የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.11K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም

ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና።

እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።

ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖራለች።

   ፈጣሬ ዓለማት ቅዱስ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ያሳትፈን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን!!
''የእጮኝነት ጊዜ ''

            የመጨረሻ  ክፍል

            በመ/ር ያሬድ ጥላሁን

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ቅዳሜ  ታኅሣሥ 04/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በትላንትናው ዕለት ታኅሣሥ 05/2018 ዓ.ም የተጠራው የሰንበት ትምህርት ቤታችን ጠቅላላ ጉባኤ ተከናወነ።


ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
የደስታ መልእክት

🙏 የተከበራችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ በባለቤቴ  ታምራት አሻግሬ  በመጥፋቱ ምክንያት ለተጨነቃችሁ እና  ላዘናችሁ እንዲሁም በአካል መጥታችሁ  ላበረታችሁኝ በሙሉ በፈጣሪ ስም አመሰግናለሁ ።

        ባለቤቴ  ተገኝቷል  ።
    ደውሎ ድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል አካባቢ እንዳለ ነግሮናል ።
    ከክፉ ነገር ጠብቆ በህይወት እንዲኖር ያደረገ  እግዚአብሔር  ይክበር ይመስገን 🙏🙏🙏
      
           እህታችሁ ሙሉ  በርሄ ።
ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት፣ ካህናት እና የአጥቢያችን ምዕመናን በሙሉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በቅርብ ቀን በደብራችንና በሰንበት ትምህርት ቤታችን ሲያገለግሉ የነበሩ አሁን ግን በሕይወት የሌሉ ካህናትና የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችን የምናስብበት ዝክረ ካህናት ወአባላት የተሰኘ ልዩ መርሐግብር እያዘጋጀን በመሆኑ በየትኛውም ጊዜ በደብራችን ሲያገለግሉ የነበሩ (ያረፉ)ካህናትንና የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮችን ስም ዝርዝር ፣ ፎቶ ግራፍ እና ዓ.ም የምታውቋቸውን በሙሉ
+251911458862 በዚህ ስልክ በቴሌግራም ገጽ /በሜሴጅ/ እንድትልኩልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

   አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ከሁላችንም ጋር ይሁን