#መልካም_ዜና
በዛሬው እለት በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የቅዱስ ሚካኤል ማኅበር ልጆች መካከል የሆኑት መልአከ ሰላም ቀሲስ እስክንድር ወ/ማርያም እና ወንድማችን ሄሎም ተስፋዬ ከባለቤቱ አርቲስት አዚዛ አህመድና ልጆቻቸው ጋር በሰንበት ት/ቤታችን ጽ/ቤት በመገኘት ለሚዲያ ክፍሉ አገልግሎት ማጠናከሪያ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በድጋፍ አስረክበውናል። በዕለቱ የሰንበት ት/ቤታችን ሰብሳቢ መ/ር ተስፋዬ ተሾመ እና ምክትል ሰብሳቢ ወጣት ካሳሁን እሸቱ እንዲሁም ከስራ አመራር የሚዲያ ክፍሉ ሰብሳቢ ወጣት አፈወርቅ በላቸው ፣የሕጻናት ክፍል ሰብሳቢ ኢ/ር ዳዊት አበበ ፣ እና የሚዲያ ክፍል አባላት ተገኝተው ተረክበዋል።በቀጣይ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል የገቡ ሲሆን በተጨማሪም የማኅበሩ አባላት በሆሣዕና አገልግሎት ላይ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦም የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል። በተያያዘ መልካም ዜና የሰንበት ት/ት ቤታችን አባል በሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ተክሌ ለሚዲያ ክፍሉ ፕሮጀክተር ገቢ ተደርጎለታል እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የሚገኙት የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባል አቶ ብሩክ ገ/ሥላሴ ከነባለቤታቸው ለሚዲያ ክፍሉ ማጠናከሪያ እንዲሆን የ10,000# (አስር ሺህ ብር) ድጋፍ አድርገውልናል ።
ድጋፍ ያደረጉልን ሁሉንም አምላከ ቅዱስ ሚካኤል በነፍስ በስጋ ይጠብቅልን በማለት የሰንበት ት/ቤታችን ሰብሳቢ ምስጋና አቅርበዋል።
በመጨረሻም የሰንበት ትምህርት ቤታችን ሚዲያ ክፍል ራሱን ለማደራጀትና ለማሳደግ እያደረገ ላለው የስቱዲዮ ግንባታ እንቅስቃሴ ሁላችንም በገንዘብ ወይም የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ የድርሻችንን አበርክቶ ልንወጣ ይገባል።
የኢ/ያ ንግድ ባንክ - 1000555650594 (media/ሚዲያ) በማለት የበረከቱ ተሳታፊ ይሁኑ እግዚአብሔር ይስጥልን
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
https://t.me/finotebirhan12
የዩቲዩብ ቻናላችን
https://youtube.com/@finotebirhan12
የፌስቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Fbirhan?mibextid=2JQ9oc
የቲክቶክ አካውንታችን https://www.tiktok.com/@finotebirhan?_t=8i8eHwFI3Es&_r=1
የዌብሳይት ገጻችን
https://finotebirhan.com

Telegram
የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዓለ ጰራቅሊጦስ
'' የቤተክርስቲያን የልደት ቀን '' በደብራችን ጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

የጎፋ መካነ ሕያዋን ሰንበት ት/ቤት ለመቄዶንያ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ !
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት በርቀት ከሚያስተምራቸው ተማሪዎች ያሰባሰበውን አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ሰባ ሺህ ብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቡራኬ ለመቄዶንያ መሥራች ለክቡር ዶክተር ብኒያም አስረክበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚገኙ አገር በቀል ተቋማት መካከል በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ከተቋቋመ ስምንት ዓመታትን ባስቆጠረው በመቄዶኒያ ከ8,000 በላይ በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ተረጂዎች ይገኙበታል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት “መቄዶንያ ለተቸገሩ ሰዎች የሚረዳ ትልቅ ተቋም ነው፡፡ መንግሥትም የማይችለውን ነው መቄዶንያ የያዘው፤ ለዚህ ተቋም ርዳታ የሚያደርጉ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ትልቅ ዋጋ ያገኛሉ፡፡ ሀብታቸውም ይባረክላቸዋል፡፡ እስከ አሁንም ርዳታ ላደረጉት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡ ቅዱስነታቸው አያይዘውም “በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች ችግረኞች እየተበራከቱ በመሆኑ፤ የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት በኩል ለመቄዶንያ የምትችሉትን ርዳታ በመርዳታችሁ በረከት ታገኛላችሁ፤ብዙ ዋጋ ያስገኝላችኋል፤ይሄ በጎ ሥራችሁ ለሁሉም አርአያ በመሆኑ እግዚአብሔር ይባርካችሁ” በማለት አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሰብሳቢ ቀሲስ ዮናስ ኢሳይያስ እንደገለጹት “የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት ከ6‚500 ተማሪዎች ይገኛሉ፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ በርቀት ትምህርት ማስተማር ነው፡፡ በርቀት ትምህርት የሚማሩት በተሠማሩበት የሥራ ዘርፍ ክርስትናቸውን እንዲገልጹ ማድረግ” መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም “በቤተክርስቲያን ተቋማት በርካታ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ከመንፈሳዊ ትምህርቷ በተጓዳኝ በማኅበራዊ ጉዳይ ተሳታፊ እንዲሆኑ መቄዶንያ አረጋውያንን እንዲረዱ እያደረግን ነው፤ በዚህም መሠረት የሰንበት ትቤቱ የርቀት ትምህርት አስተባባሪዎች ተወካዮች ቅዱስነትዎ ጋር መጥተን ለመቄዶንያም የበኩላችንን አስተዋጽኦ እንድናደርግ አባታዊ በረከትዎን ለመቀበል መጥተናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
“የካቴድራሉ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ አባ ኃይለ ኢየሱስ ተመስገን እንዳብራሩት “የሰንበት ትምህርት ቤቱ ወጣቶች በርካታ ሥራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ” ገልጸዋል፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ባዘጋጀው የርቀት ትምህርት በርካታ ተማሪዎች ከተለያዩ ቦታዎች መጥተው ይማራሉ፡፡ ዶክተር ቢኒያም በሀገራችን ላይ በየመንገዱ ወድቀው የሚኖሩ ወገኖቻችንን እያነሡ የጀመሩት ራዕይ ተስፋፍቶ አሁን ፍሬ አፍርቷል፡፡ እኛም በበኩላችን ይህን ለምን አንደግፍም ብለን ካቴድራሉ፣ሰንበት ት/ቤቱ በማስተባበር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፤ቅዱስነትዎ ለዶክተር ቢኒያም እንዲሰጡልን” ነው የመጣነው ብለዋል፡፡
አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና በመሰብሰብ “ሰው ለመርዳት ሰው ብቻ መሆን በቂ ነው” የሚል መርህ አንግቦ ከተነሣ ዓመታት ያስቆጠረው መቄዶንያ፤ በእነዚህ ዓመታትም በርካታ አረጋውያንንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና ሕይወት መታደግ ችሏል፡፡ የተቋሙ መሥራች ክቡር ዶክተር ቢኒያም እንደገለጹት “መቄዶንያ ምንም ገቢ የለውም፡፡ በቀን ከ 2.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚያወጣ ማዕከከል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት በ46 ከተሞች ላይ ከጎዳና ሰዎች ተነሥተው እየተረዱ ይገኛሉ፡፡” ብለዋል፡፡
“ዛሬ የአንድ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት 1.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገው ሌሎችም አብያተ ክርስቲያናትና ሰንበት ት/ቤቶች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያነሣሣ ነው፡፡ ሌሎችም ይህን አርአያ አድርገው ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው፡፡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናትም የረዱን አሉ፤ ሌሎችም ድጋፍ በማድረግ እንዲሳተፉ ቢያደርጉ፤ ድጋፍ የሚያደስፈልጋቸውን እነዚህ መርዳት ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ስለሚያሰጥ ሁሉም ኅብረተሰብ እንዲሳተፍ ቅዱስነትዎ መመሪያ ለሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ቢያስተልላልፉልን” ብለዋል፡፡
©️ EOTCTV

''ሥርዓተ ማኅሌት ዘበዓለ ጰራቅሊጦስ''
በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት
በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትና ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ
ፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት