የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.11K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
'' ወነአምን በመንፈስ ቅዱስ ዘሠረጸ እም አብ ንስግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ አብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት''
    በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረጸ ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን፤ እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው።

መንፈስ ቅዱስ ከሚጠራባቸው ስሞች አንዱ
ጰራቅሊጦስ:- ናዛዚ ፣ መጽንዒ፣ መስተፍሥሒ ፣ የሚያጽናና፣ የሚመክር፣ የሚረዳ፣ የሚታደግ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው።

ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ''እናንተ  ግን  ከላይ ኃይል እስክትለብሱ  ድረስ  በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ'' ብሎ ለሐዋርያቱ በሰጣቸው ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሳ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ ድንገት እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት መላው የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎችም በሁሉም ላይ አረፉባቸው በዚህ ጊዜ ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በተለያዩ በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጎለመሱ፤ ጥቡዓን ሆኑ፣ ፍርሃት ከውስጣቸው ተወግዶ መንፈሳዊ ድፍረት አግኝተዋል፤  ጽኑዓን ኾነዋል፤ ሰማያዊ ሀብት ዕውቀትና ጸጋን ታድለዋል።

በዚህ ዕለት ሐዋርያት በተገለጠላቸው ቋንቋ ሲያስተምሩ ተቃዋሚ አይሁዳውያን  ''ጉሽ  ጠጅ  ጠጥተው  ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ''  እያሉ ሐዋርያትን አሟቸው ቅዱስ ጴጥሮስም  ሰክረዋል  የምትሉ  እናንተ እንደምትሉት  አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ  ሰዓቱም ገና ጠዋት  ሦስት  ሰዓት  ነው   
ይልቁኑ እናንተ በተንኮል ሰቅላችሁ የገደላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መሆኑን  በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ከክፋታቸው ተመልሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመኑ በዚያች ብቻ ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ተመልሰዋል ዕለቱም የቤተክርስቲያን የልደት ቀን ይባላል።

  ከሶስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ወር በገባ በ18 በዓሉ ሲሆን በአዲስ አበባ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዋና ደብሩ ሁልጊዜም በዓሉ ይታሰባል። ከዚያ በተጨማሪም በበዓለ ሃምሳ መንፈስቅዱስ የወረደበት ዕለት በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ ይከበራል።

ከሶስቱ አካላት አንዱ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ጠብቆት አይለየን አሜን።
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው              የወንድማችን የመ/ር ወንድምዬ አዋሽ ወላጅ እናት አርፈዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ አርብ ኅዳር19/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ለቡ  በሚገኘው ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ የሚፈጸም በመሆኑ መገኘት የምትችሉ አባላት በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው 5ኛ አካባቢ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን።  የእናታችንን ነፍስ  ይማርልን ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፤ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።

በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።

የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም። የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።

የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?

ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።

ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።

አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ። እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ ያሉአትን።

አንቺ ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ስለ ተበቀልሽን የሚበቀልሽ የተመሰገነ ነው።

ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።

መዝ.137
''የእጮኝነት ጊዜ ''

            ክፍል - አንድ   
በመ/ር ያሬድ ጥላሁን

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ዛሬ ቅዳሜ  ኅዳር 20/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
ሥርዐተ ማኅሌት ዘኅዳር ጽዮን ማርያም
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
እስመ ሐረያ እግዚአብሔር ለጽዮን
ወአብደራ ከመትኩኖ ማህደሮ
ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም
         
      እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና
      ማደርያውም ትሆነው ዘንድ
      ወዷታልና እንዲህም ብሎ
      ይህች የዘለዓለም ማረፊያዬ ናት

                      መዝ.131÷13

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የኅዳር ጽዮን ዓመታዊ ክብረ በዓል ታቦታተ ሕጉ ወጥተው በታላቅ ድምቀት ይከበራል!!
ቅድስት ጽዮን ድንግል ማርያም

ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በኋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው።

ኅዳር ሃያ አንድ የምናስብበት ምክንያት


✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን  አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን!!