የኅዳር ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በፎቶ
# ሰበር_ዜና
የወይራ ሠፈር ኆኅተ ገነት ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ቃጠሎ ወደመ።
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የወይራ ሠፈር ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና መንበረ ብርሃን እጨጌ አቡነ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ሌሊት በእሳት አደጋ ምክንያት የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የቃጠሎው መነሻ የኤሌክትሪክ መስመር ችግር እንደሆነም የተገለጸ ሲሆን ከታቦቱ በስተቀር ሌሎች ንዋየተ ቅድሳት ሙሉ በሙሉ በአደጋው ምክንያት መውደማቸው ነው የተገለጸው።
ሊያገለግሉበት ሲሄዱ ቦታውን ያጡት ሊያስቀድሱበት የገሰገሱበት ቤተ ክርስቲያን በእሳት እንዳልሆነ ሆኖ ሲያዩት ልባቸው የከዳቸው ካህናትና ምእመናን በከፍተኛ ኀዘን ላይ እንደሚገኙም የደረሰን መረጃ ያለመክታል።
አቤቱ ማረን ይቅር በለን!
© የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ