የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.11K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
የሐዘን መግለጫ

“ሕያው ሁኖ የሚኖር ሞትንስ የማያይ ሰው ማን ነው ” መዝ.፹፰፥፵፰

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው እህታችን ወ/ሮ ሙናዬ በቀለ ባደረባት ሕመም በሕክምና ስትረዳ ቆይታ ኅዳር 29 አርፋለች። የቀብር ሥነ ስርዓቷ የሚፈጸመው ማክሰኞ ኅዳር 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 በአስኮ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የሚፈጸም በመሆኑ  አባላት በመገኘት ቤተሰቦቿን እንድናጽናናቸው ይሁን። እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። 

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የእህታችንን ነፍስ  በአጸደ ገነት ያኑርልን ።

        የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
ለፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
የእህታችን ወ/ሮ ሙናዬ በቀለ ሥርዓተ ቀብር ላይ ልብሰ ስብሐት እንድንለብስ ዛሬ ኅዳር 30 ከቀኑ 5:00-7:00 ስለሚሰጥ ንብረት ክፍል እየመጣችሁ እንድትወስዱ የትራንስፖርት አገልግሎትም ስለተዘጋጀ እህታችንን በክብር እንድንሸኛት ይሁን።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የእህታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን።

        የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
ከደጅህ ስደርስ

ከደጅህ ስደርስ ልቤ ይመታል
ወደ ማደሪያህ ልቤ ተነስቷል
ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ ልቤ አንተን ይመኛል

ሕይወቴን ለአንተ ልሰጥ መጣሁኝ
ለኃጢያቴ ይቅርታ ከአንተ እሻለሁኝ
ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ መንገድን አሳየኝ

የአንተ መንገድ እጅግ ይከብዳል
የጽድቅ ፈተና ማለፍ ይጠይቃል
ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ ጥበቃህ ይደንቃል

ደካማ ብሆን በእራሴ ባልችለው
አንተ በእኔ ካለህ ድል አደርገዋለው
ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ አሸንፈዋለው

ከደጅህ ስደርስ ልቤ ይመታል
ወደ ማደሪያህ ልቤ ተነስቷል
ኦ ጌታዬ ሆይ /3/ ልቤ አንተን ይመኛል
አፋልጉኝ

ከታች በፎቶ የምትመለከቱት ታምራት አሻግሬ የእህታችን ወ/ሮ ሙሉ በርሔ ባለቤት ጥቅምት 29 2018 ሥራ ብሎ ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም በወቅቱ ከቤት ሲወጣ የለበሰው ከላይ ጥቁር ጃኬት ነው ልዩ ምልክቱ ፀጉሩ ፊት ላይ ትንሽ ሽበት አለችበት ።

ፈላጊ እናቱ እና ቤተሰቦቹ

0913672432
0913074201
0929523232
በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም

ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና።

እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።

ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖራለች።

   ፈጣሬ ዓለማት ቅዱስ እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ያሳትፈን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን!!
''የእጮኝነት ጊዜ ''

            የመጨረሻ  ክፍል

            በመ/ር ያሬድ ጥላሁን

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ቅዳሜ  ታኅሣሥ 04/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
በትላንትናው ዕለት ታኅሣሥ 05/2018 ዓ.ም የተጠራው የሰንበት ትምህርት ቤታችን ጠቅላላ ጉባኤ ተከናወነ።


ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com