የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
🔴ስንክሳር_ኅደር_8

በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_አፍኒን የተሾመበት ነው፣ #ለንጉሥ_ቈስጠንጢኖስም መስቀል የተገለጸበት ነው፣ የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ #ቅዱስ_አባ_ቅፍሮንያ ያረፈበት ቀን ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አርባዕቱ_እንስሳ

ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።

እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አፍኒን_ሊቀ_መላእክት

ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ አፍኒን የተሾመበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ ይህም ሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን የሚጠብቅ ነው፡፡ ስለዚህም ክቡር መልአክ ሄኖክ እንዲህ አለ፡- "…ያንን ቤት ሱራፌልና አፍኒን ዙሪያውን እየዞሩ ይጠብቁታል፣ እነርሱም የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን ሲጠብቁ የማያንቀላፉ ናቸው፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ "በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ" (ራዕ 8፥2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤልና ኅዳር 8 ቀን የተሾመበትን ዓመታዊ በዓሉን የምናከብርለት ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ኪሩቤል፣ በቅዱሳን መላዕክት እና ሰማዕታት አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር#ከዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ እና #ከገድላት_አንደበት)
https://t.me/finotebirhan12
🔴 ስንክሳር #ኅዳር_9

በዚህችም ቀን ሃይማኖታቸው የቀና #318ቱ_ቅዱሳን_አበው_ሊቃውንት_በኒቅያ አርዮስን ያወገዙበት ዕለት ነው፤ የእስክንድርያ አገር አርባ አንደኛ ሊቃ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_ይስሐቅ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጉባኤ_ኒቅያ

ኅዳር ዘጠኝ በዚህችም ቀን የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ በኒቅያ ከተማ በጻድቅ ንጉሥ በቈስጠንጢኖስ ዘመን ሆነ። ከእርሳቸውም ጋራ አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት አሉ እሊህም አባ እለእስክንድሮስ የእስክንድርያ አባ ዮናክንዲኖስ የሮሜ አገር አባ ሶል ጴጥሮስ የቊስጥንጥንያና የአንጾኪያም ሊቀ ጳጳሳት አባ ኤዎስጣቴዎስ ናቸው። ስብስባቸውም የሆነበት ምክንያት በእስክንድርያ አገር ቄስ ሁኖ ስለ ነበረው ስለ አርዮስ ነው ። እርሱ ስቶ የክብር ባለቤት ወልድን በመለኮቱ ፍጡር ነው በማለቱ ነው።

ከእሊህም ቅዱሳን ተጋዳዮች አባቶች ከውስጣቸው እንደ ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ በሽተኞችን የሚፈውሱ ድንቆች ተአምራትን የሚያደርጉ አሉ ብዙ ዘመናትም ስለ ቀናች ሃይማኖት የተሠቃዩ አሉ። ከእርሳቸውም የእጃቸውንና የእግራቸውን ጥፍሮች ያወለቋቸው አሉ ዳግመኛም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን የቆረጧቸው አሉ። ጥርሶቻቸውን የሰበሩአቸውና ጐናቸውን የሠነጠቋቸውም አሉ።

ከውስጣቸውም ስሙ ቶማስ የሚባል የሀገረ መርዓስ ኤጲስቆጶስ አለ ከሀድያንም ሃያ ሁለት ዓመት አሥረው ርኅራኄ የሌለውን ሥቃይ አሠቃዩት በየዓመቱም ወደርሱ በመግባት ከሕዋሳቱ አንዱን ይቆርጣሉ እንዲሁም በማድረግ እጆቹን እግሮቹን ከንፈሮቹን አፍንጫውን ጆሮዎቹንም ቆርጠው ጨረሱ። ጥርሶቹንም ሰበሩ በእሳትም ተለብልቦ እንደ ጠቆረ ግንድ አደረጉት የርሱ ወገኖችም እንደሞተ አስበው እንደ ሌሎች ሰማዕታት በየዓመቱ መታሰቢያውን አደረጉ።

እሊህ አባቶችም ወደ ኒቅያ ከተማ በደረሱ ጊዜ ንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ታላቅና ሰፊ የሆነ መሰብሰቢያ አዳራሽ አዘጋጀላቸው በውስጡም ለየአንዳንዳቸው ወንበሮችን አኖረ የእርሱንም ወንበር ከእነርሱ ወንበሮች ዝቅተኛ አደረገ መሳለምን በመርዓስ ኤጲስቆጶስ በቅዱስ ቶማስ ጀመረ ሰገደለት ሕዋሳቶቹ ከተቆረጡበት ላይ ተሳለመው። እንዲሁም አባቶችን ሁሉንም ተሳለማቸው። ከዚህም በኋላ በትረ መንግሥቱን ሰይፉን ቀለበቱን ሰጣቸውና እንዲህ አላቸው እነሆ አሁን በካህናት ሁሉና በመንግሥት ላይ ሃይማኖቱ እንደናንተ የቀና ከሆነ ታኖሩት ዘንድ ሃይማኖቱ የቀና ካልሆነ ግን ከምእመናን ለይታችሁ ታሳድዱት ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ።

እነርሱም ሕግንና ሥርዓትን ሠሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመካከላቸው ይቀመጥ ነበር ልቡናቸው በመንፈስ ቅዱስ የበራላቸው ሰዎች አይተውታልና በሚቆጥሩአቸው ጊዜ ግን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ቁጥር ሁነው ያገኙአቸዋል።

ከዚህም በኋላ ለካህናትና ለሕዝባውያን ለነገሥታት ለመሳፍንት ለሚገዙና ለሚሸጡ ነጋዴዎች ለድኆችም ለሽማግሎችና ለጐልማሶች ለሙት ልጆችም ለወንድና ለሴት ሥርዓትን ሠሩ። ከዚህም በኋላ ወልድ በመለኮቱ ከአብ ጋር ትክክል እንደሆነ እያስረዱ የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩ የተረገመ አርዮስንና በረከሰች ትምርቱ የሚያምነውን አውግዘው ለዩ።

የሠሩዋት ያስተማሩዋትም የሃይማኖት ትምህርት ይቺ ናት እንዲህ ብለው ሁሉን በያዘ ሰማይና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጁ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን።

ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የሆነ የሌለ በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለ ሰው ስለ መዳናችን ከሰማይ ወረደ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ።

ሰው ሆኖ በጰንጤናዊ ጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ ተሰቀለ ታመመ ሞተ ተቀበረም በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ዳግመኛም ሕያዋንንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።

ከዚህም በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ጠላት ስለሚሆን ስለመቅዶንዮስ በቊስጥንጥንያ ከተማ መቶ ሃምሳው ኤጲስቆጶሳት በተሰበሰቡ ጊዜ ከዚህ የቀረውን ሠሩ። እንዲህም አሉ ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋራ በነቢያት የተናገረ። ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን። ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን ። የሙታንንም መነሣት የሚመጣውንም ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን።

እሊህም አባቶቻችን ይችን የሃይማኖት ትምህርት ምእመናን ሁሉ በቀንም በሌሊትም በጸሎታቸው ጊዜ እንዲአነቡዋት በቅዳሴም ጊዜ እንዲጸልዩባት አዘዙ ወንዶችና ሴቶች ሽማግሎችና ልጆች አገልጋዮችም ሁሉ እንዲማሩዋት አዘዙ። ሠርተው ወስነው ለቤተ ክርስቲያን የሃይማኖትን ፋና ከአቆሙላት በኋላ ወደ የሀገራቸው በፍቅር አንድነት ተመለሱ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)
https://t.me/finotebirhan12
🔴 ስንክሳር #ኅዳር_10

በዚህች ቀን ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው #ቅድስት_ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ፤ ቅዱሳን አባቶቻችን ስለ ጾም ሥርዓት የአንድነት ስብሰባ አድርገው #የቅዱስ_ዲሜጥሮስን_ቀመር_አቡሻህርን በሁሉም ዘንድ እንዲጠቀሙበት በጉባኤ ወሰኑ፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅድስት_ሶፍያ

ኅዳር ዐሥር በህች ቀን ቅዱሳት ንጹሐት መነኰሳይያት ደናግል እናታቸው ሶፍያም በሰማዕትነት አረፉ። እሊህም ቅዱሳት ከተለያዩ አገሮችና ቦታዎች ሲሆኑ መለኮታዊ ፍቅር በአንድነት ሰበሰባቸው የምንኲስናንም ልብስ ለበሱ ይኸውም የመላእክት ልብስ ነው። በሮሜ አገር ከአሉ ገዳማትም በአንዱ የሚኖሩ ሆኑ ቅድስት ሶፍያም በእነርሱ ላይ እመ ምኔት ሆነች።

እርሷም ጸጋንና ዕውቀትን የተመላች ናት የቅዱሳን መነኰሳትን ገድል በማንበብ እየጾሙ እየጸለዩ በምድር ላይ እንደ መላእክት እስከ ሆኑ ድረስ መንፈሳዊ ዕድገትን አሳደገቻቸው ከእነርሱም በአንድ ገዳም ውስጥ ሰባ ዓመት ያህል የኖሩ አሉ ከውስጣቸውም ልጅ እግሮች የሆኑ አሉ።

ከሀዲ ንጉሥ ዑልያኖስም ከፋርስ ንጉሥ ከሳቦር ጋር ሊዋጋ በሮሀ ሀገር በኩል በሚያልፍ ጊዜ እርሱ ሳቦር ሊወጋው ወደርሱ እንደሚመጣ ሰምቷልና አልፎ ሲሔድም በውስጡ እሊህ ደናግል ያሉበትን ገዳም አይቶ ይህ ምንድን ነው ብሎ ጠየቀ ሰዎችም ይህ የደናግሎች ገዳም ነው አሉት።

በዚያንም ጊዜ ወደዚያ ገዳም ገብተው ደናግሎችን እንዲገድሏቸው በገዳሙ ውስጥም ያለ ገንዘባቸውን ሁሉ እንዲዘርፉ ወታደሮቹን አዘዘ ወታደሮችም ገብተው እሊያን ደናግል በሰይፍ ገደሏቸው ገዳሙንም አጠፉ የገዳሙን ገንዘብ ሁሉንም ዘረፉ።

ከሀዲውን ንጉሥ ግን ስለ መንጋዎቹ በቀል እግዚአብሔር ተበቀለው ይህም እንዲህ ነው ያጠፋው ዘንድ ሰማዕት መርቆሬዎስን አዘዘው መርቆሬዎስም በአካለ ነፍስ ሒዶ በጦር ወጋውና በክፉ አሟሟት ሙቶ ወደ ዘላለም ሥቃይ ሔደ። እሊህ ቅዱሳት ደናግል ግን ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ገቡ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ባሕረ_ሐሳብ

በዚችም ዕለት በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት በድሜጥሮስ ዘመን ስለ ጾም ሥርዓት ቅዱሳን ሊቃነ ጳጳሳትና የኤጲስቆጶሳት የአንድነት ስብሰባ ተደረገ። በዚህም የአንድነት ጉባኤ የመሰብሰባቸው ምክንያት እንዲህ ነው የክርስቲያን ወገኖች በጥር ዐሥራ አንድ ቀን በከበረች በጥምቀት በዓል ተጠምቀው በማግሥቱ የከበረች የአርባ ቀንን ጾም መጾም ይጀምራሉ እስከ የካቲት ሃያ ሁለት ቀንም ጾመው ጾምን ይፈታሉ።

ከዚህም በኋላ በመጋቢት በሃያ ሦስት የሕማማትን ሰሞን መጾም ይጀምራሉ በዚህም ወር በሀያ ሰባት የስቅለቱን በዓል ያከብራሉ በሃያ ዘጠኝም ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤውን በዓል ያክብሩ ነበር።

ይህ ድሜጥሮስም በእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሁኖ በተሾመ ጊዜ በእርሻ የሚተዳደር መጻሕፍትን የማያውቅ ጨዋ ሰው ሲሆን እግዚአብሔር በመለኮታዊ ስጦታው ልቡን ብሩህ አድርጎለት የብሉይንና የሐዲስ መጻሕፍትን የቤተ ክርስቲያንንም ሕግ አወቀ ከእርሳቸውም ብዙዎችን ተረጎመ።

ከዚህም በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ባሕረ ሐሳብ የተባለ የዘመን ቁጥርን ጻፈ ይህም ክብር ይግባውና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አጽዋማትና በዓላቶቹ የሚታወቁበት እሊህም የከበረች የአርባ ቀን ጾም የሆሣዕና ዑደት ስቅለቱ ትንሣኤው በአርባ ቀን ዕርገቱ ከትንሣኤውም በኋላ በኀምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ናቸው።

ይህንንም ጽፎ ወደ ሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦር ላከ ሁለተኛም ወደ አንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ መክሲሞስ ላከ ዳግመኛም ወደ ኢየሩሳሌም አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ አጋብዮስ ላከ እነርሱም በአነበቧት ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኙባት።

የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ፊቅጦርም በሮሜ አገሮች ሁሉ ያሉትን ኤጲስቆጶሳቶቹን አዋቂዎችን ብዙዎች ሊቃውንትንም ሰበሰባቸው ይህንንም የዘመን ቁጥር አስነበበላቸው እጅግ በጣም ጥሩ ሁኖ አግኝተውት ደስ ተሸኙበት በደስታም ተቀበሉት አባዝተውም በመጻፍ ለሁሉ አገሮች ላኩት እስከዚች ዕለትም ጸንቶ ተሠርቶ ኖረ። ከዚህም በኋላ ልዩ ሦስት የሆነ አንድ እግዚአብሔርን ፈጽሞ እያመሰገኑት ወደየሀገራቸው ገቡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ደናግላን ሰማዕታት እና ሥርዓትን በሰሩልን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)
https://t.me/finotebirhan12
ኅዳር 16 "ጉባኤ ጽዮን"
የሰንበት ት/ቤታችን የአውደ ምህረት መርሐግብር
🔴 ስንክሳር #ኅዳር_11

#ቅድስት_ሐና

ኅዳር ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።

ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።

ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር)
https://t.me/finotebirhan12
የሰንበት ት/ቤታችን YouTube ቻናል እዚህ ደርሷል ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁን እንድታደረጉን እንጠይቃለን
https://m.youtube.com/channel/UCXMG9oO5j1M-lRbAn0OdVdQ
የሕዳር ሚካኤል ሥርዓተ ማኅሌት

👉 ነግሥ
ሰምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ (፪) እመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡

👉 የኅዳር ቅዱስ ሚካኤል ማኅሌት
++++
ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤
ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ ፤
እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤
ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ ፤
ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ ።

👉ዚቅ
አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤ ኢዜነዎ ለሰማይ፤
ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤ ወተከለ ፫ተ ዕፀ ሕይወት በዲበ ምድር ።

👉 ነግሥ
ጎሥዓ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤
ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤
ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትኅትና፤
አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤
ወአንተኑ ለእስራኤል ዘአውረድከ መና ።

👉 ወረብ
አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ፤
ወአንተኑ ለእስራኤል መና ዘአውረድከ።

👉 ዚቅ
አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤
ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፤
ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤
አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፤ ዘትረ ኮኲሕ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነጽፍ፤
ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ።

👉 ፫. ነግሥ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

👉 ዚቅ
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን፤
አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና፤
እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት እኅቶሙ ለመላእክት፤
አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና ።

🌹 ለዝክረ ስምከ (መልክአ ሚካኤል )

ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤
ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤
ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤
ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ።

👉 ወረብ
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን፤
በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ።

ዚቅ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤
ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤
ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ ።

👉 ወረብ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ።

🌹ለልሳንከ
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተሀበለ፤
በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበሀለ፤
ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤
ቀዊምየ ቅድመ ሥዕልከ ሶበ አወትር ስኢለ፤
በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

👉 ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስኢለ፤
በብሂለ ኦሆ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

👉ዚቅ
ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል፤
እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤
ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን።

👉ወረብ
እግዚኡ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል፤
እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ።

🌹ለኅንብርትከ
ሰላም ለኅንብርትከ ኅንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤
ነግሀ ነግህ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤
በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤
ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ።

👉ወረብ
በገዳም በገዳም በገዳም ዘሴሰይኮሙ፤
ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ።

👉ዚቅ
ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ፤
ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤ በእደ መልአኩ አቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርብዓ ዓመተ፤
ወሴሰዮሙ መና ሕብስተ፤ ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መሥፈርተ።

👉ወረብ
ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብር አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር
በእደ መልአኩ አቀቦሙ ለእስራኤል አርብዓ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/

🌹አምኃ ሰላም
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤
ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤
ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤
ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤
ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

👉ዚቅ
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤
ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ።

👉ወረብ
ተወከፍ ጸሎተነ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤
ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት።

🌹አንገርጋሪ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤
ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤
ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤
ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።

🌹እስመ ለዓለም
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምህር ለነ ሰአልናከ በ፲ ወ፬ ትንብልናከ፤
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤
ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤
ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር።

🌹አቡን (በ፮)

ዝስኩሰ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ይስአል ለክሙ ኀበ ንጉሠ ስብሐት ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን፤
ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤
ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን፤
በጽሑ መላእክት ወቦሙ መዘምራን ማእከለ ደናግል ዘባጥያተ ከበሮ ስዮም በኀበ እግዚኡ ምእመን።

🌹ዓራራይ

ሐመልማለ ወርቅ ልብሱ ዘመብረቅ፤
ሚካኤል ሊቅ ሐመልማለ ወርቅ ክነፊሁ ዘእሳት፤
አድኅን እግዚኦ ዛተ ሀገረ ወካልዓተኒ አህጉረ በሐውርተ፤
በኃይለ መላእክቲከ እለ እምዓለም አሥመሩከ ረዳእየ አንሰ ኪያከ ተወከልኩ።

🌹ዘሰንበት

ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፨ ከመ ናዕብያ ወናክብራ ለዕለተ ሰንበት ፨ መላእክተ ሰማይኒ ወኵሉ ፍጥረት ፨ እለ ውስተ ሲኦል፨ እለ ውስተ ደይን ፨ ያዕርፉ ባቲ ፨ እስመ ቀደሳ አዕበያ ወአልዓላ ለዕለተ ሰንበት፨ መኑ ከማከ ስቡሕ እግዚኦ በውስተ ቅዱሳን ፨ መንክር ስብሐቲከ እግዚኦ ወትረ እሴብሐከ፡፡

🌹 ሰላም
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ።
+++
“ ልዩ የአዳር መርሃ-ግብር ”
ቀን፡- ህዳር 11/ 2014 ዓ.ም
ቦታ፡- በሰንበት ትምህርት ቤቱ አዳራሽ
ሰዓት፡- ከምሽቱ 03፡00 ጀምሮ
............በእለቱ........
👉 ግጥም
👉 መንፈሳዊ ፊልም
👉 ጭውውት፣
👉 መዝሙር በዘማሪያን፣
👉 ትምህርተ ወንጌል፣
👉 ጥያቄና መልስ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል

ቦታ : የደብሩ ስብከተ ወንጌል አዳራሽ
🔴 ስንክሳር #ኅዳር_11 #ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት
ኅዳር ዐሥራ አምስት በዚህች ቀን የስሙ ትርጓሜ ቡሩክና የታመነ የሆነ ቅዱስ ሚናስ በሰማዕትነት አረፈ። የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና ። እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው። በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያንም ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ።

ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን አለ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል ሚናስ ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት። ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት። ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ አረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ አረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ።
መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም።

ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ ። በዚያንም ጊዜ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊሎችን ሲያቀዳጇቸው አየ። ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል የሚል ቃልን ሰማ። በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና። መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ። ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።

የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈፀም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት።
በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት።
እነርሱም በባሕር ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱስ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጠለቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና።

ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ ሀገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በገመል ላይ በጫኑት ጊዜ ገመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ። ሁለተኛም በሌላ ገመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እምቢ አለ። አብዝተውም ደበደቡት ገመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው በዚያ ቀበሩት።
ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ ይህም ቤተ ክርስቲያኑ በከበረችበት በሰኔ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል።
ነገ ሐሙስ የማይቀርበት የሰንበት ት/ቤታች የአውደ ምህረት ጉባኤ
👉 ከእህታችን ጎን እንሁን በጸሎት፣ በገንዘብ እንዲሁም በተዘጋጀው የምሳ መርሐግብር ላይ በመገኝት
#ኅዳር_16

🔴 ስንክሳር #ኅዳር_16

በዚህች ቀን #የቅዱስ_አቡናፍር ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው፣ የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ዮሐንስ ያረፈበት ነው፣ #ቅዱስ_ኪስጦስ በሰማዕትነት ያረፈበት ነው፣ #ቅድስት_ጣጡስ በሰማዕትነት ያረፈችበት ነው፣ የመነኰስ #አባ_ዳንኤልና_የንጉሥ_አኖሬዎስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው።

#ቅዱስ_አባት_አባ_ዮሐንስ

በዚህችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ አባት የቆጵሮስ ሀገር ሰው ነው እጅግም ባለጸጋ ነው በእስክንድርያ አገርም የሚኖር ሆነ አባቱ አገረ ገዥ ነበርና ሚስትም አግብቶ ልጆችን ወለደ ከዚህም በኋላ ሚስቱም ልጆቹም ሞቱ።

በዚያንም ጊዜ ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች ሰጠ መጸወተ እርሱም መንኵሶ በታላቅ ገድል የተጠመደ ሁኖ በጎ ሥራዎችን ትሩፋትን ጨምሮ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።

ከበጎ ሥራዎቹና ከትሩፋቱም ከቀናች ሃይማኖቱ ከአገልግሎቱና ከደግነቱ ከጽድቁ ማማር የተነሣ በግብጽ አገር የሚኖሩ ኤጲስቆጶሳት ሁሉም ተሰማምተው ይዘው ወሰዱት ያለ ፈቃዱም በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙትና በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ አስቀመጡት ። ያን ጊዜ የከበረ ወንጌልን አነበበ በሹመቱና በክህነቱም ብርሃን ተገለጸ ብዙዎች ድንቆች የሆኑ ተአምራትንም አደረገ።

ለድኆችና ለችግረኞች ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የሚሹትን የሚሰጣቸው ሆነ ስለዚህም የሚራራ ዮሐንስ ተብሎ ተጠራ ። በአይሁድና በአረማውያን ዘንድ የሚአስፈራ ሆነ በመጸሐፈ ገድሉ እንደተጻፈ እጅግ ይፈሩትና ያከብሩት ነበርና መንጋዎቹንም በበጎ አጠባበቅ ጠበቃቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምሰጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር እና #ከገድላት_አንደበት)
https://t.me/finotebirhan12
የእህታችን የሣምራዊት አለሙን ሕክምና ወጪ በኮሚቴውና በእርሷ ስም የንግድ ባንክ አካውንት ተከፍቷል ለመርዳት የምንፈልግ በተጠቀሰው አካውንት ቁጥር የአቅማችንን እናድርግ