የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.62K subscribers
6.21K photos
67 videos
79 files
1.72K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
ውድ የተከበራችሁ የሰንበት ት/ት ቤታችን አባላት እንዲሁም የአጥቢያችን ምዕመናን በሙሉ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
  በትላንትናው ዕለት ማለትም በ18/02/18 ዓ.ም በደብራችን የመንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓልና በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ አላግባብ ጽሑፍና ማንም ባልፈቀደው መልኩ  ህግን በጣሰ መሠረት በደብራችን የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ/ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ   የትችት ጽሑፍ በሶሻል ሚዲያ ባስተላለፈው ዲ/ን  ከሳቴ ብርሃን ዙሪያ  እንደ ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ ቤት መረጃ እያሰባሰብን እንዲሁም በግለሰቡ ላይ ማጣራት ያለብንን ጉዳዮች እየተከታተልን ሲሆን  ጽሁፉ ን እና ግላዊ ሃሳባቸውን ባስተላለፉት ግለሰብ ላይም የቤተ ክርስቲያኒቷ ህግ በሚያዘው  መሠረት የማጣራት እና እንዲጠየቅ የማድረግ ስራ ለመስራት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር እያደረግን መሆኑን ለክቡራን  አባላቶቻችን እና ወዳጆቻችን ለማሳሰብ እንወዳለን !!!

    የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጽ/ቤት
''ትምህርተ ሃይማኖት ''
   
      ክፍል ሶስት

               
በዲ/ን ሞገስ አብርሃም

የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር 

ዛሬ ቅዳሜ  ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ከምሽቱ  11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ  ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የፌስቡክ ገጻችን  https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
''ትመስሊ ምሥራቀ፤ ወትወልዲ መብረቀ፤ ወታገምሪ ረቂቀ፡፡ ትመስሊ ፊደለ፤ ወትወልዲ ወንጌለ፤ ወታገምሪ ነበልባለ፡፡ ትመስሊ ጽጌ ረዳ፤ ወትወልዲ እንግዳ፤ ወታድኅኒ እሞተ ፍዳ … ሐረገ ወይን ሐረገ ወይን ዐፀደ ወይን አንቲ ማርያም ''

   ''በምሥራቀ ፀሐይ የምትመሰይው፤ እንደ መብረቅ ኃያል የሆነውን ጌታን የወለድሽ፤ ረቂቅ ምሥጢርን የምትችዪ፤ እንደ ፊደል ባለ ብዙ ዘር (ሆሄያት) የሆንሽ፤ ወንጌልን የወለድሽ፤ ነበልባለ እሳትን (ክርስቶስን) የተሸከምሽ፤ በጽጌ ረዳ አምሳል የምትመሰይው ቅድስት ማርያም ሆይ! የዓለሙን እንግዳ ፈጣሪን የወለድሽ፤ ከፍዳ ሞት የምታድኚ፤ የወይን ሐረግ የወይን ዐፀድ (ተክል) አንቺ ነሽ …''

   ልመናዋ ክብሯ የልጅዋም ቸርነት ከሁላችንም ጋራ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን፡፡
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነችው የእህታችን ዮዲት ገ/እግዚአብሔር አባት አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል የምትችሉ አባላት መኖሪያ ቤታቸው አሸዋ ሜዳ አካባቢ በመሄድ ወይም በስልክ ቁጥር +251911124269 በመደወል  እንድናጽናናቸው ይሁን። የአባታችንን ነፍስ ይማርልን ።

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12
የሐዘን መግለጫ

የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው የወንድማችን የአብስራ አክሊሉ  አያት አርፈዋል ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ ሐሙስ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ይፈጸማል የምትችሉ አባላት በቀብሩ ላይ እንዲሁም መኖሪያ ቤታቸው ጭድ ተራ ወረድ ብሎ በመገኘት እንድናጽናናቸው ይሁን። ነፍሳቸውን ይማርልን ።

       የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን https://youtube.com/@finotebirhan12

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የዌብሳይት ገጻችን https://finotebirhan.com
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  ወርሐዊ የባለትዳር አባላት ጉባኤ

እሑድ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም

  ከ5:00- 7:00

ጉባኤው በወር አንድ ቀን ብቻ የሚከናወን በመሆኑ በእለቱ  ተገኝተው ቃለ እግዚአብሔርን ይመገቡ።

            የባለትዳር ጉባኤ

ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12

የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12

የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc

የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1

የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com
መድኃኔዓለም (በዓለ ስቅለት)

ጥቅምት ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶና ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡