''ትምህርተ ሃይማኖት ''
ክፍል አንድ
በዲ/ን ሞገስ አብርሃም
የቅዳሜ የትምህርት መርሐግብር
ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:45 ሰዓት ላይ ቀጠሮዎትን በጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ያድርጉ ይምጡ ይማሩ በብዙ ያተርፋሉ እንዳይቀሩ።
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com

የ2018 ዓ.ም የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጸሎት ተጀመረ።
የጸሎት መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።

ወይቅፅበነ ፍቁረ አምላክ ለደቂቀ ዛቲ መርጡል፤
ወይቀጥቅጦ በቅድሜነ ለመስቴማ ኅጒል፤
ወያዕድወነ በአክናፊሁ እምባሕረ እሳት ዘሲኦል፤
ወይሰደነ ቤተ ባዕል ውስተ ፒላሳሁ ለአማኑኤል፤
ወይሴስየነ እምዘገነት አስካል፤
ወያስምዐነ እምዘምሕረት ቃል፤
ለኲልነ ሰማዕያን ለዓለመ ዓለም አሜን።
እኛ የቤተክርስቲያን ልጆችን በፍቅር ወደ እርሱ አቅርቦ ጠላታችን ሰይጣንንም በፊታችን ቀጥቅጦ ያጥፋልን። ባሕረ እሳትን በክንፉ እየቀዘፈ ያሻግረን ወደ አምላካችን አማኑኤል ጽርሐ መንግሥተ ሰማያት ያግባን። የገነትንም ፍሬ ይመግበን ዘንድ ይኽን ቃል የሰማነውን የምሕረት ቃሉን ያሰማን ለዘለዓለሙ አሜን።
እንኳን ለወርሐዊው የቅዱስ ሚካኤል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
• ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
• ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ ቅዱስ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፤
የጎደለብንን እየሞላ አገልግሎታችንን እያቃና ከዚህ ላደረሰን፣ ይህንን ዓመታዊና ሐዋርያዊ ጉባኤያችንን ለማካሄድም ለሰበሰበን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና እናቀርባለን፡፡
“ወእፌጽም ታሕጻጸ ሕማሙ ለክርስቶስ በሥጋየ በእንተ ሥጋሁ እንተ ይእቲ ቤተ ክርስቲያኑ፡- ስለ አካሉ ማለትም ስለ ቤተክርስቲያኑ ስል በሥጋዬ በክርስቶስ መከራ የጎደለውን እፈጽማለሁ” (ቈላ.፩÷፳፬)
ያለንበት ዓለም በሁሉም ነገር በጉድለቱ የሚታወቅ ነው፤ ጉድለት ባይኖርና ሁሉም የሞላለት ቢሆን ኖሮ ፍጥረት እርስ በርስ የሚተረማመስበት ሁኔታ አይኖርም ነበር ወይም አሁን ባለበት ደረጃ የከፋ አይሆንም ነበር፡፡
እግዚአብሔር ሁሉንም አሟልቶ መፍጠር ወይም መስጠት የሚችል ከሃሊ አምላክ ቢሆንም፣ እሱ ባወቀ ፍጥረትን ሁሉ ጉድለት ያለበት አድርጎ ፈጥሮታል፤ በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ጉድለቱን ለመሙላት በሚያደርገው ፍትጊያ እየተጋጨ እርስ በርስ ሲተረማመስ ማየቱ የተለመደ ነው፡፡ ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያንም በጐዶሎው ዓለም እስካለች ድረስ ከሚመጣው ፈተና አታመልጥም፤ ይህም በመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ ለቈላስይስ ሰዎች “የጎደለውን እፈጽማለሁ” በማለት ሲጽፍ እናስተውላለን፡፡
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በጐዶሎው ዓለም የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ጉድለቷን ለመሙላት ብዙ መሥዋዕትነት ከፍላለች፤ ቤተ ክርስቲያን ለቀጣዩ ትውልድ መሸጋገርና የጐደለባትን ለመሙላት ስትል ከቅዱሳን ሐዋርያት አንሥቶ እስካለንበት ዘመን ድረስ ብዙና የብዙ ብዙ አበው ካህናትን፣ ሊቃውንትንና ምእመናንን ከደም ጠብታ፣ እስከ ቁስ ስጦታ ገብራለች፡፡
አሁን በምድር ላይ ያለችው ቤተ ክርስቲያን የዚህ ሁሉ ውጤት ናት፤ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ ዛሬም የጐደለባት ብዙ ነገር አለ፤ በተቻለ መጠን እርሱን ለሟሟላት መጣርና በተሻለ ሁኔታ ወደፊት ማሻገር ደግሞ የዚህ ጉባኤ ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ይህ ጉባኤ ብቻው አይደለም፤ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቈጠሩ የእግዚአብሔር ልጆች ድምፁን ለመስማት ከዙሪያው ሆነው በጉጉት ይጠብቃሉ፡፡ እነኝህ የእግዚአብሔር ልጆች ለመስማት ብቻ ሳይሆን ድምፁን ሰምተው ለመታዘዝም የተዘጋጁ ናቸው፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ “ሁለትም ሦስትም ሆናችሁ በስሜ በተሰበሰባችሁበት እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ” በማለት ጉባኤውን የመሠረተው አምላክ ከዚህ ጉባኤ መካከል አለ፡፡
በመሆኑም ይህ ጉባኤ የተወሰን አባቶች ብቻ ሳንሆን ብዙ ሰማውያንና ምድራውያን ባለድርሻ ያሉበት፣ መንፈስ ቅዱስም በመንፈስ የሚመራው እንደሆነ የማይታበል ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ጉባኤው በምድር ያለችውን የእግዚአብሔር መንግሥት በበላይነት የሚመራ ነውና፣ ያለበት ኃላፊነት ከባድና እጅግ የላቀ ነው፡፡ ጉባኤው ኃላፊነቱን በአግባቡ ሲወጣ የሚሰጠው ሽልማት ታላቅ እንደሆነ ሁሉ፣ ኃላፊነቱን በትክክል ካልተወጣ ደግሞ ተጠያቂነቱ በዚያው ልክ ከባድ ነው፤ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለጋል ተብሎአልና፡፡
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
እኛ በአገልግሎትና በመሪነት በምንገኝበት በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን የጐደሉባት ነገሮች ብዙ ናቸው፤ ከሁሉ በላይ በውስጣችን የአንድነት ጐድለት በስፋት ይታያል፤ ለተሰየምንለት መለኮታዊ ተልዕኮ አንድ ሐሳብ፣ አንድ ቃል፣ አንድ ልብ ሆነን መሰለፍ ያለመቻል ክፍተት እየተንጸባረቀ ነው፡፡ የዘመኑን ጥበብና ስልት ያልተከተለ ሐዋርያዊ ተልዕኮአችንና አስተዳደራችንም ምእመናንን አላረካም፤ ክፍተቱ የሚዲያ ቀለብ ከመሆንም አልፎ በጎቻችን በሌሎች እንዲዘረፉ ትልቅ በር እየከፈተ ነው፡፡ በእነዚህ ዓበይት ጉዳዮች እና በመሳሰሉት ጉድለቶቻች ላይ ፈጣን፣ ቈራጥና አዋጭ የሆነ ሥራ ካልሰራን ለወደፊት የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ጥያቄ ውስጥ መክተቱ አይቀሬ ነው፡፡
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ቤተ ክርስቲያናችን በተጠቀሱት ችግሮች ተከባ ባለችበት ሁኔታ የሀገራችን ሰላም መቀዛቀዝ ደግሞ ሌላው ተጨማሪ ጉድለትን እያስከተለብን ነው፡፡ አማንያን የመንፈስና የሥነ ልቡና ሰላም ከማጣታቸውም በላይ አካላቸው ለሞትና ለጉዳት፤ ሃብታቸው ለዝርፊያና ለውድመት እየተዳረገ ነው፡፡ ይኽም ሁሉ ሆኖ ፍትሕን እያገኙ አይደለም፤ አብያተ ክርስቲያናትም በምእመናን ፍልሰት እየተዘጉም እየተቃጠሉም ነው፡፡
ከዚህም ሌላ የሌለን ነገር እንዳለ አስመስሎ ከየአቅጣጫው የሚወረወረው የባዕዳን ስም የማጥፋት ዘመቻ፣ የቤተ ክርስቲያኗን እምነት ከመንቀፍና ከማብጠልጠል በላይ አልፎ የቅዱሳንን ቅዱስ ሥዕል በአደባባይ እስከ መቅደድ ተደርሶአል፤ በቤተ ክርስቲያናችን ህልውና ላይ በዓላማ የተነሡ አካላት የላኳቸው እንዳሉ በሚመስል መልኩ በስመ ተሐድሶ የሚደረገው እንቅስቃሴ የኛው መለያ የሆነውን ንዋየ ቅድሳትና ልብሰ ተክህኖ፣ መዝሙርና ሥርዓተ አምልኮ በመጠቀም ቤተ ክርስቲያናችንን በአደባባይ እየተዳፈረ ይገኛል፡፡
ይህ አላስፈላጊ ተግባር የሀገሪቱን ዜጎች በእኩልነት የሚያስተዳድረውን ሕገ መንግሥት በቀጥታ የሚፃረር ድርጊት ነው፤ ሆኖም በሕግ የሚጠይቅና የሚያስቆም አካል አልተገኘም፤ እኛም ዝምታን የመረጥን መስለናል፡፡ ነገር ግን መፍትሔው ዝምታ ሳይሆን በሕግ አግባብ ነገሩን ለመፍታት መንቀሳቀስ እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል፡፡
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በዘመናችን እየተከሠተ ያለው ችግር ስንዘረዝር ውለን ብናድር መናገሩ በራሱ መፍትሔ ሊያመጣልን አይችልም፤ ጉባኤው ከዚህ በላይ መናገር እንደሚችልም እንገነዘባለን፤ ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ የሚችል መደላድል ይህ ጉባኤ በዚህ ስብሰባ ሊተልም ይገባል ብለን ከአደራ ጋር ማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በሌላ በኩል በሀገራችን ያለው ያለመረጋጋት በሕዝባችን አጠቃላይ ሥነ ልቡና በሀገሪቱ አንድነትና ዕድገት የሚያስከትለውን ጫና በቀላሉ የሚታይ አይሆንም፤ የሕዝቡ ሥነ ልቡና ከተጐዳ የነገው ዕድል ጤናማ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡
ችግሩ እየታየ ያለው በዋናነት በሀገራችን ፖለቲከኞች በመሆኑ ነገሩ የተወሳሰበና የተራዘመ እንዲሆን አድርጎታል፤ በመሆኑም ይህ የርስ በርስ ግጭት ቆሞ ችግሮች በውይይትና በድርድር በመፍታት የወንድማማች እልቂት የሚያስቆም የሰላምና የዕርቅ ዕድል ቅድሚያ እንዲሰጠው ጉባኤው የበኩሉን ጥረት ማድረግ ይገባዋል፡፡ የነገው ትውልድ ልማታዊ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው ሰላምና አንድነት ሲኖር ነውና መንግሥት፣ ተፎካካሪ ፖለቲከኞችና ነፍጥ ያነሡ ወገኖች ሁሉ ለሰላም መስፈንና ለልማት ዕድገት መረጋገጥ ሲባል ወደ መግባባት እንዲመጡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም
ዓመታዊውና ቀኖናዊው የቅዱስ ሲኖዶስ ዓቢይ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በጸሎት የተከፈተ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በእግዚአብሔር ስም እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፰ዓመተ ምህረት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፰ዓመተ ምህረት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ሰጠ።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በሰጠው ዕለታዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከናወነው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የጥቅምት ወር ምልዓተ ጉባዔውን ጥቅምት 11 ቀን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመክፈቻ ጸሎት መጀመሩን አስታውሷል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን በመወከል መግለጫውን የሰጡት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ምልዓተ ጉባዔው ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን የመጀመሪያ ቀን ጉባዔውን ያከናወነ ሲሆን 16 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ገልጸዋል።
በጠዋቱ ውሎ 7 ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አጀንዳ እንዲቀርጹ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን እነዚህም ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ናቸው ፡፡ ኮሚቴው በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሰብሳቢነት በብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ በአስረጂነት ተሰብስቧል።
ምልዓተ ጉባኤው በከሰዓቱ ውሎም ከ16ቱ አጀንዳዎች በ4ቱ ላይ ውሳኔ የሰጠ መስጠቱን ያስታወቀ ሲሆን እነዚህም ውሳኔዎች፦
1 ቅዱስነታቸው በጠዋቱ የመክፈቻ ጸሎት ያስተላለፉት መልዕክት በቀጣይ የሥራ መመሪያ አድርጎ ምልዓተ ጉባዔው አጽድቋል፡፡
2 ከጥቅምት 4-10 በነበረው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ የነበሩ የቡድን ውይይቶች በቃለ ጉባኤ ቀርቦ ቃለ ጉባዔውን ምልዓተ ጉባዔው የ2018 ዓ.ም የሥራ መመሪያ አድርጎ አፅድቋል፡፡
3 ሀገራዊ ሰላምን አስመልክቶ ምልዓተ ጉባዔው በግንቦት ወር ተወያይቶ ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን ኮሚቴው የተሰጠውን ኃላፊነት አጠንክሮ እንዲቀጥል ተወያይቶ አጽድቋል፡፡
4 በትግራይ የተፈጠረው ወቅታዊ ክፍፍልን አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን በውይይቱም ሕዝቡ ሕዝባችን አብያተ ክርስቲያናቱም የቤተክርስቲያን ሀብት እንደመሆናቸው ቀደም ብሎ የተዋቀረው የሰላም ኮሚቴ ሥራውን አጠንክሮ እንዲቀጥል በምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
ጉባዔው በነገው ዕለትም ቀጥሎ በቀሪዎቹ 12 አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል፡፡