"አዲሱ ዓመት ለሀገር ሰላምና ልማት፣ ለሕዝቦች አንድነትና ስምምነት እንደዚሁም አለመግባባትን በፍትሕና በዕርቅ ለመፍታት ከልብ የምንተጋበት መልካም የስኬት ዘመን እንዲሆንልን እንጸልይ"
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የአዲስ ዓመት
አባታዊ መልዕክት !!!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን መግባት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል ፣ የቅዱስነታቸው ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው።
+++++++++++++++++++++++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰመንቱ ዓመተ ምሕረት፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
• በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
• ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
• የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
• በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
• እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣
አምላክነቱን አውቀን እንድናመልከው ዕድሜንና ዘመናትን የሚሰጠን እግዚብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስምንት ዓመተ ምህረት የርእሰ ዐውደ ዓመት በዓል አደረሰን አደረሳችሁ!
‹‹ወገብረ ኵሎ ኅቡረ ወኵሎ አሕዛበ እምአሐዱ ዕጓለ እመሕያው ከመ ይንበሩ ዲበ ኵሉ ገጸ ምድር፤ ወሠርዐ ዕድሜሁ ወዓመታቲሁ መጠነ ይነብሩ በዘየኃሥዎ ለእግዚአብሔር፤ እመ ይረክብዎ፤ ወያደምዕዎ፤ ወኢኮነ ርሑቀ እምኵልነ፡- ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከኣንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ደረጃ መደባላቸው፤ ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም›› (የሐ. ሥራ. ፲፯÷፳፮)፤
ፈጣሬ ፍጥረታት እግዚአብሔር ትዕይንተ ዓለምንና በውስጡ የሚገኙ ፍጥረታትን የፈጠረ ኣምላክ ነው፤ እግዚአብሔር የፈጠራቸው ፍጥረታት የሚታዩና የማይታዩ ተብለው በጥቅል በቅዱስ መጽሓፍ ተገልጸዋል፤ የሰው ልጅ ከፍጥረታት መካከል ሆኖ ከኣንድ ወገን የተገኘ እንደሆነ በዚህ ጥቅስ ተጽፎኣል፤
የሰው ልጅ ከፍጥረታት ሁሉ የተለየ ክብርና ደረጃ እንዳለው በቅዱስ መጽሐፍ በተደጋጋሚ ተገልጾኣል፤ ልዩ የሚያደርገውም ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ነው፤
ሰው ልዩ ፍጡር መሆኑን ከሚገለጽባቸው መካከል እግዚአብሔር በሦስትነቱ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” በሚል ልዩ አገላለጽ መፈጠሩ፣ አፈጣጠሩም በእግዚአሔር መልክና አምሳል መሆኑ፣ በእግዚአብሔር እፍታ ሕያው ነፍስ እንዲኖረው መደረጉ፣ በሥልጣንም የፍጥረታት ሁሉ የበላይ ሆኖ መሾሙ ከሌሎች ፍጥረታት ልዩ ያደርገዋል፡፡
ከዚህ ኣንጻር ሰው በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ከፍጥረታት ሁሉ በላይ ነው፤ የሁሉም ገዥ ነው፤ በተለይም በዚህ ዓለም ከሰው በላይ ሆኖ የፍጡራን ገዥ የሆነ ፍጡር እንደሌለ ሁላችንም የምናየውና የምናውቀው ነው፤
በላይኛው ዓለምም ቢሆን መላእክትን ጨምሮ ሰማይና ምድርን ከነግሣንግሡ እየገዛ ያለው ሰው የሆነ ጌታ ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ የፍጥረት ገዥ ነው፤ እሱ ሰብእናችንን በፍጹም ተዋሕዶ የተዋሓደ በመሆኑ ሰብእናችን በተዋሕዶተ ቃል ኣምላክ ሆኖ የፍጥረታት ሁሉ ገዥ ሆኖኣልና ነው፤
ቅዱስ መጽሓፍም “ወተኰነኑ ሎቱ መላእክት ወሥልጣናት ወኵሉ ኃይል፡- መላእክት፣ ሥልጠናትና ኃይል ሁሉ ተገዙለት” በማለት ይህንን ያረጋግጣል፤ ይህ እግዚአብሔር ለኛ ለሰዎች ያጐናጸፈን ግሩምና ኣስደናቂ ጸጋ ነው፤ ለዚህም ነው “ወሰብእ ይከብር እምኵሉ ፍጥረት፡- ሰው ከፍጥረት ሁሉ ይከብራል” ተብሎ የሚዘመረው፤
• የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያት!
እኛ ሰዎች የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ ሆነን እንድንኖር በእግዚአብሔር ስንፈጠር በሕይወት እንድንኖር ነው፤ እግዚአብሔር በምድር ላይ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሰውን ከኣንድ ፈጠረ የሚለው መጽሓፍ ቅዱሳዊ ኣስተምህሮም ይህንን ያመለክታል፤
ሰዎች በምድር ላይ በሕይወት እንዲኖሩ የተፈጠሩ ሆነው እያለ በሕይወት እንዳይኖሩ ማድረግ ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር መጋጨትን ያስከትላል፤በዘመናችን ዓለማችንን እየፈተነ ያለው ተቀዳሚ ፈተና ሰዎች በሕይወት እንዳይኖሩ የማድረግ ዝንባሌ ነው፤
እንደዚህ ዓይነቱ ዝንባሌ በዓለም ባይኖር ኖሮ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቈጠሩ ድሆች ባሉበት ዓለም ለሰው ልጅ ሕይወት ማጥፊያ የሚሆን መሳሪያ ለማምረት ኁልቈ መሣፍርት የሌለው ገንዘብ ኣይወጣም ነበር፤
ይህ ክፉ የዓለም ዝንባሌ እንደ ክፋት ብቻ ሳይሆን እንደ ሞኝነትም የሚያሳይብን ነው፤ማንኛችንም ሰዎች ‹‹ሰው ማጥፋት ይሻላል ወይስ ማዳን›› ተብለን ብንጠየቅ መልሳችን ምን እንደሚሆን ይታወቃል፤
ነገር ግን ኣንፈጽመውም፣ ሞኝነት የሚያሰኘውም እዚህ ላይ ነው፤ የሚጠቅመንንና የመሰከርንለትን ትተን የሚጐዳንንና፣ ያልመሰከርንለትን እንፈጽማለንና ነው፤
ስለሆነም በሕይወት እንዲኖር የተፈጠረውን ሰው በሕይወት የመኖር መብቱን ከመንፈግ መቆጠብ የኣዲሱ ዓመት ትልቁ ኣጀንዳ ኣድርገን ብንወስድ ለሁላችንም ይበጀናልና እንቀበለው እንላለን፤
• የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን! ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት!
ሰው በሕይወት እንዲኖር በእግዚአብሔር ሲፈጠር እግዚአብሔርን የሚፈልግበትና የሚያገኝበትን ዕድሜና ዘመንም እንደተሰጠው ከተጠቀሰው ክፍለ ንባብ እንገነዘባለን፤ መቼም እግዚአብሔር ሁሉን የፈጠረ በስራ ለስራ እንደሆነ የምንስተው ኣይሆንም፤ እግዚአብሔር ዕድሜና ዘመን ለሰዎች ሲሰጥ ሊሰራበት ነው፤ ስራውም መንፈሳዊና ዓለማዊ ነው፤ ተደምሮ ሲታይ ደግሞ ለሰው ጥቅም የሚውል ነው፤
እኛ ሰዎች በተሰጠን ዕድሜና ዘመን በመንፈሳዊው ስራችን እግዚአብሔርን ፈልገን እንድናገኝ ተፈጥረናል፤ እሱን ማግኘት የማይቻል የሚመስለን ካለንም እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ ኣይደለም ተብለናልና በመንፈስ ከፈለግነው በመንፈስ እንደምናገኘው መጽሓፉ ያስረዳናል፤ስለሆነም በተሰጠን ዘመን ይህንን ስራ መስራት ይኖርብናል፤
በሌላ በኩል ለኑሮኣችን የሚያስፈልገንን ፍጆታ በበቂ ሁኔታ እንድናገኝ ላባችንን ኣንጠፍጥፈን መስራት ይገባናል፤ ይህም ከሰራን ያለጥርጥር የምናገኘው ነው፤ ሁለቱም የጐደሉብን በኛ ኣስተሳሰብ፣ ኣሰራርና ኣጠቃቀም እንጂ እግዚአብሔር ሳይፈቅድልን ቀርቶ ወይም ነፍጎን ኣይደለም፤ እግዚአብሔር የሰጠን ምድር በልዩ ልዩ ሀብተ ጸጋ የተሞላች እንደሆነች፣ የምንረግጠው መሬትም ወደ ሀብት መቀየር እንደሚቻል የተረጋገጠ ነው፤
ነገር ግን እኛ በምንራመድበት በእግራችን ሥር ያለውን ሀብት ትተን በሩቅ ያለውን ስንመለከት ሁሉን ያጣን ሆነን በችግር ወድቀን እንገኛለን፤ በተለይም እኛ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ጊዜ እየተፈታተነን ያለው ይኸው የተሳሳተ እሳቤ ነው፤

Telegram
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
ኢትዮጵያ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን አድርገን በማመን በእኩልነት፣ በአንድነትና በስምምነት ከመጠቀም ይልቅ ያ የኔ ነው ያም የኔ ነው በሚል አባባል ምን ያህል ዋጋ እየተከፈለ እንደሆነ እያየን ነው፤ ይህ ግለኝነት ያየለበት አስተሳሰብ ገታ አድርገን በእኩልነትና በአብሮነት የሚያሳድገንን አስተሳሰብ በእጅጉ ይጠቅመናል፤ ይህንንም የኣዲሱን ዓመት ምርጥ እሳቤ ኣድርገን ብንወስድ የተሻለ መግባቢያ ሊሆን ይችላል፤ አዲሱ ዓመት በአዲስ እሳቤ ካላጀብነው አዲስ ሊሆን አይችልምና ነው፤ ስለሆነም አዲሱን ዓመት መልካም በሆነ አዲስ ሃሳብ ፣እግዚአብሔርንና ሰውን በሚያገናኝ ቅዱስ ተግባር፣ በልማት፣ በሰላም፣ በፍቅር፣ በዕርቅና በስምምነት እንድንቀበለው ወቅታዊ ጥሪያችን ነው፤
በመጨረሻም፣
ኣዲሱ ዓመት ለሀገር ሰላምና ልማት፣ ለሕዝቦች ኣንድነትና ስምምነት እንደዚሁም ኣለመግባባትን በፍትሕና በዕርቅ ለመፍታት ከልብ የምንተጋበት መልካም የስኬት ዘመን እንዲሆንልን እንጸልይ፣ በዚህም መላ ሕዝባችን ጠንክሮ እንዲሰራ ለመላ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ ኣባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤
እግዚአብሔር ኣምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣
መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼 ✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼✨🌼 ✨🌼✨🌼
"ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ" (መዝ ፷፬ ፥ ፲፩)
እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማርቆስ በሰላም አሸጋገራችሁ!!
በጊዜ ሥጦታ ቀናት ተፈጥራዊ ዑደትን ተከትለውና ወራትን ተክተው ዘመንን ይፈጥራሉ፤ የዘመናት ለውጥም አዲስ ዓመትን ይተካሉ፤ ይህ ሁሉ ግን በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ሆነ፤ እኛም ለአዲሱ ዓመት ዘመነ ማርቆስ እንደ ቸርነቱ ደረስን፡፡
በዝናብ አብቅሎ፣ በፀሐይ አብስሎ ፍጥረቱን የሚመግብ እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን መልካም እንድንሠራበት ነውና በመጪው ዘመን የትላንት ስሕተታችንን አርመን፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ለመኖር ልናቅድ ይገባናል፤ ለምድራዊ ኑሯችን የምንተገብራቸውን እንደምናቅደው ሁሉ ለመንፈሳዊ ሕይወታችንም ልናስብ ይገባል፤ የዘመናት ጌታ ብርሃንና ጨለማን፣ በጋና ክረምትን የሚያፈራርቅ ዘመንን፣ በዘመን የሚተካ የሠራዊት ጌታ የእስራኤል ቅዱስ ልዑል እግዚአብሔር ዘመነ ማቴዎስን _አሻግሮ ለዘመነ ማርቆስ አድርሶናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን! ዝናመ ምሕረቱን፣ ጠለ በረከቱን ለምድር ለግሶ፣ አለስልሶ ባዶነቷን በሰብል፣ በልምላሜ፣ በጽጌአት ውበት አስጊጦ፣ እክለ በረከቱን ለእኛ የሚያድል ፈጣሪ ዘመኑን የፍቅር፣ የሰላም፣ የምሕረት ዘመን ያድርግልን! የተሰጠንን ዘመን መልካም ልንሠራበት ይገባል! በስንፍና ያሳለፍነው ጊዜ ይብቃን! በአዲስ ዘመን በአዲስ ዕቅድ፣ በአዲስ መንፈስ ለሥራ እንነሣ! ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ እንዲህ ይለናልና ‹‹የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም፣ በስካርም፣ በዘፈንም፣ ያለ ልክም በመጠጣት፣ ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና፡፡››
የፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤታችን በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ እያለ፤ አዲሱ ዓመት መልካም ሥራ የምንሰራበት፣ በኀጢአት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ ታጥቦ ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ የምንበቃበት፣ በመልካም ተግባር የሚታደስበት እና ለስጋ ብቻ ሳይሆን ለነፍሳችንም የምንሰራበት እንዲሆን እንዲሁም አዲሱ ዓመት በሃይማኖት የምንፀናበት፣ በፍቅርና በመረዳዳት የምንኖርበት፣አንድነታችን የሚጠነክርበት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የምትሆንበት እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን፡፡
የዘመናት ጌታ ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅልን!!!
መልካም አዲስ ዓመት!!
2018 ዓ.ም
የጽ/ጽ/ሐ/ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት

ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በሰላም አደረሰዎ መርሐ ግብር ተከናወነ።
በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የምሥራቅ ደቡብ ትግራይ እና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ልዩ ልዩ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ እና ሰንበት ተማሪዎች ተገኝተዋል።
© Eotc