የጽርሐ ጽዮን ሐዋርያት ጎላ ቅዱስ ሚካኤል የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት (Official Channel)
2.58K subscribers
6.1K photos
67 videos
60 files
1.7K links
ይህ በጽ/ጽ/ሐ/ጎ/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት እውቅና የተሰጠው የቴሌግራም ቻናል ነው።
Download Telegram
🌹 ማኅሌተ ጽጌ ዘጥቅምት ፳፩ (21)

የ ፳፻፲፬ዓ.ም የአራተኛው ሳምንት የጥቅምት ፳፩ የአራተኛው ሰንበት የጽጌ ማኅሌት

ነግሥ 🌹
ሰምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ (፪) እመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡

፩/ ነግሥ ( ለኵልያቲክሙ) 🌹

ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ፦

ሃሌ በ፱ ሐረገ ወይን ፨ ሃሌ ሉያ ፱ ጊዜ ሐረገ ወይን እንተ በምድር ሥረዊሃ ፨ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፨ ሐረገ ወይን ፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፨ወታፈሪ ለነ ፤አስካለ በረከት፨ሐረገ ወይን ፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ፨ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፨ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

፪/ ትመስል እምኪ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤
ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤
ወካዕበ ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤
እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤
ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ፡፡

ወረብ፦ 🌹

ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እምኪ/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

ዚቅ፦

እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ፨ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ፨ ከመ ትኲኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ፨ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለም፡፡

፫/ ስብሐተ ፍቅርኪ ማርያም / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

ስብሐተ ፍቅርኪ ማርያም ኲሎ አሚረ፤
በልሳነ ኲሉ ይጸጊ ወኢይፈርህ አባረ፤
ዘያረጥብ የብሰ ወያየብስ ባሕረ፤
እስመ ብኪ ጠለ ተአምር እንተ ርደቶ ነጸረ፤
ጌዴዎን ኀበ ሰፍሐ አምሳለኪ ፀምረ።

ወረብ፦ 🌹

ስብሐተ ፍቅርኪ ማርያም ኲሎ አሚረ በልሳነ ኲሉ ይጸጊ ወኢይፈርህ አባረ /፪/
እስመ ብኪ ጠለ ተአምር ጠለ ተአምር ገባሪተ ኃይል /፪/

ዚቅ፦

ወዓዲ በትር እንተ ሠረፀት ፨ ወጸገየት ወፈረየት ፨ ሐውልተ ስምዕ ዘኢያሱ ፨ ፀምር ዘጌዴዎን ፨ መዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል።

፬/ እንዘ ተሐቅፊዮ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡፡

ወረብ፦ 🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ/፪/

ዚቅ፦

ንዒ ርግብየ ሰላማዊት ፨ንባብኪ አዳም፨ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ፨ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ፨ እግዚኣ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ።

፭/ ክበበ ጌራ ወርቅ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ።
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ።
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዬርጊስ ቀፀላ መንግሥቱ።
አንቲ ኩሉ ታሰግዲ ሎቱ።
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ ።

ወረብ፦ 🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ። ለከዋክብት።

ዚቅ፦

ይእቲ ተዓቢ እምአንስት፨ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ፨ መድኃኒቶሙ ለነገሥት ፨ አክሊል ንጹሕ ለካህናት ፨ ብርሃኖሙ ለከዋክብት።

፮/ እስከ ማዕዜኑ / ሰቆቃወ ድንግል / 🌹

እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ ፤
ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ ፤
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ ፤
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

🌹ወረብ ፦

በከመ ይቤ ዖዝያን ዖዝያን ለክብረ ቅዱሳን /፪/
እምግብፅ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡሁ /፪/

ዚቅ፦

ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ ፨ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ፨ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን።

🌹 መዝሙር ዘሰንበት

ሃሌ (በ፮) በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፤ ናሁ ጸገዩ ጽጌያት ፨ ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት፨
ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ፤ ምስለ ዕንጐታት ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ ነአኵቶ ለዘጸገወነ ሠናይቶ፡፡

አመላለስ ዘመዝሙር 🌹

ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጐታት ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤
ነአኵቶ ለዘጸገወነ ሠናይቶ፡፡

https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12
🔴ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት

#ጥቅምት_21 በዚህችም ቀን #እመቤታችን_ተአምራትን_አድርጋ_ሐዋርያው_ማትያስን ከእሥራት ቤት ያወጣችበት፣ #የነቢይ_ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ፣ የማርታና የማርያም ወንድም #የቅዱስ_አልዓዛር ሥጋው ከቆጵሮስ አገር የፈለሰበት፣ የቅዱስ አባት #አባ_ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እረፍት ነው፣ ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_አላኒቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#እመቤታችን_ለሐዋርያው_ማትያስ_ያደረገችለት_ተአምር
በዚህችም ቀን እመቤታችን ማርያም ተአምራትን አድርጋ ደቀ መዝሙር ማትያስን ከእሥራት ቤት አዳነችው።

የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡

ሐዋርያው ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ ጌታችንና ወደ እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡

እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡ እነርሱም ይዘው በአንገታቸው ገመድ አግብተው ለ3 ቀን በሀገራቸው ጎዳናዎች ላይ ሁሉ ጎተቱዋቸው፡፡ ሁለቱም ሐዋርያት በጸሎታቸው ከእሥር ቤቱ ምሰሶ ሥር ውኃ አፈለቁና ውኃው ሀገራቸውን ሁሉ እስኪያጥለቀልቅና ሰዎቹንም እስከ አንገታቸው ድረስ እስከሚደርስ ሞላ፡፡ ሁሉም በተጨነቁ ጊዜ ሁለቱ ሐዋርያት በፊታቸው ተገለጡና ‹‹በጌታችን እመኑ ትድናላችሁ›› በማለት ወንጌልን ሰብከውላቸው አሳመኗቸው፡፡ ምሥጢራትንም ሁሉ ገለጡላቸው፡፡ ደግሞም የአራዊት ጠባይን ከሰዎቹ ያርቅላቸው ዘንድ ወደ ጌታችንና ወደ ተወደደች እናቱ ከጸለዩ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቋቸው፡፡ ያ የአውሬነት ጠባያቸውም ጠፍቶላቸው የዋህ፣ ቅንና ሩኅሩኆቸ ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም ሃይማኖትን እያስተማሯቸው 30 ቀን አብረዋቸው ከተቀመጡ በኋላ አገልጋይ ኤጲስ ቆጶሳትን፣ ካህናትንና ዲያቆናትን ሾመውላቸው ወደ ሌላ ሀገር ሄዱ፡፡

ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት እመቤታችን ለእኛም ትለመነን!

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
የሰንበት ት/ቤታችንን ቴሌግራም ይቀላቀሉ
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
ስንክሳር #ጥቅምት_22

#ቅዱስ_ሉቃስ_ወንጌላዊ

ጥቅምት ሃያ ሁለት በዚህች ቀን ብልህ ጥበበኛ የሆነ ቅዱስ ወንጌላዊ ሉቃስ በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ የከበረ ወንጌል ከመዘገባቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የተቆጠረ ነው።

እርሱም ወንጌልን ስለማስተማር በሥራው ሀሉ ሐዋርያት ጴጥሮስንና ጳውሎስን የሚአገለግላቸው ሆነ ለታኦፊላም ወንጌልንና የሐዋርያትን ዜና የጻፈ ሉቃስ ነው።

ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስም ከተገደሉ በኋላ በሮሜ ሀገር የሚያስተምር ሆነ በቀናች ሃይማኖትም ይጸኑ ዘንድ ለምእመናን መልእክትን ይጽፍ ነበር። ስለዚህም ጣዖት አምላኪዎች ከአይሁድ ጋር በመስማማት አንድ ግምባር ፈጠሩ በንጉሥ ኔሮን ፊት ቁመው ስለ ሐዋርያው ሉቃስ እንዲህ ብለው ጮኹ ይህ ሉቃስ ብዙዎች ሰዎችን በሥራዩ ወደ ትምህርቱ አስገባቸው። ንጉሥ ኔሮንም ወደ ፍርድ አደባባይ ሉቃስን እንዲአቀርቡት አዘዘ።

ሐዋርያ ሉቃስም ከዚህ ዓለም መውጫው እንደ ደረሰ በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ። በዚያም ዓሣ የሚያጠምድ አንድ ሽማግሌ ሰው አገኘ። መጻሕፍቱንና ደብዳቤዎቹን ሰጠው ወደ እግዚአብሔር መንገድ መርተው ያደርሱሃልና እሊህን መጻሕፍት ጠብቃቸው አለው።

በንጉሥ ኔሮንም ፊት ቀርቦ በቆመ ጊዜ ንጉሡ በሥራይህ ሕዝቡን የምታስት እስከመቼ ነው አለው ቅዱስ ሉቃስም እኔ ለሕያው እግዚአብሔር ልጅ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያው ነኝ እንጂ ሥራየኛ አይደለሁም ብሎ መለሰለት።

ንጉሥ ኔሮንም ሁለተኛ እንዲህ አለው እየጻፈች ሰዎችን የምታስት ይቺን እጅህን እኔ እቆርጣታለሁ ይህንንም ብሎ የቀኝ እጁን እንዲቆርጡ አዘዘ በቆረጡትም ጊዜ ንጉሥ ሆይ እኛ የዚህን ዓለም ሞት እንደማንፈራ እወቅ ነገር ግን የጌታዬንና የፈጣሪዬን ኃይሉን ታውቅ ዘንድ አሳይሃለሁ። ይህንንም ብሎ የተቆረጠች የቀኝ እጁን በግራ እጁ አንሥቶ ከተቆረጠችበት ቦታዋ ላይ አገናኝቶ እንደ ቀድሞዋ ደኅነኛ አደረጋት። ከዚህም በኋላ ለያት በዚያም የነበሩ አደነቁ የሠራዊት አለቃውና ሚስቱ ብዙዎችም ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ቁጥራቸውም አራት መቶ ሰባ ሰባት ነፍስ ሆነ ንጉሡም ከቅዱስ ሉቃስ ጋር ራሶቻቸውን እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጡአቸው የምስክርነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሉቃስን ሥጋ በማቅ አይበት ውስጥ አድርገው ወደ ባሕር ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ አንድ ደሴት ደረሰ። ምእመናንም አግኝተው ወስደው ገነዙት በአማረ ቦታም አኖሩት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
መልካም ቀን
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12
ውድ የሰንበት ትምህርትቤታችን አባላት
በሰንበት ትምህርትቤታችን እየተገነባ ባለው ሕንጻ የ1ኛ(ግራውንድ )ፍሎር ስላብ ሙሌት በዚህ ሳምንት ለማካሔድ በዝግጅት ላይ እንገኛለን። በመሆኑም ሥራው በሚከናወንበት ቀን የሚመቻችሁ አባላት ተገኝታችሁ እንድትሳተፉ እያሳሰብን ትክክለኛውን ቀን በቅርቡ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እንገልጻለን።
🔴ስንክሳር ዘወርሃ #ጥቅምት_23

በዚህች ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሴፍ አረፈ፣ የከሀዲ ዱድያኖስ ንጉሥ ሚስት #ቅድስት_እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ ነው፣ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ዲዮናስዮስ በሰማዕትነት አረፈ፣ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተተክለው በደብረ ሊባኖስ የተሾሙት #አቡነ_ኤልሳ ዕረፍታቸው ነው፡፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ጻድቁ_አቡነ_ኤልሳ

ዳግመኛም በዚህች ቀን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተተክለው በደብረ ሊባኖስ የተሾሙት አቡነ ኤልሳ ዕረፍታቸው ነው፡፡ ጻድቁ ሀገራቸው ሸዋ ነው፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመን የነበሩ ሲሆን ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቀጥለው በደብረ ሊባኖስ ገዳም በእጨጌነት የተሾሙ የመጀመሪያ ዕጨጌ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከማረፋቸው በፊት ‹‹በእኔ ወንበር ኤልሳዕ ይሾም ነገር ግን ዘመኑ ትንሽ ስለሆነ ከእርሱ ቀጥሎ ፊሊጶስን ትሾማላችሁ›› ብለው ለቅዱሳን ተከታይ ሐዋርያቶቻቸው ተናግረው ነበር፡፡

በዚህም መሠረት አቡነ ኤልሳዕ ተሹመው ብዙም ሳይቆዩ አንድ ዲያቆን ሞተና ሊቀብሩት ሲወስዱት በመንገድ ላይ ሳለ ድንገት ከሞት ተነሥቶ ‹‹አባቴ ተክለ ሃይማኖት ኤልሳዕ አሁን ወደኔ ስለሚመጣ ፊሊጶስን ሹሙት ብለህ ተናገር ብለውኝ ነው›› ብሎ ከተናገረ በኋላ ተመልሶ ዐርፎ ተቀበረ፡፡ አቡነ ኤልሳዕም ወዲያው ዐርፈው አቡነ ፊሊጶስ 3ኛ ሆነው ተሾሙ፡፡ አቡነ ኤልሳዕ ከተጋድሎአቸው ብዛት የተነሣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ጎናቸውን አሳርፈው ተኝተው አያውቁም ነበር፡፡ ነገር ግን ማረፍ ሲኖርባቸው በወንበር ላይ ተደግፈው ትንሽ ብቻ ያርፉ ነበር፡፡ አቡነ ኤልሳዕ በሞት ያረፉትም እንደልማዳቸው ጎናቸውን ሳያሳርፉ በወንበር ላይ እንደተደገፉ ነበር፡፡ አባታችን ስለዚህም ጉዳይ ሲናገሩ እንዲህ ይሉ ነበር፡- ‹‹ነፍስ ትጋትን ትወዳለች፣ ሥጋ ግን ይደክማል፡፡ ለመነኮሳትና ለእግዚአብሔር አገልጋዮች ሁሉ መኝታ ማብዛት አይገባቸውም፡፡ መኝታ ማብዛት ሕልምን ያመጣል፣ ነፍስን ይጎዳል፣ ሰውነትንም ያደክማል፡፡››

አቡነ ኤልሳዕ በዘመናቸው ወንጌልን በማስተማርና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ይታወቁ ነበር፡፡ እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ እሳቸውም ሙት አስነሥተዋል፡፡ ባሕር እየከፈሉ ቀደ መዛሙርቶቻቸውን ያሻግሩ ነበር፡፡ በጸሎታቸው የዠማን ወንዝም ለሁለት የከፈሉ ታላቅ አባት ናቸው፡፡

ለእግዚአብርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
የሰንበት ት/ቤታችንን ቴሌግራም ይቀላቀሉ
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
🔴ስንክሳር ዘወርሃ #ጥቅምት_24

በዚህች ዕለት #የቅድስት_ጸበለ_ማርያም መታሰቢያዋ ነው፣ መስተጋድል መነኰስ #ቅዱስ_አባ_አብላርዮስ ያረፈበት ቀን ነው፣ የመፍቀሬ ነዳያን #አባ_ዘግሩም ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_አባ_አብላርዮስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን መስተጋድል መነኰስ አባ አብላርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ጋዛ ከሚባል አገር ነው ወላጀቹም አረማውያን ናቸው የዮናናውያንንም ትምህርታቸውንና ፍልስፍናቸውን አስተማሩት ሰውነቱ ለጥበብ ማደሪያዋ እስከሆነ ድረስ በዕውቀቱ ከጓደኞቹ በላይ ሆነ።

ከዚህም በኋላ ከሀገሩ የሌለ መልካም የሆነ ጥበብን ከውጭ አገር መማርን ወዶ ተነሥቶ ወደ እስክንድርያ ሀገር ሔደ መምህራንም ሁሉ ከሚኖሩበት ቦታ ገብቶ ከእሳቸው ዘንድ ብዙ ትምህርትን ተማረ በዚያንም ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ለመማር ተነሣሥቶ ቸኰለ የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት ብዙዎቹን አነበበ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ እለእስክንድሮስም ይተረጕምለትና ያስረዳው ነበር።

ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የክርስትናን ጥምቀት ተጠመቀ ከዚያም መንኵሶ በምንኵስና ሕግ ጸንቶ ገድልን ተጋደለ ወደ አባ እንጦንዮስም ሔዶ መንፈሳዊ የሆነ የትሩፋትን ሥራ እየተማረ በእርሱ ዘንድ ብዙ ወራት ኖረ።

ወላጆቹም እንደሞቱ በሰማ ጊዜ ሒዶ የተዉለትን ገንዘባቸውን ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች መጸወተ ከዚህም በኋላ ከሶርያ ገዳማት ወደ አንዱ ገዳም ገባ በዚያም በጾም በጸሎት በስግደት በመትጋት ፍጹም ገድልን ተጋደለ በየሰባት ቀን እስቲመገብ ድረስ ምግቡም የዱር ሣር ነበር።

እግዚአብሔርም ሀብተ ትንቢትን ሰጥቶት ልቡናው ብሩህ ሆነ ድንቆች ተአምራትንም የሚያደርግ ሆነ ኤጲፋንዮስንም ያመነኰሰውና ለደሴተ ቆጵሮስም ኤጲስቆጶስ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረለት እርሱ ነው።

የዚህም አባት መላ ዕድሜው ሰማንያ ዓመት ነው ከክርስትናውና ከምንኵስናው በፊት ዐሥራ ሰባት ዓመት በምንኵስናም ስልሳ ሦስት ዓመት ነው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርንም ካገለገለ በኋላ በሰላም አረፈ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም አመስግኖታል ሁለተኛም ቅዱስ ባስልዮስ በመጻሕፍቱ አመስግኖታል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገድላት_አንደበት)
የሰንበት ት/ቤታችንን ቴሌግራም ይቀላቀሉ
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
👉https://t.me/finotebirhan12👈
🔴#ስንክሳር_#ጥቅምት_25

በዚህች ቀን #ቅዱስ_አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) አረፈ፣ የመላእክት አምሳል የሆነ #አባ_እብሎይ አረፈ፣ የከበረ #ቅዱስ_ዮልዮስ_ሰማዕት ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ነው፣ የደብረ ሊባኖሱ #አባ_ሕፃን_ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#አባ_ሕጻን_ሞዐ_ዘደብረ_ሊባኖስ

በዚህችም ቀን የደብረ ሊባኖሱ አባ ሕፃን ሞዐ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ነው። በአባታቸው አርከሌድስ እናታቸው ትቤ ጽዮን ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ጥር 25 ነው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ከእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጋር የሥጋ ዝምድና አላቸው፡፡ ይኸውም አባታቸው አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ወንድማማቾቸ ናቸው፡፡ አርከሌድስና ጸጋ ዘአብ ሌሎች ሌሎች አራት ወንድሞች አሏቸው፡፡

እነርሱም እንድርያስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ቀሲስ ዮናስ እና ቀሲስ ዮሐንስ ናቸው፡፡ አርከሌድስ ሕፃን ሞዐን ይወልዳል፣ ጸጋ ዘአብ ተክለ ሃይማኖትን ይወልዳል፣ እንድርያስ ሳሙኤል ዘወገግን፣ ዘርዐ አብርሃም ታላቁ አኖሬዎዮስን፣ ቀሲስ ዮናስ ገላውዲዮስንና የፈጠጋሩን ማትያስን፣ እና ቀሲስ ዮሐንስ ዜናማርቆስን ይወልዳሉ፡፡ እነዚህ የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በእናታቸውም ወገን ቢሆን እንዲሁ በዝምድና የተቆራኙ ናቸው፡፡ አቡነ ሕፃን ሞዐ በሌላኛው ስማቸው ሕፃን ዘደብረ በግዕ ተብለውም ይጠራሉ፡፡ ይኸውም የደብረ በግዕን ገዳም የመሠረቱት እርሳቸው ስለሆኑ ነው፡፡

ከ47ቱ የሀገራችን ቀደምት ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ በመንዝና በተጉለት የሚገኙ ታላላቅ ገዳማትን አብዛኞቹን የመሠረቷቸው አቡነ ሕፃን ሞዐ ናቸው፡፡ ጻድቁ በክፉዎች ወሬና ሴራ ምክንያት ከበሬ ጋር ተጠምደው ሰማዕትነት የተቀበሉ አባት ናቸው፡፡ ከበሬ ጋር ሲታረሱ ውለው በእጅጉ ከደከማቸው በኋላ በኃይል የተነፈሱባት ምድሪቱ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው የሚሞቅ ትንፋሽ ታወጣለች፡፡ ያም በጻድቁ እስትንፋስ አምሳል ከመሬት ውስጥ የሚወጣው እስትንፋስ ለአስም በሽታ መድኃኒት ሆኖ ብዙዎችን እየፈወ ነው፡፡

ገዳማቸው ከደብረ ብርሃን ከተማ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም ከወንይዬ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አጠገብ ነው፡፡ ጻድቁ ጥር 25 ቀን ልደታቸው፣ ጥቅምት 25 ቃል ኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ሲሆን ሐምሌ 25 ደግሞ ዕረፍታቸው ነው፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት እና #ከገደላት_አንደበት)
👉https://t.me/finotebirhan12
👉https://t.me/finotebirhan12
👉https://t.me/finotebirhan12
🔴#ስንክሳር_#ጥቅምት_26

በዚህች ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ #ሐዋርያ_ቅዱስ_ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ፣ የጌታ ወንድም የተባለው #ቅዱስ_ያዕቆብ_ወልደ_ዮሴፍ መታሰቢያው ነው።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

#ቅዱስ_ሐዋርያ_ጢሞና

ጥቅምት ሃያ ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ከመረጣቸውና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣንን ከሰጣቸው ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ቅዱስ ሐዋርያ ጢሞና በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ ጢሞና ሰማያዊ ሀብትን መለኮታዊ ኃይልን ገንዘብ አድርጎ በሽተኞችን ፈወሳቸው አጋንንትም ተገዙለት ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በምድር ሳለ አገለገለው። ወደ ሰማይም ከዐረገ በኋላ ሐዋርያትን አገለገላቸው በሃምሳኛው ቀንም ጰራቅሊጦስ በወረደ ጊዜ የአጽናኝ መንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከእርሳቸው ጋር ተቀበለ።

ከዚህም በኋላ ሰባት ሁነው ከተቆጠሩት ዲያቆናት ጋር ሐዋርያት ሾሙት እነርሱ መንፈስ ቅዱስን ዕውቀትንም የተመሉ እንደሆኑ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ምስክር ሁኖአል።

በዲቁና አገልግሎትም ጥቂት ከአገለገለ በኋላ ብልቃ ከሚባል አገር በስተምዕራብ በሆነ ስብራ በሚባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾሙት በውስጧም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት አስተማረ ከዮናውያንና ከአይሁድም ብዙዎችን አጠመቃቸው።

የዚያች አገር ገዥም ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ጢሞናን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ በእሳት አቃጠለው በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉https://t.me/finotebirhan12
👉https://t.me/finotebirhan12
👉https://t.me/finotebirhan12
🔴#​​ስንክሳር_ጥቅምት_፳፯_(27) ✞

✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::

በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::

7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::

+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::

ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::

https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12

https://t.me/finotebirhan12
🔴 የባለ ትዳር አባላት ጉባኤ ነገ እሁድ ጥቅምት 28 5:00 ሰዓት ላይ ወርሐዊ ጉባኤ share
🌹 ማኅሌተ ጽጌ ጥቅምት 28 ሥርዓተ ማኅሌት

🌹🌹🌹የአምስተኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ ሥርአተ ማኅሌት እነሆ🌹🌹🌹

ነግሥ
ሰምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡

፩/ ለኲልያቲክሙ / ነግሥ/ 🌹

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡

ዚቅ ፦

አሠርገወ ገዳማተ ስን ፨ በመንክር ኪን አርአያሁ ዘገብረ ፨ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ በኲሉ ክብሩ ፨ ከመ እሎን ጽጌያት፨ ኢቀደምት ወኢደኃርት፨ አራዛተ ሠርጕ ነሢኦሙ፨ ኢክህሉ ከመ ክርስቶስ መዊዓ፡፡

፪/ ዘብኪ ተባረኩ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

ዘብኪ ተባረኩ ወተቀደሱ አሕዛብ፤
ትእምርተ ግዝረቱ ወዘርዑ ለአብርሃም አብ፤
ጽጌ ድንግልናኪ በግዕ ለቤዛ ይስሐቅ ውሁብ፤
ማርያም ዕፀ ሳቤቅ ወምሥራቅ ዘያዕቆብ፤
ወላዲቱ ለሥርግው ኮከብ ፡፡

ወረብ፦ 🌹

ዕፀ ሳቤቅ ዕፀ ሳቤቅ ማርያም ወምሥራቅ ዘያዕቆብ/፪/
ወላዲቱ ወላዲቱ ወላዲቱ ለሥርግው ኮከብ /፪/

ዚቅ ፦

ቡራኬሁ ለሴም ወክፍል ሎቱ፨ ተናግዶቱ ለአብርሃም፨ መዓዛሁ ለይስሐቅ ፨ ወሰዋስዊሁ ለያዕቆብ፨ ወናዛዚቱ ለዮሴፍ፡፡

፫ እንዘ ተሐቅፊዮ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡

ወረብ፦ 🌹

ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል /፪/
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት /፪/

ዚቅ፦

በሰላም ንዒ ማርያም ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ በሰላም ንዒ ማርያም ፨ ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፨ በሰላም ንዒ ማርያም ፨ ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፨ በሰላም ንዒ ማርያም፨ ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን ፨ በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፨ በሰላም ንዒ ማርያም ፨ ለናዝዞ ኲሉ ዓለም፡፡

፬/ ክበበ ጌራ ወርቅ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

ክበበ ጌራ ወርቀ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ፦ 🌹

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኃቱ እምዕንቈ ባሕርይ /፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ /፪/

ዚቅ ፦

አክሊል ዘእምጳዝዮን ተደለወ፨ ጌራ ባሕርይ ወቀጸላ ወርቅ ጽሩይ፨ በቤተልሔም ተወልደ እምድንግል ብሥራትክሙ መሃይምናን፨ እምአፈ ዮሐንስ ሥርግው ተቀስመ አፈው፨ ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማዕከለ አኃው።

፭/ ዘንተ ስብሐተ / ማኅሌተ ጽጌ / 🌹

ዘንተ ስብሐተ ወዘንተ ማኅሌተ፤
ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤
ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤
ምስለ እለ ሐፀቡ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤
ውስተ ባሕረ ማሕው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።

ወረብ፦

ምስለ እለ ሐፀቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/፪/
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባሕረ ማሕው/፪/

ዚቅ ፦

ማኅሌተ ነዓርግ ፨ ወስብሐተ ዘነግህ፨ ንፌኑ ለኪ ማርያም።

፮/ ኢየሱስ ስዱድ / ሰቆቃወ ድንግል / 🌹

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤
ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉዓን፤
እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤
ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤
ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን፤
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን፡፡

🌹ወረብ፦

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን /፪/
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን /፪/

ዚቅ፦

አንተ ውእቱ ምርጒዞሙ ለጻድቃን፨ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፨ መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፨ ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው።

🌹 መዝሙር ዘሰንበት

ሃሌ ሉያ (በ፭) ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን ወፈርዪ ኲሉ ዕፀወ ወገዳም ቀንሞስ ዕቊረ ማየ ልብን ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጓላት ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር። ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር ። እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ነገር ። ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት።

አመላለስ ዘመዝሙር

ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት።

#ፍኖተ_ብርሃን_ሰንበት_ት/ቤት
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12
https://t.me/finotebirhan12