🔴 ስንክሳር#ታኅሣሥ_17
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ዐስራ ሰባት በዚች ቀን #ጻድቁ_አቡነ_ሉቃስ_ዘዓምድ ፍልሠተ ሥጋው ሆነ፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ሉቃስ_ዘዓምድ
ታኅሣሥ ዐስራ ሰባት በዚች ቀን ጻድቁ አቡነ ሉቃስ ዘዓምድ ፍልሠተ ሥጋው ሆነ፡፡ እርሱም ከፋርስ አገር ነው በመጀመሪያ በመቶ ጭፍራ ላይ መኰንን ሁኖ ተሹሞ ነበር ከዚህም በኋላ ሹመቱን ትቶ የምንኵስና ልብስን ለበሰ። በምሥራቅ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ ገዳም እየተጋደለ ብዙ ወራት ኖረ የምንኵስናንም ሥራ ተጋድሎንና ትሩፋትንም በፈጸመ ጊዜ በዚያ ገዳም ውስጥ ቅስና ተሾመ። በተሾመም ጊዜ በዚያ በኖረበት መጠን የብረት ልብስ ለበሰ ከዚያቺም ወዲህ ስድስት ቀን የሚጾም ሆነ በክርስቲያን ሰንበት ቀንም ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ይቀበላል ከዚህም በኋላ ከጐመን ጋር አንድ የዳቦ ለከት ይመገባል።
ከዚህም በኋላ ከዓምድ ላይ ወጥቶ በላዩ ሦስት ዓመት ቆመ በስሙም ሲጠራውና ከዚያም ዓምድ ላይ እንዲወርድ ሲያዝዘው የመልአክን ቃል ሰማ የብርሃን መስቀል ተከተለው ከገዳማት ወደ አንዱ ገዳም እስከ አደረሰውም ድረስ መራው በዚያም የሚኖር ሆነ ሰዎችም ሁሉ ወደርሱ እየመጡ በትምህርቱ ይረጋጉ ነበር።
ከዚህም በኋላ የማይናገር ሆነ ከሰው ጋር ከቶ እንዳይናገር ከአፉ ውስጥ ደንጊያ ጐረሰ ዳግመኛም ወደ የቊስጥንጥንያ አገር ዳርቻ ይሔድ ዘንድ መልአክ አዘዘው ለእርሷም አቅራቢያ ወደ ሆነች ወደ አንዲት ቦታ ሔደ ከምሰሶ ላይም ወጥቶ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ በላዩ አርባ አምስት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጠው አስደናቂዎች ተአምራትን በማድረግ ወደርሱ የሚመጡትን ከብዙዎች በሽተኞችን ፈወሳቸው።
እግዚአብሔርም ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው በፈቀደ ጊዜ በዚህ ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን ዐረፈ የሚያገለግለውም ረድ ለጳጳሳት አለቆችና ለካህናት አለቆች ስለ ዕረፍቱ ነገራቸው እነርሱም መስቀሎችን፣ ጽንሐዎችን፣ መብራቶችን፣ ከመያዝ ጋር በዚያን ጊዜ ተነሠሰተው ወደመኖሪያው ሔዱ በላዩም ጸልየው ተሸክመው ወደ ቊስጥንጥንያ ከተማ ወሰዱት በዐረፈ በሦስተኛው ቀን ታኅሣሥ ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን አደረሱት ወደ ቤተ መቅደስም አስገብተው የከበረ ሥጋው በአለበት እንደሚገባ ጸሎትን ፈጸሙ። ከእርሱም ተባረኩ የተሰበሰቡትም ሁሉ ተባረኩ ከዚህም በኋላ ከርሱ አስቀድሞ የቅዱሳን ሥጋቸው ወዳለበት ሣጥን ውስጥ ጨመሩት እግዚአብሔርም እጅግ ጠቃመመ የሆኑ አስደናቂዎች ተአምራትን አብዝቶ ገለጠ አምነው በሚመጡ በብዙዎች በሽተኞች ላይ ታላቅ ፈውስ ሁኗልና።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ)
https://t.me/finotebirhan12

Telegram
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
🔴 ስንክሳር#ታኅሣሥ_18
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ዐስራ ስምንት በዚህቸ ቀን #አቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን ጵጵስና የተሾሙበት ዕለት ነው፣ #የሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ የሥጋው ፍልሰት የተከናወነበት ነው፣ የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር የሆነው #የቅዱስ_ቲቶ የሥጋው ፍልሰት ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን
ታኅሣሥ ዐስራ ስምንት በዚህቸ ቀን #አቡነ_ሰላማ_ከሣቴ_ብርሃን ጵጵስና የተሾሙበት ዕለት ነው፡፡ ቅዱስ አባታችን አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በኋላ በ245 ዓ.ም በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ህዳር 26 ቀን ሲወለዱ ታላቅ ብርሃን ከሰማይ ወርዶ ለ7 ቀናት አብርቷል፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ወደ ምድር ወርደው በመወለዳቸው ታላቅ ደስታን አድርገዋል፡፡ በተወለዱም ጊዜ ‹‹ለአብ ስግደት ለወልድ ስግደት ለመንፈስ ቅዱስ ስግደት ይገባል፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጡኝ ቅድመ ዓለም ለነበሩ ዛሬም ላሉ ዓለምን አሳልፈው ለሚኖሩ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ብለው ዳግመኛም አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ብለው ፈጣሪያቸውን በአንድነት በሦስትነት አመስግነዋል፡፡
ቅዱስ አባታችን በሌላኛው ስማቸው ፍሬምናጦስ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ በ40 ቀናቸው ጌታ በተጠመቀበት በዮርዳኖስ ያጠመቋቸውና ስመ ክርስትና የሰጧቸው ሊቀ ጳጳስ ‹‹ይህ ሕፃን ለኢትዮጵያውን ሁሉ ብርሃን ይሆንላቸዋል›› በማለት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ በሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ አትናቴዎስ በሚገባ ተምረው ካደጉ በኋላ በ257 ዓ.ም ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ስሙ ሜርጵዮስ ከሚባል ከአንድ ነጋዴ ጋር መጡ፡፡ ከእነሱም ጋር አድስዮስ የሚባል ልጅ ነበር፡፡ ወደ ሀገራችንም ሊመጡ የቻሉት እንዴት ነው? ቢሉ መጀመሪያ ለሰባት ወር በአንድ ሌላ አገር ኖረው ወደ ኢየሩሳሌም ሊመለሱ ሲሉ የበረሃ ሽፍቶች ሜርጵዮስንና ሌሎች መንገደኞችን ገደሏቸውና ሁለቱን ልጆች ማርከው ወስደው ስሙ አልአሜዳ ለሚባል ለአክሱም ንጉሥ ሰጡት፡፡ እርሱም አድስዮስን የቤተክርስቲያን የአልባሳትና የዕቃ ቤት ጠባቂ አድርጎ ሲሾመው ፍሬምናጦስን ደግሞ የቤተክርስቲያንና የሕግ ጠባቂ አደረገው የቤተክርስቲያንን ሥርዓቷንና አገልግሎቷን ጠንቅቆ ያውቅ ነበርና፡፡
በአክሱምም በተጋድሎና በትጋት ኖረ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ አይቀምስም ነበር፡፡ በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግድ ነበር፡፡ በእርሱም የተጋድሎ ዘመን ደጋግ የሆኑ ነገሥታት አብርሃና አጽብሓ ነገሡ፡፡ እነርሱም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍሬምናጦስን በጣም ይወዱት ነበር፡፡ አንድ ቀን ፍሬምናጦስ የአክሱሙን ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ሚናስን ‹‹ግዝረትና እምነት በእናንተ ዘንድ አለ ነገር ግን ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ መቀበል በእናንተ ዘንድ የለም›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚናስም ‹‹ግዝረትንስ አባቶቻችን ሌዋውያን አመጡ፣ በክርስቶስ ማመንን ሕንኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ጃንደረባ አመጣልን፡፡ ስለ ጥምቀትና ሥጋ ወደሙ ሐዋርያ ወደ እኛ አልተላከም ነገር ግን ያልከውን ሁሉ የሚያደርግልን የሚባርከንና የሚቀድሰን ጳጳስን ታመጣልን ዘንድ ሊቀ ጳጳሱ ወዳለበት ወደ እስክንድሪያ አገር አንተ ሂድ›› አለው፡፡ ጥምቀትስ በጃንደረባው በኩል አገራችን ገብቶ ነበር ነገር ግን ገና ስላልተጠናከና ብዙ ሕዝብም አልተጠመቀም ነበርና አባታችን ፍሬምናጦስ አጠናክሮ ያልተጠመቀውን ሁሉ አጥምቆአል፡፡
ፍሬምናጦስም ወደ እስክንድሪያ ለመሄድ አስቦ ሳለ እንደተኛ ድንግል ማርያም ተገልጣለት ‹‹ዲቁናና ቅስናን መቀበል ይገባሃል፣ ለጵጵስና ተዘጋጅ፣ እግዚአብሔር ይህችን ከፍ ያለችውን ማዕረግ ሰጥተሃልና የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትህና በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁሉ ይድናሉ፣ በእጅህ ጥምቀትንና ሥጋ ወደሙን ይቀበላሉ›› አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲሁ ተገልጦለት ‹‹ወደ ሊቀ ጳጳሳት ወደ አትናቴዎስ ሄደህ ከፍ ያችውን ማዕረግ ተቀብለህ የኢትዮጵያን ሰዎች አጥምቅልኝ፣ ነቢዩ ዳዊት ስለ እነርሱ ‹ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች› ብሎ ተናግሯልና›› አለው፡፡ እርሱም ቅዱሳኑን ነገሥታት አብርሃንና አጽብሓን አግኝቶ ከእነርሱም ጋር ተማክሮ ወደ እስክንድሪያ ሄዶ በቅዱስ አትናቴዎስ እጅ በአገራችን ላይ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ታኅሳስ 18 ቀን ተሾመ፡፡ ስሙንም ሰላማ ከሣቴ ብርሃን አለው፡፡ ሰላማ ማለት እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስታርቅ ማለት ነው፡፡ ከሣቴ ብርሃን ማለትም ሃይማኖትን ገልጦ የሚያስተምር ማለት ነው፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም ከሾመው በኋላ ታቦትና በጣም ብዙ ንዋያተ ቅድሳትንና መገልገያ ዕቃዎችን ሰጥቶ መርቆ በሰላም ወደ ኢትዮጵያ ላከው፡፡ ይህች ዕለት አባታቸን በ330 ዓ.ም በሐዋርያው ቅዱስ አትናቴዎስ እጅ ጵጵስና የተሾሙባት ዕለት ናት፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥና_ግንቦት እና #ከገድላት_አንደበት)

#ስንክሳር_ዘታኅሣሥ_19
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ 19 ቀን በዚህች ዕለት #ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ውስጥ ያዳነበት ዕለት ነው፣ መልአከ ሞትን ለሦስት ወራት ከበራቸው ላይ ያቆሙት #አቡነ_ስነ_ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፣#አቡነ_ዮሐንስ_ዘቡርልስ ዕረፍታቸው ነው፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል
ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ እንዳዳናቸው ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡
በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡
የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡
መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን መላእክት፣ በጻድቃን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ታኅሣሥ እና #ከገድላት_አንደበት)

ስንክሳር#ታኅሣሥ_20
#ቅዱስ_ሐጌ_ነቢዩ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ ሃያ በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ፣ ከሌዊ ነገድ ከአሮን ትውልድ የሆነው ቅዱስ ሐጌ ዐረፈ። እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው። ናቡከደነጾርም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ በማረከ ጊዜ የዚህ ጻድቅ ነቢይ ወላጆች ከእስራኤል ልጆች ጋር ወደ ባቢሎን አገር ተማርከው ሔዱ ዳርዮስ የተባለውም ኵርዝ በነገሠ ጊዜ በሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ይህ ነቢይ ትንቢት ተናገረ።
የእስራኤልን ልጆች ወደ አገራቸው ይገቡ ዘንድ ኵርዝ ዳርዮስ በአሰናበታቸው ጊዜ እነርሱም ከገቡ በኋላ ቤተ መቅደስን ከመሥራት ቸለል በአሉ ጊዜ እነርሱ ግን በአማሩና በተሸለመ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ ነበርና እንዲህ አላቸው። "ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ አለ የኔ ቤት ፈርሷል እናንተ ግን ሁላችሁም ቤታችሁን ታጸናላችሁ" አላቸው። "ስለዚህ ከምድር በላይ ያለች ሰማይ ዝናም ለዘር ትነሣለች ምድርም ፍሬዋን አትሰጥም" አላቸው።
ከሕዝቡም ደናጎቻቸው ሰምተው እጅግ ፈሩ የእግዚአብሔርንም መመስገኛ ቤት እንደሚገባ መሥራት ጀመሩ። ይህም ጻድቅ ነቢይ ሰባ ዓመት ያህል ኖረ የትንቢቱም ወራት ክብር ይግባውና ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። ከዚህ በኋላም በሰላም በፍቅር ታኅሣሥ 20 ቀን ዐረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሐጌ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

...............የቦታ ለውጥ
ሜክሲኮ በተፈቀደልን የሽያጭ ቦታ ጊዜው ስለተጠናቀቀ አሁን በደብራችን ውስጥ ግርሞችን ቅዱሳን መጻሕፍቶችን በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ዘርግተን በድንኳን እያከፋፈልን እንገኛለን
#አድራሻ: ከኢሚግሬሽን ከፍ ብሎ ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

🔴#ስንክሳር_ታህሳስ_22
~~~~~~~~~~
ታህሳስ 22 በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ብስራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታን እንደምትወልድ ብስራቱን የነገረበት ቀን ነው፤ እንዴት ብስራቱንማ የነገራት መጋቢት 29 ቀን ነው ቢሉ ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው።
ታዲያ ዛሬ ለምን እናከብረዋለን ካሉ ምክንያቱ እንዲህ ነው፤ ምንግዜም ወርሃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር ነው በዚህ በዓቢይ ጾም ደግሞ ሐዘን፤ ለቅሶ፤ ጾም፤ ጸሎት እንጂ ደስታ፤ ፌሽታ እልልታ፤ ጭብጨባ የለም ፍጹም የሐዘን ወራት ነው ፍትሃ ነገስት አንድምታ አንቀጽ 15 ፡፡
የመጋቢት 29 ብስራቱን ደግሞ ታህሳስ 22 ቀን ዞሮ እንዲከበር ያደረገው ታላቁ አባት የጥልጥልያ ኤጲስ ቆጶስ ደቅስዮስ ይባላል በእመቤታች ፍቅር ልቡ የነደደ ታላቅ ጻድቅ ነው የእመቤታችንን ተአምራቷን የሚናገር መጽሐፍ የሰበሰበ አባት ነው፡፡
የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብስራቱ መከበር አለበት ብሎ ስርዓት ሰራ አገሬውንም ሰብስቦ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ እመቤታችን ተገለጸችለት ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ እንዳከበርከኝ እኔም አከብርሃለው አለችው ሰማያዊ ልብስና ሰማያዊ ወንበር ሰጠችው ይህችን ልብስ ካንተ ሌላ ማንም አይለብሳትም ይህችንም ወንበር ካንተ ሌላ ማንም አይቀመጥባትም አለችው፡ የዚህ ታላቅ አባት እረፍቱ ታህሳስ 22 በዛሬዋ ቀን ነው፡ ከእርሱ በኃላ ሌላ ኤጲስ ቆጶስ ተሾመ ልብሱን እለብሳለው በወንበሩም እቀመጣለው አለ ተው ይቅርብህ እመቤታችን እንዲህ ብላ ተናግራለች ይሉታል እርሱም ሰው እኔም ሰው እርሱም ኤጲስ ቆጶስ እኔም ኤጲስ ቆጶስ ብሎ በትዕቢት ልብሱን ለበሰው በወንበሩም ተቀመጠ ክፉኛ አወዳደቅ ወደቀ ደቅስዮስ ሰርቶልን ያለፈውን ስርዓት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡
https://t.me/finotebirhan12
ታህሳስ 22 በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ብስራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታን እንደምትወልድ ብስራቱን የነገረበት ቀን ነው፤ እንዴት ብስራቱንማ የነገራት መጋቢት 29 ቀን ነው ቢሉ ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው።
ታዲያ ዛሬ ለምን እናከብረዋለን ካሉ ምክንያቱ እንዲህ ነው፤ ምንግዜም ወርሃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር ነው በዚህ በዓቢይ ጾም ደግሞ ሐዘን፤ ለቅሶ፤ ጾም፤ ጸሎት እንጂ ደስታ፤ ፌሽታ እልልታ፤ ጭብጨባ የለም ፍጹም የሐዘን ወራት ነው ፍትሃ ነገስት አንድምታ አንቀጽ 15 ፡፡
የመጋቢት 29 ብስራቱን ደግሞ ታህሳስ 22 ቀን ዞሮ እንዲከበር ያደረገው ታላቁ አባት የጥልጥልያ ኤጲስ ቆጶስ ደቅስዮስ ይባላል በእመቤታች ፍቅር ልቡ የነደደ ታላቅ ጻድቅ ነው የእመቤታችንን ተአምራቷን የሚናገር መጽሐፍ የሰበሰበ አባት ነው፡፡
የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብስራቱ መከበር አለበት ብሎ ስርዓት ሰራ አገሬውንም ሰብስቦ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ እመቤታችን ተገለጸችለት ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ እንዳከበርከኝ እኔም አከብርሃለው አለችው ሰማያዊ ልብስና ሰማያዊ ወንበር ሰጠችው ይህችን ልብስ ካንተ ሌላ ማንም አይለብሳትም ይህችንም ወንበር ካንተ ሌላ ማንም አይቀመጥባትም አለችው፡ የዚህ ታላቅ አባት እረፍቱ ታህሳስ 22 በዛሬዋ ቀን ነው፡ ከእርሱ በኃላ ሌላ ኤጲስ ቆጶስ ተሾመ ልብሱን እለብሳለው በወንበሩም እቀመጣለው አለ ተው ይቅርብህ እመቤታችን እንዲህ ብላ ተናግራለች ይሉታል እርሱም ሰው እኔም ሰው እርሱም ኤጲስ ቆጶስ እኔም ኤጲስ ቆጶስ ብሎ በትዕቢት ልብሱን ለበሰው በወንበሩም ተቀመጠ ክፉኛ አወዳደቅ ወደቀ ደቅስዮስ ሰርቶልን ያለፈውን ስርዓት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፡፡
https://t.me/finotebirhan12
Telegram
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
🔴#ስንክሳር_ታኅሣሥ_23
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሃያ ሦስት በዚች ቀን የከበረ ተጋዳይ አባት ገዳማዊ አባ ጢሞቴዎስ አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባት ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እያስተማሩ አሳደጉት የምንኵስናንም ልብስ ሊለብስ ሽቶ ከአባቱ ዘንድ ወጥቶ ወደ አንድ ገዳም ሒዶ በዚያ የሚኖር ሆነ በውስጧም መነኰሰ።
ከዚህም በኋላ የተራቡ ድኆችን መጻተኞችን ተቀብሎ ይመግባቸው ዘንድ በገዳሙ አቅራቢያ ለብቻው መኖርን አሰበ ከገዳሙም ወጥቶ ማደሪያውን ሠራ። እየተጋደለና እጅ ሥራውንም እየሠራ በውስጡ አምስት ዓመት ያህል ኖረ የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣንም ከእርሱ እጅ ሥራውን ትገዛ ዘንድ በምክንያት ጋለሞታ ሴትን ወደርሱ አመጣ ብዙ ጊዜ ወደርሱ ከመመላለሷ የተነሣ የኃጢአት ፍቅር አድሮባቸው በመብል ጊዜ በአንድነት የሚበሉ ሆኑ ከዚህም በኋላ ከእርሷ ጋር በኃጢአት ወደቀና በኃጢአት ሥራ ውስጥ ሰባት ወር ያህል ኖረ።
በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር እርሷንም እርሱንም ፈጽሞ አልጣላቸውም የሞትን ጊዜ በምታስፈራና በምታስደነግጥ ቀን በንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት መቆምን አሳሰባቸው እንጂ። ከዚያም ቦታ ተነሥቶ ጥቅጥቅ ካለ ዱር ውስጥ ገባ ልዑል እግዚአብሔር መርቶታልና በዚያም ጣፋጭ የውኃ ምንጭና ተምር አለ በዚያም ቦታ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ።
ከዚህም በኋላ ሰይጣን በእርሱ ቀንቶ አስጨናቂ የሆነ የሆድ በሽታ አመጣበት ከሕማሙም ጽናት የተነሣ በግንባሩ በምድር ላይ የወደቀ ሁኖ ኖረ እርሱም ሲጸልይ ነፍሱን እንዲህ ይላት ነበር። ነፍስ ሆይ ይህ የሠራሽው የኃጢአት ፍሬ ነውና በዚህ ደዌ ላይ ታገሺ በዚህ ሕማምም አራት ዓመት ኖረ። ከዚህም በኋላ መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔር ራራለት መልአኩንም ላከለት እርሱም በእጁ ሆዱን አሸው ጐኑንም በጣቱ ሠነጠቀ ጨጓራውንና አንጀቱንም አፀዳ ከዚህም በኋላ ወደቦታው መልሶ እንደቀድሞው አያይዞ አዳነው። እነሆ እንግዲህ ጤነኛ ሆንክ ዳግመኛ አትበድል ከዚህ የከፋ እንዳይደርስብህ አለው።
በበረሀም ውስጥ እየተጋደለ አርባ ዓመት ኖረ ከዚህ በፊት በገዳም ዐሥራ ሰባት ዓመት በዋሻም ዐሥር ዓመት ኖሮዋል በዚህም ረጂም ዘመን ከልብስ የተራቈተ ነው ልዑል እግዚአብሔርም የራሱን ጠጕር አስረዘመለት በርሱም በፊቱም በኋላውም ተሸፈነበት።
ለዚህም አባት ስለ አገልግሎቱ ስለ ተጋድሎው ስለ በጎ አምልኮቱ አራዊት እስከሚጐበኙትና የእግሩን ትቢያ እስከሚልሱ ድረስ ታላቅ ጸጋ ተሰጠው እግዚአብሔርንም ከአገለገለ በኋላ አክሊሉን እንደተሸከመ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

🔴ስንክሳር_ታኅሣሥ_24
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን
ቅዱስ #ተክለ_ሃይማኖት ሐዋርያዊ
#ልደት
መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ #ጸጋ_ዘአብ ካህኑና #እግዚእ_ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ እርሷ በደግነቷ በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው #ቅዱስ_ሚካኤል ጸጋ ዘአብን ከሞት እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::
አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::
#ዕድገት
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " #ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያትና ሐዲሳትን) ተምረዋል በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ #አባ_ጌርሎስ ተቀብለዋል::
#መጠራት
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ
"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::
#አገልግሎት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ ( #ጽላልሽ ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ #ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት::
1.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት #ሐዲስ_ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::
#ገዳማዊ ሕይወት
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::
እነዚህም በአቡነ #በጸሎተ_ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ #ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ #ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ #ዞረሬ ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::
#ስድስት_ክንፍ
ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ #እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት #አባ_ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
¤በቤተ መቅደስ ብስራቱን
¤በቤተ ልሔም ልደቱን
¤በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው #ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::
+በዚያም:-
¤ የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤ 6 ክንፍ አብቅለው
¤ የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
¤ ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤ "ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::
#ተአምራት
=>የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
• ሙት አንስተዋል
• ድውያንን ፈውሰዋል
• አጋንንትን አሳደዋል
• እሳትን ጨብጠዋል
• በክንፍ በረዋል
• ደመናን ዙፋን አድርገዋል::
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::
#ዕረፍት
ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው አእላፍ ፍሬን አፍርተው በተወለዱ በ99 ዓመት ከ8 ወር ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24, በ1306 (1296) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::
=>የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች :-
1. ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
2. ፍስሐ ፅዮን
3. ሐዲስ ሐዋርያ
4. መምሕረ ትሩፋት
5. ካህነ ሠማይ
6. ምድራዊ መልዐክ
7. እለ ስድስቱ ክነፊሁ (ባለስድስት ክንፍ)
8. ጻድቅ ገዳማዊ
9. ትሩፈ ምግባር
10. ሰማዕት
11. የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
12. ፀሐይ ዘበፀጋ
13. የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
14. ብእሴ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሰው)
15. መናኒ
16. ኤዺስ ቆዾስ (እጨጌ)
=>እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:
=>ታሕሳስ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱሳን ጸጋ ዘአብና እግዚእ ኃረያ
3.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያ
4.ቅድስት አስቴር
5.አባ ፊሎንጐስ ሊቀ ዻዻሳት
6.አባ ዻውሊ ጻድቅ
7.ጻድቃን ቅዱሳን ዘከዲህ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
2.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
3.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
4.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
5."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን ባጸናበት ቅዱስ መንፈሱ እኛንም ያጽናን ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🔴ስንክሳር#ታኅሣሥ_25
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ታኅሣሥ 25 በዚህች ዕለት #የአቡነ_ዮሐንስ_ከማ_ዘግብጽ፣ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አቡነ_ዮሐንስ_ከማ_እጨጌ፣ #አምስቱ_መቃባውያን ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ዮሐንስ_ከማ_ዘእጨጌ_ኢትዮጵያዊው
በዚህችም ዕለት ኢትዮጵያዊው አቡነ ዮሐንስ ከማ ዘእጨጌ ዐረፉ፡፡ ይኸውም ጻድቅ አባት አገራቸው ሰሜን ጎንደር ነው፡፡ በብዙዎቹ ቅዱሳን ገድል ላይ ታሪካቸው ተደጋግሞ የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ በድርሰቱ ደጋግሞ ያመሰገናቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ከቀደምት አንጋፋ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ሲሆኑ መጽሐፍ "ኮከብ ዘገዳም" ይላቸዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ይህኛውንም አባት ግብፃዊ ናቸው ይሏቸዋል፡፡ ነገር ግን ስማቸውን ከላይ ከጠቀስናቸው ከግብፃዊው አባት ከአባ ዮሐንስ ከማ ጋር አንድ አይደሉም፡፡ ኢትዮጵያዊው አቡነ ዮሐንስ ከማ ትግራይ የሚገኘውን ቀብፅያ ገዳምን የቆረቆሩ ሲሆን ብዙ ቅዱሳን አባቶችንም በማመንኰስ የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት የተባሉትን ቅዱሳን መነኰሳትን አፍርተዋል፡፡ በገዳማቸው ቀብፅያ የምትገኘው እጅግ አስገራሚዋና ተአምራትን የምትሠራው መቋሚያቸው ዛሬም ድረስ አለች፡፡
1250 ዓመት ያስቆጠረችውን ይህችን የጻድቁን ተአምረኛ መቋሚያ ሀገሬው በጠመንጃ ይጠብቃታል፡፡ እንደ ሰው ድምፅ የምታሰማበት ጊዜ አለ፡፡ ጻድቁ ሰሜን ጎንደር ምድረ ጸለምት ትልቅ ገዳም አላቸው። ዕረፍታቸው በዚህች ቀን ነው።

...............4 ቀን ብቻ ቀረው................
የፊታችን ሐሙስ ድረስ ብቻ የሚቆይ ሽያጭ ግርግሞችን መጥተው ይግዙ በደብራችን ያገኛሉ
#አድራሻ: ከኢሚግሬሽን ከፍ ብሎ ጎላ ሚካኤል ቤ/ክ ውስጥ
Share