን ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን አሜን!!
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤
     ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤
        ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤
        ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤
        ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤
       ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤
   ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤
    ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤
     ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤

ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤
      ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

                       መዝሙር 136
“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።” መዝሙር 22፥4
በጋራ መታሰቢያቸውን ለማድረግ የተዘጋጀ ዝክረ ካህናት ወአባላት ልዩ ጉባኤ ይታደሙ አበረዋችሁ ያገለገሉትን አባላትና የምታውቋቸውን አባቶች ፎቶ ይላኩልን በዕለቱም በጉባኤው ይታደሙ